Related Posts

አጫጭር የዝውውርና ሌሎች ስፓርታዊ ወሬዎች

በዕለቱ በአበይት የአውሮፓ የስፖርት ሚዲያዎች የተዘገቡ አጫጫር የዝውውርና ሌሎች ስፖርታዊ ወሬዎች እንደሚከተለው በኢትዮአዲስ ስፖርት ተሰናድተዋል።


ቼልሲዎች ለ23 ዓመቱ የፊት ተጫዋች ሮሜሉ ሉካኩና ለ23 ዓመቱ አማካኝ ተጫዋች ሮዝ ባርክሌይ ዝውውር ለኤሸርተን 100 ሚሊዮን ፓውንድ ዋጋ ለማቅረብ እያቀዱበት ይገኛሉ። (ደይሊ ቴሌግራፍ)


ቼልሲዎች ለሉካኩ እና ለ24 ዓመቱ የሪያል ማድሪድ አጥቂ አልቫሮ ሞራታ ዝውውር እንዲደጉማቸው የ26 ዓመት አጥቂያቸውን ዲያጎ ኮስታን የሚሸጡ ይሆናል። (ዘ ሰን)


ሮሜሉ ሉካኩ በኤቨርተን የቀረበለትን ኮንትራት ላለመቀበል ውሳኔ ላይ ካደረሱት አሳሳቢ ምክኒያቶቹ መካከል አንዱን ሲገልፅ “ባለፈው ነገር ከመኖር ይልቅ ስለወደፊቱ ማሰብ ይኖርብሃል።” ሲል ተናግሯል። (ሊቨርፑል ኢኮ)


የኤቨርተን ክለብ ከፍተኛ የሃብት ድርሻ ያላቸው ፋርሃድ ማሺሪ ሮሜሉ ሉካኩ በክለቡ የቀረበለትን አዲስ ኮንትራት ለመፈረም ቁርጠኛ እንደሚሆን ተናግረዋል። (ቶክስፖርት)


ኤቨርተኖች ቤልጂየማዊውን አጥቂያቸውን ሮሜሉ ሉካክን ቼልሲዎች ሊያስፈርሙት ፍላጎት ካላቸው ከ65 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ መክፈል እንደሚኖርባቸው ነግረዋቸዋል። (ኢቭኒንግ ስታንዳርድ)ዘ ታየምስ ጋዜጣ በሀሙስ ዕለት እትሙ ስለማንችስተር ሲቲ ከቻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ውጪ መሆን ፅፏል


ማንችስተር ዩናይትዶች የ20 ዓመቱን የሴልቲክ የፊት ተጫዋች የሆነውንና በስኮትላንዱ ሻምፒዮና ክለብ 30 ሚ.ፓ ዋጋ የተቆረጠለትን ሙሳ ዴምቤሌን በቅርበት ለመከታተል ቼልሲዎችን ተቀላቅለዋል። (ዘ ኢንዲፔንደንት)


ማንችስተር ዩናይትድና የከተማው ተቀናቃኝ ማንችስተር ሲቲ ቀጣዩ የውድድር ዘመን ከመጀመሩ በፊት በወዳጅነት ጨዋታ በአሜሪካ ሳንቲያጎ ይጫወታሉ። (ዘ ታየምስ)


ባርሴሎናዎች የ19 ዓመቱን ፈረንሳያዊ የዶንትሙንድ የፊት ተጫዋች ኦስማኔ ዴምቤሌን በመጪው ክረምት የማስፈረም ፍላጎት አላቸው። (ሙንዶ ዲ ፖርቲቮ በስፔንኛ)


የ29 ዓመቱ የናፖሊ የፊት ተጫዋች ድሪስ መርተንስ ከጣሊያኑ ክለብ ጋር አዲስ ስምምነት የማያደርግ በመሆኑ ፊቱን ወደፕሪሚየር ሊግ አዙሯል። (ኸት ላትስተ ኑውስ በሆላንድኛ)


የ25 ዓመቱ ኔዘርላንዳዊ ተከላካይ ብሩኖ ማርቲንስ በስቶክ ለመቆየት ፍላጎት ያለው ሲሆን፣ ከፖርቶ ወደስቶክ ያደረገው የውሰት ስምምነት ወደቋሚነት ስለሚቀየርበት ጉዳይም ንግግር ጀምሯል። (ደይሊ ሚረር)


የዝላታን ኢብራሂሞቪች ወኪል ስለ36 ዓመቱ የማንችስተር ዩናይትድ አጥቂ የወደፊት እጣ ፈንታ ከኤልኤ ጋላክሲ ጋር ለመደራደር በዩናይትድ ስቴት ቆይታ አድርጓል። (ማርካ)


የቀድሞው የእንግሊዝ አሰልጣኝ ሮይ ሆጂሰን የኖርዊች ቀጣይ አሰልጣኝ የሚሆኑበትን ጥያቄ ውድቅ ሊያደረጉ ነው። (ኢስተርን ደይሊ ፕሬስ)


ባየር ሙኒኮች የ20 ዓመቱን የባየር ለቨርኩሰን የክንፍ ተጫዋች የሆነውን ዡሊያን ብራንድትን የማስፈረም ከፍተኛ ፍላጎት አላቸው። (ቢልድ በጀርመንኛ)


ይሁን እንጂ የሊቨርፑሉ አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ለብራንድት 20 ሚ.ፓ ለመክፈል የተዘጋጁ በመሆኑ ቀዮቹም የተጫዋቹ ፈላጊ ናቸው። (ደይሊ ሚረር)


የ31 ዓመቱ የክሪስታል ፓላስ ግብ ጠባቂ ስቲቭ ማንዳንዳ በመጪው ክረምት ወደማርሴይ ለመመለስ ተስማምቷል የሚለውን ዘገባ አስተበብሏል። (ፌስቡክ በፈረንሳይኛ)


አርሰናል የ19 ዓመቱን የሽቱትጋርት አማካኝ ተጫዋች የሆነውን በርካይ ኦዝከንን ከሚከታተሉት በርካታ ክለቦች መካከል አንዱ ነው። (ፉትቦል.ለንደን)የፔፕ ጋርዲዮላ ብስጭት የደይሊ ሚረር ጋዜጣ የዕለተ ሃሙስ እትም ሰፊ ዘገባ ነበር


የዌልሱ አሰልጣኝ ክሪስ ኮልማን የ17 ዓመቱን የሊቨርፑል የፊት ተጫዋች ቤን ዉድበርንን የመጀመሪያውን ጨዋታ እንዲያደርግ ዛሬ ወደዋናው ብሄራዊ ቡድን ጠርተውታል። (ዘ ሰን)


ሊቨርፑሎች በ21 ዓመቱ የአርቢ ሌፕዚግ አጥቂ፣ ቲሞ ወርነር ላይ ፋላጎት አድሮባቸዋል። (ደይሊ ሜል)


ዌስት ሃሞች አዲስ አጥቂ ፍላጋቸውን ቀጥለውበት የሚገኙ በመሆኑ የ25 ዓመቱን የሳምፕዶሪያ የፊት ተጫዋች ልዊስ ሙሬልን ለማስፈረም እንቅስቃሴ ለማድረግ እያጤኑበት ይገኛሉ። (ደይሊ ሚረር)


ኒውካሰሎች ከወዲሁ አዲስ አጥቂ መፈለጋቸውን የጀምሩ ቢሆንም የ22 ዓመቱን የፊት ተጫዋቻቸውን አሌክሳንደር ሚትሮቪችን የመሸጥ ዕድቅ ግን የላቸውም። (ኢቭኒንግ ክሮኒክል)


ሪያል ማድሪዶች የፖርቶውን የ27 ዓመት ብራዚላዊው ተከላካይ ፊሊፔ ሜንቴሮን ለማስፈረም ተቃርበዋል። (አስ)


የማንችስተር ዩናይትዱ አሰልጣኝ ሆዜ ሞሪንሆ ቡድናቸው የረቡዕ ዕለት መደበኛ ልምምዱን ከመጀመሩ በፊት ከአካል ብቃት ባለሙያቸው ካርሌስ ላሊን ጋር ተጨቃጭቀዋል። (ዘ ሰን)


ቼልሲዎች የ30 ዓመቱን የጋላታሳራይ ግብ ጠባቂ ፈርናንዶ ሙስሌራን የማስፈረም ፍላጎታቸው ዳግም አገርሽቷል። የ29 ዓመቱ የሰማያዊዎቹ ሁለተኛ ግብ ጠባቂ አስሚር ቤጎቪች በመጪው ክረምት በ10 ሚ.ፓ ቦርንማውዞችን እንደሚቀላቀል ይጠበቃል። (ደይሊ ሜል)


ይሁን እንጂ የሰማያዊዎቹ አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ በመጪው ክረምት አዲስ ኮንትራት ከመፈፀማቸው በፊት የክለቡን የዝውውር ፖሊሲ ይበልጥ የመቆጣጠር ፍላጎት አላቸው። (ዘ ታየምስ)