Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Zmeselo
Senior Member+
Posts: 33606
Joined: 30 Jul 2010, 20:43

"ኢትዮጵያውያን ወገኖች ሁሉ ልብ እናድርግ!"- Neamin Zeleke

Post by Zmeselo » 02 Dec 2019, 09:41

(Courtesy of Neamin Zeleke)

ኢትዮጵያውያን ወገኖች ሁሉ ልብ እናድርግ!

መቀሌ የመሸጉት ወያኔዎች እንደተጠበቀው ጮቤ ረግጠዋል፣ ሰርግና ምላሽ ሆኖላቸዋል። የሰሞኑን የአቶ ለማ መገረሳ የፓለቲካ እርምጃ እስከመጨረሻው ለማጦዝና ከዚህም ልዩነት ለመጠቀም/ለማትረፍ ያለ የሌለ ሃይላቸውን ሲያስተባብሩ፣ ልዩነቶችን እንደለመዱት ለማስፋትና ትርፍ ለማግኘት በርካታ ታክቲኮችን እየተጠቀሙ ስለመሆኑ እየታዘብን ነው። ከዚህ በታች በፌስ ቡክ ተለቆ የምናየው ለአቶ ለማ ከመቄሌ ቁጭ ብሎ የተንኮልና የክፋት ሴራዎችና ቀመር ከሚያሰሉት አንዱ "የቀድሞ ወዳጅ" የተለገሰ ምክር እንዱ ታክቲካቸው ነው።

ይህ የቀድሞ ወዳጅ፦ አቶ ለማን "ቀድሞ እንዲገኝ" "ኮ/ል አብይ" ሳይቀድመው አቶ ለማ እንዲቀድመው እየመከረ ነው።

አይናቸውን በትላልቅ የጨው ድንጋይ የታጠቡት ወያኔዎች እውን ለአቶ ለማ አስበው ወይንስ አሁንም ልባቸው ያልሞተለትን የማእከላዊ መንግስትን ዳግም የመቆጣጠር ቀቢጸ ተስፋ እውን ለማድረግ? በኢትዮጵያውያን ብጥብጥ፣ በህዝብ ደም መፋሰስ፣ በማእከላዊ መንግስት መዳከም፣ በወንድማማቾች መካከል ደም መፋሳስና ሌላውም የእነሱን የበላይነት/ሄጀመኒ እስካሳካ ድረስ ለወያኔ ምኑም አይደለም።

በዚህ ሂደት ኢትዮጵያ ሀገራዊ አንድነት ቢፈራርስ ለእነዚ እኩዮች ቁብ የሚስጥ አይደለም፣