Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
MatiT
Senior Member
Posts: 11549
Joined: 16 Feb 2013, 10:18

ሰበር ዜና!!! አክቲቪስት እና የ ፖለቲካ ምሁሩ ጃዋር መሀመድ ግብፅን አስጠነቀቀ!!!

Post by MatiT » 08 Nov 2019, 13:47

https://m.facebook.com/story.php?story_ ... 7990522468
ሰበር ዜና!!!
አክቲቪስት እና የ ፖለቲካ ምሁሩ ጃዋር መሀመድ ግብፅን አስጠነቀቀ!!!
በ ዛሬው እለት ጃዋር መሀመድ በ sonama tawik ራዲዮ ላይ እንደተናገረው "ግብፅ በ ኢትዮጲያ የ ሚገኙት ሁለት ትላልቅ ብሔረሰቦች በ ፖለቲካ ግጭት ውስጥ ስለሆኑ ይሄን እድል ተጠቅሜ ጦርነት ብከፍት ይሳካልኛል ብላ አስባ ከሆነ ፍፁም ተሳስታለች። የ አማራ እና የ ኦሮሞ ፖለቲከኞች ዋና የ ጥል ምክንያታቸው ምን አይነት ኢትዮጲያ እንገንባ እንጂ ሁለታችንም በ ሀገር ህልውና የምንደራደር አይደለንም። ግብፅ ኢትየጵያን ለመውረር ብትሞክር ሁሉም የ ኢትዮጵያ ህዝብ እርስ በእርስ የሚጣላበትን ጉዳይ አስቀምጦ በ አንድ ላይ ተባብረን ነው እንደለመደችው አዋርደን እምንልካት። ግብፅ ብቸኛ ያላት እድል ድርድር ብቻ ነው!!!" ጃዋር መሀመድ ጥቅምት 28/2012 ዓ.ም



Jirta
Member
Posts: 1505
Joined: 30 Sep 2018, 07:07

Re: ሰበር ዜና!!! አክቲቪስት እና የ ፖለቲካ ምሁሩ ጃዋር መሀመድ ግብፅን አስጠነቀቀ!!!

Post by Jirta » 08 Nov 2019, 14:25

በተለያዩ የሀገሪቱ አከባቢዎች ከሚፈፀሙ የተቀናጁ የወንጀል ተግባሮች፣ የብሔር ግጭቶች፣ የዜጎች መፈናቀል፣ ወዘተ በስተጀርባ የህወሓቶች እጅ እንዳለ ስንናገር ለአንዳንዶች ውሸት ይመስላቸዋል። በእርግጥ ለህወሓት አባላትና ደጋፊዎች በተጨባጭ ማስረጃ የተደገፈ መረጃ ማቅረብ ቀርቶ ድርጊቱ ከዓይናቸው ስር የተፈፀመ ቢሆን እንኳን አምነው ለመቀበል ይቸግራቸዋል። ምክንያቱም እንዲህ ያለ የማፍያ ቡድን አባልና ደጋፊ መሆንን አምኖ ከመቀበል ይልቅ በተግባር ያዩትን እውነት መካድ ይቀላቸዋል። ነገር ግን ሌላውም የህብረተሰብ ክፍል ቢሆን በተደጋጋሚ የህወሓቶችን እኩይ ተግባራት የሚያሳዩ መረጃዎች ሲቀርቡለት በሙሉ ልብ አምኖ ለመቀበል ይቸግረዋል። ምክንያቱም ህወሓት ጨቋኝና ዘራፊ የሆነ የፖለቲካ ቡድን እንጂ የተደራጀ የማፍያ ቡድን እንደሆነ በግልጽ መገንዘብ ተስኖታል። ሆኖም ግን በተደጋጋሚ የሚደርሱን ሚስጥራዊ መረጃዎች የሚያሳዩት ቢኖር ህወሓት ትክክለኛ የማፍያ ቡድን መሆኑን ነው። ዛሬም የደረሰን ሚስጥራዊ መረጃ ይህንን እውነት የሚያረጋግጥ ነው።

በዛሬው ዕለት የደረሰን ሚስጥራዊ መረጃ አንድ ማንነቱ ያልተገለፀ የደህንነት ሰራተኛ የህወሓቶችን እንቅስቃሴ አስመልክቶ ያዘጋጀው ሪፖርት ነው። በዚህ መሰረት ህወሓት ሱዳን ውስጥ ወታደራዊ የጦር ማሰልጠኛ ካምፕ ከፍተው ወደ 8ሺህ ሰራዊት በድብቅ እያሰለጠኑ እንደሆነ፣ የኤርትራ ተቃዋሚ ቡድኖችን መቀሌ ላይ በመሰብሰብ እየሸረቡት ያለው ሴራ፣ መቀሌ ላይ የመሸገው የህወሓት ማፊያ ቡድን በሀገራችን የተጀመረውን ለውጥ ለማደናቀፍ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ፣ እንዲሁም አንዳንድ የደቡብ ልሂቃን ከህወሓት ጋር በመመሳጠር በተለይ በወላይታ ዞን ሁከትና ብጥብጥ ለማስነሳት እየሰሩት ያለው ስራ በሪፖርቱ ተካትቷል። ይህ ሪፖርት በአጠቃላይ ሰባት ገፆች ያሉት ሲሆን ከዚህ ውስጥ አምስቱ ገፅ ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው አንድ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን ደርሶናል። በዚህ መሰረት ከላይ በተገለፁት አራት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ የቀረበውን ሪፖርት እንደሚከተለው ቀርቧል።

Post Reply