Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Tintagu wolloye
Member
Posts: 1433
Joined: 02 Sep 2016, 16:59

"ቀድሞ ማመስገን ኋላ ለማማት ያስቸግራል"ነው ተረቱ።ኢሳቶች! እባካችሁ አብይነቱ ወይም እቡይነቱ ያልለየነትን አዲስ ሹም አንድ ነገር ሳይሰራ አታሞካሹት!ሳይጀመር በጭብጨባ ጥምቢራው ዞሮ ከአለቆቹ በተማረው መከፋፈል አገር ቤት ያለነውን ከተሰደዱት ግን ጠበቃ ከሆኑን ወገኖቻችን መነጠል አምሮታል!

Post by Tintagu wolloye » 16 Apr 2018, 17:54

አብይ ወይስ እቡይ?

መልሱን ከተግባሩ እስክናገኘው ለሰውየው 3A ሰጩ ተቦርነም ሆነ የኢትዮጵያን ስም አነሳ ብሎ የተደመመው ታማኝ መታገስ ይችሉ ዘንድ እንመክራለን።ሰውየው ይቅርታ የጠየቀው ለተገደሉትና ለተፈናቀሉት ይሁን ወይም ገና በእሱ ዘመን ለሚያልቁት አልታወቀም።ትንታጉ እንዳለው ያው ጭፍጨፋና መፈናቀልም በእሱ ዘመን አልቆመ።ጊዜ ስጡት ባይ ሰባክያን ሰውየው የቸገረው ጊዜ ሳይሆን ከ15 አመቱ ጀምሮ ከአደገበት የህወሀት ፖለቲካና ርእዮተ አለም ጓንታናሞ ሰብሮ መውጣት ነው።ለእዚህ ነው "ግድያውንና ማፈናቀሉን ማስቆም ነበረብን" ብሎ በደሰኮረ ማግስት ነፍሰጡር በቀየዋ በአስራ አስር ጥይት ተደብድባ የተገደለችው።መፈናቀሉ ከሀረር ወደ ሲዳሞ ተዛወረ እንጅ አልቆመም። በኦሮሞና ጌዲኦ፣መለስ በትእዛዝ ከሶማሊያ ጭኖ ሞያሌ አካባቢ በአሰፈራቸው ገሪወችና ቦረናወች መካከል ቀጥሎ ሺወች እየሞቱ እየተፈናቀሉ ነው።ይህ ህወሀት የመንግስትን መዋቅር ተቆጣጥሮ፣በስውር ተደራጅቶ የራሱን የስለላና የሽብር መረብ ዘርግቶ እንዲኖር፣የመንግስት ላይ መንግስት ሆኖ እስካለ ድረስ ይቀጥላል!!

አብይ አባይን ያህል ግዝፈት የሚኖረው፣
1) ህወሀትን ከጦሩና ደህንነት ተቋማት የመነጠረ እለት፣
2) ህወሀት በዘረፋ የገነባቸውን የኢኮኖሚ ተቋማት የወረሰና "የተበላሸ ብድር" እየተባለ የተዘረፈውን ጥሬ ገንዘብ ጨምሮ ከኤሌክትሪክ ፖል እስከ ሀይል ማመንጫ ጀነሬተሮች ከሌላው የኢትዮጵያ አካባቢ ተነቅለው ወደትግራይ የተወሰዱና የህወሀት ሀብት የሆኑ ንብረቶችን ያስመለሰ እለት፣
3) በህወሀት በግፍ ከወሎና ከጎንደር ተቆርሰው የተወሰዱ ቦታወችን፣ወልቃይት፣ፀገዴና ፀለምት፣ከማይጨው መለስ እስከ ዋጃና አካባቢዋ ያሉ የራያ መሬቶች ያስመለሰ ጊዜ፣
4)የሀገሪቱን አፋኝ አዋጅ ያነሳ፣አፋኝ ህጎችን የሻረ፣ ሁሉንም አካታች የሰላምና እርቅ ጉባኤ የጠራጊዜ፣
5) በእዚህም ጉባኤ ቢያንስ ነፃ የምርጫ ኮሚሽን፣ነፃ ቅድመ ምርጫ ስርአትን የሚመለከት የጋራ ስምምነት እንዲደረስ ያረገ ጊዜ ነው

አብይ እቡይ የሚሆንበት ምልክቶች መታየት ጀምረዋልና የብዙወቹ ህልም ቅዠት መሆኑ አያጠራጥርም።የሀገር ቤቱን ለማዳ ተቃዋሚ ሰብስቦ ግብር ሲያበላ ወጭ የሚኖረውን ወገናችንን "ዲያስፖራ" በሚል ጠቅልሎ ቤንዚን አርከፍካፊ ነገር ለኳሽ ማድረጉ ተደምጣል።ያው የእጅ እባሽ ሰጥተን የአንበሳውን ድርሻ እንወስዳለን የሚለው የእነ አቦይ ስብሀትና አባይ ፀሀየ የከረመ ብልጠት አካል ነው።

ጆሞ ኬንያታ "መፀሀፍ ቅዱስ ሰተው አንብቡ አሉን።አንብበን ቀና ስንል አገራችንን ወረው መሬቱ ሁሉ እነሱ ብቻ ሆነውበታል" እንዳለው ነው።ህወሀት ሲጨንቀው ኢትዮጵያን መጥራቱ ያልተለመደ አይደለም።መሀሙድም፣ታምራት ሞላም፣ጥላሁን ገሰሰም ረድተውታል።ባድሜን ተቆጣጠርኩ ያለ ቀን የሰቀለው እውነተኛውን ባንዲራ ነው።ሲረጋጋ ግን ኢትዮጵያም፣ባንዲራውም ሲኦል ተጣሉ።

አሁን ቢያንስ ኢትዮጵያ ከተጣለችበት ትቢያዋ ተራግፎ እንደገና ህወሀትን እንድታድን ፊት ለፊት ተጥዳለች።አገር ወዳዱ በአብይ አፍ አስራ አስር ጊዜ ሀገሩ መነሳቷ አስደምሞት ይህን እንደ ኬኒያታው መፀሀፍ ቅዱስ ሲደግም ወገኑ ደቡብ ላይ እቶን እሳት እየነደደበት መሆኑን ያጤን ይሆን?ቀደም ሲል የህወሀቱ የጌዴኦ ክንፍ " እንግዶች ነበራችሁና አገራችንን ልቀቁ" በአላቸው ላይ የፈፀመውን ግድያና ሰቆቃ፣የንብረት ውድመት ሁሉም አይዘነጋው።ዛሬ በሀረር እንደሆነው በደቡብም የኦሮሞ ወገኖቻችን "እጣ" ወጥቶ ጉጂ ከቦረና በጌዴኦ ይጨፈጨፋል።

አብይ ያለውን እየደገምን ሀገራችን እቶን እሳት ስነድባት ከማየት ተዘናግተን የተውነውን ትግል እስከ ስርአት ለውጥ መቀጠል አለብን!!

Tintagu wolloye
Member
Posts: 1433
Joined: 02 Sep 2016, 16:59

Re: "ቀድሞ ማመስገን ኋላ ለማማት ያስቸግራል"ነው ተረቱ።ኢሳቶች! እባካችሁ አብይነቱ ወይም እቡይነቱ ያልለየነትን አዲስ ሹም አንድ ነገር ሳይሰራ አታሞካሹት!ሳይጀመር በጭብጨባ ጥምቢራው ዞሮ ከአለቆቹ በተማረው መከፋፈል አገር ቤት ያለነውን ከተሰደዱት ግን ጠበቃ ከሆኑን ወገኖቻችን መነጠል አምሮታል!

Post by Tintagu wolloye » 17 Apr 2018, 03:30

አብይ አባይን ያህል ግዝፈት የሚኖረው፣
1) ህወሀትን ከጦሩና ደህንነት ተቋማት የመነጠረ እለት፣
2) ህወሀት በዘረፋ የገነባቸውን የኢኮኖሚ ተቋማት የወረሰና "የተበላሸ ብድር" እየተባለ የተዘረፈውን ጥሬ ገንዘብ ጨምሮ ከኤሌክትሪክ ፖል እስከ ሀይል ማመንጫ ጀነሬተሮች ከሌላው የኢትዮጵያ አካባቢ ተነቅለው ወደትግራይ የተወሰዱና የህወሀት ሀብት የሆኑ ንብረቶችን ያስመለሰ እለት፣
3) በህወሀት በግፍ ከወሎና ከጎንደር ተቆርሰው የተወሰዱ ቦታወችን፣ወልቃይት፣ፀገዴና ፀለምት፣ከማይጨው መለስ እስከ ዋጃና አካባቢዋ ያሉ የራያ መሬቶች ያስመለሰ ጊዜ፣
4)የሀገሪቱን አፋኝ አዋጅ ያነሳ፣አፋኝ ህጎችን የሻረ፣ ሁሉንም አካታች የሰላምና እርቅ ጉባኤ የጠራጊዜ፣
5) በእዚህም ጉባኤ ቢያንስ ነፃ የምርጫ ኮሚሽን፣ነፃ ቅድመ ምርጫ ስርአትን የሚመለከት የጋራ ስምምነት እንዲደረስ ያረገ ጊዜ ነው

Post Reply