Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Masud
Member+
Posts: 8502
Joined: 18 Jun 2013, 09:06

Re: ‘የብልህነት መንገድ’ - ምርጥ መጠሓፍ በምርጥ ተርጓሚ - ይዘቷን እንካችሁ አጣጥሙ!

Post by Masud » 15 Jun 2019, 05:33

Let me join Maxi in commending Meleket for tirelessly sharing words from ‘የብልህነት መንገድ’ . Kudos to Meleket! Your generosity made you shine; keep up the good job man!

Meleket wrote:
15 Jun 2019, 05:13
Maxi wrote:
15 Jun 2019, 04:35
Meleket, 30 more to go!! :P

You are doing great job. God bless you!!
ወዳጄ Maxi

ከተቀመጥኩበት ተንስቼ ጎንበስም ብዬ “አሜን” ብያለሁ!

ሐቅን በመግለጥ፣ ትምህርት ሰጪ የሆኑ ጽሑፎችንም በማጋራት፣ አጉራዘለሎችን ለመግራት በምናደርገዉ ትግል የትውልድ ሚናችንን እየተወጣን እንዳለን ጠንቅቀው የሚያዉቁ የወዳጄ Maxiና የሌሎች ቅን ሰዎች ሞራል ስላልተለየን በእጅጉ እናመሰግናለን!!! በትግርኛም ከልባችን “ክብረት ይሃበልና” ብለናል!!!
:D

Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ‘የብልህነት መንገድ’ - ምርጥ መጠሓፍ በምርጥ ተርጓሚ - ይዘቷን እንካችሁ አጣጥሙ!

Post by Meleket » 16 Jun 2019, 02:58

Masud wrote:
15 Jun 2019, 05:33
Let me join Maxi in commending Meleket for tirelessly sharing words from ‘የብልህነት መንገድ’ . Kudos to Meleket! Your generosity made you shine; keep up the good job man!
Meleket wrote:
15 Jun 2019, 05:13
Maxi wrote:
15 Jun 2019, 04:35
Meleket, 30 more to go!! :P

You are doing great job. God bless you!!
ወዳጄ Maxi

ከተቀመጥኩበት ተንስቼ ጎንበስም ብዬ “አሜን” ብያለሁ!

ሐቅን በመግለጥ፣ ትምህርት ሰጪ የሆኑ ጽሑፎችንም በማጋራት፣ አጉራዘለሎችን ለመግራት በምናደርገዉ ትግል የትውልድ ሚናችንን እየተወጣን እንዳለን ጠንቅቀው የሚያዉቁ የወዳጄ Maxiና የሌሎች ቅን ሰዎች ሞራል ስላልተለየን በእጅጉ እናመሰግናለን!!! በትግርኛም ከልባችን “ክብረት ይሃበልና” ብለናል!!!
:D
ወዳጄ Masud በጣም አመሰግናለሁ።

ይህና መሰል መልካም ጽሑፍና ሌሎች ሃሳቦችን እንዳሻን ለመጋራት የዘመኑን ቴክኖሎጂ ተጠቅሞ እድሉንና መድረኹን ላመቻቸው፣ በነጻነት ሰዎች ነጻ እይታቸዉን እንዲያንሸራሽሩም ሳያሰልስ ከማለዳ ጀምሮ ለተጋዉ ለኤልያስ ክፍሌ እንዲሁም ለመጸሓፉ ደራሲ ለባልታሳር ግራሽያንና በድንቅ አተረጓጎም ለተረጎመው ለአያሉ አክሊሉ ምስጋናዉን አስተላልፊያለሁ!!! “ክብረት ይሃበለይ!” ብያለው ወዳጄ Masud!
:D
Meleket wrote:
15 Jun 2019, 02:16
ጎበዝ የዛሬ አስር የብልህነት መንገዶችን ወርሃ ሰኔ እውነተኞቹ ኤርትራዉያን አንበሶች ይበልጥ የሚዘከሩበት ግዜ እንደመሆኑ መጠን ለፍትህ ለእኩልነት ለነጻነት ሲሉ ሕዝባቸውንም ከግፈኞችና ጨካኞች መንጋጋ ለማላቀቅ በቅን ልቦና ሕይወታቸውን ያለማወላወል ለገበሩ ለኤርትራዉያን እውነተኛ አንበሶች ማለትም ለ“ሰማእታት” ክብር እንዲሁም በመሰሪዎች ተደናግረው ጦርነት ውስጥ ገብተው ሕይወታቸው ላለፈ ኢትዮጵያዉያን ወንድሞቻችን ክብር ጭምር እንካፈለዋለን። ይህን ስናደርግም የነዚህን እውነተኛ ኤርትራዉያን አንበሶች መካነ መቃብር በማፈራረስ ድርብ በደል የፈጸሙ፣ በኤርትራ ልዑላዊ መሬት ውስጥ እስከ አሁኗ ደቂቃ በማን አለብኝነት ሰፍረው የሚገኙትን፣ ኤርትራም ልዑላዊ መሬቷን ያላንዳች መሸራረፍ እንዳታስተዳደር እንቅፋት የሆኑትን ወራሪ የትግራይ ወያኔዎችን በጨዋ ደንብ አሁንም ደግመን ደጋግመን በኤርትራ ህዝብ ስም “ዓገብ” በማለት ነው። አያይዘንም ወጣቱን የኢትዮጵያ ጠቅላዪንም “ቃልህን ተግብር” እያልን ከኤርትራ ምድር የሚገኙ ያገርህን ሠራዊት እንድታስወጣ በሰማእታቶቻችን ስም ደግመን ደጋግመን እየጠየቅን ነው።

261. በሞኝነት ተግባር አልሞት ባይ ተጋዳይ እንዳትሆን። አንዳንድ ለስህተታቸዉ ታማኝ የሆኑ ሰወች ስህተት ከፈጸሙ በኋላ በስህተታቸው መቀጠልን እንደ እርጋታ ወይም ጽናት አድርገው ይቆጥሩታል። እነዚህ ሰዎች በዉስጣቸው ራሳቸውን ቢወቅሱም ለሰዎች ግን ትክክል መሆናቸዉን ይናገራሉ። እንዲህ አይነት ግለሰቦች የሞኝነት ተግባር የፈጸሙ ጊዜ ሰዎች ግዴለሽ ናቸዉ እያሉ ያስባሉ፤ በዛ ተግባራቸዉ የገፉበት እንደሆነ ደግሞ ሞኝ ናቸዉ ይላሉ። በስህተት በገባነዉ ቃልኪዳን ሆነ በስህተት በወስደነው ዉሳኔ ለዘላለሙ ልንታሰር አይገባም። አንዳንዶች ደደብነታቸዉን ያራዝሟትና ታማኝ ጅሎች ለመሆን ይሞክራሉ።

262. መርሳትን እወቅ። ይህ ነገር ከችሎታ ይልቅ እድልን ይጠይቃል። በጣም መርሳት ያለብን በቀላሉ የማናስታዉሳቸዉን ነገሮች ነዉ፣ ትዝታ ባለጌነቱ ስንፈልገዉ አለመምጣቱ ሲሆን፤ ጅልነቱ ደግሞ መምጣት በሌለበት ጊዜ መምጣቱ ነዉ። ትዝታ ስቃይን ሲፈጥርብን አሰልች፤ ሀሴትን ሲፈጥርብን ደግሞ ግድ የለሽ ነዉ። አንዳንዴ የችግሮች መድሀኒታቸዉ መርሳት ቢሆንም መድሀኒቱን እንረሳዋለን። ትዝታ ሕይወታችንን ሲኦል ወይም ገነት ልታደርገዉ ስለምትችል ትኩረት ሰጥተን ልንኮተኩታት ይገባል። በራሳቸዉ የሚደሰቱ ሰወች ግን በቂላቂል የዋህነታቸዉ ሁሌም ደስተኞች ስለሆኑ ይህ ነገር አያስጨንቃቸዉም።

263. ብዙ መልካም ነገሮች በሌሎች ሰዎች እጅ ቢሆኑ የተሻለ ነዉ። በደንብ ልትደሰትባቸዉ የምትችል ይህ የሆነ እንደሆነ ነዉ። በመጀመሪያዉ ቀን ደስታዉ የባለቤቱ ሲሆን በኋላ ግን ለሌሎች ነዉ። ይጠፉብናል ብለን ስለማንሰጋ እና አዲስ ስለሚሆኑብን የሰዉ የሆኑ ነገሮችን እጥፍ ጊዜ እንደሰትባቸዋለን። የተከለከሉት ነገር ሁሉ ስለሚጣፍጥ የሌላ ሰዉ ዉሀ እንኳ ማር ማር ይላል።

264. ግዴለሽ የምትሆንባቸዉ እለታት እንዳይኖሩህ። እጣ ፋንታ ባልተዘጋጀንበት አጋጣሚ እኛን የምታስደነግጥበትን አጋጣሚ እንደተጠባበቀች ነዉ። እናም ለዚህ የፍርድ ቀን እዉቀታችንን፤ ማስተዋላችንን እና ብርታታችንን ብቻ ሳይሆን ዉበታችን እንኳ መዘጋጀት አለባት። እነሆ እነዚህ ነገሮች እንዝላል የሆኑበት ቀን የዉርደታችን ቀን ነዉ። ጥንቃቄ ሁሌም የሚጠፋዉ በጣም በሚያስፈልግበት ጊዜ ነዉ። ሀሳብ የለሽነት ለዉርደት ይዳርጋል። በደንብ የሚከታተሉን ሰዎች ደግሞ ይህን ህግ ስለሚረዱ ችሎታችንን የሚፈታተኑት ባልተዘጋጀንበት ሰአት ነዉ። እነዚህ ሰዎች ችሎታችንን በደንብ የምናሳይባቸዉን ቀናት በመተዉ ባልጠበቅነዉ ቀን ፈተና ላይ ይጥሉናል

265. የበታቾችህን አጣብቂኝ ዉስጥ መክተት እወቅበትዋና የምትለምደዉ እየሰጠምክ እያለህ ስለሆነ በተገቢዉ ጊዜ የተከሰተ አደገኛ ሁኔታ ብዙ ታላቅ ሰዎችን ፈጥሯል። እንዲ አይነቱ አጋጣሚ ብዙ ሰዎችን ምን ያህል እንደሚያዉቁ ብቻ ሳይሆን ትክክለኛ ዋጋቸዉንም እንዲረዱ አስችሏቸዋል። እነሆ አደገኛዉ አጋጣሚ ባይኖር ኖሮ የእነዚህ ሰዎች ችሎታ በፍርሀታቸዉ ዉስጥ ተቀብሮ ይቀር ነበር። አስቸጋሪ ሁኔታዎች ታላቅ የምንሆንበትን አጋጣሚ ያቀርቡልናል። ታላቅ ሰዉ ክብሩ አደጋ ላይ መዉደቁን የተረዳ እንደሆን ሽህ ሰዎች ሊሰሩ ከሚችሉት በላይ ሊያከናዉን ይችላል። እንግዲህ ታላቅ ሰዎች የሚፈጠሩት በዚህ መንገድ ነው።

266. በጣም መልካም በመሆን መጥፎ አትሁን። የማትቆጣ ከሆነ ደግሞ መጥፎ ትሆናለህ። በእዉነት ምንም የማይሰማቸዉ ሰዎች ከሰዉ አይቆጠሩም። እነሆ የእነዚህ ሰዎች ባህሪ እንደዛ የሆነዉ ደደብ በመሆናቸዉ እንጅ ምንም ስሜት ስለማይሰማቸዉ አይደለም። ስለዚህ በተገቢዉ አጋጣሚ በስሜት መሞላት እዉነተኛ ሰዉ ያደርጋል። ወፎች እንኳ ወፈከልክል ምንም ስሜት ባለማሳየቱ ያላግጡበታል። ጣፋጭ ብቻ ለሞኞች እና ለህጻናት የተገባ በመሆኑ ጣፋጩን ከመራራዉ ጋር ማፈራረቅ ችሎታን ያሳያል። እራስን እስኪስቱ ድረስ እጅግ መልካም መሆን ታላቅ ሀጢአት ነዉ።

267. ቃላቶችህ ለስላሳ ምግባሮችህ ደግሞ ገራገር ይሁኑ። ቀስት ሰዉነታችንን ሲወጋ ቃላት ደግሞ መንፈሳችንን ይወጋሉ። ጣፋጭ ኬክ ለአፋችን መልካም ሽታን ይሰጠዋል። ንፋስን መሸጥ መቻል ታላቅ ችሎታ ነዉ። ብዙ ነገሮች በቃላት ስለሚከፈሉ በቃላት ብቻ ከባድ የሚባሉ ነገሮችን ማለፍ ይቻላል። እናም ሰዎች የተወጣጠሩብህ ወይም የፈዘዙብህ ጊዜ በአየር አስተናግዳቸዉ። ዘዉዳዊ ትንፋሽ በተለየ ሁኔታ የማሳመን ችሎታ አለዉ። አፍህ በማር የተሞላ ይሁን እና ጠላቶችህ እንኳ እስኪወዷቸዉ ድረስ ቃላቶችህን ወደ ከረሜላ ለዉጣቸዉ። ለመወደድ ብቸኛዉ መንገድ ገራገር እና ሰላማዊ መሆን ነው።

268. ሞኝ በመጨረሻ የሚሰራዉን ብልህ በቅድሚያ ይሰራዋል። ሁለቱም ተመሳሳይ ነገር እየፈጸሙ ቢሆንም እንኳ የሚለያዩት በሚፈጽሙበት ጊዜ ነዉ፤ አንደኛዉ በትክክለኛዉ ሰአት ሲፈጽም ሌላኛዉ በአጉል ሰአት ይፈጽማል። በተሳሳተ እሳቤ ከጀመርክ ሁሉንም ነገር የምትፈጽመዉ በተሳሳተ መንገድ በመሆኑ አናትህ ላይ ልታደርገዉ የሚገባዉን በእግርህ ትረግጠዋለህ፤ ቀኝ የሚሆነዉን ግራ ታደርገዋለህ፤ እናም ስራህ በሙሉ ብስለት የጎደለዉ ይሆናል። በዚህ አጋጣሚ ለእንዲህ አይነቱ ሰዉ ያለዉ መፍትሄ በተቻለ ፍጥነት ወደ ትክክለኛዉ አቅጣጫ ማምራት ነዉ። ይህ ባይሆን ግን በዉዴታ ሊሰራ የነበረዉን በግዴታ ይሰራዋል። ብልሆች ወዲያዉኑ ወይም ቆይተዉ መፈጸም ያለባቸዉን በፍጥነት ለይተዉ ደስ እያላቸዉ በማከናወን ዝናቸዉን ከፍ ያደርጋሉ።

269. አዲስ መሆንህን ተጠቀምበት። አዲስ እስከሆንክ ድረስ ከበሬታን ታገኛለህ። በሚያመጣዉ ለዉጥ ምክንያት ስለሚያስደስት እና መንፈስን ስለሚያድስ አዲስ የሆነ ተራ ነገር ከተላመድነዉ ታላቅ ነገር ይበልጥብናል። ላቅ ያሉ ነገሮች ከኛ ጋር ሲቀላቀሉ ቶሎ ያረጃሉ። ሆኖም ግን የአዲስነት ግርማ ሞገስ የሚቆየዉ ለጥቂት ጊዜ በመሆኑ በአራት ቀናት ዉስጥ ሰዎች ላንተ ያላቸዉን ክብር ያጣሉ። እናም በመጀመሪያወቹ ቀናት የምታገኘዉን መከበር በተቻለህ መጠን ተጠቀምበት እና መኮብለል ሲጀምር ደግሞ የተቻለህን ያህል ለማስቀረት ሞክር። የአዲስነት ሞቅታ እንዳበቃ ስሜት ይቀዘቅዛል፤ ደስታም ወደ ንዴት ይቀየራል። ሁሉም ነገሮች የራሳቸዉ ጊዜ እንዳላቸዉ እና እንደሚያልፍባቸዉም ጠንቅቀህ እወቅ።

270. ብዙዎችን እያስደሰተ ያለዉን ነገር ብቻህን እንዳትነቅፍ። ሊገለጽ ባይችል እንኳ እንዲህ አይነቱ ነገር ብዙዎችን ሊያስደስት የቻለበት አንዳች ነገር አለዉ። ለየት ብሎ መታየት ሁሌም አስጠሊታ ሲሆን፤ ለየት ያልከዉ በስህተት ከሆነ ደግሞ አስቂኝ ነዉ። ብዙ ሰዉ የሚወደዉን ነገር ስደበዉ እና አንተዉ ራስህ ትሰደብና ከአጉል ምርጫህ ጋር ብቻህን ትቀራለህ። ምርጫ አለማወቅ የሚወለደዉ ከደደብነት ስለሆነ መልካም የሆነዉን ነገር መለየት ካልቻልክ አለማወቅህን ደብቅ እንጅ ነገሮችን በጥቅሉ አትኮንን። ሁሉም ሰዉ ነዉ የሚለዉ ነገር በትክክል ነዉ፤ ይህ ካልሆነ ደግሞ ነገሩ ሊሆን ነው።

ጎበዝ፣ በብልህነት መንገድ እንጓዝ፣ ብልሆችም እንሁን!
:mrgreen:

Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ‘የብልህነት መንገድ’ - ምርጥ መጠሓፍ በምርጥ ተርጓሚ - ይዘቷን እንካችሁ አጣጥሙ!

Post by Meleket » 24 Jun 2019, 10:31

ጎበዝ ተወደ ኢጦቢያ እየሰማነው ያለው ነገር በጣም አሳዝኖናል። የዛሬ አስር የብልህነት መንገዶችን ኢትዮጵያ ውስጥ ሰሞኑን በተከሰተው ቁርቁስ ውስጥ ቅን አስተሳሰብ አንግበው እያሉ ከግራም ከቀኝም ህይወታቸው መስዋእት ለሆነ ዜጎች በሙሉ ለክብራቸው እንካፈለዋለን የዓላማ ጽናትንም ከእያንዳንዳቸው እንማራለን፤ ለቤተሰቦቻቸዉም አምላኽ ጽናቱንና መጽናናቱን ይስጥ ስንል ሃዘናችሁ ሃዘናችን መሆኑን እየገለጥን ነው።ይህንን ስናደርግም በሰላሙ ዘመን ከመደማመጥ ይልቅ መደማሰስን በመምረጥ ከበስተጀርባ ሆነው ከሃሳብ ልዕልና ይልቅ የዜጎችን መብት ለመደፍጠጥ ኃይልን ለመጠቀም የገፋፉና መሰሪ ሴራ ጠንስሰው ለመተግበር ከግራም ከቀኝም ያሸረገዱትን አካላት ሁሉ ከተራው ህዝብ እይታ ቢሰወሩም ከእግዜሩ እይታ ሊሰወሩ አይችሉምና አንድዬ ለሁሉም እንደየስራው ይሰጥ ዘንድ እንማጠናለን የተበደሉትን አካላትም ከግራም ከቀኝም በረቂቅ ጥበቡ የሚካሰውን ይክስ ዘንድ እንማጠነዋለን። ሰላምንና መረጋጋትን መደማመጥንና መቻቻልን ለማስፈን ሳያሰልሱ የሚተጉ ቅን ዜጎችንም በርቱ አይዟችሁ እኛ ኢምንቶቹ ብቻ ሳንሆን ራሱ ፈጣሪ ከጎናችሁ ስላለ ተስፋ አትቁረጡ ልንላቸው እንወዳለን።

271. በማንኛዉም ሙያ ይሁን ጥቂት ከሆነ የምታዉቀዉ ከአደጋ የራቀዉን ወይም እርግጠኛ የሆንክበትን መንገድ ተከተል። ሊቅ ነዉ ባትባል እንኳ ጽኑ ነዉ ትባላለህ። አዋቂ ሰዉ ወደ አስጊ ሁኔታወች ሊገባ እና በቅሌቱ ሊደሰት ቢችልም አንተ ግን ምንም ሳታዉቅ እቀላለሁ ብትል በምን ልጥፋ እንደማለት ይሆንብሃል። የተሞከረ እና የተመረመረ ነገር ሊሳሳት ስለማይችል ትክክል ነዉ የሚባልለትን ነገር ተከተል። ይህ ነገር ጥቂት ለሚያዉቁ ሰዎች ትክክለኛ መርህ ነዉ። አዋቂ ሆንክ አላዋቂ እርግጠኝነት ከአፈንጋጭነት በተሻለ ሁኔታ ከአደጋ የራቀ ነዉ።

272. ከምትሸጠው ነገር ላይ ትህትናን ጨምርበት እና ሰዎችን የዉዴታ ግዴታ ያስገባልሃል። የገብጋባ ሰዉ ጥያቄ እና ዉለታ የተዋለለት ሰዉ መልስ ለየቅል ናቸዉ። ትህትና የሚያደርገዉ መስጠት ብቻ ሳይሆን ሰዎችንም በዉለታ ያስራል። ለጋስነት ደግሞ የበለጠ ዉለታ ዉስጥ ይከተናል። ለጨዋ ሰዉ በነጻ የሚሰጠዉን ነገር ያህል ዋጋዉ ዉድ የሆነበት ነገር የለም። አንድን ነገር በትህትና ስትሸጥ በተለያየ ዋጋ ሁለት ጊዜ እንደሸጥክ ይቖጠራል፤ አንደኛዉ ዋጋ እቃዉ በራሱ የሚያወጣዉ ሲሆን ሁለተኛዉ ደግሞ የትህትና ዋጋ ነዉ። ጨዋነት የሚባል ነገርን ስለማይረዱ ትህትና በስዶች ፊት ፍሬ ከርስኪ ናት።

273. ሀሳባቸዉን ታዉቅ ዘንድ የምትቀርባቸዉን ሰዎች ባህሪ ተረዳ። የአንድን ነገር መንስኤ ስትረዳ ዉጤቱንም አብረህ ትረዳለህ። ዉጤቱ ደግሞ ከጀርባ ያለዉን አላማ ይነግርሃል። የሀዘንተኝነት ባህሪ ያለባቸዉ ሰዎች ሁሌም ሀዘንን ሲተነብዩ፤ የተቃዋሚነት ባህሪ ያለባቸዉ ሰዎች ደግሞ ሁሌም ስለመጥፎ ነገር ስለሚያስቡ እፊታቸዉ ላይ ያለዉን መልካም ነገር በመተዉ ሊከሰት ስለሚችለዉ መጥፎ ነገር ይለፍፋሉ። በዉስጡ አድሮ የሚያናግረዉ ምክንያታዊነት ሳይሆን ስሜት በመሆኑ በስሜታዊነት የተዋጠ ግለሰብ ስለነገሮች ትክክለኛ የሆነ ገለጻ ሊያቀርብ አይችልም። እናም እያንዳንዱ ሰዉ ስሜቱን ተከትሎ ስለሚያወራ የሚናገረዉ ነገር ከእዉነታ የራቀ ነዉ። ስለዚህ የሰዉን ፊት ማንበብ እና መንፈሱንም መረዳት ያስፈልጋል። አንድ ሰዉ ሁሌ የሚስቅ ከሆነ ሞኝ መሆኑን ተረዳ ምንም የማይስቅ ከሆነ ደግሞ የዉሸት መሆኑን እወቅ። ሰላይ ሊሆን ስለሚችል አጥብቆ የሚጠይቅህን ሰዉ ተጠንቀቀዉ። በተፈጥሮ መልከ ጥፉ ወይም ሰንካላ ከሆኑ ሰዎች ደግሞ ምንም አትጠብቅ። የእያንዳንዱ ሰዉ ቂልነት ደግሞ በመልከ መልካምነቱ ልክ ነዉ።

274. የደስደስ ይኑርህ። ይህ ጠቢብነትን የተላበሰ የማፍዘዣ ስልት ነዉ። ይህን ስልት የሰዎችን ጥቅም ለማግኘት ሳይሆን ተወዳጅነትን ለማግኘት አስበህ ሁሌም ተግባር ላይ አዉለዉ። ሰዎች አድናቆትን የሚቸሩህ ስታስደስታቸዉ በመሆኑ ሰዎችን ማስደሰት ካልታከለበት ችሎታ ብቻዉን በቂ አይደለም። አድናቆት ደግሞ ሰዎችን ለማስተዳደር የሚጠቅም መሳሪያ ነዉ። በሰዎች ዘንድ ተወዳጅነት ካገኘህ በጣም እድለኛ ነህ፤ ሆኖም ግን ይህ ነገር ጥበብ ሊታከልበት ይገባል፤ ጥበብ ደግሞ በደንብ የሚሰራዉ የተፈጥሮ ስጦታ ያለ ጊዜ ነዉ። በዚህ መንገድ ተወዳጅነትን ማትረፍ እና ብዙ ልቦችን ማሸነፍ ይቻላል።

275. ከነፈሰዉ ጋር ንፈስ፤ ይህን ስታደርግ ግን ክብርህን ጠብቀህ መሆን አለበት። የትሁትነት ምልክት ስለሆነ ሁሌም ኮስታራ ወይም ቁጡ አትምሰል። የሰዎችን መዉደድ ታገኝ ዘንድ ክብርህን በጥቂቱ ማጣት ግድ ይልሃል። በህዝብ ፊት ከሞኝ የተቆጠረ በግል ብልህ ይሆናል ተብሎ ስለማይታሰብ፥ አንዳንዴ መንጋወችን መከተል ካለብህ ክብርህን ጠብቀህ መሆን አለበት። በብዙ አመት ኮስታራነት የተገኘ ነገር በአንድ ቀን ቧልት ሊታጣ ይችላል። ወጣ ያለ ባህሪ ማሳየት ሌሎችን እንደመኮነን ስለሚቆጠር ሁሌም ከሰዉ የተለየህ ሆነህ አትታይ። ወግ አጥባቂነትን እና በቶሎ የስሜት መጎዳትን ለሴቶች ተዉላቸው። በሀይማኖት እንኳ ወግ አጥባቂነት አስቂኝ ነገር ነዉ። ወንድ የመሆን ደስ የሚለዉ ነገር ወንድ መስሎ መገኘት ነዉ። ሴቶች ወንድን መምሰል ቢችሉም ወንዶች ግን የሴቶችን ባህሪ ሊቀዱ አይገባም።

276. ጥበብ እና ተፈጥሮ በመጠቀም እራስህን አድስ። የሰዉ ልጅ ሁኔታ በየሰባት አመቱ ይቀየራል የሚል አባባል ስላለ ይህ ለዉጥ መንፈስህን የሚያሻሽል እና ላቅ የሚያደርግ እንዲሆን አድርግ። ከመጀመሪያወቹ ሰባት አመታት በኋላ ወደ ምክንያታዊነት እድሜ ስለምንደርስ ከዚህ በኋላ ባሉት ተከታታይ ሰባት አመታት አዳዲስ መሻሽሎችን የምናመጣባቸዉ ይሁን። ይህን የተፈጥሮ ለዉጥ ልብ በል እና ተጠቀምበት፤ ሌሎችም በተመሳሳይ ሁኔታ ይሻሻላሉ ብለህ ጠብቅ። በዚህ ምክንያት ነዉ እንግዲህ ብዙወች ባህሪያቸዉን፤ ርስታቸዉን እና ስራቸዉን የሚቀይሩት። ይህ ሁሉ ሲሆን ለዉጡ ትልቅ ካልሆነ በስተቀር ለማስተዋል ያዳግታል። ሀያ አመት ሲሞላህ ጣዎስ ትሆናለህ፤ ሰላሳ ዓመት ላይ አንበሳ፤ አርባ አመት ላይ ግመል፤ ሀምሳ አመት ላይ እባብ፤ ስልሳ አመት ላይ ዉሻ፤ ሰባ ኣመት ላይ ጦጣ ትሆን እና ሰማኒያ አመት ላይ ግን ምንም አይደለህም።

277. ችሎታህን አሳይ፤ ማሳየት መቻል የችሎታ ነጸብራቅ ነዉ። ሁሌም ምቹ ቀን ሊሆንልህ ስለማይቻል እያንዳንዱን ችሎታህን ባገኘሀዉ ምቹ አጋጣሚ እየተጠቀምክ አሳይ። እነሆ ጥቂት የሚባለዉ ነገር በደንብ የሚያንጸባርቅላቸዉ፤ ብዙ የሆነው ደግሞ ማስደነቅ እስኪችል ድረስ የሚያንጸበርቅላቸዉ ጨዋ የሆኑ ሰዎች አሎ። ችሎታ እና ችሎታህን የማሳየት ብቃት ሲኖርህ ዉጤቱ ታላቅ ነገር ነዉ። ሌሎችን ማማለል የሚችሉበት ሀገራት ቢኖሩም እንደ እስፓኞች የሚሆን ግን የለም። አለም እንደተፈጠረች ትታይ ዘንድ ብርሃን የበራዉ ወዲያዉኑ ነበር። በተለይ በእዉነታ ላይ የተመሰረተ እንደሆን የማሳየት ችሎታ ከፈለገ የጠፋዉን ነገር እንኳ ያቀርባል፤ ነገሮችንም ሁለተኛ ሕይወት ሊዘራባቸዉ ይቻለዋል። ልቀትን የሚለግሱት ሰማየ ሰማያት ስጦታችንን እንድናሳይ ያበረታቱናል። ይህን ለማድረግ ግን ችሎታ ያስፈልጋል። ምንም አይወጣለትም የሚባለዉ ነገር እንኳ እንደ ሁኔታዉ እንጅ ሁሌም ተገቢ አይደለም። ማሳየት ታስቦበት ከተደረገ አይሰራም። እዩልኝ ማለት ከንቱነት በመሆኑ እና ከንቱነት ደግሞ አስጸያፊ በመሆኑ የታይታ ተግባር መፈፀም የለብንም። ወደ ስድነት ስለሚያመራ እና በብልሆች ዘንድ ደግሞ ከልክ በላይ ችሎታን ማሳየት የሚደገፍ ተግባር ባለመሆኑ ችሎታችንን ስናሳይ በልክ መሆን አለበት። ማሳየት አብዛኛዉን ጊዜ ዝምታ የተቀላቀለባት ንግግር ስትሆን የተወሰነ ግዴለሽነትንም ኣዝላለች። ነገርን ዘወር ማድረግ የስዎችን የማወቅ ፍላጎት ስለሚቀሰቅስ አንዳንዴ በብልሀት ችሎታህን መደበቅ ከማሳየት በላይ የሚሆንበት ጊዜ አለ። ችሎታን ባንዴ ሳይሆን በጥቂት በጥቂቱ እያደረጉ ማሳየት ጥበብ ይጠይቃል። ስለዚህ ተከታታይ አጋጣሚወች ችሎታህን የምታሳይባቸዉ ይሁኑ እና በአንደኛዉ ያሳየኸዉ ችሎታህ ጭብጨባን እያተረፈልህ ሌላኛዉ ችሎታህን የምታሳይበትን አጋጣሚ ደግሞ ሰዉ በጉጉት እንዲጠብቅ አድርግ።

278. ትኩረትን አትሳብ። ትኩረትን ለመሳብ ጥረት ስታደርግ ሌሎች ሰዎች የተመለከቱህ እንደሆን ያለህ ስጦታ እንደ እንከን መቆጠር ብቻ ሳይሆን በሰዎች ዘንድ መገለል እና ነቀፋም ይደርስብሀል። ቁንጅና እንኳ ከልክ በላይ የሆነ እንደሆን ለስምህ ጥሩ አይደለም። የሌሎችን ሰዎች ትኩረት የሚስብ ነገር ሁሉ አስጸያፊ ነገር ነዉ፤ በተለይ ደግሞ ነገሩ መጥፎ ከሆነ። አንዳንድ በመጥፎ ምግባር መታወቅ የሚሹ ሰዎች በየእለቱ ራሳቸዉን የሚያረክሱባቸዉን መንገዶች እንዳፈላለጉ ነዉ። በእዉቀት ዘንድ እንኳ ከልክ ማለፍ ወደ ጥራዝ ነጠቅነት ያወርዳል።

279. ለሚቃወሙህ መልስ አትስጣቸዉ። መጀመሪያ የእነዚህ ሰዎች ተቃዉሞ የመነጨዉ ከብልጠት ነዉ ወይስ ከስድነት የሚለዉን ነገር አጣራ። አንዳንዴ ማታለያ ሊሆን ስለሚችል ተቃዉሞ ሁሌም የግትርነት ተግባር አይደለም። ስለዚህ ግትርነት እንቅፋት ስለሚፈጥርብህ እና ማታለያ ደግሞ አደጋ ዉስጥ ሊጨምርህ ስለሚችል ጠንቀቅ ማለት አለብህ። በተለይ ሰላዩችን በእጅጉ መጠንቀቅ ያስፈልጋል። እናም የልብህን ቁልፍ ለመስረቅ የሚሹ ሰላዮችን ለመጋፈጥ ቁልፍህን ከቤት ዉጭ ሳይሆን ቤት ዉስጥ ከቁልፉ ቀዳዳ በስተጀርባ መተዉን የመሰለ ነገር የለም።

280. ክብር ያለህ ሰዉ ሁን። እነሆ መልካም ምግባር ጠፍቷል፤ ዉለታዎች ደግሞ እየተመለሱ አይደለም፤ ለሰዎችም የሚገባቸዉን ክብር የሚሰጡ በጣም ጥቂቶች ናቸዉ። በአለሙ ሁሉ ታላቅ የሆኑት አገልግሎቶች ሽልማታቸዉ በጣም ያነሰ ነዉ። እንዲሁ ሌሎችን በመጥፎ ሁኔታ የማስተናገድ ዝንባሌ ያላቸዉ ሀገሮች አሉ። ከነዚህ ሀገሮች ዉስጥ አንዳንዶቹ በክህደት ይፈራሉ፤ ሌሎች በተለዋዋጭነት፤ የተቀሩት ደግሞ በማጭበርበር ተግባር ይፈራሉ። የእነሱን ባህሪ ለመቅዳት ሳይሆን ራስህን ለመከላከል በማሰብ ለሰወች መጥፎ ባህሪ ትኩረትን ስጥ። የራስህ ሀቀኝነት በሌሎች ሰዎች አጥፊ ተግባር ሊበላሽ ይችላል። ሆኖም ግን ጨዋ ሰዉ የሌሎችን ሁኔታ በማየት የራሱን ማንነት አይረሳም።

ጎበዝ፣ በብልህነት መንገድ እንጓዝ፣ ብልሆችም እንሁን!
:cry:

Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ‘የብልህነት መንገድ’ - ምርጥ መጠሓፍ በምርጥ ተርጓሚ - ይዘቷን እንካችሁ አጣጥሙ!

Post by Meleket » 15 Jul 2019, 05:07

ጎበዝ የዛሬ አስር የብልህነት መንገዶችን በተለያዩ የትምህርት ተቋማት ትምህርታቸዉ ሲከታተሉ ቆይተው ለምረቃ የበቁትን የአፍሪካ ቀንድ ልጆች ክብር እንጋራለን። አያይዘንም በሙያቸውና በተመረቁበት ዓውድ ስራ እንዲያገኙ ኣንመኝላቸዋለን። በተመሳሳይ መልኩም የአፍሪካ ቀንድ ትጉሃን ገበሬዎችንም የላባቸውን ፍሬ አበርክቶ ይለግሳቸው ዘንድ ፈጣሪንም እንማጠናለን። ይህን ስናደርግም ትግራይ ውስጥ ሆነው የሚያንገራግሩትን የቀድሞ ስርኣት ናፋቂዎችን ኣደብ እንዲገዙ ከትላንት ይልቅ ዛሬ ነገሮች እየጠሩ የነሱም መወሸቂያ ፍንትዉ ብሎ እየታየ ስለሆነ ባለችው አጭር ጊዜ ማለትም የባከነ ግዜን ለማካካስ በተጨመረችው አጭር ግዜ ተገቢዉን ንስሓ አድርገው “ከኅሊናቸው” ጋር በመታረቅ የሰውን መሬትና ንብረት በግዜ እንዲመለሱ በማስገንዘብ ነው! :mrgreen:

281. የአስተዋይ ሰዎችን ድጋፍ አግኝ። ቀዝቀዝ ያለዉ የታላቅ ሰዉ “አወንታ” ካልሰለጠኑት ሰዎች የድጋፍ ጫጫታ የበለጠ ነዉ። ጠቢቦች የሚናገሩት ገብቷቸዉ በመሆኑ ሙገሳቸዉ የማይሞት እርካታን ይፈጥራል። አንዳንዶች ሆዳቸዉን ስድ በሆነ ፋጉሎ ብቻ ለመሙላት ይጣጣራሉ። መሪዎች እንኳ ስለራሳቸዉ ሌላ ሰዉ እንዲጽፍላቸዉ ይፈልጋሉ፤ ሆኖም ግን የጸሀፊወችን ብዕር መልከ ጥፉ ሴት የሰአሊን ቡርሽ ከምትፈራዉ በላይ ይፈሩታል

282. ገለል በማለት በሰዎች ዘንድ ያለህን ከበሬታ ጨምር። ከሰዉ ፊት አለመጥፋት ዝናን ይቀንሳል፤ ከሰዉ ፊት ገለል ማለት ደግሞ ያበዛታል። ገለል ብሎ እያለ እንደ አንበሳ የሚቆጠረዉ ሰዉ በሰዉ ፊት ሲቀርብ ወደ አይጥነት ይቀየራል። ሀሳብ (መንፈስ) የያዘዉን ጸጋ ከማየት ይልቅ መሸፈኛዉን ማየት ስለሚቀል ታላቅ የሚባሉት ስጦታወች የሰዉ እጅ ሲነካቸዉ አንጸባራቂነታቸዉን ያጣሉ። ምናባችን የሚጓዘዉ ከእይታችን በበለጠ ፍጥነት ነዉ። ብዙዉን ጊዜ ማታለል የሚገባዉ በጆሯችን ሲሆን የሚወጣዉ ደግሞ በአይናችን ነዉ። የዝናዉ ማዕከል ወደሆነዉ ወደ ራሱ ራሱን የሚያገል ሰዉ መልካም ስሙን መጠበቅ ይቻለዋል። ፎኒክስ እንኳ ክብሯን ለማስጠበቅ እና ኣምሮትን ወደ ከበሬታ ለመቀየር የምትጠቀመዉ መሰወርን ነዉ።

283. የመፍጠር ችሎታ ይኑርህ ግን በልኩ አድርገዉ። ፈጠራ በጣም ላቅ ያለን የማሰብ ችሎታን ያመላክታል። ግን እብድ ሳይመስል ፈጣሪ መሆን የሚቻለዉ ማን አለ? ፈጣሪዎች በጣም ብልህ የሆነ አእምሮ አላቸዉ፤ ይህም ላቅ ያለ የአእምሮ ምርጫን ያሳያል። ሆኖም ግን የመፍጠር ችሎታ ከሰማየ ሰማያት የሚገኝ ፀጋ እና በጣም ብርቅየ የሆነ ነገር ሲሆን፤ የመምረጥ ችሎታ ግን ለብዙ ሰዎች የተቸረ ነገር ነዉ። የግኝት ችሎታ ደግሞ የተቸረዉ ጥቂት ለሆኑ ሰዎች ብቻ ሲሆን እነዚህም ሰዎች ባሉበት ጊዜ ሆነ በልቀታቸዉ ቀደምት የሆኑ ናቸዉ። አዲስ የሆነ ነገር ሀሴትን ይሰጣል፤ ነገሩ በእጥፉ እንዲያንጸባርቅ ያደርገዋል። ሆኖም ግን ቀደምት የሆነዉ ነገር በአመዛዛኝነት ዙሪያ ከሆነ እንቆቅልሽ የተቀላቀለበት ስለሚሆን አደገኛ ነዉ፤ የእዉቀት ጉዳይ ከሆነ ደግሞ የሚያስመሰግን ይሆናል፤ እነዚህ ሁለቱም አይነት ቀድምትነት ያላቸው ነገሮች ስኬታማ ከሆኑ ደግሞ ጭብጨባ የተገባቸዉ ናቸዉ።

284. በማያገባህ አትግባ እና ንቀት አያገኝህም። በሌሎች ዘንድ መከበር ብትፈልግ መጀመሪያ ራስህን አክብር። ራስህን ቆጥብ እንጅ አታባክን። ወደምትፈልግበት ሂድ እና መልካም አቀባበልን ታገኛለህ፤ ካልተጠራህ ደግሞ አትምጣ፤ ካልተላክ በስተቀር አትሂድ። በራሱ ተነሳሽነት የሚሰራ ሰዉ ያልተሳካለት እንደሆን ጥላቻን በራሱ ላይ ሲጋብዝ፤ የተሳካለት ጊዜ ደግሞ ምስጋናን አያገኝም። በማያገባቸዉ የሚገቡ ሰዎች ለስድብ የተጋለጡ ሲሆኑ፤ ጉዳዮች ዉስጥም ያለሀፍረት ተጋፍተዉ ስለሚገቡ የሚወጡት ተገፍትረዉ እና ግራ በመጋባት ነው።

285. በሌላ ሰዉ መጥፎ እድል ምክንያት አንተ እንዳትጠፋ ይሁን። ችግር ዉስጥ የገባን ሰዉ እወቀዉ እና ለእርዳታ እና ለመጽናናት እንደሚጠጋህ ጠብቅ። መከራ ጓደኛን ስለምትፈልግ መከረኞች ጀርባቸዉን ሰጥተዋቸዉ ወደ ነበሩ ሰዎች ፊታቸዉን ያዞራሉ። ራስህን አደጋ ዉስጥ ሳትጨምር ልትረዳቸዉ ስለማትችል እየሰመጠ ያለን ሰዉ ለማዳን ስትሞክር በጥንቃቄ መሆን አለበት።

286. ማንም እና ሁሉም ባለዉለታህ እንዳይሆኑ ተጠንቀቅ። ይህ የሆነ እንደሆን የጋራ ባሪያ ትሆናለህ። አንዳንዶች ሲፈጠሩ በተለየ ሁኔታ እድለኛ በመሆናቸዉ የተወሰኑት መልካም ነገር የማድረግ ልማድ ሲኖራቸዉ ሌሎች ደግሞ በዚህ ልክ መልካም ነገር ይደረግላቸዋል። ነፃነት ማለት ነፃነታችንን ከሚያሳጣን ስጦታ በላይ በጣም ዉድ የሆነች ነገር ናት። የበለጠ ሊያረካህ የሚገባ ሌሎች ያንተ ጥገኛ ሲሆኑ እንጅ አንተ የማንም ጥገኛ ስትሆን መሆን የለበትም። ባለስልጣን የመሆን ብቸኛዉ መልካም ጎን ብዙ መልካም ነገር ለማድረግ ማስቻሉ ነዉ። አብዛኛዉን ጊዜ እዛ ቦታ ላይ ያስቀመጠህ የሌሎች ሰዎች ብልጣብልጥነት በመሆኑ ከሁሉም በላይ ሀላፊነት የተሰጠህ ጊዜ ነገሩን እንደዉለታ ልትቆጥረዉ አይገባም።

287. ጉዳይህን ስሜታዊ ሆነህ እያለ አትፈጽም። አለዚያ ሁሉንም ነገር ታበላሸዋለህ። ሁሌም ስሜት ምክንያታዊነትን ወደ ግዞት ስለምትልከዉ፣ ስሜታዊ ሆነህ እያለህ ራስህን በሚጠቅም መልኩ እርምጃ ልትወስድ አትችልም። ስለዚህ ስሜታዊ ያልሆነን ሶስተኛ ወገን ተጠቀም። ተመልካቾች ኣብዛኛዉን ጊዜ ስሜታዊ ስለማይሆኑ ከተጫዋቾች በላይ ይመለከታሉ። እናም አስተዋይነት ስሜታዊነት እየመጣ መሆኑን ሲረዳ ጊዜዉ ለማፈግፈግ የተገባ ነዉ። ይህ ያልሆነ እንደሆን ግን ደም ፍላት ዉስጥ ትገባ እና ስራህ ሁሉ ደም በደም ይሆናል። ይህን ተከትሎም የአጭር ጊዜ መገንፈል ለብዙ ቀናት ግራ መጋባት እና ስም መጥፋት ይዳርግሃል።

288. ራስህን ከሁኔታወች ጋር አስማማ። አስተዳደር ወይም ምክንያታዊነት ሆነ የተቀሩት ነገሮች ሁሉ መፈጸም ያለባቸዉ በተገቢዉ ሰአት ነዉ። ጊዜ እና አጋጣሚ ማንንም ቆመዉ ስለማይጠብቁ አንድን ነገር ማድረግ እየቻልክ እያለ አድርገዉ። አስፈላጊ በሚባሉት የጨዋነት ህግጋት ካልሆነ በስተቀር በማይቀየሩ ህጎች አትገዛ። እንዲሁ ዛሬ ከሰደብከዉ ዉሀ ነገ መጠጣት ሊኖርብህ ስለሚችል ፍላጎትህም ቋሚ ህግጋትን እንዲከተል አትመኝ። አንዳንድ ሰወች እንቆቅልሽነትን የተላበሱ ስዶች በመሆናቸዉ ምክንያት ሁኔታወች በነሱ ፍላጎት መልክ ተቀይረዉ ወደ ስኬት እንዲያመሯቸዉ ይመኛሉ፤ መሆን የሚገባዉ ግን የዚህ ተቃራኒ ነበር። ጠቢቦች የአስተዋይነት መሰረት ያለችዉ ራስን ከሁኔታወች ጋር ማስማማት ላይ መሆኑን ይረዳሉ።

289. ከሁሉም የበለጠዉ ዉርደት ወራዳ መሆንን ማሳየት ነዉ። የሰዉ ልጅ ፍጹም ሰዉ ሆኖ የታየ ጊዜ በሌሎች ዘንድ እንደመለኮት መታየቱን ያጣል። ቅብጠት ለዝና ታላቅ እንቅፋት ነዉ። ራሱን ገለል የሚያደርግ ሰዉ ከሰዉ በላይ እንደሆነ ተደርጎ ሲቆጠር፤ ቂላቂሎች ደግሞ እንደታናሽ ይታያሉ። ከከበሬታ ጋር ፍፁም የተቃረነ በመሆኑ የቅብጠትን ያህል የሚያዋርድ ነገር የለም። ጅል በተለይም አሮጌ ጅል በዛ እድሜዉ ማስተዋልን ማግኘት ይገባዉ ስለነበር ቁም እስረኛ ነኝ ብሎ ሰዎችን ሊያሳምን ኣይችልም። ምንም እንኳ ይህ እንከኑ የብዙወች እንከን ቢሆንም በተለየ ሁኔታ አዋራጅ መሆኑ ግን ሊካድ የማይችል ነገር ነዉ።

290. ተወዳጅነትን እና ምስጋናን መቀላቀል በጣም ድንቅ የሆነ ነገር ነዉ። ሆኖም ግን የሰዎችን ከበሬታ ጠብቀህ መቆየት ብትሻ በጣም እንዳትወደድ ይሁን። ፍቅር ከጥላቻ ይልቅ ደፋር ሲሆን፤ መዉደድ እና ከበሬታ ደግሞ መዳበል የሚከብዳቸዉ ነገሮች ናቸዉ። በጣም አትወደድ፤ በጣምም አትፈራ። ፍቅር መላመድን ስለሚያስከትል፣ ፍቅር አንድ እርምጃ ወደፊት በገሰገሰ ቁጥር መከባበር አንድ እርምጃ ወደኋላ ያፈገፍጋል። ስለዚህ ለታላላቆች የተገባ ፍቅር በመሆኑ በስሜታዊነት ከመወደድ ይልቅ እየተመሰገንክ መወደድ ይሻልሀል

ጎበዝ፣ በብልህነት መንገድ እንጓዝ፣ ብልሆችም እንሁን!
:mrgreen:

Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ‘የብልህነት መንገድ’ - ምርጥ መጠሓፍ በምርጥ ተርጓሚ - ይዘቷን እንካችሁ አጣጥሙ!

Post by Meleket » 26 Jul 2019, 11:25

የዛሬ ሶስት የብልህነት መንገዶችን ለታዋቂዎቹ የመረጃ “ዲቴክቲቮች” ‘ለነእንቶኔ’ ክብር እንጋራዋለን! እነ ‘እንቶኔ’ መረጃ ውስጥ ብዙ በመቆየታቸው “ክብር የምንሰጣቸው” ፣ ነገር ግን፣ ‘ስድብ ቀንሱ፣ አእምሯችሁ ውስጥ በዘፈቀደ ስድቦችን አጭቃችሁ ይህን የመረጃ መድረኽ አታጉድፉ፣ አንድ ደረጃ “ኢቮልቭ” አድርጉ’ የሚል ምክር ሲሰጣቸው፣ ያንገሸገሻቸው ኣዛውንቶች ከነዚያ “ከምናውቃቸው ወንድሞቻችን” ጋር ንክኪ ያላቸው መሆናቸውን እንጠረጥራለን። :mrgreen: ስለሆነም እነዚህ “ዲቴክቲቮች”ን በመከታተል፣ መቐሌ የተወሸቁትን ቀንደኛ ወንጀለኞችን ማለትም እነ “እንቶኔንም” በምን ጥበብ ቀርቀብ ልናደርጋቸው እንደምንችል ፍንጭ ሊሰጡን ስለሚችሉ፣ እነዚህ ወንድሞቻችንን 'በክብር' እንንከባከባቸዋለን። :mrgreen: ይህን ስናደርግም የመረጃ አባላት በሙሉ፡ አንድ ደረጃ “ኢቮልቭ” ያላደረጉ የስድብና የቆሻሻ አስተሳሰብ ቋቶችን ከወዲሁ አነጥሮ በማወቅ በሚቀጥለው የጽዳት ዘመቻ አስፈላጊዉን ጥንቃቄ በማድረግ ከተላላፊዉ በሽታቸው ራሱን እንዲከላከል በኤርትራዊ ጭዋነት በመምከር ነው! :mrgreen:

291. ሰዎችን መመርመር እወቅበት። በትኩረትና በአመዛዛኝነት የሌላዉን ሰዉ ኮስታራነት እና ቁጥብነት መርምር። ሰዉን መመርመር ታላቅ የሆነ የማመዛዘን ችሎታን ይጠይቃል። አትክልትን እና የማዕድናትን ባህሪ ከማወቅ ይልቅ የሰወችን ባህሪ ማወቅ የበለጠ ጠቃሚ ነዉ። በርግጥ ይህ ነገር ብልጠት ከተሞላባቸዉ የህይወታችን ገፅታወች አንዱ ነዉ። ብረታብረቶችን በሚሰጡት ድምጽ መመርመር እንደሚቻለዉ ሁሉ ሰወችን ደግሞ በንግግራቸዉ መመርመር ይቻላል። ቃላት ችሎታን ቢያመላክቱም፤ ተግባር ከቃላት በበለጠ ሁኔታ ችሎታን ያሳያል። እዚህ ላይ ነዉ እንግዲህ ታላቅ ጥንቃቄ፤ ጠለቅ ያለ ትኩረት፤ ብልጠት የታከለበት ማገናዘብ እና ላቅ ያለ ማመዛዘን የሚያስፈልገን።

292. ችሎታህ ስራህ ከሚጠይቀዉ በላይ እንጅ ያነሰ እንዳይሆን። የያዝከዉ ቦታ የፈለገ ታላቅ ቢሆን እንኳ አንተ የበለጠ ታላቅ መሆንህን ማሳየት አለብህ። ትልቅ የሆነ ችሎታ በየትኛዉም ሙያ ቢሆን የበለጠ ትልቅ እየሆነ እና ታላቅነቱ እየተገለፀ ይሄዳል። የልብ እና የችሎታ ማነስ ያለበት ሰዉ ደግሞ በቀላሉ ይደረስበታል፤ ዉሎ አድሮም የስራዉ ክብደት ዝናዉን ያጎድፈዋል። ታላቁ አጉስተስ ከመስፍን የበለጠ ሰው በመሆኑ ደስተኛ ነበር። እዚህ ላይ ነዉ እንግዲህ ሀያል መንፈስ እና ተጨባጭ የሆነ በራስ መተማመን የሚያስፈልገዉ።

293. ብስለት። ይህ ነገር በዉጭ ሲታይ ብቻ ሳይሆን በሰዉየዉ ምግባር ላይም የበለጠ የሚንፀባረቅ ነገር ነዉ። ብስለት የሰዎችን ተሰጥኦ በማጀብ ከበሬታን ያስገኛል። እርጋታ የተቀላቀለበት ግርማ የመንፈስ መገለጫ ነዉ። ረጋ ማለት የሀያልነት እርጋታ እንጅ መንጋዎች እንደሚያስቡት የቂሎች ደነዝነት እና ጸጥታ አይደለም። የእነዚህ ሰወች ንግግር ቁርጥ ያለ ሲሆን ነገራቸዉ ደግሞ የተግባር ነዉ። የአንተ እዉነተኛነት የብስለትህን ያህል ነዉ። እንደ ህጻን መሆንህን አቁመህ ኮስተር ስትል ሀያልነትን ትላበሳለህ።

ጎበዝ፣ በብልህነት መንገድ እንጓዝ፣ ብልሆችም እንሁን!
:mrgreen:

Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ‘የብልህነት መንገድ’ - ምርጥ መጠሓፍ በምርጥ ተርጓሚ - ይዘቷን እንካችሁ አጣጥሙ!

Post by Meleket » 13 Aug 2019, 10:00

ጎበዝ የዛሬ አራት የብልህነት መንገዶችን በወንድሞቻችንና እህቶቻችን አማካኝነት ተወጣትነት ግዜው ጀምሮ በተገቢዉ ሁኔታ ተመልምሎ፡ በአስተዳደርና ውትድርና ጥበብ ደቁኖና ተክኖ ጰጵሶና ፐትርኮ ሓጂጆም፡ በትህትና ተጉዞ፡ ሽ ጊዜ ተጠላት አፈሙዝ ተርፎ፡ አገሬ ኤርትራን ከተራ ታጋይነት እስከ ጀኔራልነትና ምኒስተርነትም ደረጃ በአንደበተ ርቱዕነት ሳያሰልስ ላገለገለው ለወዲ ኤፍሬም ክብር እንጋራለንይህን ስናደርግም የሱና የመሰል ትሁት ግን ደግሞ ቆራጥና ጀግና ኤርትራዉያን የህዝብ አገልጋዮች ህላዌ እንቅልፍ የሚነሳቸውንና የሚያስደነብራቸውን ንንያውታቢደደ፡ “እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል” እያልን፣ ዛሬም እንደ ወትሮው ኤርትራዊ የንቃተ ህሊና ትምህርትን እየሰጠን፣ ምንም እንኳን እጅግ ቢረፍድባቸውም፡ “የሰው ወርቅ አያደምቅ” መሆኑን ተገንዝበው ለሕግ ልዕልና ተገዝተው ታገራችን መሬት በሰላም እንዲወጡ እያሳሰብን ነው! :mrgreen:

294. አቋምህ የተለሳለሰ ይሁን። እያንዳንዱን ሰዉ ሀሳቡን የሚሰነዝረዉ ከራሱ ጥቅም አንፃር ሲሆን ሀሳቡን ለማስረገጥ ደግሞ ብዙ ምክንያቶችን ይደረድራል። የብዙ ሰዎች አመዛዛኝነትም ስሜታዊነት የነገሰበት ነዉ። አብዛኛዉን ጊዜ ሁለት ሰዎች ይፋጠጡ እና ሁለቱም እኔ ነኝ ምክንያታዊ እያሉ ያስባሉ። ሆኖም ግን ምክንያታዊነት እዉነት ብትሆንም ሁለት ፊት የላትም። እንዲህ አይነት አጋጣሚወችን በጥበብ እና በጥቃቄ ልትይዛቸዉ ይገባል። እናም አንዳንዴ የራስህን አቋም በባልንጀራህ አይን እየተመለከትክ ብትመረምር ባልንጀራህን አለመኮነን ብቻ ሳይሆን እንዲሁ በጭፍኑ ትክክል ነኝ ለማለትም አትደፍርም።

295. ወሬን ትተህ የስራ ሰዉ ሁን። በጣም የሚያጋንኑ ስዎች በጣም ጥቂት የሰሩ ናቸዉ። እንዲህ አይነት ሰዎች ሁሉንም ነገር በሚያስቅ ሁኔታ ላቅ ያለ እንዲመስል ያደርጉታል። አስቂኝ እስስቶች ከመሆናቸው የተነሳ ደግሞ የማያስቁት ሰዉ የለም። ከንቱነት ሁሌም የሚያናድድ ተግባር ቢሆንም እንዲህ አይነቱ ከንቱነት ግን አስቂኝ ነዉ። አንዳንድ ሰዎች የጀግንነት ለማኞች በመሆናቸዉ ምክንያት ጥቃቅን ክብርን እንደሚቆልሉ ጉንዳኖች ይቆጠራሉ። ግብርህ ታላቅ በሆነ ቁጥር የታይታ ተግባርህም በዛዉ ልክ ያነሰ ሊሆን ይገባዋል። እናም ወሬን ለሌሎች ተዉላቸዉ እና በመስራትህ ብቻ ተደሰት። ስለዚህ ስራ እንጅ አትለፍልፍ፤ በአዋቂዎች ዘንድ ደግሞ መሳለቂያ ስለሚያደርግህ ጭቃ ላይ ሙገሳን የምትጽፍበት ብዕር እንዳትከራይ። ጀግና ለመምሰል ሳይሆን ጀግና ለመሆን ተጣጣር።

296. ታላቅ ተሰጥዖዎች። ታላቅ ተሰጥዖዎች ታላቅ ሰዉ ይፈጥራሉ። አንድ ላቅ ያለ ተሰጥዖ ዋጋዉ ከሽህ አልባሌ ነገሮች የበለጠ ነዉ። የጓዳ እቃወቹ ሳይቀሩ ሁሉም ነገሮቹ ትልቅ እንዲሆኑለት የፈለገ አንድ ሰዉ ነበረ፤ እነሆ ታላቅ ሰዉ ደግሞ የመንፈስ ስጦታወቹ የበለጠ ታላቅ እንዲሆኑለት ሊጥር ይገባዋል። በእግዚአብሄር ዘንድ ሁሉም ነገሮች ህልቆመሳፍርት እና ፍጹም ሰፊ ስለሆኑ የጀግና ደግሞ ምግባሮቹ እና ቃላቶቹ ሀያል የሆነ ግርማን ይላበሱ ዘንድ ሁሉም ነገሩ ታላቅ እና ግርማን የተመላ መሆን አለበት።

297. ሁሌም የምታደርገዉን ነገር ሁሉ ሰዎች እንደሚመለከቱ አድርገህ አስብ። እየታየ እንደሆነ ወይም ቆይቶ እንደሚታይ የሚያዉቅ ሰዉ ዙሪያዉን በደንብ የሚያስተዉል ሰዉ ነዉ። ሰዎች ሁሌም እንደሚያዳምጡ እና መጥፎ ተግባርም እንደሚገለጥ ያዉቃል። ብቻዉን እያለ እንኳ የአለም ሁሉ አይን እርሱ ላይ እንዳረፈ ይረዳል፤ ሁሉም ነገር መገለጡ እንደማይቀርም ያዉቃል። ጉዳዩን ሲያከናዉን ደግሞ በኋላ አንድ ነገር ቢሰሙ የሚመሰክሩለት ምስክሮች እንዳሉት እያሰብ ነዉ። አለሙ ሁሌም ቢመለከተኝ እያለ የሚያስብ ሰዉ ጎረቤቶቹ ግድግዳቸዉን ተገን አድርገዉ ወደ ቤቱ ቢያጮልቁበት ምንም አይመስለዉም።

ጎበዝ፣ በብልህነት መንገድ እንጓዝ፣ ብልሆችም እንሁን!
:mrgreen:

TGAA
Member+
Posts: 5598
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

Re: ‘የብልህነት መንገድ’ - ምርጥ መጠሓፍ በምርጥ ተርጓሚ - ይዘቷን እንካችሁ አጣጥሙ!

Post by TGAA » 13 Aug 2019, 12:15

I have respect the wisdom contained here in , but as chain’s proverb says it “Give a man a fish and he will eat for a day. Teach a man how to fish and you feed him for a lifetime” we rather teach people how to think rather than trying to imprint the words of a wise man by rote. As the great thinker Socrates said ““Education is the kindling of a flame, not the filling of a vessel.”

TGAA
Member+
Posts: 5598
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

Re: ‘የብልህነት መንገድ’ - ምርጥ መጠሓፍ በምርጥ ተርጓሚ - ይዘቷን እንካችሁ አጣጥሙ!

Post by TGAA » 13 Aug 2019, 12:19

I have respect the wisdom contained here in , but as chain’s proverb says it “Give a man a fish and he will eat for a day. Teach a man how to fish and you feed him for a lifetime” we rather teach people how to think rather than trying to imprint the words of a wise man by rote. As the great thinker Socrates said ““Education is the kindling of a flame, not the filling of a vessel.”

Degnet
Senior Member+
Posts: 25078
Joined: 16 Feb 2013, 11:48

Re: ‘የብልህነት መንገድ’ - ምርጥ መጠሓፍ በምርጥ ተርጓሚ - ይዘቷን እንካችሁ አጣጥሙ!

Post by Degnet » 13 Aug 2019, 12:49

Meleket wrote:
13 Aug 2019, 10:00
ጎበዝ የዛሬ አራት የብልህነት መንገዶችን በወንድሞቻችንና እህቶቻችን አማካኝነት ተወጣትነት ግዜው ጀምሮ በተገቢዉ ሁኔታ ተመልምሎ፡ በአስተዳደርና ውትድርና ጥበብ ደቁኖና ተክኖ ጰጵሶና ፐትርኮ ሓጂጆም፡ በትህትና ተጉዞ፡ ሽ ጊዜ ተጠላት አፈሙዝ ተርፎ፡ አገሬ ኤርትራን ከተራ ታጋይነት እስከ ጀኔራልነትና ምኒስተርነትም ደረጃ በአንደበተ ርቱዕነት ሳያሰልስ ላገለገለው ለወዲ ኤፍሬም ክብር እንጋራለንይህን ስናደርግም የሱና የመሰል ትሁት ግን ደግሞ ቆራጥና ጀግና ኤርትራዉያን የህዝብ አገልጋዮች ህላዌ እንቅልፍ የሚነሳቸውንና የሚያስደነብራቸውን ንንያውታቢደደ፡ “እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል” እያልን፣ ዛሬም እንደ ወትሮው ኤርትራዊ የንቃተ ህሊና ትምህርትን እየሰጠን፣ ምንም እንኳን እጅግ ቢረፍድባቸውም፡ “የሰው ወርቅ አያደምቅ” መሆኑን ተገንዝበው ለሕግ ልዕልና ተገዝተው ታገራችን መሬት በሰላም እንዲወጡ እያሳሰብን ነው! :mrgreen:

294. አቋምህ የተለሳለሰ ይሁን። እያንዳንዱን ሰዉ ሀሳቡን የሚሰነዝረዉ ከራሱ ጥቅም አንፃር ሲሆን ሀሳቡን ለማስረገጥ ደግሞ ብዙ ምክንያቶችን ይደረድራል። የብዙ ሰዎች አመዛዛኝነትም ስሜታዊነት የነገሰበት ነዉ። አብዛኛዉን ጊዜ ሁለት ሰዎች ይፋጠጡ እና ሁለቱም እኔ ነኝ ምክንያታዊ እያሉ ያስባሉ። ሆኖም ግን ምክንያታዊነት እዉነት ብትሆንም ሁለት ፊት የላትም። እንዲህ አይነት አጋጣሚወችን በጥበብ እና በጥቃቄ ልትይዛቸዉ ይገባል። እናም አንዳንዴ የራስህን አቋም በባልንጀራህ አይን እየተመለከትክ ብትመረምር ባልንጀራህን አለመኮነን ብቻ ሳይሆን እንዲሁ በጭፍኑ ትክክል ነኝ ለማለትም አትደፍርም።

295. ወሬን ትተህ የስራ ሰዉ ሁን። በጣም የሚያጋንኑ ስዎች በጣም ጥቂት የሰሩ ናቸዉ። እንዲህ አይነት ሰዎች ሁሉንም ነገር በሚያስቅ ሁኔታ ላቅ ያለ እንዲመስል ያደርጉታል። አስቂኝ እስስቶች ከመሆናቸው የተነሳ ደግሞ የማያስቁት ሰዉ የለም። ከንቱነት ሁሌም የሚያናድድ ተግባር ቢሆንም እንዲህ አይነቱ ከንቱነት ግን አስቂኝ ነዉ። አንዳንድ ሰዎች የጀግንነት ለማኞች በመሆናቸዉ ምክንያት ጥቃቅን ክብርን እንደሚቆልሉ ጉንዳኖች ይቆጠራሉ። ግብርህ ታላቅ በሆነ ቁጥር የታይታ ተግባርህም በዛዉ ልክ ያነሰ ሊሆን ይገባዋል። እናም ወሬን ለሌሎች ተዉላቸዉ እና በመስራትህ ብቻ ተደሰት። ስለዚህ ስራ እንጅ አትለፍልፍ፤ በአዋቂዎች ዘንድ ደግሞ መሳለቂያ ስለሚያደርግህ ጭቃ ላይ ሙገሳን የምትጽፍበት ብዕር እንዳትከራይ። ጀግና ለመምሰል ሳይሆን ጀግና ለመሆን ተጣጣር።

296. ታላቅ ተሰጥዖዎች። ታላቅ ተሰጥዖዎች ታላቅ ሰዉ ይፈጥራሉ። አንድ ላቅ ያለ ተሰጥዖ ዋጋዉ ከሽህ አልባሌ ነገሮች የበለጠ ነዉ። የጓዳ እቃወቹ ሳይቀሩ ሁሉም ነገሮቹ ትልቅ እንዲሆኑለት የፈለገ አንድ ሰዉ ነበረ፤ እነሆ ታላቅ ሰዉ ደግሞ የመንፈስ ስጦታወቹ የበለጠ ታላቅ እንዲሆኑለት ሊጥር ይገባዋል። በእግዚአብሄር ዘንድ ሁሉም ነገሮች ህልቆመሳፍርት እና ፍጹም ሰፊ ስለሆኑ የጀግና ደግሞ ምግባሮቹ እና ቃላቶቹ ሀያል የሆነ ግርማን ይላበሱ ዘንድ ሁሉም ነገሩ ታላቅ እና ግርማን የተመላ መሆን አለበት።

297. ሁሌም የምታደርገዉን ነገር ሁሉ ሰዎች እንደሚመለከቱ አድርገህ አስብ። እየታየ እንደሆነ ወይም ቆይቶ እንደሚታይ የሚያዉቅ ሰዉ ዙሪያዉን በደንብ የሚያስተዉል ሰዉ ነዉ። ሰዎች ሁሌም እንደሚያዳምጡ እና መጥፎ ተግባርም እንደሚገለጥ ያዉቃል። ብቻዉን እያለ እንኳ የአለም ሁሉ አይን እርሱ ላይ እንዳረፈ ይረዳል፤ ሁሉም ነገር መገለጡ እንደማይቀርም ያዉቃል። ጉዳዩን ሲያከናዉን ደግሞ በኋላ አንድ ነገር ቢሰሙ የሚመሰክሩለት ምስክሮች እንዳሉት እያሰብ ነዉ። አለሙ ሁሌም ቢመለከተኝ እያለ የሚያስብ ሰዉ ጎረቤቶቹ ግድግዳቸዉን ተገን አድርገዉ ወደ ቤቱ ቢያጮልቁበት ምንም አይመስለዉም።

ጎበዝ፣ በብልህነት መንገድ እንጓዝ፣ ብልሆችም እንሁን!
:mrgreen:
The highest thing in human life is to be happy and this is adding some thing to our happiness/ke talalak sewoch tsehuf belay lela astemari yelem.University west ketemarkut yelek metsaheft ke manbeb yetemarkut yebelete tekmognal,Oscar Wilde.

Post by Meleket » 14 Sep 2019, 03:30

ለዛሬ አንዲት የብልህነት መንገድ ለአርበኛዉ ወልቃይቴ አቶ ገብረ እግዚአብሔር ክብር እና የኒህን ጀግና ታሪክ በጨረፍታም ይሁን ላካፈሉን ለአርበኛው ተስፋ ሚካኣኤል ትኩእ ክብር እንጋራለንይህን ስናደርግም አዲሱ ዘመነ ምሕረት ለኤርትራና ለኢትዮጵያ ህዝቦች ሰላምንና ወንድማማችነትን እየተመኘን፣ አፈንጋጯ ህወሓትም ከሰፈረችበት ልዑላዊ መሬታችን በኤርትራኛ ሆነ በወልቃይትኛ እንዲሁም በራይኛሂጂ ወደናትሽ የወለደ አይጥልም!እያልን ከወዲሁ ልኳን እየነገርንና እያሳሰብን ነው! :mrgreen:

298. ሶስት ነገሮች ታላቅ ሰዉን ይፈጥራሉ። እነሱም ታላቅ የመለኮት ስጦታ የሆኑት ብሩህ አእምሮ፣ ጥልቅ የሆነ የመረዳት ችሎታ እና ላቅ ያለ የመምረጥ ችሎታ ናቸዉ። ምናብ ታላቅ ስጦታ ቢሆንም ከዚህ የበለጠዉ ግን በደንብ ማሰብ እና መልካሙን ነገር መረዳት መቻል ነዉ። ማሰቢያችን ጠቃሚ እንጅ አድካሚ እንዳይሆን አከርካሪያችን ላይ መቀመጥ የለበትም። በደንብ ማሰብ መቻል ከምክንያታዊ ተፈጥሮ የሚቸር ፍሬ ነዉ። የሰዉ ልጅ በሀያ አመቱ የማድረግ ፍላጎቱ፤ በሰላሳ አመቱ እዉቀቱ፤ በአርባ አመቱ ደግሞ አመዛዛኝነቱ የጸና ይሆናል። የአንዳንድ ሰዎች አይን የተኩላ አይን ይመስል በጨለማ ጊዜ ከማንጸባረቁ በላይ በደንብ ጥርት አድርጎ የሚያስበዉ ራሱ በጣም በጨለመ ጊዜ ነዉ። የአንዳንድ ሰዎች አእምሮ ደግሞ ለእያንዳንዱ አጋጣሚ ተገቢዉን ነገር ማሰብ ስለሚችል በጣም ድንገተኛ ለሆነዉ ነገር ሁሉ አስፈላጊ የሆነዉን ነገር በቶሎ መለየት ይችላል። እንዲህ አይነት ተሰጥኦ የበዛ እና መልካም የሆነ ነገር የሚወጣዉ አስደሳች የሆነ ነገር ነዉ። መልካም ምርጫ ደግሞ ህይወታችንን በሞላ የምታጣፍጥ ነገር ነች።

ጎበዝ፣ በብልህነት መንገድ እንጓዝ፣ ብልሆችም እንሁን!
:mrgreen:

Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ‘የብልህነት መንገድ’ - ምርጥ መጠሓፍ በምርጥ ተርጓሚ - ይዘቷን እንካችሁ አጣጥሙ!

Post by Meleket » 27 Sep 2019, 07:57

ጎበዝ የዛሬ የመጨረሻ ሁለት የብልህነት መንገዶችን የመስቀልን ማለትም የደመራዉን በዓል ምክንያት በማድረግ በዋነኛነት መስቀሉ ላይ ለዋለው ሰላማዊዉና ሰማያዊው ንጉሠነገሥት ክብር፣ መስቀሉን ፈልጋ ላገኘችዉ ምድራዊቷ ንግሥትና ለአጋሮቿ ክብር እንዲሁም ይህን ድንቅ መጠሐፍ ለደረሰልን ለባልታሳር ግራሽያን፡ በድንቅ አማርኛ ለተረጎመልን ለአያሉ አክሊሉና ይህን ድንቅ ድረገጽ በመመስረት ይህንና መሰል ርእሶችን እንድንጋራና እንድንወያይ ለተጋዉ ለኤልያስ ክፍሌ ክብር እንጋራለንይህን ስናደርግም አሁን በዘመናችን እውነትን ዘቅዝቀው ለሰቀሏትና በጥልቅ ጉድጓድ እዉነትን ለመቅበር አጉል የሚውተረተሩትንና ከሕግ የበላይነት ለመሸሽ በከንቱ የሚፍጨረጨሩትን የትግራይ ወያኖችን ሆነ መሰሎቻቸውን በመስቀሉ ስም ለሓቅና ለኅሊና ተገዙ እያልን ደግመን ደጋግመን እየመከርን ነው! :mrgreen:

299. ሰዎች እንዲጠሙ አድርግ። የማሩን ሳህን እንኳ ከንፈር ላይ ማንሳት አለብህ። አንድ ነገር ዋጋዉ የሚወሰነዉ በተፈላጊነቱ ልክ ነዉ። ስጋዊ ጥምን እንኳ ማጠጣት ግን አለማርካት መልካም ነዉ። አንድ ነገር ዋጋዉ በተፈላጊነቱ ልክ ነዉ። መልካም ነገር በጥቂቱ የሆነ እንደሆነ እጥፍ ጊዜ መልካም ነዉ። የአንድ ነገር ዉድቀቱ ለሁለተኛ ጊዜ ሲቀርብ ነዉ። ከልክ ያለፈ ደስታ አደገኛ ብቻ ሳይሆን የፈጣሪን ቁጣም የሚያወርድ ነገር ነዉ። ማቅመስ ግን አለማርካት ሰዎችን የምናስደስትበት ብቸኛዉ መንገድ ነዉ። አምሮትን ማነቃቃት ከፈለግህ ሀሴት የተሞላ እርካታን ሳይሆን በፍላጎት ማጣደፍን ተጠቀም። ተለፍቶ የተገኘ ነገር የሚፈጥረዉ ሀሴት እጥፍ እጅ ነዉ።

300. ባጭሩ፤ ቅዱስ ሁን። ይህ ሁሉንም ይናገራል። ጨዋነት የሁሉም ልቀቶች አገናኝ ሰንሰለት እና የሀሴቶች ሁሉ ማዕከል ናት። ጨዋነት አስተዋይ፣ ጥንቁቅ፣ አመዛዛኝ፣ ብልጥ፣ ጠቢብ፣ ጀግና፣ ታማኝ፣ አሳቢ፣ ደስተኛ፣ ክቡር፣ ምስጉን እና . . . ሁሉን አቀፍ ጀግና ታደርግሃለች። አንድን ሰዉ ደስተኛ የሚያደርጉት ሶስት ነገሮች ጤና፤ ቅዱስነት እና ጠቢብነት ናቸዉ። ጨዋነት የአለሙ ሁሉ ተምሳሌት ፀሀይ ስትሆን፤ መልካም ህሊና ደግሞ የአለሙ አድማስ ነች። ጨዋነት ዉብ ነገር በመሆኗ ምክንያት የእግዚአብሔርን ብቻ ሳይሆን የሰዎችንም ደግነት ታስገኝልናለች። እንደ ጨዋነት ዉብ እንደ እርኩስነት ደግሞ አስጠሊታ የሆነ ነገር የለም። እዉነትነት ያለዉ የጨዋነት ነገር ብቻ በመሆኑ የተቀረዉ ሁሉ የሀሰት ነዉ። ታላቅነት እና ችሎታ ደግሞ መሰረታቸዉ ጨዋነት እንጅ እጣ ፋንታ አይደለም። ራስ በራሱ ምሉኡ የሆነ ነገር ጨዋነት ብቻ ነዉ። ጨዋነት ሰዎችን በሕይወት እያሉ ተወዳጅ፤ ከሞቱ በኋላ ደግሞ ታሳቢ ታደርጋቸዋለች።

ጎበዝ፣ በብልህነት መንገድ እንጓዝ፣ ብልሆችም እንሁን! :mrgreen:

ተፈጠመ።

Post Reply