Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
samsom
Member
Posts: 72
Joined: 05 Aug 2016, 19:52

Re: ጉራጌ ማነው? የስረ ጉራጌ ውይይት አጭር መነሻ

Post by samsom » 11 Aug 2019, 23:01

ወይ አቶ Horus ምን ነክቶህ ነው ግን በጉራጌ ሳባ የሚባል ስም የለም ነበር ይልከው?
የምን ቅርስ ቋንቋ social anthropologist ነው በቀላሉ DNA እያለ:: ለምን በራስህ አትጀምርም ?
ጉራጌ ከሰሜን ያልፈለሰ ጎሳ ካልሆነ እኮ ውጤቱ ይለያል ለምሳሌ ሀድያ የተለየ ውጤት አለው ጉራጌ ከሰሜኑ ህዝብ የተለየ ውጤት አለው እንዴ?

Horus
Senior Member+
Posts: 30908
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ጉራጌ ማነው? የስረ ጉራጌ ውይይት አጭር መነሻ

Post by Horus » 11 Aug 2019, 23:36

ሳምሶን
እኔ ከዚህ ዘር ልወለድ ብዬ በምርጫ አልተወለድኩም። የጄኔቲክ ማፒንግ ከአካለ ጉዛይ መጣህ ካለኝ በትልቅ ደስታ እቀበለዋለሁ ። እኔ የአካለ ጉዛይ ወይ የሃማሴን ዘር የመሆን ችግር የለኝ። ግን አለቃ ታየ ዝም ብለው ብዙ ተረት ወርውረዋል። ለምሳለ ጉራጌ ግራ (left) ከሚለው ፍጹም አይገናኝም ። ጉራጌ የእምነት ስም ነው ። የጉራጌ እምነት ተከታዮች እንደማለት ነው ።

አንድ ምሳሌ ልንገርህ ስለ አለቃ ታየ ሚትዶሎጂ ። ጋፋት የሚባለው የክስታኔ ጉራጌ ወንድም የነበረ ህዝብ በዛሬ አምቦ አዲስ አለም ሙገርና ዙሪያ ይኖሩ ነበር። በኦሮሞ ወረራ አልቀው ጥቂቱ ሸሽተው አባይን ተሻግረው የዛሬ ደጋ ዳሞ ጎጃም ተጠለሉ ። ጋፋቶች ዝነኛ ብረት አቅላጮች ነበሩ ። ከቀይ አፈር ደወል ይባላ ቀቅለው iron ore የሚሰሩ ነበሩ ። አጼ ቴዎድሮስ ይህን ችሎታቸው ሰምቶ ጥቂቱን መቅደላ ወስዶ ዛሬ የምታየውን የቴዎድሮስ መድፍ አሰራቸው ። እንሱም ረብተው በጎንደር ጋፋት የቢባል ትንሽ ዘር ተመሰረተ ። አሁን አለቃ ታየ ጋፋት የሚለው ስም ከየት መጣ ተብለው ሲመልሱ ያሉት ይህ ነው። ንግስት ሳባ ትሁን ሌላ (ረሳሁት) ታቦት ይዘው ጠባብ ገደል ወስጥ ሲሄዱ ገፋት ገፋት ስላለ ጋፋት ተብሎ ቀረ ይላሉ ። ስለ ጉራጌም ያሉት ከዚህ አይሻልም ። ጉራጌ የሚለው ቃል ከየት መጣ ቢባሉ ጉራ ከሚለው አከለ ጉዛይ ነው አሉ ። አለቃ ታየ ግ ን አንድ ግዜ በጉራጌ ኖረው ቋንቋውን ተምረው ታሪኩን አጥንተው ሽማግሎችህን አናግረው አያቁም።

ሌላው ካሻህ ርታኝ ። ማክዳ፣ ሳባ፤ አዜብ በፍጹም የጉራጌ ሴት ስም አይደሉም። ስም ከዘር ግንድ ና ከባህል ጋር ይያያዛል። ነገር ግ ን ግለሰብ የትግራይም ሆነ የኤርትራ በተሰቦች በጉራጌ ሊኖሩ እንደ ሚችሉ አምናልሁ ። ይህም ሆነ ያ ጉራጌ ከጉዛይ መጣ በመባልኡ the 2 peoples have a great loving relationship - that is all good ! Keir

mitmitaye
Member
Posts: 680
Joined: 29 Mar 2018, 15:18

Re: ጉራጌ ማነው? የስረ ጉራጌ ውይይት አጭር መነሻ

Post by mitmitaye » 12 Aug 2019, 09:21

samsom wrote:
11 Aug 2019, 23:01
ወይ አቶ Horus ምን ነክቶህ ነው ግን በጉራጌ ሳባ የሚባል ስም የለም ነበር ይልከው?
የምን ቅርስ ቋንቋ social anthropologist ነው በቀላሉ DNA እያለ:: ለምን በራስህ አትጀምርም ?
ጉራጌ ከሰሜን ያልፈለሰ ጎሳ ካልሆነ እኮ ውጤቱ ይለያል ለምሳሌ ሀድያ የተለየ ውጤት አለው ጉራጌ ከሰሜኑ ህዝብ የተለየ ውጤት አለው እንዴ?
Guraghe culturally and linguistically is very different from the north. Of course, guraghe like his brothers in northern Ethiopia, love and will die for enat Itopiya. That is it!

Guraghe has a Qicho culture. That's not the case in the north. Qocho culture is quite different. The story of guraghe came from gura in ertra doesn't hold water. Is there a Qocho culture in ertra? As far as I know the answer is NO!

Guraghe is one of the ancient tribes of Ethiopia in its own right, not an extension of the north!!

Horus
Senior Member+
Posts: 30908
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ጉራጌ ማነው? የስረ ጉራጌ ውይይት አጭር መነሻ

Post by Horus » 12 Aug 2019, 23:36

ሚጥሚጣዬ

ይሀው አንድ አስገራሚ ነገር ልጨምር ። እንደ አለቃ ታየ አባባል ካምደ ጽዮን ጋር መጡና ጉራጌን አቆሙ የተባሉት ስብሃት እና ሃጎስ ይባላሉ ተባለ። ስብሃቶ የሚለው ስም አልፎ አልፎ አለ፣ እሱም ስብሃት ለአማልክ እንዲሉ በቀጥታ ከከርስቲና ጋር የመጣ ነው።

እስከ ዛሬ ድረስ አንድ ሃጎስ የሚባል ጉራጌ የለም ። ሃጎስ የሚለው ቃል እንኳ በጉራጐኛ ወስጥ ፈጽሞ የለም ። ደስታ ለሚለው ቃል ጉራጌ ያለው ፍስሃ (ተፊሳነም ማለት ደስ ብሎናል ማለት ነው) ደስታ፣ ሌላውና እውነተኛ ጉራጌኛው ቃል ብልቃት ነው ። ሌላው ትልቁ የደስታ ቃል ጌሳት ናቸው ። ብልቃት፣ ጌሳት፣ ተፊሳት፣ ፍስሃ፣ ደስታ በቃ ። ሃጎስ የጉራጌ አባት ቢሆን ቢያንስ 50% በመቶ የወንድ ልጅ ሃጎስ ይባል ነበር።

Post Reply