Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
MINILIK SALSAWI
Member
Posts: 4407
Joined: 24 Aug 2012, 12:02

መንግስት እርምት እንዲወስድ መጠየቅ እና መተቸት የለውጥ አጋርነትን ያሳያል።(ምንሊክ ሳልሳዊ)

Post by MINILIK SALSAWI » 10 Jul 2019, 14:15

መንግስት እርምት እንዲወስድ መጠየቅ እና መተቸት የለውጥ አጋርነትን ያሳያል።(ምንሊክ ሳልሳዊ)

ካለፈው ኢሕአዴጋዊ ስርዓት ወደ አዲሱ የለውጥ ኃይል ወደሆነው ኢሕአዴጋዊ ስርዐት ስንሸጋገር በለውጡ ሂደት ውስጥ የተለያዩ መሰናክሎችን እየየንና እያለፍን እንገኛለን። በዚህ የለውጥ ሂደት ባልነው መስመር ላይ በተለያዩ መንገዶች የተከሰቱ የለውጥ ማበረታቻዎችና የለውጥ እንቅፋቶችን መመልከታችን የማይካድ ሐቅ ነው።

የለውጡን ጉዞ ከሚደግፉ ጀምረው እስከ በጥንቃቄ እንመልከተው እስከሚሉት ድረስ የሚቃወሙትን ጨምሮ የተለያዩ አመለካከቶችን እያየን እየሰማን ነው። እንዲሁም ከፖለቲካ ሴራ ጀምሮ እስከ ግል ጥቅም አነፍናፊ አደርባይ ፤ ከለውጥ አደናቃፊ ጀምሮ እስከ ጭፍን ደጋፊ ድረስ ሕሊናው ከታወረ እስከ ተገለጠለት ድረስ በርካታ ውስጠቶችን ታዝበናል። የለውጡ ጉዞ በተሳካ መንገድ እንዳልሔደ ከሚናገሩና ለውጡን ከሚሸረሽሩ የውስጥ ቦርቧሪዎች ድረስ ብዙዎችን ስናይ ለውጡ የሰጠው እድሎችን እየተጠቀም ነው ከሚሉ ተቃዋሚዎች ጀምሮ እስከ ተረኝነትን ተገን አድርገው እስከሚያሽካልሉ ጽንፈኛና ዘረኛ መንገኝነት እስከተጠናወታቸው ቡድኖች ያለውን እውነት ታዝበናል።

መንግስት በለውጥ ሂደት ውስጥ እንዳለን በሚነግረን ሰዓት አደርባዮች፣ የፖለቲካ አረሞች ፣ የውስጥ ቦርቧሪዎችና አስመሳዮችን አስመልክቶ የለውጡ መሪ አካል የእርምት እርምጃዎችን እንዲወስድና ለውጡ የተሳካ እንዲሆን ያላሰለሰ ጥረት እንዲደረግ ለሃገር አንድነትና ለሕዝብ ሰላም የሚጮኹ አካላት በመንግስት ላይ ግፊት በማድረግ እየታገሉ ሲገኙ ይህ ትግል መንግስት እርምት እንዲወስድ መጠየቅ የለውጥ አጋርነትን ያሳያል።

ሕግና መንግስታዊ ስርዓት እንዲከበር የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ የሚታገሉ አካላት መንግስት እርምት እንዲወስድ መተቸታቸው በበጎ ጎኑ ለመመልከት አልታደልንም። መንግስት አምባገነን እንዲሆንና ከሕዝብ ጋር እንዲጋጭ በመንግስት ጉያ የተወሸቁ ቡድኖችና ግለሰቦች በጭፍን ለሃገር አደጋ እየሆኑ እንደሚገኙ መንግስት በጥሞና ሊገነዘብ ይገባል። የለውጡ ዋና አደናቃፊዎች በመንግስት ጉያ የተደበቁ ጽንፈኞችና የድል አጥቢያ አርበኞች እንጂ መንግስት እርምት እንዲወስድ የሚተቹና የሚመክሉ አካላት አይደሉም።

መንግስትም ሆነ በመንግስት ውስጥ በቅንነት ለለውጡ እየሰሩ የሚገኙ አካላት ያለውን እውነት በጥልቀት እንዲገነዘቡ ራሳቸውን ማዘጋጀት ይጠበቅባቸዋል። የለውጡ ዋና ግቦች ለሕዝቦች ተጠቃሚነት እንዳይውሉ በየክልሉና በየማሕበራዊው ሚዲያ የጥላቻ መርዞችን የሚረጩ ፅንፈኞችንና የስልጣን ጥመኞችን መንግስት በጥንቃቄና በንቃት ተከታትሎ እርምጃ ሊወስድባቸው ይገባል። ባሁን ወቅት የለውጡ ዋና አደናቃፊዎች የውስጥ ለውስጥ ቅስቀሳ የሚያደርጉ፣ የራሳቸውን ቡድን በሕቡህ እና በግልፅ አሰማርተው የሚበጠብጡ፣ ተመሳስለው ሃገርንና ሕዝብን ለአደጋ የሚዳርጉ፣ ዘርን ተገን አድርገው ለመጠፋፋት የሚሰሩ፣ በፖለቲካ ሴራ ወደኋላ የሚጎትቱ በመንግስት ጉያ ስር የተወሸቁ ጥቅመኞች መሆናቸውን መንግስት ጠንቅቆ አያውቅም ማለት የዋሕነት ነው።

በየክልሎችና በዋና ከተማዎች የሚነሱ ትልቅም ይሁኑ ትንንሽ ግጭቶችና መፈናቀሎች ጥላቻዎችና ሴራዎችን በግንባር ቀደምትነት የሚያንቀሳቅሱ የመንግስት መዋቅር አካላትና ውርንጭሎቻቸው መሆኑን በቅርብ ጊዜያት ያየነውና የተገነዘብነው ጉዳይ ሲሆን እንዚህንም ፀረ ለውጦች መንግስት ማሰሩና ለፍርድ ማቅረቡ ባይካድም የቀሩ በፅንፍና በጥላቻ የሰለጠኑ እኩያን መኖራቸውንም አምነን መቀበል አለብን። እነዚህ አሁንም በየጎሯቸው ተሰግስገው መርዛቸውን እየረጩ ይገኛሉ።ስለዚህ መንግስት የለውጡ ሂደት በተፋተነ መልኩ ለማስኬድ አርምጃዎችን ሊወስድ ይገባል።

ከዚህም ጎን ለጎን በተቃዋሚና በጭፍን ጭብጨባ የታወሩ በጎ ነገር የማይታያቸው የስደት ጥቅማ ጥቅም ሕሊናቸውን ያሳወራቸው በውጪው አለም ምቾትን ተደግፈው ለደሃው ሕዝብ ሞትን የሚደግሱ ሆዳሞች ሞልተዋል። ይህም የማይካድ ሐቅ ነው። ዜግነታቸውን ለሆዳቸው ቀይረው በማይረባ የፖለቲካ ቀመር በሕዝብ ደም ቁማር መጫወት የሚያምራቸው በውጪ የሚኖሩ አካላትንም አደብ ማስገዛትና በማይጥማቸው ጉዳዮች ላይ በስነስርዓት እንዲታገሉ በሕግ መስመር ማስያዝ ያስፈልጋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ በመረጃና ማስረጃ ተደግፈው በትክክለኛው መንገድ መንግስትን የሚቃወሙ ጠንካራ ሃገር ወዳድ ተቃዋሚዎች እንዳሉ መዘንጋት የለበት። ሃገር ወዳድ ዲያስፖራ ተቃዋሚዎች ለመንግስት ብርታት እንጂ ውጋት አይደሉም።

መንግስት እርምት እንዲወስድ መጠየቅ የለውጥ አጋርነትን ያሳያል ስንል መንግስትን በጭፍን የሚደግፉ አካላት ሊገነዘቡትም ይገባል። በሃገሪቱ ገና ሀ ብሎ የጀመረው ለውጥን ከማበረታታት ጀምሮ እርምቶችም እንዲወሰዱ እስከመተቸት መጓዝ ማለት ለለውጡ እምርታ መስራት ማለት ሲሆን መንግስትን በጭፍን መደገፍ ማለት ደግሞ በመንግስት ጉያ የተሸሸጉ የለውጥ መሰናክሎችን ማግነንና ማበረታታት መሆኑ ሊታወቅ ይገባል። መንግስት የለውጥ እንቅፋቶችን እያስወገደ ለሕግ የበላይነት፣ ለሃገር አንድነትና ሰላም እንዲሰራ ሁላችንም የዜግነት ድርሻችንን ልንወጣ ሲገባ በመንግስት ላይ የሚሰነዘሩ ትችቶችን በጭፍን መቃወም የሃሳብ ነጻነት እንዳይገለጽ ለማፈን የሚንቀዥቀዡ መንግስታዊ አካላትንና የድል አጥቢያ አርበኞችንም ልንዋጋ ይገባል። መንግስት እንደሚበረታታው ሁሉ ሊተችም ይገባል ይህ ማለት ደግሞ መንግስት እርምት እንዲወስድ መጠየቅ የለውጥ አጋርነትን ያሳያል።መንግስት ለምን ተተቸ ብለው ቡራ ከረዩ የሚሉና የለውጥ አደናቃፊዎችን እኩይ ጉዞ የሚደብቁ አካላትንም አጥብቀን ልንዋጋቸው ይገባል። መንግስትም ራሱን እያረመ የውስጥ ቦርቧሪ የሆኑ የፖለቲካ አረሞቹን የራሱን ሰዎች ከጎኑ እየነቀለ ታሪካዊ የለውጡን ጉዞ ከሕዝብ ጋር በመሆን ለስኬት ሊያበቃው ይገባል።(ምንሊክ ሳልሳዊ)

mollamo
Member
Posts: 600
Joined: 12 Dec 2018, 12:22

Re: መንግስት እርምት እንዲወስድ መጠየቅ እና መተቸት የለውጥ አጋርነትን ያሳያል።(ምንሊክ ሳልሳዊ)

Post by mollamo » 10 Jul 2019, 16:09

ምንሊክ ሳልሳዊ
I agree with the last statement.
"መንግስትም ራሱን እያረመ የውስጥ ቦርቧሪ የሆኑ የፖለቲካ አረሞቹን የራሱን ሰዎች ከጎኑ እየነቀለ ታሪካዊ የለውጡን ጉዞ ከሕዝብ ጋር በመሆን ለስኬት ሊያበቃው ይገባል"
The problem in todays Ethiopia is the governments actions. We see lawlesnnes in one part of Ethiopia and the government simply not doing its job to safegurd its people, on the other hand we see people put in prison simply because they criticize the governments actions.
This is not the way to lead a country that have so many problems.

Degnet
Senior Member+
Posts: 23765
Joined: 16 Feb 2013, 11:48

Re: መንግስት እርምት እንዲወስድ መጠየቅ እና መተቸት የለውጥ አጋርነትን ያሳያል።(ምንሊክ ሳልሳዊ)

Post by Degnet » 10 Jul 2019, 16:58

mollamo wrote:
10 Jul 2019, 16:09
ምንሊክ ሳልሳዊ
I agree with the last statement.
"መንግስትም ራሱን እያረመ የውስጥ ቦርቧሪ የሆኑ የፖለቲካ አረሞቹን የራሱን ሰዎች ከጎኑ እየነቀለ ታሪካዊ የለውጡን ጉዞ ከሕዝብ ጋር በመሆን ለስኬት ሊያበቃው ይገባል"
The problem in todays Ethiopia is the governments actions. We see lawlesnnes in one part of Ethiopia and the government simply not doing its job to safegurd its people, on the other hand we see people put in prison simply because they criticize the governments actions.
This is not the way to lead a country that have so many problems.
Agree with both of you.

Post Reply