Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30829
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የሆረስ አዲስ አመት መልክት ለኢትዮጵያ ምሁራን ሁሉ !!

Post by Horus » 10 Sep 2019, 01:19


አዲሱ የኢትዮጵያ ካልቸርና የኢትዮጵያ ምሁራን
መስክረም 1 2012

የአንድ አገር ስልጣኔም ሆነ የአንድ ሕዝብ ካልቸር የሚፈጠረው፣ የሚጠበቀው፣ የሚያድገውና የሚለወጠው ባሉት ልሂቃና እና ምሁራን ነው። የዚያ አገር ስልጣኔም ሆነ እድገት የሚደክመውና የሚፈርሰው ባሏት ደካማ ልሂቃና ምሁራን ነው፤ ማለትም ምሁር አልባ አገር ስትሆን ማለት ነው።

በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ስላገራችን ካልቸርና ስልጣኔ ቀውስ ብዙ እየተባለ ነው። ብዙም አበረታች አዝማሚያዎች እየታዩ ነው ። ይህም ማለት ስለምሁርን፣ ስለካልቸር፣ ስለስልጣኔ እድገትና ሂደት በቅጡ ማሰብና መወያየት መጀመር ያለብን ግዜ ነው ።

ባሁኑ ዘመን በኢትዮጵያም ሆነ በሌላ አገር ያሉት የካልቸር ፈጣሪ የሆኑት ምሁራን በአራት ክፍል ይመደባሉ። እነሱም ሳይንቲስቶች፣ አርቲስቶች፣ ሂዩማኒስቶች እና ቴክኖሎጂስቶች ናቸው። እነዚህ ግዙፍ የምሁራን ክፍሎች እያንዳንዳቸው በውስጣቸው ንኡስ ክፍሎች አላቸው ። እንዲሁም እያንዳንዱ የምሁር መደብ የራሱ የሆነ ያስተሳሰብ ዘይቤ፣ የምክንያት አሰጣጥ ስልት፣ ንድፈ ሃሳብ እና ክህሎት አለው።

እዚህ እጅግ አጭር ማሳሰቢያ ላይ ስለያንዳንዱ የምሁራን ምድብ ዝርዝር ተልእኮና ተግባር ማንሳት አይቻልም። በአንድ ቃል የጉዳዩን ፋይዳ መጥቀስ ይቻላል።

ኢትዮጵያዊያን የምር ባራት መሰረቶች ማለትም በአንድ ፈጣሪ ገናናነት፣ በሰው ልጅ ልዕልና፣ በስራ ክቡርነት እና በኢትዮጵያዊያን አንድ ቤተሰብነት ካመንን ባጭር ግዜ ታላቁን የኢትዮጵያ ካልቸር እንገነባለን ። የዚህ ካልቸር ተግባር ወይም ተልእኮ የኢትዮጵያን አጀንዳ ከስኬት ማድረስ ነው ። ይህ የኢትዮጵያን አጀንዳ ምንድን ነው?

አንድ፣ የኢትዮጵያን አገራዊ አንድነት፣ መረጋጋትና ጥንካሬን ማረጋገጥ፤
ሁለት ፣ ኢትዮጵያን ዴሞክራሲያዊ፣ ነጻና ፍትሃዊ ማህበረሰብ ማደግ፤
ሶስት፣ ኢትዮጵያዊያንን ሃብታም፣ የተማሩ፣ ጤነኛ ሕዝብ ማድረግ፤
አራት፣ በፈጠራ የተካነ፣ ከባቢውን የሚጠብቅ፣ መንፈሳዊ ካልቸር መገንባት ናቸው ።

በጽንሰ ሃሳብ ደረጃ ከላይ የጠቀስኳቸው አራት የምሁራን ክፍሎች የኢትዮጵያን አጀንዳ እንደ ሚከተለው ይከፋፈላሉ ።

የኢትዮጵያን አገራዊ አንድነት፣ መረጋጋትና ጥንካሬን የሚያረጋግጡት ሳይንቲስቶቿ ናቸው። በዚህ አጀንዳ ስር ያሉት ተግባራት ሁሉም ሳይንሳዊ ስነ ሃሳብ፣ ሳይንሳዊ ዘዴ እና ሳይንሳዊ ትግበራ የግድ የሚሉ ናቸው።

ኢትዮጵያን ዴሞክራሲያዊ፣ ነጻና ፍትሃዊ ማህበረሰብ ማደግ የሂዩማኒስት ምሁራን ተግባር ነው። ይህም ግዙፍ መስክ የራሱ የሆነ ፊሎሶፊ፣ ስነ ሃሳብ፣ ዘዴና ትግበራ አለው።

ኢትዮጵያዊያንን ሃብታም፣ የተማሩና፣ ጤነኛ ሕዝብ ማድረግ የቴክኖሎጂስት ምሁራን ተግባር ነው። እዚህ ላይ ቴክኖሎጂን ሰፋ ባለው ጽንሱ መወሰድ አለበት ። የኢኮኖሚ ፈጠራም ሆነ የእውቀት ግንባታ ስራ በመሰረቱ የቴክኖሎጂ፣ የክህሎት፣ የብልሃት ፈጠራ ተግባር ነው።

በፈጠራ የተካነ፣ ከባቢውን የሚጠብቅ፣ መንፈሳዊ ካልቸር መገንባት የአርቲስት ምሁራን ተግባር ነው።

ስለዚህ መጀመሪያ የኢትዮጵያ ታልቅ ካልቸር የቆመበትን መሰረት ጥርት አድርጎ መግለጽ ። ቀጥሎ የዚህ ታላቅ ካልቸር ፋይዳ የሆነውን የኢትዮጵያ አጀንዳን ጥርት አድርጎ መዘርዘር ። ቀጥሎ አራቱ የስልጣኔ ተሟጋች የሆኑት ምሁራኖችን መለየት ። በመጨረሻም አራቱ የኢትዮጵያ አጀንዳ ክፍሎች ለአራቱ የምሁራን መደቦች በግልጽ ማከፋፈል ።

ይህን ዙሪያ ገብ ራዕይ በያላችሁበት አይምሮ ጫሪ የሃሳብ ጮራ አርጉት ። ርእሱ ሙሉ መጽሃፍ ይፈልጋል፤ ግን ሃተታ ቢበዛ ባህያ አይጫንም ብዬ ነው ። መልካም አዲስ አመት! ኬር !!