Related Posts

ማንችስተር ሲቲ ከ ሊቨርፑል፡ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የጨዋታ ቅድመ ዳሰሳ - በኢትዮአዲስ ስፖርት

ማንችስተር ሲቲ ከ ሊቨርፑል፡ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የጨዋታ ቅድመ ዳሰሳ - በኢትዮአዲስ ስፖርትማንችስተር ሲቲዎች ከሊቨርፑል ጋር ያደረጓቸውን ያለፉት አራት ተከታታይ ጨዋታዎችን በሙሉ ተሸንፈዋል። ለመጨረሻ ጊዜ ቀዮቹን ማሸነፍ የቻሉትም በ2014 በኢትሃድ ስታዲየም 3ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ በቻሉበት ጨዋታ ነበር። አሁን ግን የፔፕ ጋርዲዮላው ቡድን እነዚህ ውጤቶች በሙሉ ወደጎን ብሎ አንድም በሻምፒዮንስ ሊጉ የደረሰበትን ሽንፈት ለመርሳት አንድም ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው ከሊቨርፑል ጋር ያለውን ልዩነት በአራት ነጥቦች ለማስፋት ሲል ይህን ጨዋታ ለማሸነፍ ይጫወታል።


ስለጨዋታው


ሰዓት፡ እሁድ ምሽት 1፡00 ሰዓት


ሜዳ፡ ኢትሃድ ስታዲየም


ባለፈው የውድድር ዘመን፡ ማን ሲቲ 1-4 ሊቨርፑል


ቀጥታ ስርጭት፡ በእንግሊዝ ስካይ ስፖርት 1፣ በአፍሪካ ከሰሃራ በታች ሱፐር ስፖርት 3 እንዲሁም በሰሜን አፍሪካና በመካከለኛው ምስራቅ ቤን ስፖርት 11


ዳኛ፡ ሚካኤል ኦሊቨር


ዳኛው በዚህ የውድድር ዘመን፡ አጫወቱ23፣ ቢጫ75፣ ቀይ2፣ 3.35 ካርዶች በአማካኝየክለቦቹ ዜናዎች


ማንችስተር ሲቲዎች ረቡዕ ምሽት በሞናኮ በተሸነፉበት ጨዋታ ተጠባባቂ ወንበር ላይ እንዲቀመጡ ተደርገው የነበሩት ያያ ቱሬና ኒኮላስ ኦታሜንዲ በዚህ ጨዋታ ላይ እንዲሰለፉ ጥሪ ሊቀርብላቸው ይችላል።


ሲቲዎች የረጅም ጊዜ ጉዳት ላይ የሚገኙትን ጋብሬል የሱስንና አይካይ ጉንዶጋንን ግልጋሎት አሁንም ሳያገኙት ይቀጥላሉ።


በሌላ በኩል ባለፈው ሳምንት ገጥሞት በነበረው ቀላል ጉዳት ምክኒያት በበርንሌው ጨዋታ ላይ ተሰልፎ ያልነበረው የሊቨርፑሉ ሮቤርቶ ፊርሚኖ በዚህ ጨዋታ ላይ ሊሰለፍ ይችላል።


ከገጠመው የጉልበት ጉዳት እንዲድን እንክብካቤ እየተደረገለት የቆየው ደያን ሎቭረንም ሰኞ ዕለት ከ23 ዓመት በታች ቡድኑ ጋር መጫወት የቻለ ሲሆን፣ ከጥር ወር ወዲህም ከዋናው ቡድን ጋር የመጀመሪያውን ጨዋታ ለማድረግ በጥሩ አቋም ላይ ይገኛል።


ዲቮክ ኦርጊ በደረሰበት ህመም መሰለፉ አጠራጣሪ ሲሆን፣ በጉዳት ላይ የሚገኙት ሁለት ተጫዋቾች ጆርዳን ሄንደርሰንና ዳንኤል ስተርጂም አሁንም ይህ ጨዋታ የሚያልፋቸው ይሆናል።ግምታዊ አሰላለፎች 


ማንችስተር ሲቲ


ተጠባባቂዎች፡ ብራቮ፣ አዳራቢዮ፣ ገን፣ ኢሄናቾ፣ ሳኛ፣ ደልፍ፣ ፈርናንዶ፣ ኮላሮቭ፣ ናቫስ፣ ደ ብሩይኔ


አጠራጣሪ፡ የለም


ጉዳት፡ የሱስ (የእግር)፣ ጉንዶጋን (የጉልበት)


ቅጣት፡ የለም


ወቅታዊ አቋም፡ አቻ፣ድል፣ድል፣ድል፣ ድል፣ አቻ


ካርድ፡ ቢጫ53 ቀይ4


ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ፡ አጉዌሮ 12
ሊቨርፑል


ተጠባባቂዎች፡ ካሪዩስ፣ ማኒንገር፣ ኦሪጊ፣ ክላቫን፣ ሞሬኖ፣ ስትዋርት፣ ሄንደርሰን፣ ራንዳል፣ አሌክሳንደር-አርኖልድ፣ ዉድበርን፣ ኦጆ፣ ዊልሰን፣ ጎሜዝ፣ ሉካስ


አጠራጣሪ፡ ፊርሚኖ (የብሽሽት)፣ ኦሪጊ (በህመም)


ጉዳት፡ ሄንደርሰን (የእግር)፣ ስተሪጅ (የዳሌ)፣ ኢንግስ (የጉልበት)፣ ኢጃሪያ(የቁርጭምጭሚት)


ቅጣት፡ የለም


ወቅታዊ አቋም፡ አቻ፣ሽን፣ድል፣ ሽን፣ድል፣ ድል


ካርድ፡ ቢጫ43 ቀይ0


ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ፡ ማኔ 12


ቁጥራዊ መረጃዎች


እርስበርስ ባደረጓቸው ጨዋታዎች


ማንችስተር ሲቲ ሁለቱ ቡድኖች በተገናኙባቸው የመጨረሻዎቹ ስድስት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች በአምስቱ ሽንፈት ደርሶበታል።
ሲቲዎች ከሊቨርፑሎች ጋር በሁሉም ውድድሮች ላይ ለመጨረሻ ጊዜያት ጋር ባደረጓቸው 12 ጨዋታዎች ግብ ሳይቆጠርባቸው መውጣት አልቻሉም።
ሊቨርፑሎች ባለፈው የውድድር ዘመን ማሸነፍ የቻሉት የ4ለ1 ድል ለመጨረሻ ጊዜያት በኢትሃድ ካደረጓቸው ሰባት ጨዋታዎች ውስጥ የመጀመሪያው ነበር።
ይህን ጨዋታ ቀያዮቹ የሚያሸንፉ ከሆነ በፔፕ ጋርዲዮላ የሚሰለጥነውን ቡድን ለሁለት ጊዜያት ያህል መርታት የቻለ የፕሪሚየር ሊጉ ትልቅ ቡድን መሆን ይችላል።


ማንችስተር ሲቲ


ሲቲዎች ይህን ጨዋታ የሚያሸንፉ ከሆነ በፕሪሚየር ሊጉ በሜዳቸው ማሸነፍ የቻሉት 200ኛ ድላቸው ሆኖ ይመዘገባል።
ሲቲዎች በዚህ የውድድር ዘመን በፕሪሚየር ሊጉ አምስት ጊዜ ተሸንፈዋል። ፔፕ ጋርዲዮላ ደግሞ በዋና አሰልጣኝነት ዘመናቸው በአንድ የውድድር ዘመን ፈፅሞ ስድስት ጊዜ ሽንፈት ደርሶባቸው አያውቁም።
ማን ሲቲ ከሊቨርፑል ጋር በኢትሃድ ባደረጋቸው አራት ጨዋታዎች ላይ በሙሉ ሰርጂዮ አግዌሮ ግብ (አራት)ማስቆጠር ችሏል። ይሁን እንጂ በአንፊልድ ፈፅሞ ግብ አስቆጥሮ አያውቅም።
ጆን ስቶንስ በዚህ ጨዋታ 100ኛ የፕሪሚየር ሊግ ተሳትፎውን ሊያደርግ ይችላል።


ሊቨርፑል


ሊቨርፑሎች በደረጃ ሰንጠረዡ አናት ላይ ከሚገኙት ስድሥት ክለቦች ጋር በዚህ የውድድር ዘመን ባደረጓቸው ዘጠኝ ጨዋታዎች ላይ ሽንፈት አልገጠማቸውም። ከእነዚህም አምስቱን ድል ማድረግ ችለዋል።
ቀዮቹ በዚህ ዲቪዚዮን ከየትኛውም ቡድን በበለጠ ሜዳውን አካለው ሮጠዋል። ይህም በአማካኝ 117.3 ኪ.ሜ ነው። በ114.8 ኪ.ሜ ቀጥለው የተወመጡ ደግሞ ተጋጣሚዎቻቸው ማን ሲቲዎች ናቸው።
ሊቨርፑሎች ከሜዳቸው ውጪ በተከታታይ ስድስት ጊዜ ማሸነፍ የቻሉት በጥር ወር በኤፍኤ ዋንጫው ፕሌይማውዝን ባሸነፉበት ጨዋታ ነበር።
ፊሊፔ ኮቲንሆ ከማንችስተር ሲቲ ጋር በተደረገ አምስት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች የትኛውም ክለብ ላይ ካስቆጠረው በላቀ 4 ግቦችን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል። ባለፍው የውድድር ዘመን የሊግ ካፕ ፍፃሜ ላይም በሲቲዎች ላይ ማስቆጠር ችሏል።
ሳዲዮ ማኔም ከሲቲዎች ጋር ለመጨረሻ ጊዜያት ባደረጋቸው ሶስት ጨዋታዎች ለአራት ግቦች መቆጠር እጁ አለበት። (ሁለት ሲያስቆጠር ሁለቱን ደግሞ አመቻችቶ አቀብሏል።)