እነ እስክንድር ነጋ ከጥቃት ተርፈው አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ይገኛሉ
የባለአደራ ምክር ቤቱ አመራሮች በቢሮ ስብሰባ አድርገው ሲወጡ የተወሰኑ ሰዎች ከበባ አድርገው ጉዳት ሊያደርሱባቸው እንደሞከሩ ተሰምቷል።
ከበባ ካደረጉባቸው መካከል አንድ ሰው በፖሊስ አስይዘው አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ውስጥ ይገኛሉ። ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የተያዘው ሰው ምርመራ እንዲደረግበት እየጠየቀ እንደሆነና ፖሊስ ግን ሰውየውን ሊለቀው እንደሆነ ታውቋል።
እነ እስክንድር ነጋ ሁኔታውን ለፖሊስ እያስረዱ ነው። ከበባ አድርገው ጉዳት ሊያደርሱብን ነበር ካሏቸው መካከል የተያዘው ላይ ፖሊስ ምርመራ እንዲያደርግ እየጠየቁ ነው። ሰዎቹ የተናበቡና ከፖሊስ እገዛ ያላቸው እንደሆኑ ለመጠርጠር በቂ ማሳያ አለን ብለዋል እነ እስክንድር። ከበባ ካደረጉት መካከል አንዱ ከመያዙ ውጭ ሌሎች መኪና ይዟቸው ተሰውሯል።
-
- Member+
- Posts: 9499
- Joined: 24 Aug 2012, 12:02
-
- Member+
- Posts: 9499
- Joined: 24 Aug 2012, 12:02