Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Maxi
Member
Posts: 3685
Joined: 06 Mar 2014, 04:33

ፌድራል ፖሊስ ወደ መቀሌ ተላከ!!

Post by Maxi » 10 Nov 2018, 19:02

ከፌድራል ፖሊስ ተመርጠው የተውጣጡ አባላት የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ይዘው መቀለ የመሸጉ የMETEC እና የደህንነት ሰወችን በቁጥጥር ሥር ለማዋል ወደ ትግራይ ሄደዋል።

#ትኩስ_መረጃ
---------------------
"የጠ/ሚር አብይ ጥርስ እየተሳለ ነው። አድፍጦ መገዝገዝ ጀምሯል። የህወሀትን የጥፋት እጆች ከየክልሉ በመቁረጥ የቀጠለው ህወሀትን የማፈራረስ እርምጃ ወደ ጡዘቱ የደረሰ መስሏል።"

(መሳይ መኮንን)
----------------

በትናንትናው እለት የመከላከያ እና የደህንነት ሰዎች ሲግናል የሚገኘው መኖሪያ ቤታቸውን ለመፈተሽ የሄደውን ግብር ኃይል የግቢው ጠባቂ ወታደሮች አናስገባም ብለው ቢያግዱም በኢታማጆር ሹሙ ጀነራል ሠዐረ ቀጥተኛ ትእዛዝ ተሰጥቷቸው ክፍት አድርገዋል።

የተላከው ግብር ኃይልም በተጠርጣሪ ወንጀለኛ የመከላከያ እና የደህንነት ሰዎች ቤት በመግባት አስፈላጊውን መረጃ ወስዷል።

በተጨማሪ የውስጥ አፈትላኪ ምንጮች መቀሌ የመሸጉት፡ ከአክሱም ሆቴል ውስኪ እየላፉ፡ ለህግ የበላይነት እጅ አንሰጥም ያሉት የህወሀት ባለሟሎች ቀን እየጨለመባቸው ስለመሆኑ የሚያረጋግጡ ምልክቶችን እያየን ነው።

ጠ/ሚር አብይ አህመድ ከሰሞኑ እየወሰዷቸው ያሉት እርምጃዎች የመንግስታቸውን ቁመና እያሳመረው እንዲሄድ አድርጎታል። ቀደም ብለው በደህንነት መስሪያ ቤቱ ውስጥ ያለውን የህውሀት የበላይነት መስበር የቻሉት ጠ/ሚሩ ወደ መከላከያው ፊታቸውን አዙረው ስር ነቀል ለውጥ ጀምረዋል።

ከህዝብ ልብ መግባት ያቃተውና፡ በቴሌቪዝን፡ በመከላከያና በደህንንነቱ እየተደገፈ ከቤተመንግስት የቆየው የህወሀት አገዛዝ የመጨረሻው መደበቂያው እየተደፈነበት ይገኛል። በቅርቡ የተሞከረው መፈንቅለ መንግስት ለዶ/ር አብይ እርምጃ መፍጠን አስተዋጽኦ አድርጓል።

ህወሀትና ኦነግ ጥምረት የፈጠሩባቸው የሁለት ጊዜያት የግድያ ሙከራዎች ዶ/ር አብይ በአፋጣኝ ደህንነቱንና መከላከያ ውስጥ የተከመረውን ቆሻሻ እንዲያስወገዱ ገፋፍቶአቸዋል።

ባለፉት ሁለት ቀናት በመከላከያ ውስጥ የተወሰደው እርምጃ የለውጥ ሂደቱ ከተጀመረ ወዲህ ካየናቸውና ከሰማናቸው አጀብ ካሰኙን የዶ/ር አብይ ውሳኔዎች አንዱና ዋናው ነው ማለት ይቻላል። እሳቸውም የመከላከያ አዛዦችን ሰብስበው በተናገሩ ጊዜ ያሉት ይሄንኑ ነው።

''በኢትዮጵያ ውስጥ ለውጡ ከመጣበት ካለፉት 7 ወራት ወዲህ ትርጉም ያለውና መሬት የረገጠ ስራ የተሰራው በሃገር መከላከያ ሚኒስቴር ውስጥ ነው'' ብለዋል ጠ/ሚሩ። ልክም ናቸው። አቅም ያለው መከላከያ ውስጥ ነው። ሰራዊቱን ያልያዘ መንግስት የቱን ያህል ህዝባዊ ተቀባይነት ቢኖረውም እንደጸጉራም በግ ውጭው እያማረ ከውስጥ እየሞተ ሊመጣ የሚችል አይነት ነው። ህወሀት በዘርና ጎሳ ያዋቀረውና በፍጹም የበላይነት ቀፍድዶ የያዘውን መከላከያ መቆጣጠር ደግሞ የድሎች ሁሉ ድል ነው ማለት ይቻላል። ከመነሻው ስጋቴ የነበረው መከላከያን ከህወሀት እጅ ፈልቅቆ ለመውሰድ የጠ/ሚር አብይ መንግስት እንዴት ይቻለዋል? የሚል ነበር። አሁን የማየው ስጋቴን የሚቀርፍ ነው።

በመከላከያው ላይ የተወሰደው እርምጃ ህውሀት ላይ ያነጣጠረ እንደሆነ መረዳት የሚቻል ነው። መከላከያው የበላይ አመራሩ በአንድ መንደር ልጆች የተያዘ ሆኖ ቆይቷል። ሰባቱም የመከላከያ ስታፍ መምሪይያዎች በህወሀት ሰዎች የተያዘበት፡ ኤታ ማዦር ሹምነቱን በርስትነት የተቆጣጠሩበት፡ ቁልፍ የሆኑ የመከላከያ መዋቅሮችን የትግራይ ተወላጆች ብቻ እንዲይዙት ከፈጣሪ ጭምር ትዕዛዝ የተሰጠ እስኪመስል የደረሰበትን ታሪክ ጠ/ሚር አብይ ግልብጠውት አረፉት።

ከ160 በላይ ጄነራሎችና የጦር አዛዦች የተሰናበቱበት የሰሞኑ እርምጃቸው በዋናነት ይሄንኑ የህወሀትን የበላይነት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማጥፋት መሆኑን የውስጥ የመረጃ ምንጮች ገልጸዋል። ከክፍለጦር አዛዥነት እስከ እዝ ኣዛዥነት በአንድ ስፍራ ከአንድ በላይ የተመሳሳይ ብሔረሰብ ተወላጆች እንዳይኖሩ ተደርጓል ብለዋል ጠ/ሚሩ። ይህ እንግዲህ ጠ/ሚር አብይ የህግ የበላይነትን አሰፍናለሁ ብለው በተደጋጋሚ ለሚገቡት ቃል ማስፈጸሚያ የሚሆናቸው ትልቅ አቅም የሚፈጥር እርምጃ ነው።

የዶ/ር አብይ አመራር ጥርስ ካወጣ አይቀር ሶማሌ ክልልን የሚያምሱትን የህወሀት ሁለቱን ጄነራሎችንም አደብ ማስገዛት አለበት። ከሶማሌላንድ እስከ ደቡብ ሱዳን ጁባ የተዘረጋውን የኮንትሮባንድ ንግድ የሚቆጣጠሩት ጄነራል አበረሃም ወልደማርያም ኳርተርና ጄነራል ገብሬ ዲላ ሰሞኑን የጥፋት እጃቸውን ዘርግተዋል። ጂግጂጋን ውጠረት ውስጥ ከከተታት ያለፈው ሳምንት ግጭት ጀርባ እነዚህ ሁለቱ የህውሀት ጄነራሎች እንደሚገኙ የሶማሌ ክልሉ ፕሬዝዳንት ነግረውናል። ታዲያ በህውሀት የንግስና ዘመን እንዳሻቸው ሲፈነጩ ለነበሩት ለእነዚህ ነጋዴ ጄነራሎች ዘንድሮም የማርያም መንገድ ተሰጥቷቸው በደም የደለበ ንግዳቸውን እንዲቀጥሉበት መደረጉ ተገቢ አይደለም። ማሰር ባይቻል ከጥፋት መንገዳቸው ማስቆም ግን ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም።

በተረፈ ተስፋው ደምቆ ይታየኛል። ሊነጋ ሲል ጨለማው እንደሚበረታ፡ በሽታ ሊለቅ ሲል ህመሙ እንደሚጸና ሁሉ ኢትዮጵያን የተጣቧት ችግሮች ሊፋቷት በዋዜማው ላይ በመሆናቸው አቅማቸው የፈረጠመ መስሏል። ግን ጊዜያዊ ነው። የዶ/ር አብይ መንግስት በመከላከያው ላይ የጀመረውን ስር ነቀል ለውጥ ካጠናቀቀ በኋላ ነገሮች መልክ መያዛቸው አይቀርም።

ቸር ወሬ እንደሰማን ለከርሞውም እንደዚያው ያዝልቀን!
Maxi
Member
Posts: 3685
Joined: 06 Mar 2014, 04:33

Re: ፌድራል ፖሊስ ወደ መቀሌ ተላከ!!

Post by Maxi » 10 Nov 2018, 19:09

TPLF in Mekele

Revelations
Senior Member
Posts: 17231
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: ፌድራል ፖሊስ ወደ መቀሌ ተላከ!!

Post by Revelations » 10 Nov 2018, 19:39

Axuamwi has checked in on social media to say he is safe. Of course he is. :lol:

tarik
Senior Member
Posts: 12845
Joined: 26 Feb 2016, 13:04

Re: ፌድራል ፖሊስ ወደ መቀሌ ተላከ!!

Post by tarik » 10 Nov 2018, 19:46

Maxi wrote:
10 Nov 2018, 19:02
ከፌድራል ፖሊስ ተመርጠው የተውጣጡ አባላት የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ይዘው መቀለ የመሸጉ የMETEC እና የደህንነት ሰወችን በቁጥጥር ሥር ለማዋል ወደ ትግራይ ሄደዋል።

#ትኩስ_መረጃ
---------------------
"የጠ/ሚር አብይ ጥርስ እየተሳለ ነው። አድፍጦ መገዝገዝ ጀምሯል። የህወሀትን የጥፋት እጆች ከየክልሉ በመቁረጥ የቀጠለው ህወሀትን የማፈራረስ እርምጃ ወደ ጡዘቱ የደረሰ መስሏል።"

(መሳይ መኮንን)
----------------
ከፌድራል ፖሊስ ተመርጠው የተውጣጡ አባላት የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ይዘው መቀለ የመሸጉ የMETEC እና የደህንነት ሰወችን በቁጥጥር ሥር ለማዋል ወደ ትግራይ ሄደዋል።

በትናንትናው እለት የመከላከያ እና የደህንነት ሰዎች ሲግናል የሚገኘው መኖሪያ ቤታቸውን ለመፈተሽ የሄደውን ግብር ኃይል የግቢው ጠባቂ ወታደሮች አናስገባም ብለው ቢያግዱም በኢታማጆር ሹሙ ጀነራል ሠዐረ ቀጥተኛ ትእዛዝ ተሰጥቷቸው ክፍት አድርገዋል።

የተላከው ግብር ኃይልም በተጠርጣሪ ወንጀለኛ የመከላከያ እና የደህንነት ሰዎች ቤት በመግባት አስፈላጊውን መረጃ ወስዷል።

በተጨማሪ የውስጥ አፈትላኪ ምንጮች መቀሌ የመሸጉት፡ ከአክሱም ሆቴል ውስኪ እየላፉ፡ ለህግ የበላይነት እጅ አንሰጥም ያሉት የህወሀት ባለሟሎች ቀን እየጨለመባቸው ስለመሆኑ የሚያረጋግጡ ምልክቶችን እያየን ነው።

ጠ/ሚር አብይ አህመድ ከሰሞኑ እየወሰዷቸው ያሉት እርምጃዎች የመንግስታቸውን ቁመና እያሳመረው እንዲሄድ አድርጎታል። ቀደም ብለው በደህንነት መስሪያ ቤቱ ውስጥ ያለውን የህውሀት የበላይነት መስበር የቻሉት ጠ/ሚሩ ወደ መከላከያው ፊታቸውን አዙረው ስር ነቀል ለውጥ ጀምረዋል።

ከህዝብ ልብ መግባት ያቃተውና፡ በቴሌቪዝን፡ በመከላከያና በደህንንነቱ እየተደገፈ ከቤተመንግስት የቆየው የህወሀት አገዛዝ የመጨረሻው መደበቂያው እየተደፈነበት ይገኛል። በቅርቡ የተሞከረው መፈንቅለ መንግስት ለዶ/ር አብይ እርምጃ መፍጠን አስተዋጽኦ አድርጓል።

ህወሀትና ኦነግ ጥምረት የፈጠሩባቸው የሁለት ጊዜያት የግድያ ሙከራዎች ዶ/ር አብይ በአፋጣኝ ደህንነቱንና መከላከያ ውስጥ የተከመረውን ቆሻሻ እንዲያስወገዱ ገፋፍቶአቸዋል።

ባለፉት ሁለት ቀናት በመከላከያ ውስጥ የተወሰደው እርምጃ የለውጥ ሂደቱ ከተጀመረ ወዲህ ካየናቸውና ከሰማናቸው አጀብ ካሰኙን የዶ/ር አብይ ውሳኔዎች አንዱና ዋናው ነው ማለት ይቻላል። እሳቸውም የመከላከያ አዛዦችን ሰብስበው በተናገሩ ጊዜ ያሉት ይሄንኑ ነው።

''በኢትዮጵያ ውስጥ ለውጡ ከመጣበት ካለፉት 7 ወራት ወዲህ ትርጉም ያለውና መሬት የረገጠ ስራ የተሰራው በሃገር መከላከያ ሚኒስቴር ውስጥ ነው'' ብለዋል ጠ/ሚሩ። ልክም ናቸው። አቅም ያለው መከላከያ ውስጥ ነው። ሰራዊቱን ያልያዘ መንግስት የቱን ያህል ህዝባዊ ተቀባይነት ቢኖረውም እንደጸጉራም በግ ውጭው እያማረ ከውስጥ እየሞተ ሊመጣ የሚችል አይነት ነው። ህወሀት በዘርና ጎሳ ያዋቀረውና በፍጹም የበላይነት ቀፍድዶ የያዘውን መከላከያ መቆጣጠር ደግሞ የድሎች ሁሉ ድል ነው ማለት ይቻላል። ከመነሻው ስጋቴ የነበረው መከላከያን ከህወሀት እጅ ፈልቅቆ ለመውሰድ የጠ/ሚር አብይ መንግስት እንዴት ይቻለዋል? የሚል ነበር። አሁን የማየው ስጋቴን የሚቀርፍ ነው።

በመከላከያው ላይ የተወሰደው እርምጃ ህውሀት ላይ ያነጣጠረ እንደሆነ መረዳት የሚቻል ነው። መከላከያው የበላይ አመራሩ በአንድ መንደር ልጆች የተያዘ ሆኖ ቆይቷል። ሰባቱም የመከላከያ ስታፍ መምሪይያዎች በህወሀት ሰዎች የተያዘበት፡ ኤታ ማዦር ሹምነቱን በርስትነት የተቆጣጠሩበት፡ ቁልፍ የሆኑ የመከላከያ መዋቅሮችን የትግራይ ተወላጆች ብቻ እንዲይዙት ከፈጣሪ ጭምር ትዕዛዝ የተሰጠ እስኪመስል የደረሰበትን ታሪክ ጠ/ሚር አብይ ግልብጠውት አረፉት።

ከ160 በላይ ጄነራሎችና የጦር አዛዦች የተሰናበቱበት የሰሞኑ እርምጃቸው በዋናነት ይሄንኑ የህወሀትን የበላይነት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማጥፋት መሆኑን የውስጥ የመረጃ ምንጮች ገልጸዋል። ከክፍለጦር አዛዥነት እስከ እዝ ኣዛዥነት በአንድ ስፍራ ከአንድ በላይ የተመሳሳይ ብሔረሰብ ተወላጆች እንዳይኖሩ ተደርጓል ብለዋል ጠ/ሚሩ። ይህ እንግዲህ ጠ/ሚር አብይ የህግ የበላይነትን አሰፍናለሁ ብለው በተደጋጋሚ ለሚገቡት ቃል ማስፈጸሚያ የሚሆናቸው ትልቅ አቅም የሚፈጥር እርምጃ ነው።

የዶ/ር አብይ አመራር ጥርስ ካወጣ አይቀር ሶማሌ ክልልን የሚያምሱትን የህወሀት ሁለቱን ጄነራሎችንም አደብ ማስገዛት አለበት። ከሶማሌላንድ እስከ ደቡብ ሱዳን ጁባ የተዘረጋውን የኮንትሮባንድ ንግድ የሚቆጣጠሩት ጄነራል አበረሃም ወልደማርያም ኳርተርና ጄነራል ገብሬ ዲላ ሰሞኑን የጥፋት እጃቸውን ዘርግተዋል። ጂግጂጋን ውጠረት ውስጥ ከከተታት ያለፈው ሳምንት ግጭት ጀርባ እነዚህ ሁለቱ የህውሀት ጄነራሎች እንደሚገኙ የሶማሌ ክልሉ ፕሬዝዳንት ነግረውናል። ታዲያ በህውሀት የንግስና ዘመን እንዳሻቸው ሲፈነጩ ለነበሩት ለእነዚህ ነጋዴ ጄነራሎች ዘንድሮም የማርያም መንገድ ተሰጥቷቸው በደም የደለበ ንግዳቸውን እንዲቀጥሉበት መደረጉ ተገቢ አይደለም። ማሰር ባይቻል ከጥፋት መንገዳቸው ማስቆም ግን ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም።

በተረፈ ተስፋው ደምቆ ይታየኛል። ሊነጋ ሲል ጨለማው እንደሚበረታ፡ በሽታ ሊለቅ ሲል ህመሙ እንደሚጸና ሁሉ ኢትዮጵያን የተጣቧት ችግሮች ሊፋቷት በዋዜማው ላይ በመሆናቸው አቅማቸው የፈረጠመ መስሏል። ግን ጊዜያዊ ነው። የዶ/ር አብይ መንግስት በመከላከያው ላይ የጀመረውን ስር ነቀል ለውጥ ካጠናቀቀ በኋላ ነገሮች መልክ መያዛቸው አይቀርም።

ቸር ወሬ እንደሰማን ለከርሞውም እንደዚያው ያዝልቀን!Maxi

Good Evening Sir

Good I want z terrorist-tigray-tplf killers 2 be arrested 2.

Good Evening SirPost Reply