Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Revelations
Senior Member+
Posts: 20941
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

የመስከረም 4 የሰልፍ አስተባባሪ ቀሲስ ምትኩ ታስረዋል

Post by Revelations » 13 Sep 2019, 16:49

Please wait, video is loading...


Revelations
Senior Member+
Posts: 20941
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: የመስከረም 4 የሰልፍ አስተባባሪ ቀሲስ ምትኩ ታስረዋል

Post by Revelations » 13 Sep 2019, 17:18

★ ቀሲስ ምትኩ ደምሌን በአስቸኳይ ፍቱአቸው !!!

★ መንግሥት ሆይ በገዛ እጅህ ነገር አታበላሽ። መብትን መጠየቅ አያሳስርም። ይሄ እንደ ፖለቲካው አይደለም። ካህን አስረህ ዝም የሚልህ አይኖርም። እየመከርኩ ነው።

•••
ከመስከረም 4ቱ ሰልፍ አደራጆች መካከል በጥብዓት ሲንቀሳቀሱ ከነበሩት መካከል የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ወኪሉ ቀሲስ ምትኩ ደምሌን የፌደራል ደኅንነቶች ነን ያሉ አካላት አሁን እንደያዙአቸውና ወደ ፖሊስ ጣቢያም እንደወሰዷቸው እየተነገረ ነው።

•••

ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጋር በነበረው ወይይት በኃይልና በሥልጣን በጥበብም ይሞግቱ የነበሩት እሳቸው እንደነበሩም ተነግሯል። ዛሬ ከክልል ፕሬዘዳንቶች ጋር በነበረው ስብሰባም ዋነኛ ሞጋች እንደነበሩ ተሰምቷል።

•••
የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅን ብልሹ አሰራርም በጥብአት ተሟግተው የኮሌጁን ችግር እንዲቀረፍ በፅኑ የታገሉም ካህን ናቸው ቀሲስ ምትኩ። በእነ መብራቱ ኪሮስ ጥርስ የተነከሰባቸው ካህን ምትኩ ዛሬ ከክልል ፕሬዘዳንቶች ጋር በነበረው የኮሚቴ ውይይት ላይ ቆይተው ሲመለሱ ቅድስት ማርያም አካባቢ በደኅንነቶች ታፍነው በቁጥጥር ስር መዋላቸው ነው የተነገረኝ። ስልካቸው ተዘግቷል። ጥሪም አይቀበልም።

•••
እናም ወዳጄ ሰልፉ ተደረገም አልተደረገ አውሬው እንደሆን መናደፉን አይተውህም። ወይ ቀድሞ አለመጀመር ነበር። አሁን ሁሉ ነገር ጫፍ ከደረሰ በኋላ መንሸራተት ኮሚቴዎቹንም ሆነ ቤተ ክርስቲያኒቱን ከመበላት አያድናቸውም።

•••

ሻሎም ! ሰላም !

ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
መስከረም 2/2011 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።

Revelations
Senior Member+
Posts: 20941
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: የመስከረም 4 የሰልፍ አስተባባሪ ቀሲስ ምትኩ ታስረዋል

Post by Revelations » 13 Sep 2019, 19:39

----------- ታሪካዊ ስህተት ----------------
የመንግስት ማደንዘዣ መርፌ ለተወጋችሁ
እኔ ግን አልቀርም

🌿🌿🍁🌿🌿

ወይኔ እናቴ ተዋሕዶ ለካ ሰው የላትም የመንግስት የማደንዘዣ መርፌ እንዴት ተወጋችሁ በእውነት ትልቅ ዋጋ የከፈልንበት ቀን ነው ስሙኝ እኔግን እግዚአብሔር ምስክሬ ነው ብቻዬ አልቅሼ ቢሆን እመለሳለሁ መስከረም 4 አልቀርም።

መንግስት " የደህንነት ስጋት ስላለብኝ ነው አለ" እኔ ምለው ምንድነው የደህንነት ስጋቱ እስኪ በዝርዝር ይነገረን ስጋት አለብኝ ካለ ጥብቅ ቁጥጥር ማድረግ ነው እኛ በሃገራችን የዜግነት መብታችን እንዴት ይገፈፋል ይህ ተራ ትርክት ነው ሆን ተብሎ የተፈጸመ ታሪክ የማይረሳው ውንብድና ነው።

እስካሁን በሃገራችን በኢትዮጵያ ታሪክ ሰላማዊ ሰልፍ ሲደረግ :-

➾ ቤተመንግስት ተጠርቶ የተጠየቀ የለም
➾ የክልል ፕሬዝዳንቶች ጋር ውይይት የተቀመጠ የለም።

ለእኛ ለኦርቶዶክሳውያን መስከረም 4ቱ ሰልፍ
ከምንተነፍሰው አየር ከምንጠጣው ውኃ ሁሉ በላይ አስፈላጊያችን ነበር። እውነት ነበር ጥቅምት 30 ለእኔ ሞራሌ ከሞተና ከደቀቀ በኃላ አይ ተውኝ እስኪ ጉዟችን ቀራንዮ ነበር ቤተመንግስት ሆኖ አረፈው። እኔ ግን ጉዞዮ እስከ ቀራንዮ ነው አልቀርም። ጠብቁኝ የምፋታችሁ እንዳይመስላችሁ። አለቀ

ይህ የመጀመሪያ በኦርቶዶክስ ላይ የተፈጸመ አሳፋሪ ድርጊት ነው። መስከረም 4 ስዘክራት እኖራለሁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን አንድ ያደረገ የልብ ሕብረ ዝማሬ የተሰማበት ነው። አይ እኔን ብቻዬን መስከረም 4 መስቀል አደባባይ ጠብቁኝ አልቅሼ እመለሳለሁ እምባዬን ወደ ሰማይ እረጫለሁ።

እኔን እወቁኝ ለቤተክርስቲያኔ ለተዋሕዶ ለአባቶቼ ክብር ስል የታመመኩ ነኝ 1000000000%%%

እመኑኝ ዛሬ በዚህ ምክንያት መስቀል አደባባይ አልወጣንም እንበል ነገ በጥምቀትና በመስቀል በዓላት ላይ የደህንነት ስጋት አለብኝ ብሎ ሽባ ያደርገናል ።


ግልባጭ ለሰራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር

ተዋሕዶ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ

ፈለገ ጎርጎርዮስ
2/1/2012

AbebeB
Member
Posts: 3650
Joined: 15 Oct 2016, 10:31

Re: የመስከረም 4 የሰልፍ አስተባባሪ ቀሲስ ምትኩ ታስረዋል

Post by AbebeB » 13 Sep 2019, 20:15

Revelations,
Think of sending him bottle of local beer (Tela) and bread (dabo). That is all he might need for he missed it.

Post Reply