Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Revelations
Senior Member
Posts: 15555
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

[PHOTO] የአማራ ወጣቶች ማህበር በጎንደር ከተማ ተመሰረተ፤ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ንግግር አድርጓል

Post by Revelations » 12 Aug 2018, 08:21

የአማራ ወጣቶች ማህበር ተመሰረተ። በጎንደር ከተማ በተደረገው መስራች ጉባኤ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተወጣጡ የአማራ ወጣቶች ተሳትፈዋል።
Revelations
Senior Member
Posts: 15555
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: [PHOTO] የአማራ ወጣቶች ማህበር በጎንደር ከተማ ተመሰረተ፤ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ንግግር አድርጓል

Post by Revelations » 12 Aug 2018, 08:40

''የጎንደር ህብረት የሚባለው ለኮሎኔል ደመቀ 30,000 ሽህ ዶላር ላክንለት ብለው አውርተዋል። እኔ በበኩሌ ግን የጎንደር ህብረት የሚባል አላውቅም። ትናንትም ጎንደር ገቡ ተብሏል መልካም ይግቡ ነገር ግን የአማራን ብሔርተኝነት አደረጃጀት የሚቀበሉ ከሆነ አብረውን ሊሰሩ ይችላሉ። ሌላው በተለያዩ የአለማችን ክፍል የሚኖሩ ግለሰብ አማራዎች የላኩልኝ ገንዘብ ይኖራል፤ እሱን እቀበላለሁ። ይህ ግን የኔን ልብ ለመግዛት ከሆነ ይቅርብኝ አልፈልግም።

የአማራን ብሔርተኝነት የሚቀበል ከሆነ ማንም ይምጣ እንቀበለዋለን!!''


present
Member+
Posts: 6023
Joined: 22 Feb 2016, 17:37

Re: [PHOTO] የአማራ ወጣቶች ማህበር በጎንደር ከተማ ተመሰረተ፤ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ንግግር አድርጓል

Post by present » 12 Aug 2018, 11:15

This is great and timely. Strong Amara is important to protect Amara from ye ken jiboch and for the unity Ethiopia.

Revelations
Senior Member
Posts: 15555
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: [PHOTO] የአማራ ወጣቶች ማህበር በጎንደር ከተማ ተመሰረተ፤ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ንግግር አድርጓል

Post by Revelations » 12 Aug 2018, 13:02ይህ ጀግና የአማራን ብሎም የኢትዮጵያን ፖለቲካ እስከ መቅኔዉ ነዉ የሚያቀዉ።

ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ በስሙ ለሚነግድበት ይቅር እና ከባድ መሳርያ ለታጠቀ ጦር ወደኋላ እንዳላለ መታወቅ አለበት!

ማንኛውም በሕዝብ ደምና አጥንት የሚነግድ፣ የሕዝብ ትግል ላይ የሚቆም ፊት ለፊት ሊነገረው ይገባል!

ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ የጎንደር ሕብረት ገንዘብ ልኬለታለሁ የሚለው ሀሰት መሆኑን፣ ወጣቱም በገንዘብ እንዳይገዛ አፅንኦት ሰጥቶ ተናግሯል።

“ጎህ የሚባል አላቅም ” ብሎ አዳራሹን በድጋፍ ጩኸት ያነቃነቀዉ ኮ/ል ቀጥሎም ይህን ይናገራል።

“~”የአማራን መደራጀት የሚቀበል ከሆነ ሰይጣንም ቢሆን አብረነው እንሰራለን፣ የአማራን መደራጀት የማይቀበል ከሆነ መላዕክም ቢሆን አብረነው አንሰራም”

~አንዳንዶቹ ኮ/ል ደመቀን ይህን ገንዘብ ላክንለት ሲሉ እሰማለሁ። አልደረሰኝም። ልኬለታለሁ የሚል ካለ ከዚህ ቀርቦ ለኮ/ል ደመቀ ይህን ያህል ላኩለት ብሎ መናገር ይችላል። ከእናንተ የምደብቀው ነገር የለም። እኔ ለጥቅም፣ ነገም ከነገም በኋላ በጥቅም አልቆምም። ዛሬ ነው በፌስቡክ የማየው ። ለኮ/ል ደመቀ 30ሺህ፣ ለንግስት ይህን ያህል ሺህ ልኬያለሁ እንዳለ ተፅፏል። እውነት አይደለም። ጎንደር ሕብረት የሚባለው ለእኔ 30 ሺህ ቀርቶ አንድ ሽህ ብር አልሰጠኝም። መጀመርያ እኔ የጎንደር ሕብረትን የምደግፋቸው የአማራን ሕልውና የሚቀበሉ፣ በብሄርተኝነት እንዲደራጅ የሚቀበል ከሆነ ብቻ ነ! ”

ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ

“አማራ ኢትዮጵያን አላገኘም፣ አማራን አላዳነም፣ ተንሳፍፈናል። ከአሁን በኋላ አማራ ነኝ ማለት ኩራት፣ መልካም እንደሆነ ለማሳየት አማራ በማንነት መደራጀት ይኖርበታል። አንዳንድ ወገኖች አማራ በብሔር እንዳይደራጅ ሲሰብኩ ቆይተዋል።በዚህ ጦር ነው አማራ እንደ በግ ሲጎተት የኖረው። ለውጥ ስንደግፍ አማራነታችን፣ ማንነታችን፣ ድንበራችን፣ ጥቅማችን ተከብሮ ነው መደመር የምንፈልገው። ለአማራ ብዙ ጥያቄዎች አልተመለሱም። ስንደመር ቢያንስ የአማራን ማንነት እውቅና የሚሰጥ መሆን አለበት። የአማራ ሕልውናን የሚያምን ሁሉ ሰይጣንም ይሁን አብረን እንሰራለን። የአማራን ህልውና የማያምን፣ አማራ መስሎ ሰይጣናዊ ስራ የሚሰራ ካለ መዕላክም ቢሆን አብረነው አንሰራም። የአማራ ወጣት ስም እየነገደ፣ በገንዘብ አስራ አራት ቡድን አደራጅቶ የሚመጣ፣ አማራ ካለ፣ አሁንም እንቃወማለን! ግለሰብ ይሁን ድርጅት መጀመርያ ስለ አማራ ያለውን አቋም ማወቅ አለባችሁ። የአማራን ሕልውና የሚቀበል ከሆነ ብቻ አብራችሁት ስሩ። የማያምነውን አትቀበሉ። ኢትዮጵያዊ ከሆነ በቂ ነው ይል ነበር አማራ። አሁን ከውስጥ ው ውጭ መለየት አለብን። አማራ ክልል ተብሎ፣ አማራ ላይ ተወልዶ ለምሳሌ ከሽሬ አንድ ፍሬ አመጣች፣ አማራ መሬት ላይ በቀለ። ብርቱካኑ የአማራ ነው። አንድ የትግራይ ሰው ጎንደር ወልዶት እኛ አሳድገነው፣ አባቱ ትግሬ ስለሆነ ብቻ የአማራ ሕዝብ ስልጣን ሰጥቶት የሚሰራው ለትግራይ ነው። ይህን የሰራው ህወሓት ነው። የትግራይ ተወላጆች ካላችሁ፣ እናታችሁ አማራ አባታችሁ ትግራይ ከሆነ ወይንም አባታችሁ ትግራይ፣ ለምን አላስገቡንም ብለችሁ አትቀየሙ። እባብ ያየ በልጥ ደነገጠ ነው። ትናንት ጎንደርን ያህል አብረው ደጋፊ መስለው መኪና እንዲቃጠል ያደረጉ ጎንደር የተወለዱ ነገር ግን የህወሓት ደህንነቶች ነበሩ። ለዚህም መሰለኝ የወጣቶቹ ማህበር መስፈርት አማራ ብቻ ብሎ መስፈርት ያስቀመጠው። ቅሬታ እንዳይሰማችሁ። እኛ ለትግራይ ሕዝብ ጥላቻ የለንም። የሚከፋፍሉ ቡድኖችን ግን አሉ። ከአጎቶቻችሁ፣ ከአክስቶቻችሁ እያቆራረጧችሁ ነው። ከአማራ ተወልዳችኋል፣ በአማራ በጀት ተምራችኋል፣ በአማራ ክልል ስልጣን አላችሁ። ለአማራው ስሩ! ወጣቱ ለሆዳቸው ከሚኖሩት ተጠንቀቁ። ወጣቱ ጥላቻ ሳይኖረው መጠንቀቅ አለበት። ……ወጣቶች ከይሉኝታ፣ ከጓደኝነት፣ ነፃ መሆን አለበት። አማራዊ ጉዳይ አላማ ነው። እኔ እንድኖር ያደረገኝ ይህ ወጣት ነው። እንድንፈታ ያደረጋችሁን እናንተ ናቸው። ሕዝብ ነው! ይህ ሕዝብ ነው። ጎንደር ወጣቱን ለመከፋገል እየተሰራ ነው። ከእስር የተፈታነው ተገርፈናል ብለን የምንናገረው ለማስተማር ነው እንጅ አማራ ተገረወፌያለሁ ብሎ መናገር ሀፍረቱ ነው። እናንተ ተገረፍን ስትሉ መስማት አልፈልግም። ከህግ ውጭ መጥቶ ማንም ከእየ ቤቱ እየመጣ እየለቀመ እንዲወስድ አትፍቀዱ።

አማራ መጀመርያ የሚፈራው እግዚያብሄር፣ አላህን ብቻ ነው። የሚያከብረው ህግንና አባትና እናቱን ነው። ከዚህ የተረፈው በሕግ መሆን አለበት። ለመግደል የሚመጣ አካል ሁሉ እንደ እኔ ህይወት ይዞ ነው የሚመጣው። በስሜት እንዳንነዳ፣ ሁሉን ነገር በማስተዋል ማድረግ አለበት። አባቶችን አማክሩ። በስሜት ከተነገዳን አላማ እንስታለን። አማራ ትልቅ ሕዝብ ነው፣ ነገም ትልቅ ይሆናል። በጥቅማጥቅም እንዳንደለል። አንዳንዶቹ ኮ/ል ደመቀን ይህን ገንዘብ ላክንለት ሲሉ እሰማለሁ። አልደረሰኝም። ልኬለታለሁ የሚል ካለ ከዚህ ቀርቦ ለኮ/ል ደመቀ ይህን ያህል ላኩለት ብሎ መናገር ይችላል። ከእናንተ የምደብቀው ነገር የለም። እኔ ለጥቅም፣ ነገም ከነገም በኋላ በጥቅም አልቆምም። ዛሬ ነው በፌስቡክ የማየው ። ለኮ/ል ደመቀ 30ሺህ፣ ለንግስት ይህን ያህል ሺህ ልኬያለሁ እንዳለ ተፅፏል። እውነት አይደለም። ጎንደር ሕብረት የሚባለው ለእኔ 30 ሺህ ቀርቶ አንድ ሽህ ብር አልሰጠኝም። መጀመርያ እኔ የጎንደር ሕብረትን የምደግፋቸው የአማራን ሕልውና የሚቀበሉ፣ በብሄርተኝነት እንዲደራጅ የሚቀበሉ ከሆኑ ብቻ ነው። መጀምርያ የእነሱ አላማ ጤነኛ ከሆነ ነው የምቀበለው። …አማራን በጠላት የሚፈርጀውን መቼም ቢሆን የአማራ ወጣቶች ይቀበሉታል ብየ አላምንም”


Post Reply