Browse Members

772 members found.

  • al mariam Ethiopia: State of Emergency or T-TPLF S.O.S. (Save Our Souls/Ship) Emergency? https://goo.gl/JFcIPv
    October 12, 2016
  • yetanaw Lij ትንሽ ማብራሪያ ስለ እረኝነት ሰሞኑን "እረኛ" በምትል ቃል የተነሳ ጫጫታ በዝቶ ነበር።ጫጫታ ያልኩት ነገሩ ምንም ጭብጥ የሌለዉ አፍ መክፈት ስለሆነ ነው።መነሻዉም አላዋቂነት፣በራስ ያለመተማመን፣ጥራዝ ነጠቅንት ነዉ።አፍ ሲከፈት ጭንቅላት ይታያል ነዉ። ባዶነታቸዉን በአደባባይ በራሳቸዉ ፍቃድ አሳይተውናል ።ለዚህ ሊመሰገኑ ይገባል። በዛላይ ለ3 ስአት ያን የመሰለ ቁም ነገር ሲወራ አንድ ቃል ብቻ መያዝ በጣም ያሳዝናል።ፕ/ር ሀይሌ ላሬቦ በድጋሚ "እረኛ" የምትለዉን ቃል ትርጉም ከተለያየ አቅጣጫ አስረድተዋል። እኔም በዚህ ጽሁፍ ከሊቁ ፕ/ር ሀይሌ የበለጠ ለማብራራት ሳይሆን ፤ እንደው ቀለለ ባለ አቀራረብ ቢገባቸዉ ከሚል ነዉ። እኔ ያደግኩበት ሰፈር ዮናስ የሚባል የ5 አመት ህጻን ነበር።ዮናስ ከእድሜ ጏደኞቹ የተለየ ልጅ ነበር።ጥሎበት አልቃሻ ልጅ ነበር።ስምህ ማን ነዉ ቢሉት ማልቀስ የሚቃጣዉ አይነት ልጅ ነበር።ጏደኞቹ ሲመቱት፣ሲሰድቡት እያለቀሰ ወደ አባቱ ነበር የሚሄደዉ። አባቱ ድግሞ በዚህ በጣም ይናደዳል። ወንድ ልጅ ነህ ፤ ሲመቱህ ተማታ፣ ሲሰድቡህ ተሳደብ ሁሌ እያለቀስክ አትምጣ ይለዋል። ዮናስ ግን ታጥቦ ጭቃ።አገሌ መታኝ፣አገሌ ሰደበኝ እያለ ሁሌም ወደ አባቱ። አንድ ቀን ቤት ቁጭ እያለቀሰ መጣ።አባቱም ተናዶ ደሞ ዛሬ ማን መታህ? አለዉ። እሱም ሰድበዉኝ ነው አለ እንባዉን እየጠረገ። አባቱም ምን ብለው ሰደቡህ? አለዉ። ዮናስም "የሃብታም ልጅ" ብለው አለ።ሁላችን የልጅ ነገር ብለን ሳቅን። እንግዲህ ስድብ እናርገዉ ከተባለ ሁሉም ቃል ስድብ ይሆናል። አንተ ሃኪም፣አንተ መሃንዲስ፣አንተ አስተማሪ ...ወዘተ።ዮናስ አሁን የ 20 ልጅ ነዉ ። ይሄን ገጠመኝ ልጅ ስለነብር አያስታዉስም። ግን ካደገ በሁዋላ አባቱ እያስታወሰ የልጅነት ጸባዩን ይነግረዋል። አሁን አሜሪካ እየሰራ ይማራል። ኑሮ ሲከብደዉ የሃብታም ልጅ እየተባልኩ አባቴ ጋር ብኖር ይሻለኛል እያለ ይቀልዳል። "እረኛ" የምትል ቃል ያንጫጫቸዉ ሁሉ ከ5 አመቱ ዮናስ በአስተሳሰብ ምንም አይለዩም።ሳይብሱም አይቀሩም እንዳያያዛቸዉ። ለመሆኑ "እረኛ" ምን ማለት ነው?ስድብስ ነው ወይ?አሮሞወችስ እረኛ ከልነበሩ ምን ነበሩ? 1- የመዝገበ ቃላት ትርጉም "እረኛ" ማለት ከብትን አሠምርቶ ወደ ክፉ ቦታ እንዳይሔድ የሚጠብቅ ማለት ነዉ።በእንግሊዝኛዉም ተመሳሳይ ነው።ምንም ማብራራት አይጠይቅም ።ስራ ሁሉ ደግሞ ክቡር ነዉ።አለምን አለም ያረጋት ሁሉም ስዉ በተለላይ ሞያ መሰማራቱ ነው። ዛሬ አለም የሚጠጣዉን ቡና ያበረከተዉ ካልዲ የሚባል የፍየል እረኛ አይደለምን? 2-"እረኛ" በመጽሃፍ ቅዱስ ዉስጥ በመጽሃፍ ቅዱስ ዉስጥ እረኛ" የሚል ቃል ቢያንስ 6 ቦታ ተጠቅሶ ይገኛል። እነሱም: - ትንቢተ ኢሳይያስ 40:11 መንጋውን እንደ እረኛ ያሰማራል፥ ጠቦቶቹን በክንዱ ሰብስቦ በብብቱ ይሸከማል፥ የሚያጠቡትንም በቀስታ ይመራል። -ትንቢተ ሕዝቅኤል 34:23 በላያቸውም አንድ እረኛ አቆማለሁ እርሱም ያሰማራቸዋል፥ እርሱም ባሪያዬ ዳዊት ነው፤ ያሰማራቸዋል እረኛም ይሆናቸዋል። ትንቢተ ሕዝቅኤል 37:24 ባሪያዬም ዳዊት ንጉሥ ይሆናቸዋል፤ ለሁሉም አንድ እረኛ ይሆንላቸዋል፤ በፍርዴም ይሄዳሉ ትእዛዜንም ይጠብቃሉ ያደርጓትማል 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 5:4 የእረኞችም አለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማያልፈውን የክብርን አክሊል ትቀበላላችሁ። የዮሐንስ 10:11 “መልካም እረኛ እኔ ነኝ፤ መልካም እረኛ ሕይወቱን ስለ በጎቹ አሳልፎ ይሰጣል ወደ ዕብራውያን 13:20 በዘላለም ኪዳን ደም ለበጎች ትልቅ እረኛ የሆነውን ጌታችንን ኢየሱስን ከሙታን ያወጣው የሰላም አምላክ፥ ከላይ እዳየነው "እረኛ" የምትል ቃል ለጥሩ ነገር እንጂ መጽሃፉም በስድብ አይጠቀምበትም። ትርጉሙም መጋቢ፣ ጠባቂ፣ ተንከባካቢ ማለት ነው። 3-አሮሞወችስ እረኛ ከልነበሩ ምን ነበሩ? አሮሞወቹ እረኛ ነበሩ ማለት አኮ: ወተቱን ይጠጡ ፣እርጎዉን፣ስጋዉን፣አይቡን አንደ ልብ ይበሉ ነበር ማለት ነዉ።ይሄ ምኑ ክፉ ነው?ነዉሩ ምን ላይ ነው? አሁንስ ቢሆን አኦሮሞወች ላም አላቸዉ አይደል አንዴ?አለም በሙሉ ከብት ያረባ የል አንዴ? የት ሃገር ነው ከብት ማርባት ስድብ ና ዉርደት የሆነዉ? አሮሞወችስ ለከብት ሲያረቡ ላሞቸ ከአውሬ የሚጠብቅላቸዉ ማን ነበር? መላእክት ከሰማይ ወርደው ወይስ አሮሞወች እረኛ ከቻይና ና ህንድ እያስመጡ ወይስ በሮቦት በመታገዝ? ላሞች ለምለም ሳር ና ጥላ ስር የሚሰማሩት በርቀት መቆጣጠሪያ ወይስ በእረኛ? ከቤት ለሳር ግጦሽ የወጣ ከብት ቤቱ የሚመለሰዉ በጂፒኤስ መታገዝ ነበር ወይስ በእረኛ? ቸር አንሰንብት። የጣናዉ ከምድረ አዉሮፓ yetanawlij2000@gmail.com
    February 14