Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Hameddibewoyane
Member
Posts: 3890
Joined: 25 Sep 2019, 02:42

የህወሓት ልጆች በቅንጦት ምግብ ሲያማርጡ ድሃው የትግራይ ህዝብ ግን ዳቦ ለመግዛት እንዲህ ይሰለፋል!!!!

Post by Hameddibewoyane » 04 Dec 2019, 21:14

ከመሸ አንድ ባር ውስጥ ሶስት ጓደኛሞች የሞቀ ጨዋታ ይዘዋል አንዱ ከመሐል የህወሓት መንግስትን እያማ እንዲህ ይላል "ዳቦ ዋጋው ጨመረ ዱቄትም ጠፋ" ብሎ እንደተናገረ በሌላ ጥግ የተቀመጠው ጆሮ ጠቢ ሰውዬውን አንጠልጥሎ ይወስደዋል። ሌሎቹ በፍርሀት በተቀመጡበት ቀሩ ከአንድ ሰአት በሃላ ከእስር ተፈቶ ሲመጣ ከነልብሱ ዱቄት በዱቄት ሆንዋል ጓደኞቹ ደንግጠው "ምንድነው የሆንከው? ብለው ሲጠይቁት " እግዚአብሔር ነው የረዳኝ እንኳንም በርበሬ ወይም ሚጥሚጣ ጠፋ አላልኩኝ ይሄው በዱቄት አጠቡኝ"አላቸው። ለማንኛውም የህወሓት ልጆች በቅንጦት ምግብ ሲያማርጡ ድሃው የትግራይ ህዝብ ግን ዳቦ ለመግዛት እንዲህ ይሰለፋል። ለእዛም የዳቦ ግራም ቀንሰው ወጋውን ጨምረው ህዝባችንን ለችግር ዳርገው እነሱ ግን የህዝብ ገንዘብ የዘረፉትን ኢትዮጵያን ለማተረማመስና እንዲሁም በስመ ፌደራሊዝም እናድን በማለት ህሊናቸውን ጥለው ለሆድ ያደሩትን ሰብስባ እያበላች ትገኛለች።

Digital Weyane
Member+
Posts: 8489
Joined: 19 Jun 2019, 21:45

Re: የህወሓት ልጆች በቅንጦት ምግብ ሲያማርጡ ድሃው የትግራይ ህዝብ ግን ዳቦ ለመግዛት እንዲህ ይሰለፋል!!!!

Post by Digital Weyane » 04 Dec 2019, 23:50

The people are standing in line to buy Sim Cards for their Smart Phones. My country Tigray is Africa's Singapore.

Post Reply