Related Posts

አጫጭር የዝውውርና ሌሎች ስፖርታዊ ወሬዎች = በኢትዮአዲስ ስፖርት


ኤቨርተኖች የፕሪሚየር ሊጎቹ ክለቦች ማንችስተር ዩናይትድና ቼልሲ ለ23 ዓመቱ አጥቂያቸው ሮሜሉ ሉካኩ ያላቸውን ፍላጎት ለመግታት ሲሉ በተጫዋቹ ላይ የዓለም የዝውውር ክብረወሰን የሆነ 100 ሚ.ፓ ዋጋ ለጥፈውበታል። (ሊቨርፑል ኢኮ)


የሪያል ማድሪዱ ፕሬዝዳንት ፍሎረንቲኖ ፔሬዝ የ26 ዓመቱን የቼልሲ የፊት ተጫዋች ኤዲን ሃዛርድ የዓለም ክብረወሰን በሆነ 100 ሚ.ፓ የዝውውር ዋጋ ለማዛወር አረንጓዴ መብራት አብርተዋል። (ደይሊ ስታር ዲያሪያ ጎልን ጠቅሶ)


ነገር ግን ከስፔን የወጡ ዘገባዎች እንዳመለከቱት ከሆነ ቤልጂየማዊው ተጫዋች የዝውውር መስኮቱ ዳግም ሲከፈት ሪያል ማድሪድን ለመቀላቀል ከወዲሁ ከስምምነት ላይ ደርሷል። (ኤክስፕሬስ ዶን ባሎንን ጠቅሶ)


የሪያል ማድሪዱ የፊት ተጫዋች ካሪም ቤንዜማ ሃዛርድ ለስፔኑ ታላቅ ክለብ ጥሩ ፈራሚ እንደሚሆን ተናግሯል። (ደይሊ ሜል)
አርሰናል ሚድልስብሮን የማሸነፍ ጉዳይ አብዛኛውን የደይሊ ስታር ጋዜጣ የጀርባ ገፅ ተቆጣጥሯል


አርሰናል የ28 ዓመቱ የፊት ተጫዋቹ አሌክሲ ሳንቼዝ ከመድፈኞቹ ጋር ለመቆየት ከምምነት ላይ መድረስ የማይችል ከሆነ ወደቼልሲና ማንችስተር ሲቲ ከማምራት ይልቅ ወደፒኤስጂ እንዲያመራ ግፊት ያደርጉበታል። (ዘ ሰን)


የ36 ዓመቱ የቼልሲ የመሃል ተከላካይ በውድድር ዘመኑ መጨረሻ ክለቡን እንደሚለቅ ይፋ ማድረጉን ተከትሎ የአሜሪካኑ ሜጀር ሊግ ሶከር ክለቦች ጆን ቴሪን የማስፈረም “ፍለጎት እንደሌላቸው” የሜጀር ሊግ ሶከር ምንጮች ተናግረዋል። (ኢኤስፒኤን)


ነገር ግን ቶኒ ፑሊስ ሁለተኛ ጥያቄ በማቅረብ ወደሃውትሮን የማምጣት ፍላጎት ያላቸው በመሆኑ ዌስት ብሮምዊች አልቢዮኖች የቀድሞውን የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን አምበል በመጪው ክረምት ለማስፈረም ዳግም ፉክክሩን ይመራሉ። (ደይሊ ሚረር)


የ30 ዓመቱ የሊቨርፑል አማካኝ ሉካስ ሊየቫ በሚቀጥለው ወር ከአሰልጣኙ የርገን ክሎፕ ጋር ስለኮንትራቱ ጉዳይ ንግግር ከማድረጉ በፊት አንፊልድን እንደሚለቅ ፍንጭ ሰጥቷል። (ደይሊ ቴሌግራፍ)የጆን ቴሪ ቼልሲን የመልቀቅ ጉዳይ የአይ ስፖርት ጋዜጣ የጀርባ ገፅ አብይ ጉዳይ ነው


የአርሰናል የዝውውር ዒላማ የሆነው የ22 ዓመቱ ጆርን ኢንገልስ የሰሜን ለንደኑ ክለብ ባለፈው ክረምት ለማስፈረም ሳይችል ከቀረ በኋላ አሁን ከክለብ ብሩዥ ወደፕሪሚየር ሊጉ ለመዛወር በሩን ወለል አድርጎ ከፍቷል።(ደይሊ ኤክስፕሬስ)


የቼልሲው አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ ቁጥር አንድ የዝውውር ዒላማ የሆነው የ24 ዓመቱ የፊት ተጫዋች አልቫሮ ሞራታ በክረምቱ ክለቡን እንደሚለቅ ለሪያል ማድሪዶች የነገረቸው ስለመሆኑ ከስፔን የወጡ ዘገባዎች ገልፅዋል። (ደይሊ ስታር ዲያሪዮ ጎልን ጠቅሶ)


ማንችስተር ዩናይትዶች በዚህ የውድድር ዘመን ከቤኔፊካ ወደቤሽኪታሽ በውሰት በመዛወር ተስፋ ሰጪ ብቃት ማስየት የቻለውን የ13 ዓመቱን አንደርሰን ተሊስካን የሚያስፈርሙ ከሆነ አማካኛቸውን ሁዋን ማታን ለቤሽኪታሽ ሊሸጡ ይችላሉ። (ኤክስፕሬስ ፋናቲካን ጠቅሶ)


የ25 ዓመቱ የባርሴሎናና የብራዚል ብሄራዊ ቡድን የፊት ተጫዋቹ ኔይማር ወደፊት በብራዚሉ ክለብ ፍላሚንጎ ለመጫወት እንደሚፈልግ ገልፅዋል። (ደይሊ ሜል ካናል ኢስፖርቴ ኢንተራቲቮንንጠቅሶ )የደይሊ ቴሌ ግራፍ መሪ አንቀፅ ብራይተንፕሪሚየር ሊጉን ስለመቀላቀሉ ጉዳይ ላይ ያተኮረ ነው


ሳውዛምፕተኖች በበልጂየሙ ክለብ ኬ.ኤ.ኤስ ኡፐን እየተጫወተ የሚገኘውን የ19 ዓመቱን ናይጄሪያዊ የክንፍ ተጫዋች ሄነሪ ኦንየኩሩን ወደክለባቸው ለማምጣት ሲሉ ፉክክሩን ለመቀላቀል ዝግጁ ሆነዋል። (ደይሊ ሪኮርድ)


ኢንተር ሚላኖች የቼልሲ የዝውውር ዒለማ የሆነውንና በሴሪ ኣው ሳሡሎ ክለብ የጉዳት ችግር ውስጥ ገብቶ የውድድር ዘመኑን ያሳለፈውን የ22 ዓመቱን ዶሚኒኮ ቤራርድን ለማስፈረም መልካም የሚባል ንግግር አድርገዋል። (ደይሊ ስታር ካልቾመርካቶን ጠቅሶ)


የባየር ሙኒኩ አማካኝ ዣቢ አሎንሶ ሊቨርፑልን በ2009 እንዲለቅ ያስገደደውን ግጭት ከራፋ ቤኒቴዝ ጋር የፈጠረው ክለቡ በሻምፒየንስ ሊጉ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ከኢንተር ጋር ያደርግ በነበረው ጨዋታ ላይ ከመሰለፍ ይልቅ በባለቤቱ የወሊድ ምጥ ላይ መገኘትን በመምረጡ እንደሆነ ተናግሯል። (ደይሊ ስታር ኤል ፓይስን ጠቅሶ)


የ32 ዓመቱ የስቶክ ሲቲው የቀድሞ የሊቨርፑልና የቼልሲ ተከላካይ ግሌን ጆንሰን ከፖተርሶቹ ጋር ያለውን ኮንትራት ለአንድ ዓመት ስለማራዘም ጉዳይ ከክለቡ መነጋገር ጀምሯል። (ዘ ሰን)
በመጨረሻም


የማንችስተር ዩናይትዱ አርመኒያዊ አማካኝ ሄንሪክ ምክሂታሪያን በማንችስተር ከተማ አንድ ሬስቶራንት 70,000 ፓውንድ ዋጋ የላትን መርሴዲስ መኪናውን አቁሞ ለሰዓታት ቆይቶ ሲወጣ ከአንድ የትራፊክ አስተናባሪ ጋር ተጨቃጭቆ በአቅራቢያው ለሚገኝ ቤት አልባ ችግረኛ ሰው 5 ፓውንድ በመለገስ የምፅዋት እጁን ዘርግቷል።(ደይሊ ሚረር)