የእግር ኳስ ፌደሬሽን ታዛቢ ኮሚሽነር እገዳ ተጣለበት

የእግር ኳስ ፌደሬሽን ታዛቢ ኮሚሽነር እገዳ ተጣለበት Muluken Tesfawበየባሕር ዳር ከነማ ቡድን በመቀሌ ስታዲየም ሁላችንም በሕይወት መትረፍ የማንችልበት ሁኔታ ተፈጥሮ ነበር ሲል አቤቱታ ጽፏል፤


በባሕር ዳር ከነማና በመቀሌ ከተማ መካከል በነበረው የአዲ ሀቂ ስታዲየም ጨዋታ ለመታዘብ ከእግር ኳስ ፌደሬሽን የተላከው ታዛቢ ኮሚሽነር ከሥራ እገዳ ተጥሎበታል፡፡ ለእገዳው እንደ ምክንያት የቀረበው ደግሞ ትክክለኛ ሪፖርት አላቀረበም በሚል ነው ተብሏል፡፡ ታዛቢ ኮሚሽነሩ በባሕር ዳር ከነማ የእግር ኳስ ተጫዋቾችና ደጋፊዎች ላይ የደረሰውን ስድብና ጭፍጨፋ እንዳለ በማቅረቡ ምክንያት ነው እገዳ የተጣለበት፡፡ የእግር ኳስ ፌደሬሽን በሁለቱ ክልሎች መካከል የሚካሔዱ ጨዋታዎችን ላልተወሰነ ጊዜ አራዝሞ የመቀሌውን ጨዋታ ጉዳይ ፖለቲካዊ ውሳኔ እንደሚሰጠው ገልጧል፡፡ ዛሬ ጠዋት በነበረው ስብሰባ የሁለቱ ክልሎች ተነጋግረው መፍትሔ ይፈልጉለት የሚል መልስ ተሰጥቷል ተብሏል፡፡


በሌላ በኩል ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ባሕር ዳር የተመለሱት የባሕር ዳር ከነማ ቡድን አባላት በዐማራነታችን ከዚህ ላይ መዝግበን ልንጽፈው የማንችለው ስድብ ከገባንበት ጊዜ አንስቶ ደርሶብናል ሲሉ በአቤቱታቸው ላይ ገልጸዋል፡፡ የትግራይ ክልል የፖሊስ አባላት በባሕር ዳር ከነማ ደጋፊዎችና አባላት ላይ ድንጋይ ሲወረወርባቸው ከወገንተኛነት ነጻ ሆነው እርምጃ መውሰድ አለመቻላቸው፣ አላስፈላጊ ቅጣት መስጠትና አደጋው ከተፈጠረ በኋላም ሕክምና እንዳናገኝ መሰናክሎች ነበሩብን ካለ በኋላ ፌደሬሽኑ ጣልቃ ባይገባ አንድም ሰው በሕይወት የመትረፍ እድል አልነበረንም ሲል በማመልከቻው ገልጧል፡፡