Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30668
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

አምስቱ ዋና ዋና የፖለቲካ ፓርቲዎች

Post by Horus » 02 Dec 2019, 03:17


እንደ ተለምዶ ቢሆን የዚህ ሃረግ ርዕስ መባል የነበረት አምስቱ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ርዕዮቶች ነው ። በተግባር ደረጃ ግን ከዚህ በኋላ ለመደራጀት በቅተው ፋይዳ ያለው ፖለቲካ ይሰራሉ የሚባሉት ፓርቲዎች በነዚህ 5 መስመሮች መሰረት ከቆሙ ብቻ ነው።

ታዲያ እነዚህ 5 ፓርቲዎች የተኞቹ ናቸው?

ፓርቲ ቁጥር አንድ፣

የአንድ ኢትዮጵያ ወይም ኢትዮጵያዊነት ፓርቲ። ይህ አሃዳዊ ፓርቲ በኢትዮጵያ ብሄረተኝነት ርዕዮት ላይ የቆመ ሲሆን ባሁን ሰአት ብዙ የተበታተኑ ቡድኖች የሚያራምዱት መስመር ነው ። ለምሳሌ ያዲስ አበባ ባልደራስ እና ሌሎች የከተማ ፣ የድሮ ባንዲራ ፣ ያድዋ ቀርስ የመሳሰሉ ማህበሮች፣ ድርጅቶች፣ ስብስቦች አንድ ቀን በዚህ የኢትዮጵያ ናሽናሊስት ፓርቲ ዙሪያ የሚቆሙ ናቸው ። ይህን እኔ ያክራሪ ኢትዮጵያዊነት ፓርቲ እለዋለሁ ።

ፓርቲ ቁጥር ሁለት፣

ይህ ኢዜማ ፓርቲ ነው። ይህ ፓርቲ የሚከተለው የሶሺያል ዴሞክራሲ ርዕዮት ቢሆንም ለኢትዮጵያዊነት ፓርቲ በብዙ ነገሮች ስለሚቀርብ ዞሮ ዞሮ የሚደጋገፉ ይሆናሉ ። እኔ ኢዜማን የልዝብ ኢትዮጵያዊነት ፓርቲ እለዋለሁ ።

ፓርቲ ቁጥር ሶስት፣

ይህ የጎሳ ፌዴሬሽን ወይም የጎሰኝነት ፓርቲ ነው። ዛሬ እስከ 80 የሚደርሱት በዘር የተፈለፈሉት ድርጅቶች የየራሳቸውን ጎሳ መወከል ይፈልጋሉን ግን እንዴት አድርገው አገር አቀፍ ፖለቲካ ውስጥ እንደሚገቡ ግልጽ አይደለም ። ባሁን ሰአት ቲፒኤልፍ እያረገ ያለው ይህን ጎሰኝነት ፓርቲ ማቆም ይመስላል ። ይህን እኔ ያክራሪ ጎሰኝነት ፓርቲ እለዋለሁ

ፓርቲ ቁጥር አራት፣

ይህ አዲሱ የብልጽግና ፓርቲ ነው ። ይህ ፓርቲ ለጎሳ ፌዴሬሽን ስብስብ በጣም ይቀርባል ። በየክልሉ የሚያጋጥሙት ተፎካካሪም ተባባሪም ድርጅቶች ቁጥር 3 የጎሳ ፓርቲዎች ናቸው። በአገር አቀፍ ደረጃ ዋና ተፎካካሪ ፓርቲዎች ብልጽግና ፓርቲ እና ኢዜማ ፓርቲ ናቸው ። እኔ ብልጽግናን የልዝብ ጎሰኘነት ፓርቲ እለዋለሁ ።

ፓርቲ ቁጥር አምስት፣

የኢትዮጵያ ሊበራል ፓርቲ፣ ኢዜማ ራሱን በሶሺያ ዴሞክራሲ ርዕዮት ላይ በማቆሙ በግድ የሊበራል ዴሞክራሲ ፓርቲ አገሪቱ ትፈልጋለች ። ስለሆነም አሁን ካሉት ጥቃቅን ቡድኖች እና ሌሎችም የተውጣጣ የሊብራል ዴሞክራሲ መቋቋሙ የግድ ነው ።

በመሰረቱ ይህ ነው የሚባል ፋይዳ የሚፈጥሩት እናም በመፎካከር ሆነ በመተባበር የወደ ፊቱን ፖለቲካችን የሚያንቀሳቅሱት እነዚህ አምስት አይነት ፓርቲዎች ናቸው።







Last edited by Horus on 02 Dec 2019, 14:45, edited 3 times in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 30668
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አምስቱ ዋና ዋና የፖለቲካ ፓርቲዎች

Post by Horus » 02 Dec 2019, 14:21

ይህን ሃረግ ገና እነደለጥፍኩ ኢዜማና ብልጽግና ሊተባበሩ ይችላሉ የሚል ወሬ ተናፈሰ ። ብዙ አላስገረመኝም። እኔም አንድ ጉዳይ ሲከነክነኝ ነበር ።

ኢዜማ በገሃድ ርዕዮቱ ሶሺያል ዴሞክራሲ እንደ ሆነ አስታውቋል ። ብልጽግ ና አብዮታዊ ዴሞክራሲን ከተወ በኋላ በምን አይነት ዴሞክራሲ አመነ? በሊብራል? በሶሺያ? በክርስቲያን?

በእኔ ግምት እነ አቢይ ከጎሳ ዴሞክራሲ ከወጡ ሊሆኑ የሚችሉት ወይ ሶሺያ ወይ ሊብራል ዴሞክራሲ ነው። ይህ ከሆነ ከኢዜማ ጋር የማይዋሃዱበት ምክንያት የለም ። ግን ብልጽግና በጎሳ ዴሞክራሲ ከቀጠለ ከኢዜማ ጋር ፓርላማ ውስጥ በነጠላ ጉዳዮች ላይ አብረው ድምጽ ይሰጡ እነሆነ እንጂ በአንድ ፓርቲ ሊዋሃዱ አይችሉም።

የተባለው ውህደት እውነትም ሆነ ወሬ የሚያሳየው ያገራችን ፖለቲካ እጅግ በፍጥነት እየተለዋወጠ መሆኑን ነው ። ይህ ደሞ ጥሩ ምልክት ነው ።

Horus
Senior Member+
Posts: 30668
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አምስቱ ዋና ዋና የፖለቲካ ፓርቲዎች

Post by Horus » 02 Dec 2019, 14:58

ይህን ስሙ ! ይህ ቡድን ካምስቱ የተኛውን ፓርቲ ይሆናል ? !!


Dawi
Member
Posts: 4311
Joined: 30 Aug 2016, 03:47

Re: አምስቱ ዋና ዋና የፖለቲካ ፓርቲዎች

Post by Dawi » 02 Dec 2019, 15:02

Horus wrote:
02 Dec 2019, 14:21
ያገራችን ፖለቲካ እጅግ በፍጥነት እየተለዋወጠ መሆኑን ነው ። ይህ ደሞ ጥሩ ምልክት ነው ።

ሆረስ

ጥሩ ብለሃል፣

ኢዘማም ሆኑ ብልጽግና መሯሯጥ ያለባቸው ባልደራስን ለመሳብ ነው፣
ባልደራስን ያቀፈ አዲስ አበባንና ዲያስፖራን አስገባ ማለት ነው፣

ብልጽግና ፅንፈኛውን ጃአ-ቄሮ መፋታት ይኖርበታል፣

ታከለ ኡማ የባልደራስን ድጋፍ ማግኘት ይችላል፣
ማድረግ ያለበት ጃአ-ቄሮን ማራቅና አዲሳባ የሁሉ ናትን መቀበል፣ በቃ!

የሚገርመው፣ እነበቀለ ገርባ ግራ ተጋብተዋል ፣ ሕወሐት ቢያንስ ባሉበት እየረገጡ ነው።
Horus wrote:
02 Dec 2019, 14:21
ይህን ሃረግ ገና እነደለጥፍኩ ኢዜማና ብልጽግና ሊተባበሩ ይችላሉ የሚል ወሬ ተናፈሰ ። ብዙ አላስገረመኝም። እኔም አንድ ጉዳይ ሲከነክነኝ ነበር ።

ኢዜማ በገሃድ ርዕዮቱ ሶሺያል ዴሞክራሲ እንደ ሆነ አስታውቋል ። ብልጽግ ና አብዮታዊ ዴሞክራሲን ከተወ በኋላ በምን አይነት ዴሞክራሲ አመነ? በሊብራል? በሶሺያ? በክርስቲያን?

በእኔ ግምት እነ አቢይ ከጎሳ ዴሞክራሲ ከወጡ ሊሆኑ የሚችሉት ወይ ሶሺያ ወይ ሊብራል ዴሞክራሲ ነው። ይህ ከሆነ ከኢዜማ ጋር የማይዋሃዱበት ምክንያት የለም ። ግን ብልጽግና በጎሳ ዴሞክራሲ ከቀጠለ ከኢዜማ ጋር ፓርላማ ውስጥ በነጠላ ጉዳዮች ላይ አብረው ድምጽ ይሰጡ እነሆነ እንጂ በአንድ ፓርቲ ሊዋሃዱ አይችሉም።

የተባለው ውህደት እውነትም ሆነ ወሬ የሚያሳየው ያገራችን ፖለቲካ እጅግ በፍጥነት እየተለዋወጠ መሆኑን ነው ። ይህ ደሞ ጥሩ ምልክት ነው ።

Horus
Senior Member+
Posts: 30668
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አምስቱ ዋና ዋና የፖለቲካ ፓርቲዎች

Post by Horus » 02 Dec 2019, 15:16

ዳዊ፣

ባልደራስ የተወለደው በአክራሪ ኦሮሞች ማስፈራራት እና ስልጣን ለግሌ ሳቢያ ነው። አሁን ልዝቡ ኦሮሞ የበላይ ሲሆንና የኦሮሞ ብቸኛ ሄጂሞኒ የማይቻል ሲሆን ነገሮች ይለወጣሉ ። ያዲሳባ ጥያቄ ምንም አተካራ የማያሻው የከተማ ራስ ገዝነት ጉዳይ ነው ። ይህን ኢዜማ ሆነ ብልጽግና ካልተቀበሉ ከሸገር ይባረራሉ ። እነ ጃዋር ጦርነት ካልፈለጉ በተቀር አዲሳባ ውስጥ የጎሳ ፖለቲካ ሊያካሂዱ አይችሉም። እናም አሁን ልክ እንደ ክረምቡላ ጠረፔዛ ጠጠሮችሁ ሁሉ እየተነቃነቁ ነው ። ይህ ደሞ ጥሩ ነገር ነው ።

Horus
Senior Member+
Posts: 30668
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አምስቱ ዋና ዋና የፖለቲካ ፓርቲዎች

Post by Horus » 03 Dec 2019, 01:07

እንደምታዩት ፖለቲካው ደርቷል ! በየደቂቃው አዳዲስ ሁነቶች (ኢቬንትስ) ይሰማሉ ። በመቶዎች የሚቆጠሩት ፓርቲና ድርጅቶች፣ በሺዎች የሚቆጠሩት አንድ ቀን ስም አግኝተን፣ ስልጣን ይዘን፣ መሪ ተብለን በጋዜጣ ዝናችን ይጻፋል የሚሉት ግለሰብ መሪ ተብየዎች እዚም እዚያም እየታመሱ ነው ።

ግን ሃቁ ምንድን ነው? ይህ ሁሉ ግርግር ያንድ ሰፈር መታመስ ነው፣ የጎሳ ልግዛ ባዮች፣ አዲስ ባለተራዎች፣ ከታሪክ የልተማሩ የስልጣን ሰካራሞች ውዥንብር ነው !!!

የኦሮሞ ልሂቅ ነኝ ባይ ስልጣንና ሃብት ፈላጊዎች አንዱ ሃረር ነው፣ አንዱ ባሌ ነው፣ አንዱ አሩሲ ነው፣ አንዱ ኦርቶዶክስ ነው፣ አንዱ ሉተራን ነው፣ አንዱ ሙስሊም ነው አንዱ ሌላ ነው፣ አንዱ ዝሸዋ ነው ፣ አንዱ ዎለጋ፣ አንድ ጂማ አንዱ ሌላ ነው። ስለዚህ የኦሮሞ ልሂቅ ነን ባዮች እርበርስ በታመሱ ሌላው በምን እዳው!!

እኔ ከላይ ይህን ሁሉ በብልሃት መመልከቻ ዘዴ (ሜትዶሎጂ) አሳይቻለሁ፤ ተጠቀሙበት ።

ለምሳሌ ስለ ጃዋር ስታነቡ ወይም ስታስቡ እሱ የአክራሪ ጎሰኛ ፓርቲ እንደ ሆነ ወስዳችሁ አስቡ፣ ያኔ ሁሉ ነገር ግልጽ ይሆናል ።

ለምሳሌ የነእስክንድር ንቅናቄ ጃዋርን ለተባበሩ መንግስታት ባሸባሪነት ለማስፈረጅ ቀጠሮ ወስዷል ።

ልክ ይህን ስትሰሙ በአክራሪ ጎሰኝነት እና ባሸባሪነት መካከል ዝምድና አለን ብላችሁ እንድትጠይቁ ትገደዳላችሁ!!


ethiopian
Member+
Posts: 5313
Joined: 09 Oct 2011, 21:29

Re: አምስቱ ዋና ዋና የፖለቲካ ፓርቲዎች

Post by ethiopian » 03 Dec 2019, 01:16

Eskinder plays burger pumped Abyssinian diaspora really well and that is as far as he can go .... his mission is abuara masnesat and I will give him that . Burger lover idiots can't think more than their weekly check and kuzir belly .... Horus is one of them .... They don't have the mental capacity to think what other Ethiopians are going through as long as their ugly belly is filled with Big Mac or u-street Kitfo

Horus
Senior Member+
Posts: 30668
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አምስቱ ዋና ዋና የፖለቲካ ፓርቲዎች

Post by Horus » 03 Dec 2019, 03:59


Horus
Senior Member+
Posts: 30668
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አምስቱ ዋና ዋና የፖለቲካ ፓርቲዎች

Post by Horus » 04 Dec 2019, 00:19

present,

እንደ ምታየው መአት አይነት የፓርቲዎች፣ ድርጅቶች ወሬ ድራማ ይሰማል ግን ሁሉም የሚረዳቸውና የሚያስበው አለምንም ሞዴል ነው። አንድን ነገር ወይም እውነታ ለመመልከት፣ ለመገንዘብ ወይም ለመተንተን የሪያሊቲ ሞዴል እንዲኖር ግድ ነው። ሞዴል ደሞ ሁኔታዎች ሲለወጡ ይሻሻላል ወይም ይለወጣል ።

በአሁን ሰአት ከላይ የሰፈሩት ባለ 5 ፓርቲዎች ሞዴል መጠቀም ነገሮችን ሁሉ በቀላሉ ለመመልከት ይረዳል ።

ለምሳሌ መቀሌ የሚደረገውን ያክራሪ ጎሰኝነት ስብስብ ወስደን እንደ አክራሪ ጎሳ ፓርቲ ብንከታተለው የስብስቡ ሂደት፣ ስኬት ወይም ውድቀት በደንብ ያሳየናል ። በተስብሳቢዎቹ ውስጥ ያሉት ልዩነቶች ባክራሪው ጎሳ ክንፍ ውስጥ ሊኖሩ የሚችሉትን የወደፊት ችግሮች ያሳየናል ማለት ነው።

በሌሎቹም የፓርቲ አይነቶች እንዲሁ !
Last edited by Horus on 04 Dec 2019, 01:05, edited 3 times in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 30668
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አምስቱ ዋና ዋና የፖለቲካ ፓርቲዎች

Post by Horus » 04 Dec 2019, 00:40

ለምሳሌ መራራ ጉዲና አቢይን ተቃውሞ ለማን መደገፉ የሚጠበቅ ነው። ወደዱም ጠሉም ግማሹ የኦሮሞ ብሄረተኛ ልሂቆች ያቢይ አይነት ልዝብ ፓርቲ ይዋሃዳሉ፣ የቀሩት ኦነግ አይነት አክራሪ ጎሳ ፓርቲ ይደባለቃሉ ። ለማም ኦነግ ይገባል ወይ ታርቆ ብልጽኛ ይቆያል።

Horus
Senior Member+
Posts: 30668
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አምስቱ ዋና ዋና የፖለቲካ ፓርቲዎች

Post by Horus » 04 Dec 2019, 03:00

ሰዎች ሆነ ብለው የሚሰሩ ስለ ሆነ አንድ ነገር ወደ ፊት እንዲህ ይሆናል ብሎ በርግጠኝነት የሚደምድሙ ወይ ጠንቋይ ወይ ልዩ ችሎታ ያላቸው ሰዎች ናቸው። ነገን መርጠን ወደን እንዋሃደዋለን እንጂ በግድ አንወስነውም ። ጎሰኝች ብዙ ሊመኙ መብታቸው ነው። ግን ህዝቡ ደሞ ይህን እያረገ ነው ።


Horus
Senior Member+
Posts: 30668
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አምስቱ ዋና ዋና የፖለቲካ ፓርቲዎች

Post by Horus » 04 Dec 2019, 03:04


Horus
Senior Member+
Posts: 30668
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አምስቱ ዋና ዋና የፖለቲካ ፓርቲዎች

Post by Horus » 04 Dec 2019, 14:49

በመቀሌ ያለው አዲሱ ያክራሪ ጎሳ ማደራጃ ስብሰባ እጣ ፈንታው ምንድን ነው?

ስብስቡ ዝም ብለው የንዴት ጩሀቱን ትተው አዲስ ራዲካል የጎሳ ፓርቲ በሆነ ስም መስርተው ለምርጫ ቦርድ ህጋዊነት ፈቃድ ማመልከት ግድ ይላቸዋል። ይህ ካልሆነ እንዴ ብለው ነው ለምርጫ ሚቀርቡት?

ያ ካልሆነ በየጎሳው አንጃ እየሆኑ ሽብር ለማስነሳት ሲሞክሩ ከፊሉ እስር ቤት፣ ከፊሉ እስከ ወረዳቸው ባስቸኳይ ግዜ አዋጅ መገዛት ይገባሉ። ይህ ነው የመቀሌው ስብሰብ ወደፊት እድል ።

ከላይ እንዳልኩ ባሁን ሰአት አምስት አይነት ፓርቲዎች ሁሉም በፌዴራል አወቃቀር ያምናሉ ። የሁሉም ልዩነት ምን አይነት ፌዴራሊስዝም በሚል ነው። ስለሆነም የመቀሌ አክራሪዎች ፈዴሬሽን ፌዴሬሽን እያሉ ግዜ ከማጥፋት ልክ እንደ ብልጽግና ፣ ልክ እንደ ኢዜማ ፕሮግራም ጽፈው አዲስ ፓርቲ ከመሆን ሌላ አማራጭ የላቸውም ።

ይህም ሆነ ያ የኢ ህ አዴ ግ አዲስ ፓርቲ መሆንና ኢዜማ ባገር ውስጥ መዘርጋቱ የኢትዮጵያን ፖለቲካ ጨዋታ መቶ በመቶ ለውጦታል ።

ከላይ ካሉት 5 ፓርቲዎች ውጭ ሆነው መግዛት የሚሹ እንደ ኦነግ ምናምን አይነት የጎሳ ወይም እዚህ ግባ ማይባሉ ጥቃቅን የዜጋ ፓርቲዎች በጥቂት አመታት ውስጥ ወደ 5ቱ ፓርቲዎች ይገባሉ ወይ ይከስማሉ ።

ይህ ነው የሂደቱ አቅጣጫና መድረሻው ።

Horus
Senior Member+
Posts: 30668
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አምስቱ ዋና ዋና የፖለቲካ ፓርቲዎች

Post by Horus » 04 Dec 2019, 15:17

በዘመናዊ ዴሞክራሲ ውስጥ 'all politics is local' ይባላ ። እነዚህ ሁሉ ብትንትን ፓርቲ ተብዬዎች ህጋዊ መሆን ብቻ ሳይሆን በየቀበሊው፣ ወረዳው፣ ታች ድረስ ወርደው ለዚያ ቀበሌና አካባቢ ህዝብ የልማትና እድገት ፋይዳ ካላቀረቡ የትም አይደርሱም ።

የፖለቲካ ነጋዴዎች ለራሳቸው ስልጣን እና ሃብት ህዝቡን ማታለል አሁን አይቻልም ። ሌሎች ፓርቲዎች አሉ፣ ሚዲያ አለ ፣ ፉክክር አለ። በአንድ ጎሳ ውስጥ እንኳን እንደ ድሮ በብሄር ጭቆና ስም ህዝብ ማታለል አብቅቷል ። ያንድ ጎሳ ልሂቃን ናቸው በራሳቸው ጎሳ ፊት የሚፎካከሩት፣ ማለትም የህዝቡ የሶሺያል፣ የትምህርት፣ የኢኪኖሚ ጥቅም ጉዳይ ነው መፎካከሪያው ።

ይህን የጨዋታ ለውጥ ያልተገነዘቡ አክራሪ ጎሰኞች ናቸው መቀሌ ውስጥ የሚያጨበጭቡት ።

Horus
Senior Member+
Posts: 30668
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አምስቱ ዋና ዋና የፖለቲካ ፓርቲዎች

Post by Horus » 04 Dec 2019, 17:27

በኢትዮጵያ ከዚህ በኋላ ዝም ብሎ በጉልበት የሚካሄድ ግድያ ዘር ማጥፋት ቤተ ክርስቲያን ማቃጠል ከዚህ በኋላ የማይቻል ነው። ሁሉም ተደራጅቷልና !!


Horus
Senior Member+
Posts: 30668
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አምስቱ ዋና ዋና የፖለቲካ ፓርቲዎች

Post by Horus » 07 Dec 2019, 00:06

ዛሬ ስለ አክራሪው ጎሰኛ ሰፈር የሚባለውን ስሙ ምክንያቱም የዚህ ሰፈር ወይም ፓርቲ ወደፊት እጣ ፈንታም ይህን መሰል መከፋፈልን መፍረክረክ ስለሚሆን ማለት ነው።

አሁን እንደ ምንሰማው ይህ አክራሪ ጎሳ ሰፈር በሶስት ወይም በአራት ቡድኖች ዙሪያ ለመሰባሰብ ትግል እየተደረገ ነው ።

ሲጀመር አንዱ በኦሮሞ አክራሪዎች ሰር ሌላው በትግሬ አክራሪዎች ስር ለመሰብሰብ ሲታገሉ ነበር ። የመቀሌ አክራሪዎች ስብሰባ አንዱ ነው። ሌላው የኦሮም ጃንጥላ የተባለው ነበር።

አሁን ግን በኦሮሞ ጎሰኞች ውስጥ ባለው የሃይል ሽኩቻ የተነሳ ጃዋር የራሱን አንጃ ይዟል፣ ኦነግ የራሱን አክራሪዎች ቅንጅት ስብሰባ ጠርቷል። የመቀሌው ስብስብም ካንድ በላይ አንጃ መፍጠሩ አይቀሬ ነው ።

ትግሬ ፑንትላንድ ከሆነች እነ ጫሚሶ የት እንደሚገቡ እናያለን ።

እንግዲህ ይህ ያክራሪ ገና አንድ የፖለቲካ ወይም የፓርቲ ብሎክ ሳይሆን የጀመረው መሰባበር ያገሪቱ ፖለቲካ ሲጦዝ ምን እንደሚሆን መገመት ይቻላል ።

አንድ ነገር ወደ ፊት የሚያመርተው ውጤት አሁን በያዘው ባህሪ ስለሚወሰን ፡

Post Reply