Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
derreview
Member
Posts: 90
Joined: 09 Feb 2013, 11:43

በዩጋንዳ የኢትዮጵያ ኤንባሲ አዘጋጅነት የለውጥ ጉዞውን ሂደት የሚዳስስ ህዝባዊ ስብሰባ ተካሄደ!

Post by derreview » 10 Nov 2018, 16:24

በዩጋንዳ የኢትዮጵያ ኤንባሲ አዘጋጅነት የለውጥ ጉዞውን ሂደት የሚዳስስ ህዝባዊ ስብሰባ ተካሄደ!

ህዳር 01 ቀን 2011ዓ/ም ከሠዓት በኋላ በዩጋንዳ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በኤንባሲያቸው ቅጥር ግቢ በወቅታዊው የሃገራችን ጉዳዮች ዙርያ ነጻ ውይይት መደረጉን ፔን ዘ ኢትዮጵያ ዘገበ።
የአሳዳጅና ተሳዳጅ የፖለቲካ ሽኩቻ በዶክተር አቢይና በለውጡ ኃይሎች
ድባቅ ከተመታና የመደመርና የፍቅር ጉዞ ከተጀመረ ወዲህ ለሁለተኛ ጊዜ በርካታ ኢትዮጵያዊያን በታደሙበት በዚህ ስብሠባ ላይ በክብር አምባሳደሩና በኤንባሲው ተወካዮች በቀረበው የመንደርደርያ ሃሳብ ዙርያ ሁሉን አሳታፊ ነጻ ውይይት ተደርጓል።
የተጀመረውን የለውጥ ሂደት ከዳር ለማድረስ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በህብረት ሆኖ መስራት እንደሚጠበቅበትና የ27 ዓመቱ የጭቆናና የአፈና ስርዓት በህዝባዊ ትግል ተደርምሶ ሃገራችን በለውጥ ጎዳና የምታደርገው ጉዞ በርካታ ተግዳሮቶች ቢደነቀሩበትም ለውጡ የማይቀለበስበት ደረጃ በመድረሱ የሃገሬ ጉዳይ ያገበኛል በሚል ቀና መንፈስ መንቀሳቀስ ከሁሉም ዜጋ የሚጠበቅ ዐቢይ ተግባር መሆኑ ተጠቁሟል።
በተለይ በውጭ ሃገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ወገኖች በሃገራቸው የልማትና የኢንቨስትመት ዘርፍ እንዲሳተፉ በመንግስት በኩል ምቹ ሁኔታዎች መሟላት እንዳለባቸውና የመንግስት ፖሊሲዎችም በአግባቡ ተፈትሸው በአዲስ መልክ መቀረስ እንዳለባቸውና የውጭ ምንዛሪ ማዕቀቦችንም በማስወገድ ከጎረቤት ኬንያና ዩጋንዳ ልምዶችን በመቅሰም ዘርፉን ነጻና አሳታፊ ማድረግ እንደሚገባና የጣምራ ዜግነት መብትም በህግ መረጋገጥ እንዳለበት ለሚመለከተው አካል ጥያቄ ቀርቧል።
ህገ መንግስቱም ሁሉን አሳታፊ በሆነ መልኩ ተከልሶ ጠቃሚ ህጎችን በማካተት እንደገና ሊታይ እንደሚገባውና ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ የሚረዱ ተቋማትን በማጠናከር ህዝቡ የመረጠው የስልጣን ባለቤት እንዲሆን የተጀመረውን የለውጥ ጉዞ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ በእለቱ ስብሰባ የተካፈሉ ኢትዮጵያዊያን በአንድነትና ወንድማማችነት መንፈስ ገንቢ የሃሳብ ልውውጥ አድርገዋል።
በዩጋንዳ የሚገኙ የሱማሌና የኦሮሞ ማህበረሰብን የሚወክሉ ወገኖችና በስራና በንግድ በዩጋንዳ ተሰማርተው የሚኖሩ ባለሃብቶችና ሙሁራን የታደሙበት ስብሰባ እንደነበር ሂደቱን የተከታተለው ፔን ዘ ኢትዮጵያ ዘግቦ ሁሉንም ኢትዮጵያዊያውያን ያካተተ አንጋፋ ኮሚኒቲ ለመመስረት ሂደት ላይ መሆኑንም ለመገንዘብ ተችሏል።