Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Ejersa
Member
Posts: 3976
Joined: 05 Nov 2019, 10:39

አሁን ሙሉ በሙሉ ሰላም ነው።

Post by Ejersa » 10 Nov 2019, 10:54

ትላንት ቅዳሜ ጥቅምት29/2012 ዓ.ም በግቢው ውስጥ ኳስ በሚያዩ በኳስ ደጋፊዎች የተፈጠረች ትንሽ ግጭት፣ ከምሽቱ 6፡30 ቡሃላ ከመጠን በላይ መጠጥ ጠጥተው ወደ ግቢው በገቡ ተማሪዎች ተባብሶ እረብሻ ተፈጥሯል። እረብሻውም ወደ ግጭት ተለውጦ ለ2 ተማሪዎች ሞት እና ለተወሰኑ ተማሪዎች መጠነኛ ገዳት መድረስ ምክንያት ሁኗል። አሁን በዩንቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ነው ያለሁት፣ ሁሉም ነገር ወደ ነበረው ሰላም ተመልሷል። የወልዲያ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ እና የዞን አመራሮች ወደ ግቢው ገብተው የተማሪዎች ተወካዮች ጋር ውይይት አድርገዋል።

ከውይይቱ ቡሃላም ለችግሩ ምክንያት የሆኑ፣ ተማሪዎችን በብሄር ከፍለው ወደ ግጭት ለማስገባት ተልዕኮ ይዘው የገቡ ተማሪዎችና ሌሎች አካላትን የፀጥታ አካላቱ በፍጥነት አድኖ ለህግ እንዲያቀርብም ተወስኗል።

ከአንድ ከትግራይ ክልል ተማሪ ጋር ተገናኝተን እንደነገረኝ ከሆነ፣ ግርግሩ ከተነሳ ቡሃላ ነገሩን ወደ ረብሻ የቀየሩት ልጆች ወዲያውኑ ከግቢው ተሰውረዋል። የፀጥታ አካላትም በወቅቱ ስላልደረሱልን ጉዳቱ እስከ ሞት ደርሷል። ግጭቱ የተነሳው በሁለት ግሩፓች ቢሆንም፣ እየቆየ ግን የብሄር መልክ ለማስያዝ እየተሞከረ ነበር። እኛ ከትግራይ ክልል የመጣን ልጆች ግን ቀድመንም ከእንደዚህ አይነት ግርግር እንድንርቅ ስለተስማማን ቤተሰብም አደራ ስላለን፣ አንድም የትግራይ ተማሪ ረብሻው ላይ አልገባም፣ አንድም የትግራይ ተማሪም ላይ ጉዳት አልደረሰበትም ብሎኛል። ሆስፒታል ተገኝቸም ተማሪው የነገረኝን እውነት አረጋግጫለሁ።

ባሁኑ ሰአት ህክምና የተደረገላቸው ተማሪዎችም ወደ ግቢያቸው እየተመለሱ ሲሆን፣ የፀጥታ አካላትም የችግሩን ፈጣሪዎች ከተማ ውስጥ ሳይቀር እያደኑ ለህግ እያቀረቡ ነው። ግቢው አሁን ሙሉ በሙሉ ሰላም ነው።

ከዚህ በተጨማሪም ግጭቱን የብሄር መልክ እንደያዘ አድርገው የእለት እንጀራቸውን የሚያበስሉ ግለሰቦች የሚለቁትን አሉባልታ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሊያወግዘው ይገባል። ግቢው ውስጥ የተፈጠረው ሀቅ እነዚህ አካላት እንደሚሉት የብሄር ግጭት አይደለም።

በዚህ አጋጣሚ ግን የወልዲያ ዩንቨርስቲ አመራሮችም እራሳቸውን ሊፈትሹ እንደሚገባ ሊታወቅ ይገባል። በቅድሚያ ከመግቢያ ሰአት ውጭ ያውም የሰከረ ተማሪ ወደ ግቢ የሚገባበት አሰራር እንዴት እንደተፈጠረ!?

ከብዙ ተማሪዎችም እንደተነገረን በወቅቱ ግቢው ውስጥ የነበሩ የጥበቃ እና የተማሪ ፕሮክተሮችን የፀጥታ ሀይል በፍጥነት እንዲጠሩ ቢነገራቸውም የፀጥታ ሀይሉ በፍጥነት እንዲደርስ አልተደረገም፣ ለምን!?

በመጨረሻም የወልዲያ ከተማ ወጣቶችና ትላልቅ አባቶች የተጎዱ ተማሪዎችን ሆስፒታል ድረስ እየሄዱ እየጠየቁና አይዟችሁ ሲሉም ታዝቤያለሁ፣ የወልዲያ ወጣትም በቁጭት አጥፊዎቹን የማደኑን ስራ ከፀጥታ እካላት ጋር በመተባበር እያገዘ ነው፣ በዚህም አጋጣሚም የወልዲያ ወጣት 'ለወልዲያ ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች' አለኝታነቱን እያሳየ ነው።

እንደ Solomon Addisie አይነት የወልዲያ ልጆች፣ ሆስፒታል ድረስ በመሄድና ከኪሳቸው አውጥተው ሚሪንዳ ገዝተው ለተጎዶ ተማሪዎች ሲሰጡ ታዝቢያለሁ። የሚያኮራና የስልጡን ሰው መገለጫ ነው። በርቱ።

ህይወታቸውን ላጡ ተማሪዎች ጓደኞች፣ቤተሰቦችና ወዳጆች መፅናናቱን አብዝቶ ይስጣቸው።

Anteneh Berhanu በቦታው ተገኝቶ ያጠናቀረው መረጃ ነው።

Ejersa
Member
Posts: 3976
Joined: 05 Nov 2019, 10:39

Re: አሁን ሙሉ በሙሉ ሰላም ነው።

Post by Ejersa » 10 Nov 2019, 11:48

መንግስት ህግን የማስከበር ግዴታ ቢኖርበትም ተማሪዎችም የፖለቲካ አጀንዳ ከመቀበል ወጥተው ትምህርታቸው ላይ ብቻ ማተኮር አለባቸው!
Ejersa wrote:
10 Nov 2019, 10:54

Post Reply