Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

‘የብልህነት መንገድ’ - ምርጥ መጠሓፍ በምርጥ ተርጓሚ - ይዘቷን እንካችሁ አጣጥሙ!

Post by Meleket » 03 Apr 2019, 09:32

በዚህ ርእስ ስር፡ ባልታሳር ግራሽያን የጻፈውን፡ የሐረማያ ዩኒቨርስቲው አያሉ አክሊሉ የተረጎመዉን ድንቅ መጣህፍ ይዘት እናጣጥመዉ ዘንድ በዝግታ ማለትም በኤሊ አካሄድ እንጎማለልበታለን። እዚህ የምንጋራዉ ጽሑፍ መታሰቢያነቱ “የሔጉን ውሳኔ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ እተገብራለዉ” ብለው በይፋ በኢትዮጵያ ህዝብ ፓርላማ ውስጥም ሳይቀር ቃል የገቡትን የኦሕዴዱ ወጣት ጠቅላይ አብይ ወደ ስልጣን የተፈናጠጡበትን፡ እንዲሁም አፈንጋጯ ሕወሓት መቐለ የተወሸቀችበትን፣ የኤርትራና የኢትዮጵያ ህዝብም ሰላም በመስፈኑና የድንበሩ ብይን ትግባሬ ላይ ይውላል ብለው ሙሉ ተስፋ የጣሉበትንና ልባዊ ፈንጠዝያ ያደረጉበትን አንደኛ ዓመት የድል በአል እያከበርን ነው። :mrgreen:

የብልህነት መንገድ ይዘቷ በዚህ ፎረም ወይ መድረክ ተጠቃሚ ዜጎች በሙሉ፡ በተለይ ደግሞ አንዳንድ ስድነትን የምናስተጋባና ምላሳችን ሆነ ልባችን ያልተገረዘ ዋልጌዎችን የስነምግባር ትምህርት የምትሰጥ በመሆኗ፡ እግረመንገዳችንን ወደዝች ገጥ ጎራ ባልን ቁጥር ይህችን በምርጥ አማርኛ የተቀነባበረች ምርጥ ሃሳብን የምትዘራ መጽሐፍ ይዘት እንድትጋሩ በአፍሪካዊ ትህትና እጠይቃችኋለሁ!!! መጸሓፊቱን በመግዛትም ተርጓሚዉን ታበረታቱ ዘንድም በኤርትራዊ ወኔ ላሳስባችሁ እወዳለው። :lol:

የመጸሐፏን ደራሲ እስፓኛዊዉ ባልታሳር ግራሽያን (1601-1658 እኤኣ)፣ በድንቅ አማርኛ እጅግ ዉብ በሆነ አገላለጽ የተረጎማትን የሐረማያ ዩኒቨርስቲዉን አያሉ አክሊሉ እንዲሁም ይህን መድረኽ እዉን አድርጎ መልካም አስተሳሰቦች 20 እጥፍ፣ 60 እጥፍ፣ 100 እጥፍ፣ ፍሬ እንዲያፈሩ የተጋዉን ኤልያስ ክፍሌን ከልብ እያመሰገንን፡ ብቀጥታ የመጸሐፊቷን ይዘት ከዛሬ ጀምሮ አንድ ሁለት ሶስት እያልን እንቀጥላል። ለዛሬ ሶስቱን እንሆ! መልካም ማጣጣም ያድርግልዎ!!!

1. ሁሉም ነገር እጅግ ልቋል፤ እናም ምልኡ* ሰው መሆን ከሁሉም የበለጠ የልቀት ደረጃ ነዉ። ዛሬ አንድ ጠቢብን ለመፍጠር ጥንት በግሪክ ዘመን የነበሩ ሰባት ጠቢባንን ለመፍጠር የሚያስፈልገዉን ግብአት ይጠይቃል።

ምልኡ= ባልታሳር ግራሻን እንደሚያምነዉ ከሆነ ማንኛዉም ሰዉ እንደ እዉነተኛ ሰዉ አይቆጠርም። አንድ ሰዉ እዉነተኛ (ምልኡ) ሰዉ የሚሆነዉ ለሞራላዊ ልቀት ጥረት በማድረግ ነዉ።

2. ባህሪ እና እዉቀት። እነዚህ የተፈጥሮ ስጦታህን ደግፈዉ የያዙት ዋልታዎች ናቸዉ። አንደኛዉ በሌለበት ሌላኛዉ ግማሽ ስኬትን ብቻ ነው የሚፈጥርልህ። እናም እዉቀት ብቻዉን በቂ ስላልሆነ መልካም ባህሪም ሊጨመርበት ይገባል። ሞኝ ዉድቀቱን የሚያመጣት ባህሪዉ ሁኔታዉን፤ በሰዉ ዘንድ ያለዉን ተቀባይነት እና ጓደኞቹን ያገናዘበ ባለመሆኑ ነዉ።

3. ነገሮችን አንጠልጣይ አድርጋቸዉ። ላቅ ያሉ ስኬቶች አድናቆትን ያተርፋሉ። በጣም ግልጽ መሆን ጣፋጭም ጠቃሚም አይደለም። በተለይ የያዝከዉ ቦታ በጣም ተፈላጊ ከሆነ እራስህን ቶሎ ግልጽ አለማድረግ የሰወችን ትኩረት ይስብልሃል። ማንኛዉም ሰዉ ዉስጥህን እንዲያዉቅ አትፍቀድለት። ራስህን ስትገልጽ እንኳ ሙሉ በሙሉ መሆን የለበትም። እነሆ ብልህነት የምትገኘዉ ጥንቃቄን መሰረት ባደረገች ዝምታ ዉስጥ ነዉ። ሀሳቦች አንዴ ግልጽ ከተደረጉ በኋላ ከበሬታን አለማግኘት ብቻ ሳይሆን ለነቀፋም የተመቻቹ ናቸዉ። እነዚሁ ሀሳቦችህ ግባቸዉን ሳይመቱ የቀሩ እንደሆን ደግሞ እጥፍ ጊዜ እንደከሰርክ ይቆጠራል። የሰወችን ትኩረት የምትሻ ከሆነ መለኮታዊነትን ተከተል።

ወዳጄ “በብልህነት መንገድ ተጓዝ ብልህም ሁን፤ አንቺም እንዲሁ!”!!!
:mrgreen:

Maxi
Member+
Posts: 5951
Joined: 06 Mar 2014, 04:33

Re: ‘የብልህነት መንገድ’ - ምርጥ መጠሓፍ በምርጥ ተርጓሚ - ይዘቷን እንካችሁ አጣጥሙ!

Post by Maxi » 03 Apr 2019, 10:19

ስላካፈልከን እናመሰግናለን!! አለፍ አለፍ እያልክም ቢሆን ከመጽሃፏ እንደምትጨምርል ተስፋ እንደርጋለን!!

"The Art of Worldly Wisdom" by Baltasar Gracian (Author), Christopher Maurer (Translator)

Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ‘የብልህነት መንገድ’ - ምርጥ መጠሓፍ በምርጥ ተርጓሚ - ይዘቷን እንካችሁ አጣጥሙ!

Post by Meleket » 03 Apr 2019, 11:53

ብልሁ ወዳጄ Maxi
እንዴታ ለደራሲዉ፣ ለተርጓሚዉና ይህን የመወያያ መድረክ እዉን አድርጎ የተለያዩ ሃሳቦች በነጻነት ይስተናገዱ ዘንድ በትጋት የለፋዉን ኤልያስ ክፍሌን ለማክበር ስንል የዚህ ብርቅ መጠሓፍ ይዘትን በተለይም ቅልብጭብጭ ያለዉን የአማርኛ ትርጉሙን በደንብ በጋራ እንካፈለዋለን እንጂ። ላንተ ለወዳጄ ክብርም እነዚህ ቀጣይ አራት ነጥቦችን ለዛሬ አክያቸዋለዉ!

4. ጠቢብነት በብርታት ሲታገዝ ታላቅ ያደርጋል። እነዚህ ደግሞ ዘላለማዊ ስለሆኑ አንተንም ዘላለማዊ ሊያደርጉህ ይችላሉ። አንተ የብልጠትህን ያህል ነህ፤ ብልጥ ከሆንክ ደግሞ የፈለከዉን ማድረግ ትችላለህ። መረጃ የሌለዉ ሰዉ ብርሃንን በተነፈገ አለም እንደሚመሰለዉ ሁሉ ማመዛዘን እና ብርታት ደግሞ በአይን እና እጅ ይመሰላሉ። ጉብዝና ያልታከለባት ብልህነት ፍሬዋን አትሰጥም።

5. ሰዎችን ያንተ ጥገኛ አድርጋቸዉ። ጣኦት ጣኦት የሆነዉ በመልኩ ሳይሆን በመመለኩ ነዉ። አስተዋይ የሆነ ሰዉ ሰዎች ከሚያመሰግኑት ይልቅ ቢፈልጉት ይመርጣል። ተስፋ ስለምትታወስ ዉለታ ግን ስለምትረሳ፤ ስድ የሆነች ዉለታ ዋጋዋ ትህትናን ከተላበሰች ተስፋ ያነሰ ነዉ። ከሰዎች ትህትና ይልቅ በጥገኝነታቸዉ ብዙ ታተርፋለህ። ከምንጭ ጠጥቶ የረካ ጀርባዉን እንደሚሰጣት ሁሉ የተጨመቀች ብርቱካንም ከወርቅነት ወደ ቆሻሻነት ትቀየራለች። ጥገኝነት ሲጠፋ መልካም ምግባርም አብሮ ይሰወራል፤ መከባበርም ትፈረጥጣለች። ላቅ ካሉት የሕይወት አስተምህሮቶች ዉስጥ አንዱ ሰወችን ጥገኛ ማድረግ፤ እሷንም መንከባከብ ግን አለማርካት ነዉ። ሆኖም ግን ለራስህ ጥቅም ብለህ በዝምታህ ሌሎችን እስከማሳሳት ሆነ ያመረቀዘ ቁስላቸዉን አክሜ አላድንም እስከማለት ድረስ ከልክ እንዳታልፍ።

6. ታላቅ ሰዉ ሁን። ታላቅ ሆኖ የተወለደ የለም። ታላቅ ሰዉ ትሆን ዘንድ ራስህን በየቀኑ አሻሽል። ታላቅ መሆንህን ደግሞ ላቅ ባለዉ የመምረጥ ችሎታህ፤ በማድረግ ፍላጎትህ ላይ ባለህ የበላይነት እና በጠራዉ አስተሳሰብህ ታዉቀዋለህ። አንዳንድ ሰዎች ሙሉ ሰዉ መሆን ስለማይችሉ ሁሌም አንዳች ነገር እንደጎደላቸዉ ነዉ። ሌሎች ደግሞ ራሳቸውን ለመገንባት ብዙ ጊዜ ይወስድባቸዋል። ጠቢብ በሆነ አንደበቱ እና አስተዋይ በሆነ ምግባሩ የታወቀው ሰዉ የአዋቂዎችን ማህበር ተጋብዞ ይቀላቀላል።

7. ከአለቃህ በላይ እንዳታንጸባርቅ። መበለጥ ጥላቻን ይፈጥራል፤ አለቃን በልጦ መታየት ደግሞ አንድም ቂልነት ሌላም አደገኛ ነዉ። መበለጥ በተለይ በባለስልጣናት እና በበላዮች ዘንድ እጅግ የተጠላ ነገር ነዉ። እናም ጉብዝናህን በጥንቃቄ ደብቀዉ። አብዛኛዉ ሰዉ በመልካም እድል ሆነ በመልካም ጸባይ ቢበለጥ ምንም አይመስለዉም፤ በእዉቀት መበለጥን ግን ማንም አይፈቅድም፣ በተለይ ደግሞ የበላዮች እና ባለስልጣናት። ዕዉቀት የበላይነት መገለጫ ነዉ፤ ባለስልጣናት ደግሞ የበላይነት መገለጫ በሆነ ጉዳይ ላይ የበላይ መሆንን ይፈልጋሉ። እናም ይህችን ህግ ብትጥሳት በነሱ ላይ ወንጀል መፈጸምህን እወቅ። እንዲሁ ባለስልጣናት አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የበላይ ሆነዉ መገኘት ይፈልጋሉ። መሳፍንት እርዳታን እንጅ መበለጥን አይሹም። እናም አንድን ሰዉ ስትመክር የረሳዉን ነገር እንደምታስታዉስ ምሰል እንጅ የማያዉቀዉን እያሳወቅከዉ መሆኑን አታመልክት። ይህን ህግ የምንማረዉ ከከዋክብት ነዉ። ከዋክብት የፈለገ አንጸባራቂ ቢሆኑ እንኳ በፍጹም ከፀሐይ ይበልጥ ለማንጸባረቅ አይደፍሩም።

ጎበዝ፣ በብልህነት መንገድ እንጓዝ፣ ብልሆችም እንሁን! :mrgreen:

Masud
Member+
Posts: 8502
Joined: 18 Jun 2013, 09:06

Re: ‘የብልህነት መንገድ’ - ምርጥ መጠሓፍ በምርጥ ተርጓሚ - ይዘቷን እንካችሁ አጣጥሙ!

Post by Masud » 03 Apr 2019, 12:52

Meleket,
Thank you for sharing the excerpts from the book. Please continue sharing such nice knowledge. Kibur Lij Elias is quite after he went back to Ethiopia and we don't know what he is cooking. May be he will be the next Esknder Nega or Ermiyas Legesse to muddy the Ethiopian politic. In March his 31,2019 article Chris Stein of AFP wrote the following about Elias

"Elias Kifle, who heads the online news outlet Mereja, believes Oromo police officers sanctioned the February mob beating two of his journalists in the town of Legetafo."I considered it not only an attack on the media, but on the reform," he said, adding that he does not blame the prime minister for the assault."
https://news.yahoo.com/one-tough-times- ... soc_trk=fb

He is getting calm after going home, may be he got a good wife ; opps sorry I don't know if he is a man who want wife. :lol:

Anyways, anyone who want to read or download the e-copy of "The Art of Worldly Wisdom" follow the link below and get it. Don't forget to thank me, Masud the Native of Oromia, for this.

https://www.globalgreyebooks.com/art-of ... ml[pdfview][/pdfview]

Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ‘የብልህነት መንገድ’ - ምርጥ መጠሓፍ በምርጥ ተርጓሚ - ይዘቷን እንካችሁ አጣጥሙ!

Post by Meleket » 04 Apr 2019, 05:17

ወዳጄ Masud የመጠሐፉን ሊንክ እዚህ ማምጣትህ ምን ያህል ብልህ መሆንህንም ይገልጻል! በል እንግዲህ በኦሮሚፋ ሆነ በትግርኛ ወይም በሌላ ቋንቋም ጥሑፉ እስኪተረጎምልን ድረስ፣ “ባፍሪካ ህብረት” የመግባቢያ ቋንቋዎች ባንዱ ማለትም በታላቁ ባማርኛ ቋንቋ የተተረጎመዉን ጥሁፍ አጣጥም! :mrgreen: አሁን ለኤልያስ ክፍሌ ብቻ ሳይሆን ላንተም ክብር የሚከተሉትን ሶስት ነጥቦች በመጸሐፉ ቅደም ተከተል መሰረት ለብዙሃኑ እንካችሁ ብንልስ?

8. የታላቅነት መገለጫ ስለሆነ ስሜተ ግንፍል አትሁን። ታላቅነትህ ወደ ስድነት ከመዉረድ እና ለትዝብት ከመጋለጥ ሊጠብቅህ ይገባል። ራስህን እና ስሜትህን ከመቆጣጠር የሚበልጥ ነገር የለም፤ ይህ ደግሞ ፍጹም የማድረግ ፍላጎትህን ሃያልነት ያሳያል። ስሜታዊነት አንተን ቢያንበረክክህ እንኳ ስልጣንህ ላይ ጥላዉን እንዳያጠላ ተጠንቀቅ፤ በተለይ ደግሞ የተቀመጥከዉ ከፍተኛ ቦታ ላይ ከሆነ።

9. የትዉልድ ሀገርህን መጥፎ ባህሪወች አስወግድ። የጅረት ዉሃ የሚያልፍበትን አካባቢ መጥፎ እና መልካም ነገር እንደሚወስድ ሁሉ ሰዉም የተወለደበትን አካባቢ መጥፎ ባህሪዎች ይወርሳል። አንዳንድ ሰዎች መልካም ነገርን በተመሉ ቦታወች በመወለዳቸዉ ምክንያት ሀገራቸዉ ወይም ከተማቸዉ እንደባለዉለታቸዉ ትቆጠራለች። በጣም ጨዋ የሚባሉትን ጨምሮ ማናቸዉም ሀገር አንዳች ተፈጥሯዊ ጉድለት ወይም እክል አለበት፤ ይህን ጉድለት ደግሞ ጎረቤት ሀገሮች ለክርክር ወይም ራሳቸዉን ለማሞገስ ይጠቀሙበታል። ይህን መጥፎ የትዉልድ ሀገር ዉርስ ብትችል አጥፋዉ፣ ካልቻልክ ደግሞ ደብቀዉ። ይህን ብታደርግ ደግሞ ሳይጠበቅ የተገኘ ነገር ዋጋዉ ከፍ ያለ ስለሆነ በሌሎች ዘንድ ከሀገርህ ሰዎች የተለየህ ሆነህ ስለምትገኝ ክብርን ታገኛለህ። ሌሎች የሰዉ ልጅ ደካማ ጎኖች የሚመጡት ደግሞ በዘር ሀረግ፣ በስልጣን፣ በሙያ እና ባለበት ዘመን ምክንያት ነዉ። እነዚህ ነገሮች በጥንቃቄ ጉድለት ምክንያት ተመንቅረዉ ባይጣሉ እና ባንድ ሰዉ ላይ ቤት የሰሩ እንደሆን ሊጠጉት የማይቻል አዉሬን ይፈጥራሉ።

10. መልካም እድል እና ዝና። አንደኛዉ ተለዋዋጭ ሲሆን ሌላኛዉ ዘላለማዊ ነዉ። የመጀመሪያዉ በህይወት እያለህ ሲያገለግልህ ሁለተኛዉ ከዚያ በኋላ ያገለግልሃል። መልካም እድል ከቅናት ዝና ደግሞ ከታናሽነት ይጠብቅሃል። የዝና ምኞት የሚወለደዉ ከጥንካሬ እና ከብርታት ነዉ። ዝና ደግሞ ጥንት ሆነ ዛሬ የታላላቆች እህት ናት።

ጎበዝ፣ በብልህነት መንገድ እንጓዝ፣ ብልሆችም እንሁን!
:mrgreen:

Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ‘የብልህነት መንገድ’ - ምርጥ መጠሓፍ በምርጥ ተርጓሚ - ይዘቷን እንካችሁ አጣጥሙ!

Post by Meleket » 05 Apr 2019, 11:07

በሉ እስኪ አሰስ ገሰሱንና በጥላቻ የተዘፈዘፈን ጥሁፍ ከማንበብ ይልቅ እነዚህ ከ300 ዓመታት በፊት የተጻፉትን ቁምነገሮች መኮምኮም ለምትሹ፤ ለዛሬ 10 ነጥቦችን እንካችሁ ብለናል! ቍምነገር የማይጥማቸዉ በርካታ “አሸባሪዎች” እዚህ መድረኽ ውስጥ እንዳሉ ስለሚገመትም፡ ቀስ በቀስ ወደ ቀናዉ መንገድ ይመጡ ዘንድ እነዚህን ቁምነገሮች እያመነዠኹና እያላመጡ ሰልቅጠዉ ብልሆች ይሆኑ ዘንድ ጠሃፊዉን ተርጓሚዉንና የመድረኩን ባለቤት እያመሰገንን ይሀዉ ዘርገፍገፍ አድርገንላቸዋል! መልካም ንባብ። :lol:

11. ትምህርት ልታገኝባቸዉ ከምትችል ሰወች ተጠጋ። የጓደኝነት ግንኙነቶችህን የመልካም ንግግር እና የበሰለ ትምህርት መቅሰሚያ ገበታ አድርጋቸዉ። ጓደኞችህን እንደ አስተማሪ አድርጋቸዉ እና ጠቃሚ መማማርን ከአስደሳች ጨዋታ ጋር አዋህዳት። ከአዋቂወች ጋር በምታደርገዉ ዉሎ ደግሞ ደስታን ተጎንጭ። እንደተለመደዉ ሰዎች የሚሰበሰቡት የራሳቸዉን ፍላጎት ተከትለዉ ቢሆንም ለመማማር ታስቦ የሆነ እንደሆነ ግን ፍላጎቱ የተቀደሰ ነዉ። ብልሆች እንደቲያትር ቤት የታላላቅ ሰዎችን መነሀሪያ ያዘወትራሉ እንጅ ከንቱ ነገር በሚፈጸምበት ስፍራ አይዉሉም። እነዚህ ሰዎች የሚታወቁት በትምህርታቸዉ እና በአመዛዛኝነታቸዉ ጠቢብነት ብቻ ሳይሆን የከበቧቸዉ ሰዎችም ታላቅ የጥበብ ምንጮች በመሆናቸዉም ጭምር ነዉ።

12. ሥነ-ጥበብ እና ተፈጥሮ፤ ባለሙያ እና መገልገያ መሳሪያወቹ። ዉበት ሁሌም አጋዥን ትፈልጋለች። ላቅ ያሉ ነገሮች በሥነ-ጥበብ ያልተወለወሉ እንደሆን የአረመኔ ተግባር ይሆናሉ። ሥነ-ጥበብ መጥፎ የሆነዉን ነገር ህይወት ስትዘራበት፤ መልካሙን ነገር ደግሞ የበለጠ መልካም ታደርገዋለች። ተፈጥሮ እጅግ የፈለግናት እለት ስለምትከዳን ትኩረታችንን ወደ ሥነ-ጥበብ እናዙር። መልካም የሆነዉ ነገር ሁሉ ያለሥነ-ጥበብ ጎደሎ ነዉ። እንዲሁ ሥነ-ጥበብ በሌለችበት ሰዎች ስድ እና ምቾተቢስ ይሆናሉ። ስለዚህ መልካም ነገር ማሳመሪያን ይፈልጋል።

13. የሰዎችን ግልጽ እና ድብቅ ጥንስስ ለራስህ ጥቅም አዉለዉ። ሕይወት የሰዎችን ተንኮል የምትጋፈጥባት ጦር ሜዳ ናት። ብልጥ በድብቅ ያልማል፣ ብሎም ያስመስላል፣ ከዛም ሳይታሰብ እቅዱን ያሳካል እንጅ አደርጋለሁ ብሎ የሚናገረዉን አያደርግም። እንዲሁ የሰዎችን ትኩረት እና አመኔታ ለማግኘት አሳሳች ፍላጎቱን ያመላክታል፤ ከዛም አደርጋለሁ ያለዉን ተቃራኒ በመፈጸም ድልን ይጎናጸፋል። አስተዋይ ሰዉ መሰሪዎችን ቀስ ብሎ በመመልከት እና እናደርጋለን የሚሉትን ሳይሆን ተቃራኒዉን እንደእዉነት በመዉሰድ አላማቸዉን ያጨናግፍባቸዋል። አስመሳይ ሰዉ አላማዉ የተነቃበት ጊዜ ደግሞ እዉነቱን በግልጽ በመናገር ለማታለል ጥረት ያደርጋል። ይህም ቢሆን ተቃራኒ ወገን በቀን ብረሃን የሚደብቀዉን አላማ በደንብ በማስተዋል መግለጥ ይቻላል።

14. ፍትፍቱ እና ፊቱ። ማናቸዉም ነገር በራሱ በቂ ስላልሆነ አቀራረቡም ሊያምር ይገባል። ከአቀራረብ ጉድለት መልካም ፍርድ እና መልካም ምክንያት እንኳ ኮምጣጣ ይሆናሉ። መልካም አቀራረብ ብዙ ነገሮችን ያደርግልሃል። መልካም አቀራረብ እንቢታን ዉበት ይሰጣታል፤ እዉነትን ያጣፍጣታል፤ ከዚህም አልፎ በእርጅናህ እንኳ ዉበትን ያላብስሃል። የነገሮች ሁናቴ በራሱ ጠቃሚ ቢሆንም፤ መልካም አቀራረብ የሰወችን ፍቅር ይገዛልሃል። መልካም ባህሪ የሕይወት ካባ በመሆኑ መልካም ከሰራህ እና መልካም ከተናገርክ ከማንኛዉም ችግር በሰላም ትወጣለህ።

15. ሊረዱህ የሚችሉ አዋቂወችን ከጎንህ አስቀምጥ። ባለስልጣናት በአዋቂ ስዎች የተከበቡ እንደሆን ድንቁርናቸዉ ከሚያስገባቸዉ ማጥ መዉጣት ይችላሉ። ብልሆችን መጠቀም በራሱ የታላቅነት ተግባር ነዉ፤ የማረካቸዉን ነገስት ባሪያ ለማድረግ ከፈለገዉ የአርመን ንጉስ ተግባር ደግሞ በጣም የተሻለ ነዉ። ይህ መርህ አስፈላጊ በሆኑ የሕይወት ጉዳዮች ሌሎችን የምትበልጥበት መንገድ ነዉ። ተፈጥሮ ታላቅ ያደረገቻቸዉን ሰዎች በብልሃት ተገልገልባቸዉ። የምትኖረዉ በጣም አጭር ለሆነ ጊዜ፤ ማወቅ ያለብህ ግን እጅግ ብዙ፤ ካላወቅክ ደግሞ መኖር ስለማትችል ከሁሉም በላይ ታዉቅ ዘንድ ከብዙ ሰዎች ተማር። እነሆ ይህን ምክር ብትተገብረዉ ሰዉ በተሰበሰበበት ለብዙ ሰዎች መናገር ትችላለህ። በመከሩህ ብልሆች ቁጥር ልክ ስለምትናገር ደግሞ በሌሎች ልፋት አንተ እንደሊቅ ትታያለህ። እናም ርእስህን ምረጥ እና አዋቂዎች የእዉቀት ወለላን እንዲያቀርቡልህ አድርግ።

16. እዉቀት እና መልካም አላማ ፍሬያማ ስኬትን ያጎናጽፉሃል። እዉቀት እና እርኩስ አላማ የተጋቡ እንደሆን ግን ነገሩ ጋብቻ ሳይሆን አስገድዶ መድፈር ነዉ። እርኩስ ነገር መልካሙን ይበክላል። ይህ በተለይ በጣም አደገኛ የሚሆነዉ በእዉቀት የታገዘ እንደሆን ነዉ። እናም ላቅ ያለ ችሎታ ለእርኩስ ተግባር የዋለ እንደሆን ፍጻሜዉ አደገኛ ነዉ። ስለዚህ ማመዛዘን ያልታከለበት እዉቀት እብደትን ያስከትላል።

17. ያሰራር ዘይቤህን በየጊዜዉ ቀይር። ብዙ አማራጮችን ተጠቀም። ይህ ተፎካካሪወችህን ያደናግርልሃል፤ የማወቅ ፍላጎታቸዉን እና ትኩረታቸዉንም ያነቃቃልሃል። አላማህን ቀድመህ ግልጽ ካደረክ ሌሎች ቀድመዉ ያዩዋት እና በእንጭጩ ይቀጯታል። በቀጥተኛ መስመር የምትበርን ወፍ ከማደን ይልቅ አቅጣጫዋን እየለዋወጠች የምትበረዉን ማደን ይከብዳል። ክፉ ነገር ሁሌም እንዳደባች ስለሆነ ከእርሷ ለማምለጥ ብልጥ መሆን አለብህ። የቸዝ ተጫዋች ተቀናቃኙ እንደሚፈልገዉ አይጫወትም።

18. ችሎታ እና ተግባራዊነት። ሁለቱም ባንድ ላይ ሲገኙ ታላቅ ሰው ይፈጥራሉ። ታናናሾች ተግባራዊነትን ሲከተሉ ታላቅ የሚባሉትን ሰዎች ይበልጣሉ። ስራ ዋጋህን ይጨምርልሃል፤ ታዋቂነትንም ያስገኝልሃል። አንዳንድ ሰወች በቀላል ነገር ላይ እንኳ ተግባራዊ መሆን ያዳግታቸዋል። ተግባራዊነት አብዛኛዉን ጊዜ ከሰዎች ባህሪ ጋር የተቆራኘ ነገር ነዉ። በታናሽ ጉዳይ አንደኛ ከመሆን ይልቅ በታላቅ ጉዳይ ሁለተኛ መሆንን መረጥኩ ብትል ምክንያትህ በደንብ አሳማኝ ሊሆን ይችላል፤ በታናሽ ጉዳይ አንደኛ መሆን እየቻልክ ሁለተኛ በመሆንህ መርካት ግን ተቀባይነት የለዉም። እዉቀት እና ጥበብ በጣም አስፈላጊ ቢሆኑም ያለ ተግባራዊነት ፍሬ አልባ ናቸዉ።

19. አንድን ነገር ስትጀምር ሰዎች ብዙ እንዲጠብቁ አታድርግ። አብዛኛዉን ጊዜ በጣም የተሞገሰ ነገር እንደተጠበቀዉ ሆኖ አይገኝም። ይህ የሆነዉ ነገሮች በምናብ የምንጠብቀዉን ያህል መሆን ስለማይቻላቸዉ ነዉ። ምናባችን ከፍላጎታችን ጋር ይጣመር እና በተግባር ሊገኝ የማይችልን ነገር አጋኖ ያሳየናል። ቅሉ ግን ታላቅ ነገርን በምናብ መሳል ቀላል ቢሆንም በተግባር ማሳየት ግን ከባድ ነዉ። ለዚህም ነዉ አንድ ነገር የፈለገ ምርጥ ቢሆን እንኳ እንደጠበቅነዉ ሊሆን የማይችለዉ። እናም የሰዎችን ፍላጎት ማርካት ብትፈልግ ተስፋቸዉን ልጓም አበጅላት። እነሆ መልካም ጅማሮዎች የሰዎችን ትኩረት ለማነቃቃት እንጅ ብዙ ዉጤትን እንዲጠብቁ ለማድረግ መዋል የለባቸዉም። ሆኖም ግን ይህ ህግ ለክፉ ነገሮች አያገለግልም፤ ምክንያቱም መጥፎ ነገር ከመከሰቱ በፊት በጣም ከተጋነነ በተግባር ሲታይ ግን እንደተጠበቀዉ ሳይሆን አንሶ ስለሚገኝ ሰዎች መጽናናትን ስለሚያገኙ ነዉ።

20. ለምትኖርበት ዘመን የምትሆን ሰዉ ሁን። ብርቅየ የሚባሉት ታላላቅ ሰዎች ኑሯቸዉ እንዳሉበት ዘመን ነዉ። ብዙ ሰዎች በሚስማማቸዉ ዘመን አልተወለዱም፤ ተስማሚ ዘመንን ካገኙት ዉስጥ ደግሞ እድሉን የተጠቀሙበት በጣም ጥቂቱ ናቸዉ። በእዉነት አንዳንዶች የተገባ ዘመን ያስፈልጋቸዉ ነበር። መልካም የሆነዉ ነገር ሁሉ ተስማሚ ጊዜን ይፈልጋል። አንዳንድ ስኬቶች ደግሞ እንደ ፋሽን ተለዋዋጭ ናቸዉ። ከዚህ በተቃራኒ የጠቢብነት መልካም ጎን ዘላለማዊነቷ ነዉ። እነሆ ይህ ዘመን የእርሷ ባይሆን ወደፊት የሚመጡት ብዙ ዘመናት ለእርሷ የተገቡ ናቸዉ።

ጎበዝ፣ በብልህነት መንገድ እንጓዝ፣ ብልሆችም እንሁን!
:mrgreen:

Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ‘የብልህነት መንገድ’ - ምርጥ መጠሓፍ በምርጥ ተርጓሚ - ይዘቷን እንካችሁ አጣጥሙ!

Post by Meleket » 06 Apr 2019, 04:15

ያለፉት 20 የብልህነት መንገዶችን እንዲሁም የዛሬዎቹን 10 የብልህነት መንገዶች በደንብ እንደምታጣጥሙ ተስፋ እያደርግን፤ እዚህ ፎረም ዉስጥ የጠባይ (ስነምግባር) መሻሻል እያሳያችሁ ያላችሁ ወዳጆቻችንንም ሳናመሰግን አናልፍም። ወጣቱ ጠቕላዪ ወደ ስልጣን የተፈናጠጡበትን፣ የሄጉን ብይንም ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እተገብራለዉ ብለዉ ቃል የገቡበትን እንዲሁም ‘ትግርኛ ተናጋሪ’ ጎረቤቶቻችን ከስልጣን ኮረቻ ተገፍትረዉ እየተንደፋደፉም ቢሆን መቐለ የተወሸቁበትን 1ኛ ዓመት የድል በዓል እያከበርን የዚህን ብርቅ መጽሐፍ ይዘት መጋራታችንን እንቀጥላለን! :lol:

21. የእድለኛነት ሚስጥር። ጠቢብ መልካም እድል ህጎች እንዳሏት ስለሚያዉቅ ሁሉም ነገሮች በአጋጣሚ እንደማይሆኑ ይረዳል። መልካም እድልን በጥረት ማበልጸግ ይቻላል። አንዳንዶች ተረጋግተዉ የእድልን በር ይጠጉ እና እድል ስራዋን እስክትሰራ ይጠባበቃሉ። ከእነዚህ የተሻሉት ደግሞ ማስተዋል በተሞላበት ድፍረት በሩን በርግደዉ ይገቡ እና በድፍረት እና በብርታት እድል ስራዋን እንድትሰራ ያባብሏታል። ይህ ሁሉ ተብሎ ግን ከትኩረት እና ጨዋነት የበለጠ እድልን የማሸነፊያ መንገድ የለም። ምክንያቱም እድለኛ መሆን ወይም አለመሆን የሚወሰነዉ ጠቢብ በመሆን ወይም ጠቢብ ባለመሆን ስለሆነ ነው።

22. ከኢንፎርሜሽን የራቅክ እንዳትሆን። ጠቢቦች ከአሉባልታ ይልቅ ስለነገሮች ወቅታዊ የሆኑ መረጃዎችን ይሰበስባሉ። የእነዚህ ሰዎች አነጋገር ደግሞ ለዛ እና ግርማሞገስ ያለዉ ሲሆን በምን ሰዐት ምን ማለት እንዳለባቸዉ እና እንደሌለባቸዉ ደግሞ ጠንቅቀዉ የሚያዉቁ ናቸዉ። እነሆ አንዳንዴ ምክር ከመሪር ንግግር ይልቅ በጣፋጭ ቀልድ ስኬታማ ትሆናለች። እናም ከሰዎች ጋር በመነጋገር የሚገኝ እዉቀት ለአንዳንድ ሰዎች ከማንኛዉም ጥበብ የበለጠ ሊሆን ይችላል።

23. ምንም የማይወጣልህ ሁን። አንዳች የባህሪ እንከን የማይኖርባቸዉ ሰዎች በጣም ጥቂት ናቸዉ፤ ሆኖም ግን ይህን የባህሪ እንከን በቀላሉ ማጥፋት ሲችሉ ይሸነፉለታል። ይህ ማለት ፀሀይን እንደሚሸፍን አነስተኛ ደመና ነዉ። ተመልካች ደግሞ የአንድ ታላቅ ሰዉ ዝና በትንሽ እንከን ስትጎድፍ ሲያይ ሀዘን ይገባዋል። በተለይ ተንኮለኛ ሰዎች ቶሎ ስለሚደርሱበት የባህሪ ድክመት ማለት ፊት ላይ እንዳለ ለምጽ ነዉ። ድክመትን ወደ ቁንጅና መለወጥ ታላቅ ችሎታ ነዉ። ለምሳሌ ሲዛር ጭንቅላቱን በአበባ ጉንጉን በመሸፈን በራነቱን ወደ ዉበት ለዉጦት ነበር።

24. ለምናብህ ልጓም አብጅለት። አንዳንዴ ግታት፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ አበረታታት። የደስታህ ልክ የሚወሰነዉ በአይነ ህሊናህ ስለሆነ ለአይነ ህሊናህ ሚዛናዊነትን አበጅላት። አይነ ህሊናህ ክፉ ባላጋራ ልትሆንብህ ትችላለች። ይህ የሚሆነዉ ከማለም አልፋ ወደ ስራ ትገባ እና ህይወትህን በመቆጣጠር ሀሴት ወይም ሲዖል ልታደርገዉ ስለምትችል እና በራስህ እንድትረካ ወይም እንድታዝን ልታደርግህ ስለሚቻላት ነዉ። አይነ ህሊና ለአንዳንዶች ሀዘንን ብቻ ስታሸክማቸዉ ለሌሎች ደግሞ ሀሴታዊ ደስታን በማላበስ ወደ ጅልነት እና ቅዠት ትነዳቸዋለች። እናም ለምናብህ የማስተዋል እና የአመዛዝኝነትን ልጓም ካላበጀህላት ከላይ የተዘረዘሩትን መከራዎች ሁሉ በአናትህ ላይ ትዶልብሃለች።

25. ምልክቶችን ቶሎ መረዳት ቻል። ድሮ ምክንያታዊነትን ማወቅ የጥበቦች ሁሉ ጥበብ ነበር፤ አሁን ግን ዘመኑ ተለዉጧል። በተለይ ለማጭበርበር በሚያመቹ አጋጣሚዎች በጣም ብልጥ መሆን አለብህ። ምልክቶችን እንዴት እንደምታነብ ካላወቅክ አዋቂ ልትሆን አትችልም። እነሆ አንዳንድ ተኩላ የሆኑ ሰዎች የሌላው ልብ ያሰበውን እና ኩላሊት ያመላለሰዉን ጥንስስ በቶሎ ይረዳሉ። እያንዳንዳችን የልባችንን በከፊል እንጅ ሙሉ በሙሉ አንናገርም፤ የተናገርነዉን ሙሉ በሙሉ መረዳት የሚችሉት ደግሞ አስተዋዮች ብቻ ናቸዉ። ባልንጀራህ ሁሌም መልካም ነገርን የነገረህ እንደሆነ እንዳትጃጃል ጠንቃቃ ሁን፣ ክፉ ነገርን ሲነግርህ ደግሞ ጆሮህን ቀስረህ አዳምጥ።

26. የእያንዳንዱን ሰዉ ደካማ ጎን ፈልገህ አግኘዉ። እነሆ አንድ ሰዉ የምትፈልገዉን እንዲያደርግልህ የሚያስፈልግህ ብልጠት እንጅ ብርታት አይደለም። ሌላዉን ሰዉ ምን ቦታ ላይ ልትይዘዉ እንደሚገባህ ማወቅ አለብህ። እያንዳንዷን ነፍስ የሚያስደስታት አንዳች ነገር አለ፤ ሆኖም ግን ይህ ነገር ከሰዉ ሰዉ ይለያያል። አንዳንዶች ከበሬታን ሲፈልጉ ሌሎች ደግሞ የሳንቲም ትርፍን ይወዳሉ፤ ብዙዎች ደግሞ ደስታን እንደጣኦት ያመልኳታል። ጨዋታዉ ታዲያ ሰዎችን ለማንቀሳቀስ እንደመዘዉር የምታገለግለዉን ጣኦት ማግኘቱ ላይ ነዉ። እነሆ ይህን ነገር ማግኘት ማለት ደግሞ የሰወችን መልካም ሆነ እርኩስ ተግባር ጎልጉሎ የሚያወጣዉን መንጠቆ ማግኘት ማለት ነዉ። ሁሌም ሰዎችን በብርቱ የሚያማልላቸዉን ነገር ፈልገህ አግኘዉ፤ ከምግባረ ሰናይ ሰዎች ይልቅ ስዶች በቁጥር ስለሚያይሉ አብዛኛዉን ጊዜ ይህ ሰዎችን የሚነዳቸዉ ፍላጎት ርኩስ ነገር ነዉ። መጀመሪያ የግለሰቡን ጸባይ ቀስ ብለህ አጥናዉ እና ደካማ ጎኑን ነካካዉ፤ ከዛም መደሰቻዉን እያሳየህ ብትፈታተነዉ የሰዉየዉን የማድረግ ፍላጎት በቁጥጥር ስር ማዋል ይቻልሃል።

27. ሁሉንም ነገር ከመነካካት ባንዱ መበርታት። ላቅ ያለ ነገር የሚገለጸው በብዛቱ ሳይሆን በጥራቱ ነዉ። ብዛት የነገሮችን ዋጋ ስለሚቀንስ ላቅ ያሉ ነገሮች ጥቂት እና ብርቅየ ናቸዉ። ከሰዎች መካከል እንኳ ታላላቆቹ አጭሮች ናቸዉ። አንዳንዶች መፅሀፍን ለመማሪያነት ሳይሆን ለክብደት ማንሻነት የተጻፈ ይመስል በዉፍረቱ ያደንቁታል። ሁሉንም ልሁን ማለት አንዱንም አለመሆን ማለት ስለሆነ ሁሉንም ልሁን ማለት የትም አያደርስህም። ባንድ ነገር ላይ መበርታት ታላቅነትን ይፈጥራል፥፡ ነገሩ በጣም ተፈላጊ የሆነ ሲሆን ደግሞ ዝናን ጭምር ይወልዳል።

28. በምንም ነገር ስድ እንዳትሆን። በፍፁም። ነገሩ ሁሉ ሁሉንም ሰዎች እንዲያስደስትለት የማይፈልግ ሰዉ እንዴት ያለ ጥበበኛ ነዉ። አስተዋዮች በስዶች እልልታ ራሳቸዉን አይደልሉም።መንጋዎች ተአምር በሚሉት ነገር እንዳትደሰት ተጠንቀቅ፤ ነገሩ ከቂላቂልነት በስተቀር ሌላም አይደል። መንጋዉ የሚያደንቀዉ ርካሽ የሆነዉን ጅላጅልነትን እንጅ በጎ ነገርን አይደለም።

29. መልካም ስነምግባር ይኑርህ። ሁሌም ምክንያታዊ ሁንና የመንጋዎች ስድነት ሆነ የአምባገነኖች ሀይል ከምታምንበት ነገር ፍንክች አያደርጉህም። እንዲህ አይነት አመዛዛኝ ሰዉ ግን ከወዴት ይገኛል? ለመልካም ፍርድም ታማኞቿ በጣም ጥቂት በመሆናቸዉ አንዳንዶች ያደንቋታል እንጅ አያዉቋትም። አንዳንዶች ነገሮች አደገኛ እስካልሆኑ ድረስ ይከተሏታል፤ ሀሰተኞች በአደጋ ጊዜ ይክዷታል፤ ፖለቲከኞች ደግሞ ይከዷታል። መልካም ፍርድ የጓደኝነት ሆነ የስልጣን አደጋ ላይ መዉደቅ ስለማያሳስባት ሰዎች አሽቀንጥረዉ ይጥሏታል። እነሆ ለእዉነት የቆመ ሰዉ በዉሳኔዉ ፀንቶ ይቀጥላል። ይህ ሰዉ ከሌሎች ጋር ቢቃረን ተቃርኖዉ የመጣዉ ሰዎች እዉነትን ስለከዷት እንጅ የእርሱ ባህሪ ተቀያያሪ በመሆኑ ምክንያት አይደለም።

30. በቧልት ተግባር እንዳትጠመድ። በተለይ ዝናህን ከማጉላት ይልቅ ሊያኮስሱት ከሚችሉ ተግባሮች ራስህን አርቅ። ብዙ የቅዠት እምነቶች ስላሉ ጤነኛ ከሆንክ አጥብቀህ ራቃቸዉ። በዚህ አለም የመምረጥ ችሎታቸዉ ስድ የሆነ እና ብልሆች አሽቀንጥረዉ የጣሉትን የሚያግበሰብሱ ብዙ ሰዎች አሉ። እነዚህ ሰዎች ከሰዉ ለየት ማለት ያስደስታቸዋል፤ ይህ ባህሪያቸዉ በሰዉ ዘንድ እንዲታወቁ ቢያደርጋቸዉም አብዛኛዉን ጊዜ ከዝና ይልቅ መሳለቂያነትን ነዉ የሚያስተርፍላቸዉ። አስተዋዮች ጠቢብነትን እየተከተሉ እያለ እንኳ አስተዋይ ልምሰል ባይነትን እና የታይታ ስራን ማስወገድ አለባቸዉ፤ በተለይ ደግሞ የያዙት ነገር መሳቂያ የሚያደርጋቸዉ ከሆነ። እነሆ እነዚህ ነገሮች በህብረተሰብ ዘንድ ተለይተዉ የታወቁ በመሆናቸዉ ነገሮቹን መዘርዘሩ አስፈላጊ አይደለም።

ጎበዝ፣ በብልህነት መንገድ እንጓዝ፣ ብልሆችም እንሁን! :mrgreen:

Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ‘የብልህነት መንገድ’ - ምርጥ መጠሓፍ በምርጥ ተርጓሚ - ይዘቷን እንካችሁ አጣጥሙ!

Post by Meleket » 07 Apr 2019, 02:43

ጎበዝ ‘ገብርኄር’ን ምታዉቁት ለዛሬ እነኝህን 10 ነጥቦች እንደ ቆሎ ቆርጠም ቆርጠም እንድታደርጓችዉ ተጋብዛችኋል!!! :lol:

31. እድለኞችን ትጠጋቸዉ ዘንድ፤ እድለቢሶችን ደግሞ ትርቃቸዉ ዘንድ እወቃቸዉ። መጥፎ እድል የሚመጣዉ በአለማወቅ ምክንያት ነዉ። በርህ ላይ ብዙ መጥፎ ነገሮች እያደቡ ስለሚነኙ ተንደርድረዉ እንዳይገቡብህ ብትፈልግ ለትንሿ መጥፎ እድል እንኳ በርህን እንዳትከፍት። እዚህ ላይ ጨዋታዉ ካርዶችህ ዉስጥ የትኛዉን ማስወገድ እንዳለብህ ማወቅ ነዉ። ጠቀሜታዋ ያነሰ የሚመስልህ ግን እያሸነፍክባት ያለችዉ ካርድ ዋጋዋ እየተሸነፍክባት ካለችው አስፈላጊ ተብየ ካርድ የበለጠ ነዉ። ብልሆች ወዲያዉኑ ባይሆን እንኳ አመሻሹ ላይ እድለኛ መሆናቸዉ ስለማይቀር ምን ማድረግ እንዳለብህ ጥርጣሬ ያደረብህ ጊዜ አስተዋዮች እና ብልሆች የሚያደርጉትን ተከተል።

32. ሰዎችን በማስደሰት የታወቅክ ሁን፤ በተለይም የምታስተዳድራቸዉ ከሆነ። ይህ ተግባር ባለስልጣናት በህዝብ ዘንድ ተወዳጅነትን ያገኙ ዘንድ ይጠቅማቸዋል። ሌሎችን የማስተዳደር አንዱ ጠቀሜታ ከማንም በላይ ለሰዎች መልካም ነገር ለማድረግ ስለሚያስችል ነዉ። ጓደኛ ፈላጊ ጓደኞችን ያፈራል። አንዳንዶች ሰዉን ማስደሰት የማይፈልጉት አቅቷቸዉ ሳይሆን በለዛቢስነታቸዉ ምክንያት ነዉ። የእነዚህ ሰዎች ነገረ ስራ መልካም የሆነዉን ነገር ሁሉ መቃወም ነዉ።

33. ነገሮችን መቸ መተዉ እንዳለብህ እወቅ። ከታላቁ የህይወት አስተምህሮቶች ዉስጥ አንዱ መቃወምን ማወቅ ነዉ፤ በተለይም በስራህ እና ከሰዎች ጋር ባለህ ግንኙነት ራስህን መግታት መቻል። ጊዜን እንደብል የሚበሉ ጥቅም የለሽ ተግባራት አሉ፤ በእነዚህ ተግባሮች ከመጠመድ ደግሞ ምንም አለመስራት የተሻለ ነዉ። ብልህ መሆን ማለት አንተ በሌሎች ጉዳይ ገብተህ አለመፈትፈት፤ ሌሎችም ባንተ ጉዳይ ገብተዉ እንዳይፈተፍቱ መከልከል መቻል ነዉ። ስለሌሎች ስትጨነቅ ለራስህ ሳትሆን እንዳትቀር መጠንቀቅ አለብህ። ጓደኞችህን አትረብሻቸዉ፤ እንዲሁ በራሳቸዉ ፍላጎት መስጠት ከሚችሉት በላይም አትጠይቃቸዉ። ሁሉም ነገር ሲበዛ ይጠነዛል፤ በተለይ ደግሞ ከጓደኞችህ ጋር ያለህ ግንኙነት። ይህን ተገቢ የአመዛዛኝነት መርህ ከተገበርከዉ የሌሎችን መልካም ፈቃድ ታገኛለህ፤ እንዲሁ እንቁ የሆነችዉ መከባበርም ረዥም እድሜ ይኖራታል። መልካሙን ነገር ሁሉ ለመዉደድ ነጻነት ይኑርህ፣ የማትወደዉን ነገር ደግሞ በፍጹም እወዳለሁ እንዳትል።

34. ጠንካራ ጎንህን እወቅ። ይህ ላቅ ያለ ስጦታህ ነዉ። በደንብ ተንከባከበዉ፤ ሌሎቹን ችሎታወችህንም እንዲሁ። እያንዳንዱ ሰዉ ጠንካራ ስጦታዉን ቢያዉቀዉ ኖሮ ታላቅ ይሆን ነበር። እናም የስጦታዎችህን ሁሉ ንጉስ እወቀዉ እና በርትተህ ተግባር ላይ አዉለዉ። አንዳንዶች ላቅ ያለ የማመዛዘን ችሎታ ሲኖራቸዉ፤ ሌሎች ደግሞ ብርታትን የተቸሩ ናቸዉ። ብዙ ሰዎች አእምሯቸዉን ያስጨንቁት እና ምንም ነገር ላይ ልቀትን ሊያገኙ አይችሉም። እነዚህ ሰዎች በስሜት ታዉረዉ እና ተሸንግለዉ አጉል ተግባር ላይ መቆየታቸዉን በስተመጨረሻ የሚያስረዳቸዉ ጊዜ ነዉ።

35. ነገሮችን በጥንቃቄ ገምግማቸዉ። በተለይ ደግሞ በጣም ወሳኝ የሆኑት ጉዳዮች ላይ አጥብቀህ ማሰብ አለብህ። እነሆ ቂሎች የሚጠፉት ስለማያስቡ ነዉ። እነዚህ ሰዎች ነገሮችን በግማሽ እንኳ ማሰብ አይችሉም። እናም ከጉዳያቸዉ የሚያገኙትን ትርፍ ሆነ ኪሳራ መረዳት ስለማይችሉ የጥንቃቄ እርምጃን መዉሰድ ያቅታቸዋል። አንዳንዶች ደግሞ ብዙም ጠቀሜታ ለሌላቸዉ ጉዳዮች ሲጨነቁ የነገሩን ፍሬ ይረሱታል። እነሆ ሲጀመር ጭንቅላት ስሌላቸዉ የአንዳንድ ሰወች አእምሮ ማበድ አይችልም። እጅግ ልናስብባቸዉ የሚገቡ እና ሊረሱ የማይገባቸዉ አንዳንድ ጉዳዮች አሉ። ጠቢቦች ብዙ ነገሮችን ያመዛዝናሉ፤ በተለይ ብርቱ ወይም አጠራጣሪ ጉዳዮችን ጊዜ ሰጥተዉ ያብተከትኳቸዋል። እናም አንዳንዴ ስለነገሮች ያልተረዱት ነገር እንዳለ ይገለጥላቸዋል። ጠቢቦች ነገሮችን ከመፍራት ይልቅ በደንብ ይገመግሟቸዋል።

36. በአንድ ነገር ላይ እርምጃ ከመዉሰድህ በፊት እድልህን ገምግማት። ይህ ነገር የራስን ባህሪ እና አካላዊ አቋም ከማወቅ በላይ ነዉ። ከአርባ አመቱ በፊት ሒፓከራተስን ስለ ጤና፤ ይባስ ብሎ ደግሞ ሴኔካን ስለ ጠቢብነት ያላማከረ ሰዉ ቂላቂል ነዉ። ምንም እንኳ ተቀያያሪ ባህሪዋን ሙሉ በሙሉ ለመረዳት ቢያዳግትህም እድልን በአግባቡ ተጠቀምባት። አንዳንዴ ጊዜ ሊያስፈልጋት ስለሚችል ታገሳት፤ ከተፍ ያለች ጊዜ ደግሞ ተጠቀምባት። ቆንጆ ሴት ወጣትን የምትፈልገዉን ያህል እድል ደግሞ ድፍረትን ስለምትፈልግ፤ እድል ካንተ ጋር መሆኗን ካወቅክ ጉዳይህን በፍጥነት ፈጽም። እድልህ መጥፎ ከሆነ ግን አርፈህ ተቀመጥ። እንዲሁ ገለል በል እና ከዳግም ኪሳራ ራስህን ጠብቅ። እነሆ እድልን ከተረዳሃት በትልቅ እርምጃ ወደፊት ተራምደሃል ማለት ነዉ።

37. አሽሙርን እና አጠቃቀሙን እወቅበት። አሽሙርን በሰዎች መስተጋብር ከፍተኛ ብልጠት የሚያንጸባረቅበት አንጓ ነዉ። አንዳንዱ አሽሙር ክፉ፣ ልቅ እና በስሜት የተመረዘ በመሆኑ፤ ከመቅጽበት እንደመብረቅ ይመታህ እና በሰዎች ፊት ያዋርድሃል። ለግል ጥላቻ እና ለህዝብ ማጉረምረም ያልተንበረከኩ አንዳንድ ሰወች ስለታማ በሆነች አንዲት ዘለላ የአሽሙር ቃል ወድቀዋል። በተቃራኒው መልካም የሆኑ አሽሙሮች ደግሞ ዝናችንን ከፍ ያደርጉታል። ሆኖም ግን ለከፉ የተሰበቁ የአሽሙር ጦሮችን በአስተዋይነት መጠባበቅ እና በብልሃት መቅለብ አለብን። ጥሩ መከታ ደግሞ እዉቀትን ይጠይቃል። እንደሚወረወርብን ከጠበቅነዉ አሽሙር ደግሞ ራሳችንን መጠበቅ እንችላለን።

38. እያሸነፍክ እያለህ አቁም። ይህ የጎበዝ ቁማርተኞች መርህ ነዉ። መልካም የሆነች ማፈግፈግ የመልካም ማጥቃትን ያህል ጠቃሚ ነች። እናም እያሸነፍክ እያለህ ወይም በቂ የሆነ ነገር በእጅህ እንደገባ የያዝከዉን ይዘህ ጥፋ። መልካም እድል ለረዥም ጊዜ የሰነበተች እንደሆን ጥርጣሬ ሊገባህ ይገባል። መልካም እና መጥፎ እድል ሲፈራረቁ በጎ ነገር ነዉ፤ በነገራችን ላይ ህይወት እራሷ ጣፋጭ የምትሆነዉ ይህ የሆነ እንደሆን ነዉ። እድል ተንደርድራ ስትመጣ ከሀይሏ የተነሳ ነገሮችን ሁሉ ትሰባብራለች። አንዳንዴ ወይዘሮ እድል ላቅ ያለች መሆን ሲያቅታት ለረዥም ጊዜ በመቆየት ትክሰናለች። ይህም ሆኖ ወይዘሮ እድል አንድን ሰዉ ተሸክማ ለረዥም ጊዜ ስትቆይ ድካም ይጫጫናታል።

39. ነገሮችን እስኪበስሉ ጠብቅ እና አጣጥማቸዉ። ሁሉም የተፈጥሮ ስራዎች ላቅ የሚሉበት እና በጣም የሚበስሉበት ወቅት አላቸዉ። ከመብሰላቸዉ በፊት ያድጋሉ ይመነደጋሉ፤ ከበሰሉ በኋላ ግን ይቆረቁዛሉ። ለምሳሌ ከጥበብ ስራዎች ዉስጥ በጣም ጥቂቱ ብቻ ናቸዉ አንዳች መሻሻል የማያስፈልጋቸዉ። አስተዋይ የሆነ ሰዉ እያንዳንዱን ነገር በበሰለበት ወቅት ጠብቆ ማጣጣም ይችላል። ይህን ነገር ሁሉም ሰዎች አያዉቁትም፤ ከሚያዉቁት ዉስጥ ደግሞ ሁሉም ፍሬዉን ማጣጣም አይችሉም። ማስተዋል ራሱ እንደ ፍሬ የመብሰል ባህሪ አለዉ። እናም ይህን ነገር ትጠቀምበት ዘንድ ለይተህ ልታዉቀው ይገባል።

40. የሰዎችን መልካም ፈቃድ ለማግኘት ጥረት አድርግ። በሰዉ ዘንድ ታዋቂነትን ማትረፍ መልካም ቢሆንም፤ ከዚህ የበለጠዉ ግን ለጋስነታቸዉን ማግኘት ነዉ። እዚህ ላይ እድል የሚጫወተዉ ሚና ቢኖርም፤ ወሳኙ ነገር ጥንቁቅነት ነዉ። ማስጀመሪያዉ እድል ቢሆንም ነገሩ ቀጣይነትን የሚያገኘዉ በጥንቁቅነት ነዉ። ታገኝ ዘንድ ስጥ። ሁሉንም አይነት መልካም ነገር ለሰዎች አድርግ፤ መልካም ቃላት ሆነ መልካም ዉለታ። ትወደድ ዘንድ ደግሞ ዉደድ። ትህትና ታላላቆች ሰዎችን የሚያሸንፉበት መሳሪያ ነዉ። መልካም ተግባርን ስራ ቀጥሎም መልካም ነገርን ጻፍ። በጸሀፊዎች ዘንድም መልካም የሆነ የሰዎች ፈቃድ ስለሚገኝ አካሄድህ ከጎራዴ ወደ ብዕር ይሁን።

ጎበዝ፣ በብልህነት መንገድ እንጓዝ፣ ብልሆችም እንሁን!
:mrgreen:

Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ‘የብልህነት መንገድ’ - ምርጥ መጠሓፍ በምርጥ ተርጓሚ - ይዘቷን እንካችሁ አጣጥሙ!

Post by Meleket » 08 Apr 2019, 05:11

ለዛሬ አስር ቀጣይ የብልህነት መንገዶችን እንጋራለን፣ ማጣጣሙን ለ1ኛዉ ዓመት የድል በዓላችን የክብር እንግዶችና ለፎረሙ ታዳሚዎቻችን በሙሉ እንተወዋለን!!! :lol: መልካም ንባብ።

41. በፍጹም አታጋንን። እዉነትን ስለምታስቀይም እና የማመዛዘን ችሎታህንም ትዝብት ውስጥ ስለሚከተዉ ማጋነን የጠቢብነት ተግባር አይደለም። በማጋነንህ ልታገኝ የምትችለዉን ሙገሳ ማጣት ብቻ ሳይሆን አለማወቅህንም ታሳያለህ። አንድን ነገር ስታሞግስ የሰዎችን ትኩረት ከዛም ለነገሩ ያላቸዉን ፍላጎት እንዲጨምር ታደርገዋለህ እናም አመሻሹ ላይ ይህ ያሞገስከዉ ነገር እንደተለመደዉ ያዉ የተጠበቀዉን ያህል ሆኖ ስለማይገኝ ሰዎች መጨረሻ ላይ አሞጋሹን እና ተሞጋሹን ባንድ ላይ ይነቅፏቸዋል። አስተዋዮች ሙገሳን ከማብዛት ይልቅ ማሳነስ እንደሚሻል ጠንቅቀዉ ያዉቃሉ። በዚህ አለም ታላቅ የሚባሉ ነገሮች በጣም ጥቂት ስለሆኑ ስታሞግስ ለከት ይኑርህ። አንድን ነገር የማይገባዉን ያህል ማሞገስ ከመዋሸት አይለይም። እናም ይህ ተግባር አንድም ምርጫ እንደማትችል፤ ይባስ ብሎ ደግሞ ጠቢብ አለመሆንህን ይናገራል።

42. ወደዚህ አለም ለመሪነት የተላከ። ይህ ሚስጥራዊ እና ሀያልነትን የተላበሰ ማዕበል ነዉ። መሪነት ከአሰልች ብልጣብልጥነት የሚመጣ ሳይሆን በተፈጥሮ የሚገኝ ነገር ነዉ። እንደዚህ አይነት ሰዎች ሳይታወቀን በአንዳች ዉስጣዊ ሀይል ልባችንን ይረቱታል። እንዲህ አይነት ሰወች የጌትነት ጸባይ አላቸዉ፤ መስፍንነት የሚገባቸዉም ናቸዉ። እንዲሁ በሰዎች ዘንድ መከበርንም ያገኛሉ። በተለይ ከተጨማሪ ስጦታ ጋር ወደዚህ አለም ከመጡ የሰዉን ፍጡር በመላ የማንቀሳቀስ ችሎታ ይኖራቸዋል። እነሆ ለሌሎች ብዙ ጭቅጭቅ የፈጀዉን እነዚህ ሰዎች በአንድ ጥቅሻ ያስፈፅሙታል

43. ከብዙዎች ጋር ተነጋገር፤ ስሜትህን ግን ለጥቂቶች ብቻ አጋራ። ከሚወርድ ውሃ ተቃራኒ መዋኘት ነገርን አለማቅናት ብቻ ሳይሆን ለዋናተኛዉም አደገኛ ነዉ። ይህን ማድረግ የቻለዉ ሶቅራጥስ ብቻ ነዉ። ስትቃወም ሰዎች ችሎታቸዉን እንዳጣጣልክ ስለሚሰማቸዉ ተቃዉሞህን እንደ ስድብ ይቆጥሩታል። እንዲሁ የሚያምኑበትን ነገር ስለሚያናጋባቸዉ፤ ብዙዎች በተቃርኖ ይቀየማሉ። እዉነት የምትገኘዉ በጥቂቶች እጅ ነዉ። የሀሰት ነገር ግን እንደስድነት ሁሉ የበረከተ ነዉ። ምንም ዉስጣቸዉን እየረገሙ ቢሆንም ጠቢቦች ህዝብን ሲያናግሩ በህዝቡ አለማወቅ ልክ ስለሆነ ጠቢቦችን በህዝብ ፊት በሚናገሩት መለየት አይቻልም። ምክንያታዊ ሰዉ ሌሎችን መንቀፍ ሆነ በሌሎች መነቀፍን ያስወግዳል። ምንም ነገሮችን በፍጥነት መገምገም ቢችልም በሰዉ ፊት ለመናገር አይቸኩልም፤ በጸጥታ ተገልለዉ ስለሚኖሩ ስሜታቸዉንም የሚገጹት ለጥቂት አስተዋይ ሰዎች ብቻ ነዉ።

44. ታላቅ ሰዎችን ተረዳቸዉ። ከታላላቆች ጋር መግባባት መቻል በራሱ ታላቅነት ነዉ። ይህ መረዳት የሚባል ነገር አንድም በሚስጥራዊነቱ ሌላም ላቅ ባለዉ ጠቃሚነቱ ምክንያት አስደናቂ የተፈጥሮ ችሎታ ነዉ። ሰዎችን መረዳት ከሌሎች ጋር የልብ እና የሀሳብ ዉህደትን ይፈጥራል፤ ጠቀሜታዉም መደዴዎች የመስተፋቅር ሀይል ብለዉ የሚጠሩትን ያህል ነዉ። የመረዳት ችሎታ ታዋቂነትን ብቻ ሳይሆን የሰዎችን መልካም ፈቃድ እና ድጋፍም ያተርፍልናል። የመረዳት ችሎታ ያለክርክር ያሳምናል፤ ያለ ጥረት ጉዳይን ያስፈጽማል። የመረዳት ችሎታ ገለልተኛ ወይም ተሳታፊ ሊሆን ሲችል፤ ሁለቱም ታላቅ ደስታን ይፈጥራሉ። ይህን ነገር ማወቅ፤ መለየት ብሎም ተግባር ላይ ማዋል ታላቅ ጥበብ ነዉ። ምንም አይነት ጥረት መረዳትን ሊተካት አይችልም።

45. ብልጥ ሁን፤ ልክህን ግን እወቅ። ችሎታዎች ጥርጣሬን ሥለሚያጭሩ እና በሰዎች ዘንድ የተጠሉ ስለሆኑ ሁሌም መደበቅ አለባቸዉ፤ በተለይ ደግሞ አርቆ አሳቢነት። እኩይ ተግባር በሽበሽ ስለሆነ ጥንቁቅ ሁን። ሆኖም ግን ጥንቁቅነትህን ሰዎች የደረሱበት እንደሆን እምነታቸዉን ስለሚነፍጉህ ጥንቁቅነትህን ደብቀዉ። ጥርጣሬህ የታወቀ እንደሆን ሰዎችን ያስቀይማል፤ ብሎሞ ለበቀል ያነሳሳቸዋል፤ ከዛም ያልጠበቅከዉን ጣጣ ያመጣብሃል። እናም ለምታደርገዉ ነገር ሁሉ ቆም ብለህ ብታስብ እጅግ ትጠቀማለህ። ይህ ደግሞ የአመዛዛኝነት መለኪያ ነዉ። መልካም ፍጻሜ የሚወሰነዉ አፈጻጸሙ ላይ በዋለዉ ጥበብ ልክ ነዉ።

46. ለጥላቻህ ልጓም አብጅለት። አንዳንድ ሰዎችን መልካም ጎናቸዉን እንኳ ሳናውቅ እንዲሁ ከመሬት ተነስተን እንጠላቸዋለን። አንዳንዴ ይህን ስድ የሆነ ተግባር ወደ ታላላቅ ሰዎች ሳይቀር እንቀስረዋለን። ስለዚህ አስተዋይነት ይህን መጥፎ አመል ሊያርመዉ ይገባል። መልካም ሰዉን የመጥላትን ያህል ራስን የሚያዋርድ ተግባር የለም። ከታላላቆች ጋር በተስማማን ጊዜ ከበሬታን ስናገኝ የተቃወምናቸዉ ጊዜ ደግሞ ዉርደትን እንሸከማለን።

47. ከልክ ያለፈ ተግባር ላይ አትሳተፍ። ይህ ዋናዉ የአስተዋይነት መርህ ነዉ። በጣም የተካኑ ሰዎች ከልክ ካለፈ ተግባር ራሳቸዉን ያርቃሉ። ከልክ ያለፉ ተግባራት ሁሉ ሁለት ጫፍ አላቸዉ - ማነስ እና መብዛት - አስተዋይ ደግሞ የሁለቱን መሀከል ይመርጣል። አስተዋዮች ከአደጋ ዉስጥ በሰላም ከመዉጣትይልቅ ሲጀመር አለመግባትን ስለሚመርጡ ለሚያደርጉት ነገር ሁሉ ቀድመዉ ያስባሉ። አደገኛ ገጠመኞች የማመዛዘን ችሎታችንን በጣሙን ስለሚፈታተኑት ከእንዲህ አይነት አጋጣሚዎች ሙሉ በሙሉ መራቅ ያሻል። አንድ አደጋ ሌሎች ታላላቅ አደጋወችን ያስከትልና ወደ ጥፋት አፋፍ ይነዳል። በተፈጥሮ ሆነ በትዉልድ ሀገር ችኩል የሆኑ ሰዎች አሉ፤ እነዚህ ሰዎች በዚሁ ችኩልነታቸዉ ልክ ችግር ዉስጥ ይገባሉ። ሆኖም ግን በብርሃን ፋና የሚጓዝ ስለሚፈጽመዉ ጉዳይ በደንብ ያስባል፤ ከዚህም በላይ ችግርን ከመቋቋም ይልቅ ቀድሞ መከላከል የላቀ እንደሆነ ይረዳል። እንዲሁ ከማንኛዉም ችግር ዉስጥ ሌላ ቂል ቀድሞ መግባቱን ስለሚያዉቅ ራሱን ተጨማሪ ቂል ለማድረግ አይደክምም።

48. ማንነትህ በብስለትህ ልክ ነዉ። ከነገሮች ውጫዊ ገጽታ ይልቅ ውስጣዊ ይዞታቸዉ ወሳኝ ነዉ። አንዳንድ ሰዎች ልክ ተሰርቶ ሳያልቅ ገንዘብ እንዳለቀበት ህንጻ ዉጫቸዉ ብቻ ያምር እና ወደ ዉስጥ ሲገባ ግን ከጎጆ ቤት የተሻሉ አይደሉም። እንደዚህ አይነት ሰወች የአስተሳሰብ ጥልቀት ስለሌላቸዉ ከመጀመሪያዉ ሰላምታ በኋላ የሚናገሩት ይጠፋባቸዋል። የሚናገሩት የሚያጡበት ምክንያት ደግሞ የሀሳብ ምንጭ ስለሌላቸዉ ነዉ። እነዚህ ሰዎች ከዉጭ ብቻ አይቶ የሚገምትን ቢያታልሉም ጠለቅ ያለ እይታ ያለዉን እናም ዉስጣቸዉን አይቶ ባዶነታቸዉን የሚረዳዉን ሰዉ ግን ሲያታልሉ አይችሉም።

49. ነገሮችን የማጤን እና የማመዛዘን ችሎታ ይኑርህ። እንዲህ አይነት ሰዉ ሁኔታወችን ይቆጣጠራቸዋል እንጅ ሁኔታዎች እርሱን አይቆጣጠሩትም። የሰወችን ልኬታም ጠለቅ ብሎ የማንበብ ችሎታ አለዉ። አንድን ሰዉ እንዳየ ወዲያዉኑ ሊረዳዉ እና ሊገመግመዉም ይችላል። ባለዉ ከፍተኛ የማገናዘብ ሀይል ድብቅ ሀሳብን እንኳን ፈልፍሎ ማዉጣት ይችላል። እንዲህ አይነት ሰዉ ነገሮችን በጥራት እና በብቃት ገምግሞ ተገቢ ድምዳሜ ላይ መድረስ ይችላል። በተጨማሪም ነገሮችን ገልጦ አይቶ ጭብጣቸዉን መረዳት ያዉቅበታል።

50. ለራስህ ክብር ይኑርህ፤ ወይም ራስህን እንዳትንቅ። ከራስህ የሚወጣ ስነስርአተኝነት ስርአት ሊያስይዝህ ይገባል። ከማንም ዉጫዊ ሀይል ይልቅ የራስህ አራሚ እና ገሳጭ አንተዉ ራስህ መሆን አለብህ። እናም መጥፎ ነገርን ከማድረግ ስትቆጠብ ሰወችን ፈርተህ ሳይሆን ራስህን ፈርተህ ይሁን። ስለዚህ ራስህን ማክበር እና መፍራት ልመድ።

ጎበዝ፣ በብልህነት መንገድ እንጓዝ፣ ብልሆችም እንሁን! :mrgreen:

Degnet
Senior Member+
Posts: 25078
Joined: 16 Feb 2013, 11:48

Re: ‘የብልህነት መንገድ’ - ምርጥ መጠሓፍ በምርጥ ተርጓሚ - ይዘቷን እንካችሁ አጣጥሙ!

Post by Degnet » 08 Apr 2019, 06:50

Meleket wrote:
03 Apr 2019, 09:32
በዚህ ርእስ ስር፡ ባልታሳር ግራሽያን የጻፈውን፡ የሐረማያ ዩኒቨርስቲው አያሉ አክሊሉ የተረጎመዉን ድንቅ መጣህፍ ይዘት እናጣጥመዉ ዘንድ በዝግታ ማለትም በኤሊ አካሄድ እንጎማለልበታለን። እዚህ የምንጋራዉ ጽሑፍ መታሰቢያነቱ “የሔጉን ውሳኔ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ እተገብራለዉ” ብለው በይፋ በኢትዮጵያ ህዝብ ፓርላማ ውስጥም ሳይቀር ቃል የገቡትን የኦሕዴዱ ወጣት ጠቅላይ አብይ ወደ ስልጣን የተፈናጠጡበትን፡ እንዲሁም አፈንጋጯ ሕወሓት መቐለ የተወሸቀችበትን፣ የኤርትራና የኢትዮጵያ ህዝብም ሰላም በመስፈኑና የድንበሩ ብይን ትግባሬ ላይ ይውላል ብለው ሙሉ ተስፋ የጣሉበትንና ልባዊ ፈንጠዝያ ያደረጉበትን አንደኛ ዓመት የድል በአል እያከበርን ነው። :mrgreen:

የብልህነት መንገድ ይዘቷ በዚህ ፎረም ወይ መድረክ ተጠቃሚ ዜጎች በሙሉ፡ በተለይ ደግሞ አንዳንድ ስድነትን የምናስተጋባና ምላሳችን ሆነ ልባችን ያልተገረዘ ዋልጌዎችን የስነምግባር ትምህርት የምትሰጥ በመሆኗ፡ እግረመንገዳችንን ወደዝች ገጥ ጎራ ባልን ቁጥር ይህችን በምርጥ አማርኛ የተቀነባበረች ምርጥ ሃሳብን የምትዘራ መጽሐፍ ይዘት እንድትጋሩ በአፍሪካዊ ትህትና እጠይቃችኋለሁ!!! መጸሓፊቱን በመግዛትም ተርጓሚዉን ታበረታቱ ዘንድም በኤርትራዊ ወኔ ላሳስባችሁ እወዳለው። :lol:

የመጸሐፏን ደራሲ እስፓኛዊዉ ባልታሳር ግራሽያን (1601-1658 እኤኣ)፣ በድንቅ አማርኛ እጅግ ዉብ በሆነ አገላለጽ የተረጎማትን የሐረማያ ዩኒቨርስቲዉን አያሉ አክሊሉ እንዲሁም ይህን መድረኽ እዉን አድርጎ መልካም አስተሳሰቦች 20 እጥፍ፣ 60 እጥፍ፣ 100 እጥፍ፣ ፍሬ እንዲያፈሩ የተጋዉን ኤልያስ ክፍሌን ከልብ እያመሰገንን፡ ብቀጥታ የመጸሐፊቷን ይዘት ከዛሬ ጀምሮ አንድ ሁለት ሶስት እያልን እንቀጥላል። ለዛሬ ሶስቱን እንሆ! መልካም ማጣጣም ያድርግልዎ!!!

1. ሁሉም ነገር እጅግ ልቋል፤ እናም ምልኡ* ሰው መሆን ከሁሉም የበለጠ የልቀት ደረጃ ነዉ። ዛሬ አንድ ጠቢብን ለመፍጠር ጥንት በግሪክ ዘመን የነበሩ ሰባት ጠቢባንን ለመፍጠር የሚያስፈልገዉን ግብአት ይጠይቃል።

ምልኡ= ባልታሳር ግራሻን እንደሚያምነዉ ከሆነ ማንኛዉም ሰዉ እንደ እዉነተኛ ሰዉ አይቆጠርም። አንድ ሰዉ እዉነተኛ (ምልኡ) ሰዉ የሚሆነዉ ለሞራላዊ ልቀት ጥረት በማድረግ ነዉ።

2. ባህሪ እና እዉቀት። እነዚህ የተፈጥሮ ስጦታህን ደግፈዉ የያዙት ዋልታዎች ናቸዉ። አንደኛዉ በሌለበት ሌላኛዉ ግማሽ ስኬትን ብቻ ነው የሚፈጥርልህ። እናም እዉቀት ብቻዉን በቂ ስላልሆነ መልካም ባህሪም ሊጨመርበት ይገባል። ሞኝ ዉድቀቱን የሚያመጣት ባህሪዉ ሁኔታዉን፤ በሰዉ ዘንድ ያለዉን ተቀባይነት እና ጓደኞቹን ያገናዘበ ባለመሆኑ ነዉ።

3. ነገሮችን አንጠልጣይ አድርጋቸዉ። ላቅ ያሉ ስኬቶች አድናቆትን ያተርፋሉ። በጣም ግልጽ መሆን ጣፋጭም ጠቃሚም አይደለም። በተለይ የያዝከዉ ቦታ በጣም ተፈላጊ ከሆነ እራስህን ቶሎ ግልጽ አለማድረግ የሰወችን ትኩረት ይስብልሃል። ማንኛዉም ሰዉ ዉስጥህን እንዲያዉቅ አትፍቀድለት። ራስህን ስትገልጽ እንኳ ሙሉ በሙሉ መሆን የለበትም። እነሆ ብልህነት የምትገኘዉ ጥንቃቄን መሰረት ባደረገች ዝምታ ዉስጥ ነዉ። ሀሳቦች አንዴ ግልጽ ከተደረጉ በኋላ ከበሬታን አለማግኘት ብቻ ሳይሆን ለነቀፋም የተመቻቹ ናቸዉ። እነዚሁ ሀሳቦችህ ግባቸዉን ሳይመቱ የቀሩ እንደሆን ደግሞ እጥፍ ጊዜ እንደከሰርክ ይቆጠራል። የሰወችን ትኩረት የምትሻ ከሆነ መለኮታዊነትን ተከተል።

ወዳጄ “በብልህነት መንገድ ተጓዝ ብልህም ሁን፤ አንቺም እንዲሁ!”!!!
:mrgreen:
For me,just closed.

Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ‘የብልህነት መንገድ’ - ምርጥ መጠሓፍ በምርጥ ተርጓሚ - ይዘቷን እንካችሁ አጣጥሙ!

Post by Meleket » 08 Apr 2019, 10:57

Degnet wrote:
08 Apr 2019, 06:50

የመጸሐፏን ደራሲ እስፓኛዊዉ ባልታሳር ግራሽያን (1601-1658 እኤኣ)፣ በድንቅ አማርኛ እጅግ ዉብ በሆነ አገላለጽ የተረጎማትን የሐረማያ ዩኒቨርስቲዉን አያሉ አክሊሉ እንዲሁም ይህን መድረኽ እዉን አድርጎ መልካም አስተሳሰቦች 20 እጥፍ፣ 60 እጥፍ፣ 100 እጥፍ፣ ፍሬ እንዲያፈሩ የተጋዉን ኤልያስ ክፍሌን ከልብ እያመሰገንን፡ ብቀጥታ የመጸሐፊቷን ይዘት ከዛሬ ጀምሮ አንድ ሁለት ሶስት እያልን እንቀጥላል። ለዛሬ ሶስቱን እንሆ! መልካም ማጣጣም ያድርግልዎ!!! .. .. ..

:mrgreen:
For me,just closed.
ወዳጄ Degnet ደግ ነህ ወይ? የአንደኛ አመት የድል በዓሉን አብረሀን ለማክበር እዚህ በመገኘትህ ደስ ብሎናል። እንዳልከዉም ለእንደ አንተ አይነት ብልሆች የጽሑፉ ጥቂት ክፍል በቂ ሊሆን ይችላል፤ ገና ብልህ ላልሆነዉ የድል በዓሉ ተሳታፊዎች ግን ገና አንድ ሁለት ሶስት እያልን የብልህነት መንገዶቹን እንደ ቀይባህር አሳ እዚህ እናርመሰምሳቸዋለን። የፈለገ ደግሞ ያሻዉን እየመረጠና እያጠመደ ጠብሶ ይሁን ቀቅሎ መብላት መብቱ ነዉ። ቀጣዮቹ 10 የብልህነት መንገዶች ደግሞ ላንተ ለብልሁ ጓዴ ክብር ለታዳሚዎች እናበረክታቸዋለን። እስከዚያዉ ግን የዛሬዎቹን 10 የብልህነት መንገዶች ለቅኑዎቹ እንደርቴዎች ክብር በድጋሚ እዚህ አቅርበነዋል! ደህና ሁንልኝ የእንደርታዉ ብልህ ጓዴ!!! :mrgreen:
Meleket wrote:
08 Apr 2019, 05:11
ለዛሬ አስር ቀጣይ የብልህነት መንገዶችን እንጋራለን፣ ማጣጣሙን ለ1ኛዉ ዓመት የድል በዓላችን የክብር እንግዶችና ለፎረሙ ታዳሚዎቻችን በሙሉ እንተወዋለን!!! :lol: መልካም ንባብ።

41. በፍጹም አታጋንን። እዉነትን ስለምታስቀይም እና የማመዛዘን ችሎታህንም ትዝብት ውስጥ ስለሚከተዉ ማጋነን የጠቢብነት ተግባር አይደለም። በማጋነንህ ልታገኝ የምትችለዉን ሙገሳ ማጣት ብቻ ሳይሆን አለማወቅህንም ታሳያለህ። አንድን ነገር ስታሞግስ የሰዎችን ትኩረት ከዛም ለነገሩ ያላቸዉን ፍላጎት እንዲጨምር ታደርገዋለህ እናም አመሻሹ ላይ ይህ ያሞገስከዉ ነገር እንደተለመደዉ ያዉ የተጠበቀዉን ያህል ሆኖ ስለማይገኝ ሰዎች መጨረሻ ላይ አሞጋሹን እና ተሞጋሹን ባንድ ላይ ይነቅፏቸዋል። አስተዋዮች ሙገሳን ከማብዛት ይልቅ ማሳነስ እንደሚሻል ጠንቅቀዉ ያዉቃሉ። በዚህ አለም ታላቅ የሚባሉ ነገሮች በጣም ጥቂት ስለሆኑ ስታሞግስ ለከት ይኑርህ። አንድን ነገር የማይገባዉን ያህል ማሞገስ ከመዋሸት አይለይም። እናም ይህ ተግባር አንድም ምርጫ እንደማትችል፤ ይባስ ብሎ ደግሞ ጠቢብ አለመሆንህን ይናገራል።

42. ወደዚህ አለም ለመሪነት የተላከ። ይህ ሚስጥራዊ እና ሀያልነትን የተላበሰ ማዕበል ነዉ። መሪነት ከአሰልች ብልጣብልጥነት የሚመጣ ሳይሆን በተፈጥሮ የሚገኝ ነገር ነዉ። እንደዚህ አይነት ሰዎች ሳይታወቀን በአንዳች ዉስጣዊ ሀይል ልባችንን ይረቱታል። እንዲህ አይነት ሰወች የጌትነት ጸባይ አላቸዉ፤ መስፍንነት የሚገባቸዉም ናቸዉ። እንዲሁ በሰዎች ዘንድ መከበርንም ያገኛሉ። በተለይ ከተጨማሪ ስጦታ ጋር ወደዚህ አለም ከመጡ የሰዉን ፍጡር በመላ የማንቀሳቀስ ችሎታ ይኖራቸዋል። እነሆ ለሌሎች ብዙ ጭቅጭቅ የፈጀዉን እነዚህ ሰዎች በአንድ ጥቅሻ ያስፈፅሙታል

43. ከብዙዎች ጋር ተነጋገር፤ ስሜትህን ግን ለጥቂቶች ብቻ አጋራ። ከሚወርድ ውሃ ተቃራኒ መዋኘት ነገርን አለማቅናት ብቻ ሳይሆን ለዋናተኛዉም አደገኛ ነዉ። ይህን ማድረግ የቻለዉ ሶቅራጥስ ብቻ ነዉ። ስትቃወም ሰዎች ችሎታቸዉን እንዳጣጣልክ ስለሚሰማቸዉ ተቃዉሞህን እንደ ስድብ ይቆጥሩታል። እንዲሁ የሚያምኑበትን ነገር ስለሚያናጋባቸዉ፤ ብዙዎች በተቃርኖ ይቀየማሉ። እዉነት የምትገኘዉ በጥቂቶች እጅ ነዉ። የሀሰት ነገር ግን እንደስድነት ሁሉ የበረከተ ነዉ። ምንም ዉስጣቸዉን እየረገሙ ቢሆንም ጠቢቦች ህዝብን ሲያናግሩ በህዝቡ አለማወቅ ልክ ስለሆነ ጠቢቦችን በህዝብ ፊት በሚናገሩት መለየት አይቻልም። ምክንያታዊ ሰዉ ሌሎችን መንቀፍ ሆነ በሌሎች መነቀፍን ያስወግዳል። ምንም ነገሮችን በፍጥነት መገምገም ቢችልም በሰዉ ፊት ለመናገር አይቸኩልም፤ በጸጥታ ተገልለዉ ስለሚኖሩ ስሜታቸዉንም የሚገጹት ለጥቂት አስተዋይ ሰዎች ብቻ ነዉ።

44. ታላቅ ሰዎችን ተረዳቸዉ። ከታላላቆች ጋር መግባባት መቻል በራሱ ታላቅነት ነዉ። ይህ መረዳት የሚባል ነገር አንድም በሚስጥራዊነቱ ሌላም ላቅ ባለዉ ጠቃሚነቱ ምክንያት አስደናቂ የተፈጥሮ ችሎታ ነዉ። ሰዎችን መረዳት ከሌሎች ጋር የልብ እና የሀሳብ ዉህደትን ይፈጥራል፤ ጠቀሜታዉም መደዴዎች የመስተፋቅር ሀይል ብለዉ የሚጠሩትን ያህል ነዉ። የመረዳት ችሎታ ታዋቂነትን ብቻ ሳይሆን የሰዎችን መልካም ፈቃድ እና ድጋፍም ያተርፍልናል። የመረዳት ችሎታ ያለክርክር ያሳምናል፤ ያለ ጥረት ጉዳይን ያስፈጽማል። የመረዳት ችሎታ ገለልተኛ ወይም ተሳታፊ ሊሆን ሲችል፤ ሁለቱም ታላቅ ደስታን ይፈጥራሉ። ይህን ነገር ማወቅ፤ መለየት ብሎም ተግባር ላይ ማዋል ታላቅ ጥበብ ነዉ። ምንም አይነት ጥረት መረዳትን ሊተካት አይችልም።

45. ብልጥ ሁን፤ ልክህን ግን እወቅ። ችሎታዎች ጥርጣሬን ሥለሚያጭሩ እና በሰዎች ዘንድ የተጠሉ ስለሆኑ ሁሌም መደበቅ አለባቸዉ፤ በተለይ ደግሞ አርቆ አሳቢነት። እኩይ ተግባር በሽበሽ ስለሆነ ጥንቁቅ ሁን። ሆኖም ግን ጥንቁቅነትህን ሰዎች የደረሱበት እንደሆን እምነታቸዉን ስለሚነፍጉህ ጥንቁቅነትህን ደብቀዉ። ጥርጣሬህ የታወቀ እንደሆን ሰዎችን ያስቀይማል፤ ብሎሞ ለበቀል ያነሳሳቸዋል፤ ከዛም ያልጠበቅከዉን ጣጣ ያመጣብሃል። እናም ለምታደርገዉ ነገር ሁሉ ቆም ብለህ ብታስብ እጅግ ትጠቀማለህ። ይህ ደግሞ የአመዛዛኝነት መለኪያ ነዉ። መልካም ፍጻሜ የሚወሰነዉ አፈጻጸሙ ላይ በዋለዉ ጥበብ ልክ ነዉ።

46. ለጥላቻህ ልጓም አብጅለት። አንዳንድ ሰዎችን መልካም ጎናቸዉን እንኳ ሳናውቅ እንዲሁ ከመሬት ተነስተን እንጠላቸዋለን። አንዳንዴ ይህን ስድ የሆነ ተግባር ወደ ታላላቅ ሰዎች ሳይቀር እንቀስረዋለን። ስለዚህ አስተዋይነት ይህን መጥፎ አመል ሊያርመዉ ይገባል። መልካም ሰዉን የመጥላትን ያህል ራስን የሚያዋርድ ተግባር የለም። ከታላላቆች ጋር በተስማማን ጊዜ ከበሬታን ስናገኝ የተቃወምናቸዉ ጊዜ ደግሞ ዉርደትን እንሸከማለን።

47. ከልክ ያለፈ ተግባር ላይ አትሳተፍ። ይህ ዋናዉ የአስተዋይነት መርህ ነዉ። በጣም የተካኑ ሰዎች ከልክ ካለፈ ተግባር ራሳቸዉን ያርቃሉ። ከልክ ያለፉ ተግባራት ሁሉ ሁለት ጫፍ አላቸዉ - ማነስ እና መብዛት - አስተዋይ ደግሞ የሁለቱን መሀከል ይመርጣል። አስተዋዮች ከአደጋ ዉስጥ በሰላም ከመዉጣትይልቅ ሲጀመር አለመግባትን ስለሚመርጡ ለሚያደርጉት ነገር ሁሉ ቀድመዉ ያስባሉ። አደገኛ ገጠመኞች የማመዛዘን ችሎታችንን በጣሙን ስለሚፈታተኑት ከእንዲህ አይነት አጋጣሚዎች ሙሉ በሙሉ መራቅ ያሻል። አንድ አደጋ ሌሎች ታላላቅ አደጋወችን ያስከትልና ወደ ጥፋት አፋፍ ይነዳል። በተፈጥሮ ሆነ በትዉልድ ሀገር ችኩል የሆኑ ሰዎች አሉ፤ እነዚህ ሰዎች በዚሁ ችኩልነታቸዉ ልክ ችግር ዉስጥ ይገባሉ። ሆኖም ግን በብርሃን ፋና የሚጓዝ ስለሚፈጽመዉ ጉዳይ በደንብ ያስባል፤ ከዚህም በላይ ችግርን ከመቋቋም ይልቅ ቀድሞ መከላከል የላቀ እንደሆነ ይረዳል። እንዲሁ ከማንኛዉም ችግር ዉስጥ ሌላ ቂል ቀድሞ መግባቱን ስለሚያዉቅ ራሱን ተጨማሪ ቂል ለማድረግ አይደክምም።

48. ማንነትህ በብስለትህ ልክ ነዉ። ከነገሮች ውጫዊ ገጽታ ይልቅ ውስጣዊ ይዞታቸዉ ወሳኝ ነዉ። አንዳንድ ሰዎች ልክ ተሰርቶ ሳያልቅ ገንዘብ እንዳለቀበት ህንጻ ዉጫቸዉ ብቻ ያምር እና ወደ ዉስጥ ሲገባ ግን ከጎጆ ቤት የተሻሉ አይደሉም። እንደዚህ አይነት ሰወች የአስተሳሰብ ጥልቀት ስለሌላቸዉ ከመጀመሪያዉ ሰላምታ በኋላ የሚናገሩት ይጠፋባቸዋል። የሚናገሩት የሚያጡበት ምክንያት ደግሞ የሀሳብ ምንጭ ስለሌላቸዉ ነዉ። እነዚህ ሰዎች ከዉጭ ብቻ አይቶ የሚገምትን ቢያታልሉም ጠለቅ ያለ እይታ ያለዉን እናም ዉስጣቸዉን አይቶ ባዶነታቸዉን የሚረዳዉን ሰዉ ግን ሲያታልሉ አይችሉም።

49. ነገሮችን የማጤን እና የማመዛዘን ችሎታ ይኑርህ። እንዲህ አይነት ሰዉ ሁኔታወችን ይቆጣጠራቸዋል እንጅ ሁኔታዎች እርሱን አይቆጣጠሩትም። የሰወችን ልኬታም ጠለቅ ብሎ የማንበብ ችሎታ አለዉ። አንድን ሰዉ እንዳየ ወዲያዉኑ ሊረዳዉ እና ሊገመግመዉም ይችላል። ባለዉ ከፍተኛ የማገናዘብ ሀይል ድብቅ ሀሳብን እንኳን ፈልፍሎ ማዉጣት ይችላል። እንዲህ አይነት ሰዉ ነገሮችን በጥራት እና በብቃት ገምግሞ ተገቢ ድምዳሜ ላይ መድረስ ይችላል። በተጨማሪም ነገሮችን ገልጦ አይቶ ጭብጣቸዉን መረዳት ያዉቅበታል።

50. ለራስህ ክብር ይኑርህ፤ ወይም ራስህን እንዳትንቅ። ከራስህ የሚወጣ ስነስርአተኝነት ስርአት ሊያስይዝህ ይገባል። ከማንም ዉጫዊ ሀይል ይልቅ የራስህ አራሚ እና ገሳጭ አንተዉ ራስህ መሆን አለብህ። እናም መጥፎ ነገርን ከማድረግ ስትቆጠብ ሰወችን ፈርተህ ሳይሆን ራስህን ፈርተህ ይሁን። ስለዚህ ራስህን ማክበር እና መፍራት ልመድ።

ጎበዝ፣ በብልህነት መንገድ እንጓዝ፣ ብልሆችም እንሁን! :mrgreen:

Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ‘የብልህነት መንገድ’ - ምርጥ መጠሓፍ በምርጥ ተርጓሚ - ይዘቷን እንካችሁ አጣጥሙ!

Post by Meleket » 09 Apr 2019, 03:44

ጨቋኙና አድሏዊዉ የሕወሓት መንግስት የተገረሰሰበትን 1ኛ ዓመት የድል በአልን በደመቀ ሁኔታ እያከበርን፡ እንደ ቃላችን የዛሬዎቹን 10 የብልህነት መንገዶች ለብልሁ ወንድማችን Degnet ክብር እዚህ አቅርበናቸዋል! መልካም ንባብ። :lol:

51. የመምረጥ ችሎታ ይኑርህ። ለዚህ ምክንያቱ ብዙ የህይወት ጉዳዮች በዚህ ችሎታ ስለሚወሰኑ ነዉ። እዉቀት እና ተግባራዊነት ብቻቸዉን በቂ ስላልሆኑ የመምረጥ እና የማመዛዘን ችሎታ ሊጨመርባቸዉ ይገባል። ምርጫ ላይ ሁለት ችሎታወች ወሳኝ ናቸዉ፤ አንደኛዉ መምረጥ በራሱ ሲሆን ሌላኛዉ ደግሞ ላቅ ያለዉን ነገር መምረጥ መቻል ነዉ። በጣም አስተዋይ፤ አዋቂ፤ አመዛዛኝ ወይም በሳል የሚባሉ ብዙ ሰወች ምርጫ ላይ ተስፋ ቢስ ናቸዉ። እናም ደካማዉን የመምረጥ ችሎታቸዉን እወቁልኝ ለማለት የፈለጉ ይመስል ሁሌም የሚመርጡት አልባሌ የሆነዉን ነገር ነዉ። እነሆ የመምረጥ ችሎታ ከሰማየ ሰማያት የሚቸር ፍሬ ነዉ።

52. ስሜትህን መቆጣጠር ቻል። አስተዋይ ሰዉ ስሜቱ ከቁጥጥር ዉጭ እንዳይሆን ጥረት ያደርጋል። ለስሜት ቶሎ አለመሸነፍ ዉስጣዊ ዉበት እና የእዉነተኛ ሰዉ መገለጫ ነዉ። ስሜታዊነት ማለት የአእምሮ ቧልት በመሆኑ በጥቂቱ እንኳ ከልክ ካለፈ የማመዛዘን ችሎታችንን ለበሽታ ይዳርገዋል። ይህ በሽታ ወደ ምላስህ የተሻገረ እንደሆነ ደግሞ መልካም ስምህ አደጋ ላይ ይወድቃል። መልካም ሆነ መጥፎ ነገር ላይ ራስህን መቆጣጠር ብትችል ሰዎች ግልፍተኛ ብለዉ አይነቅፉህም።

53. ትጉህ እና ጠቢብ ሁን። ጠቢብነት ያሰበዉን ትጋት ያሳካዋል። ቂሎች ችኩልነትን ስለሚወዷት ለእንቅፋት ግምት ሳይሰጡ ጉዳያቸዉን ሁሉ ያለጥንቃቄ ያከናዉናሉ። ብልሆች ደግሞ አብዛኛዉን ጊዜ ነገር የሚበላሽባቸዉ ሲወላዉሉ ነዉ። አንዳንዴ ነገሮች በደንብ ብታስብባቸውም እንኳ በአፈጻጸም ብቃት ማነስ እና በክትትል እጦት ምክንያት ከግብ ሳይደርሱ ይቀራሉ። ለማንኛዉም ነገር ዝግጁነት የእድሎች ሁሉ እናት ናት። ምንም ነገር ለነገ ብሎ አለመተዉ መልካም ልምድ ነዉ። ረጋ ብሎ መፍጠን ልትከተለዉ የሚገባ ታላቅ መርህ ነዉ

54. መንፈሰ ጠንካራ ሁን። የሞተ አንበሳን ፂም ለመንካትማ ጥንቸልም አታንስለትም። ድፍረት ማለት ቀላል ነገር አይደለም። አንዴ ፍሬን ካቀዳጀህ ደግሞ ደጋግሞ ያቀዳጅሃል። አንድን ጉዳይ እያመነታህ በይደር ከመተዉ ይልቅ አነስ ያለ ሀይል ስለሚጠይቅህ ዉሎ ሳያድር መጋፈጥ ይበጃል። የመንፈስ ጥንካሬ ከሰዉነት ጥንካሬ የበለጠ ነዉ፤ ይህንንም ዝግጁ ሆኖ ሰገባዉ ዉስጥ ባለ ጎራዴ እንመስለዋለን። እነሆ ደካማ መንፈስ የሚያስከትለዉ ጉዳት ከደካማ ስዉነት የበለጠ ነዉ። ብዙ የአእምሮ ስጦታ ያላቸዉ ሰወች ጠንካራ መንፈስ ይጎድላቸዉ እና በቁማቸዉ ይሞታሉ፤ መታከት ደግሞ ግብአተ መሬታቸዉን ይፈጽምላቸዋል።

55. ትዕግስትን እወቅ። ይህ ብዙ ታጋሽነትን የያዘ የታላቅ ልብ መገለጫ ነዉ። በፍጹም እዳትቸኩል፤ ስሜትህም እንዳያጥለቀልቅህ ይሁን። በመጀመሪያ የራስህ ጌታ እና ከዚያም የሌሎች ጌታ ትሆናለህ። የነገሮችን ፍሬ ለማግኘት በጊዜ ዉስጥ መመላለስ አለብህ። ጠቢብነት የታከለበት ማቅማማት ስኬት ከተፍ ትል ዘንድ ሲረዳ፤ የተደበቁ እድሎች ደግሞ በስለዉ ብቅ እንዲሉ ያደርጋቸዋል። ነገሮችን ለመፈጸም እንደጊዜ ያለ ሀይል የለም። ፈጣሪ ራሱ የሚቀጣን በአለንጋ ሳይሆን በጊዜ ነዉ። ይህ ጊዜ የሰጠዉ ቅል ዲንጋይ ይሰብራል የሚል አባባል ምንኛ ወርቅ ነዉ? እናም እድል ለታጋሾች ሽልማቷ ላቅ ያለ ነዉ።

56. ተዘጋጅተህ ጠብቅ። ይህን የሚፈጥረዉ መልካም የሆነ የመንፈስ ንቃት ነዉ። አንዳንዶች መጨረሻ ሲሳሳቱ ብዙ የተጠበቡበትን ሌሎች ብዙም ሳያስቡ በብቃት ይደመድሙታል። የእንዲህ አይነት ቀልጣፋ ሰዎች ባህሪ ተቃርኖዎችን ያዘለ በመሆኑ ወከባ በበዛበት ጊዜ የስኬት ሰዎች ይሆኑ እና ሰላም ሰፍኖ ማሰቢያ ጊዜ ያገኙ እለት ግን በስህተት የተሞሉ ናቸዉ። ለነዚህ ሰዎች በፍጥነት ያልተሳካላቸዉ መፍትሄ ዘግይቶም ሊከሰትላችዉ አይችልም። ቅልጥፍና የመልካም አስተስሰብ እና የአስተዋይነት ተግባርን ያቀፈ ታላቅ ችሎታ ስለሆነ በሰዎች ዘንድ ደስታን ይፈጥራል።

57. ጉዳይህን ረጋ ብለህ ፈጽም። አንድን ነገር አድምቶ መስራት በእራሱ በፍጥነት እንደመፈጸም ይቆጠራል። የነቶሎ ቶሎ ቤት በፍጥነት ስለሚፈርስ ዘላቂ የሆነ ስራ ጊዜን ይጠይቃል። አንድ ነገር ላቅ ብሎ ካልተፈጸመ በስተቀር የሰዉን ትኩረት ሊስብ አይችልም። ላቅ ያለ አስተሳሰብ ደግሞ የማይሞት ስራን ይወልዳል። ታላቅ ነገር ሁሉ ታላቅ ስራን ይጠይቃል። ይህ ነገር በብረቶች ላይ እንኳ እንደሚሰራ የምናዉቀዉ ዉድ የሆኑ ማዕድናት ለማንጠር ጊዜ የሚወስዱት በመሆናቸዉን አዉ።

58. ባጠገብህ ያሉትን ሰዎች ምሰል። ሁሉንም ሰዉ በአንድ አይነት አቀራረብ አትጠጋ፤ በተጨማሪም አንድ ጉዳይ ከሚጠይቀዉ በላይ ጉልበት አታዉል። እዉቀትህን ሆነ ጉልበትህን በዘፈቀደ ማባከን የለብህም። የሰዎችን ትኩረት መሳብ ከፈለክ ያለህን ሁሉ ባንዴ አታሳይ። ችሎታህን ቀስ በቀስ ካሳየህ የሰዎችን ትኩረት ጠብቀህ ማቆየት ብቻ ሳይሆን ችሎታህንም እስከምን ድረስ እንደሆነ እንዳያዉቁ ታደርጋቸዋለህ።

59. መጨረሻህ ይመር። ወደ እድል ቤት በደስታ ከገባህ በሀዘን ትወጣለህ፤ በሀዘን ከገባህ ደግሞ በደስታ። የነገርን አጨራረስ እወቅበት፤ ላማረ አጨራረስ እንጅ ጭብጨባ ለተሞላበት ጅማሬ ትኩረት አትስጥ። እድለኛ ሰዎች ጅማሬያቸዉ ቢያምርም መጨረሻቸዉ አሳዛኝ ነዉ። የደስታ አቀባበል የተለመደ ስለሆነ ዋናዉ ትኩረትህ ከስንብት በኋላ ለመናፈቅ መሆን አለበት። ሁሌም የሚፈለጉ ሰዎች በጣም ጥቂት ናቸዉ። ብዙዉን ጊዜ መልካም እድል መልካም ማፈግፈግን አትችልበትም። እድለኛነት አዲስ መጤዎችን ስትቀበል በደስታ ቢሆንም ስንብቷ ግን የግልምጫ ነዉ።

60. የማመዛዘን ብቃት። አንዳንዶች ወደዚህ አለም የሚመጡት ብልህ ሆነዉ ነዉ። ወደዚህ አለም ሲመጡ የጥበበኝነት መገለጫ የሆነዉን የማመዛዘን ችሎታ ስለተቸሩ ወደ ስኬት ግማሽ መንገድን እንደተጓዙ ይቆጠራል። እነዚህ ሰዎች እድሜያችዉ ሲገፋ እና ልምድን ሲያካብቱ ምክንያታዊነታቸዉ እጅግ በሳል ይሆን እና በማመዛዘን የተካኑ ይሆናሉ። በተጨማሪም እነዚህ ሰወች ማስተዋልን የሚፈታተን ማናቸዉንም ስሜታዊነት እጅግ ይጠላሉ፤ በተለይም ጥንቃቄ በሚያስፈልገዉ እና ብርቱ በሆኑት የሀገራዊ ጉዳዮች ላይ። እንደዚህ አይነት ሰወች ለሀገር አስተዳዳሪነት ወይም ለአማካሪነት ሊታጩ ይገባል።

ጎበዝ፣ በብልህነት መንገድ እንጓዝ፣ ብልሆችም እንሁን! :mrgreen:

Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ‘የብልህነት መንገድ’ - ምርጥ መጠሓፍ በምርጥ ተርጓሚ - ይዘቷን እንካችሁ አጣጥሙ!

Post by Meleket » 10 Apr 2019, 09:46

የዛሬዎቹን 10 የብልህነት መንገዶች፡ የአሸባሪዉ፣ ግፈኛዉና ከፋፋዩ የሕወሓት መንግስት የተገረሰሰበትን 1ኛ ዓመት የድል በአል በድምቀት እያከበርን ነዉ የምናጣጥማቸዉ። ቀጣዮቹን የብልህነት መንገዶች በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የግፈኞች ሰለባ ለሆኑት ንጹሐን ዜጎች (ሰማእታት) ክብር እዚህ እንጋራዋለን። መልካም ንባብ።

61. መልካም በሆነዉ ነገር ሁሉ ላቅ ብለህ ተገኝ። ከሌሎች የልቀት ደረጃዎች ሁሉ ይህኛዉ ብርቅየ ነዉ። አንዳች በጎ ጎን የሌለዉ ጀግና የለም። ተራ ሰዉ መሆን በሌሎች ዘንድ ተቀባይነትን አያስገኝም። ባንድ ነገር ላይ ላቅ ብሎ መገኘት ከስድነት ያድነን እና ከመንጋዎች ለየት ያልን ያደርገናል። በታናሽ ተግባር ታላቅ መሆን ደግሞ እርባና የለዉም። በመልካም ነገሮች ላቅ ብሎ መገኘት ታላቅነትን ሲያላብስህ የሰዎችን አድናቆት እና መልካም ፈቃድም ያስገኝልሃል።

62. በጥሩ መሳሪያዎች ተጠቀም። አንዳንድ ሰዎች በመጥፎ መሳሪያወች እየተገለገሉ ብልጥ ለመሆን ይመኛሉ። ይህ አደገኛ የሆነ አስተሳሰብ ስለሆነ ቅጣት ይገባዋል። የአገልጋይ ጉብዝና የጌታዉን ታላቅነት ሊያደበዝዝ አይችልም። ሁሌም ቢሆን በስኬት ጊዜ ሽልማቱ፤ በዉድቀት ጊዜ ደግሞ ነቀፋዉ የሚያርፈዉ ዋና ተዋናዩ ላይ ነዉ። በስኬት ጊዜ ዝናን የሚያተርፉት አለቆች ናቸዉ። ይህ የሆነበት ምክንያት በስኬት ጊዜ ሰወች “መልካም ሰራተኞች ነበሩት” ወይም “መጥፎ ሰራተኞች ነበሩት” ሳይሆን “መልካም ሰዉ ነበር” ወይም “መጥፎ ሰዉ ነበር” ስለሚሉ ነዉ። ስለዚህ የማይሞተዉን ዝናህን የምታገኘዉ በስርህ በኮለኮልካቸዉ ባለሟሎች አማካኝነት ስለሆነ እነዚህን ሰወች በጥንቃቄ ምረጣቸዉ።

63. ፈር ቀዳጅ መሆን ላቅ ያለ ተግባር ነዉ። ጉዳዩ ታላቅ ነገር የሆነ እንደሆነ ደግሞ ፈር ቀዳጅነት እጅጉን የላቀ ነዉ። በሁሉም ነገር እኩል ሆነዉ የመጀመሪያዉን እርምጃ የሚራመደዉ ከሌሎች ሁሉ የበለጠ ነዉ። አንዳንድ ሰወች ሌሎች ባይቀድሟቸዉ ኖሮ በሙያቸዉ ብርቅየ ይሆኑ ነበር። ባንድ ሙያ ቀደምትነትን የተቀዳጁት ሰዎች ዝናንም አብረዉ ሲያፍሱ ከነሱ የሚከተሉት ሰዎች ግን የፈለገ ቢደክሙ ትርፋቸዉ በአስመስሎ ሰሪነት መጠራት ነዉ። ታላቅ ሰዎች ታላቅ ነገርን ያገኛሉ፤ መንገዳቸዉም በአስተዋይነት የተሞላ ነዉ። እንዲሁ በነገሮች ቀደምትነትን በመቀዳጀታቸዉ ብቻ ስማቸዉን በታላላቆች መዝገብ ያስጽፋሉ። በዚህ ምክንያት አንዳንድ ሰዎች በመጀመሪያ ደረጃ ላቅ ባለ ተግባር ሁለተኛ ከመሆን ይልቅ በሁለተኛ ደረጃ በላቀ ተግባር ቀደምት መሆንን ይመርጣሉ።

64. ራስህን ከጭንቀት አርቅ። ከእንቅፋቶች ራስን ማራቅ ጠቃሚ ብቻ ሳይሆን ጠቢብነትም ነዉ። አስተዋይነት የሰላም እና የደስታ ምንጭ ስለሆነ ከብዙ ችግር ሊያድንህ ይችላል። መፍትሄ ከሌለዉ በስተቀር ለሌሎች መጥፎ ዜናን እንዳታደርስ፤ አንተም እንዲሁ መጥፎ ዜናን ላለመቀበል የበለጠ ጥንቁቅ ሁን። ያንዳንዶች ጆሮ የተሞላዉ በሽንገላ ሲሆን፤ የሌሎች ደግሞ በመጥፎ ሀሜት ነዉ፤ ከዚህ ዉጭ ያሉት ደግሞ መጥፎ ዜናን በየቀኑ ካልሰሙ የማይሆንላቸዉ ሰዎች ናቸዉ። የፈለገ ቢቀርብህ ሌላዉን ሰዉ አስደስታለሁ ብለህ ራስህን ሀዘን ዉስጥ በመጨመር ጤናየን ጠብቄ መኖር ይቻለኛል ብለህ ተስፋ እንዳታደርግ። ከጉዳዩ ጋር አንዳች ግንኙነት የሌለዉን ሰዉ እንደ አማካሪ አሰቅምጠህም ይህንንም ሰዉ አስደስታለሁ ብለህ ምክሩን እየተከተልክ የራስህን ደስታ እንዳታጣ ይሁን። አንድን ሰዉ እያስደሰትክ ራስህን ሀዘን ዉስጥ በከተትክ ጊዜ ይህን አባባል አስታዉስ - ያለምንም ተስፋ አመሻሹ ላይ ራስህን ሀዘን ዉስጥ ከመጨመር ይልቅ ባልንጀራህ ለራሱ ሀዘን ዉስጥ ቢገባ የተሻለ መሆኑን።

65. ላቅ ያለ ምርጭ ይኑርህ። አእምሮህን እንደምታጎለብተዉ ሁሉ የመምረጥ ችሎታህንም ልታጎለብተዉ ትችላለህ። ስለምትፈልገዉ ነገር በደንብ መረዳት ለዛ ነገር ያለህን ፍላጎት ብስለት ይሰጠዉ እና ነገሩን በእጅህ ስታስገባዉ በደንብ ታጣጥመዋለህ። የአንድን ሰዉ የችሎታ ጥልቀት በሚከተለዉ አላማ ልትረዳዉ ትችላለህ። ታላቅ ሰዉን ሊያረካ የሚችል ታላቅ ነገር ብቻ ነዉ። ታላቅ ነገሮች ደግሞ ታላቅነት ላላቸዉ የተገቡ ናቸዉበጣም ልቀዋል የሚባሉ ነገሮች የጎለበተ የመምረጥ ችሎታ ባለዉ ሰዉ አይን ብዙ ጉድለት ይገኝባቸዋል። እናም ላቅ ያሉ ነገሮች በጣም ጥቂት በመሆናቸዉ ነገሮችን ስታደንቅ ቁጥብ ሁን። የመምረጥ ችሎታ የሚገነባዉ ከሌሎች ጋር በምታደርገዉ መስተጋብር ነዉ። ብዙዉን ጊዜ በልምድም ልታገኘዉ ትችላለህ። ላቅ ያለ ምርጫ ካለዉ ሰዉ ጋር ብትወዳጅ እንደ እድለኛ ትቆጠራለህ። ሆኖም ግን ምንም ነገር የማያረካህ ብትሆን ነገሩ የሞኝነት ተግባር ነዉ፤ በተለይም የእርካታ እጦትህ ምንጩ በጣም ከጎለበተ ምናብ ይልቅ ልምሰል ባይነት ከሆነ። አንዳንዶች ከልክ ያለፈ የምናብ ቅንጦታቸዉን ለማርካት በማሰብ ብቻ ፈጣሪ ሌላ አለም እና ሌሎች ላቅ ያሉ ነገሮች እንዲፈጥርላቸዉ ይመኛሉ።

66. የነገሮች መጨረሻ ያማረ ይሆን ዘንድ ጥረት አድርግ። አንዳንዶች ጉዳይን አሳምሮ ከመጨረስ ይልቅ ጉዳዩን ለመጀመር በሚያስችላቸዉ መሰናዶ ላይ ይጨነቃሉ። እነዚህ ሰዎች ዉድቀት የሚያመጣዉን ዉርደት ይከናነባሉ። አሸናፊ እንዴት እንዳሸነፈ የመግለጽ ግዴታ የለበትም። የአብዛኛዉ ሰዉ ትኩረት ስኬት ወይም ውድቀት ላይ በመሆኑ፤ ጉዳይህን በስኬት ከፈጸምክ ዝናህን ማስጠበቅ ትችላለህ። የተከተልከዉ መንገድ ምንም የማያረካ ቢሆን እንኳ ስኬትን የተላበሰ ፍጻሜ ሁሉንም ነገሮች ወርቃማ ያደርጋቸዋል። አንዳንዴ መልካም አጨራረስን ለማምጣት አስበህ ህጎችን መጣስ ግድ ካለህ ህጎቹን ልትጥሳቸዉ ይገባል

67. የስዎችን ምስጋና በሚያስገኝ ሙያ ተሰማራ። ብዙ ነገሮች የሚወሰኑት ለሌሎች ሰዎች በሚያስገኙት የእርካታ መጠን ነዉ። አንዳንድ የህዝብን ትኩረት የሚስቡ ሙያወች ሲኖሩ ከነዚህ የበለጠ በጣም አስፈላጊ የሆኑ ግን ህዝብ የማያዉቃቸዉ ሌሎች ሙያወች አሉ። የህዝብን ትኩረት የሚስቡ ሙያዎች በሁሉም ዘንድ የታወቁ ስለሆኑ ዝናን ያገኛሉ። እነዚህ ትኩረትን የማያገኙት ስራዎች ግን ብርቅየ እና ከፍተኛ ክህሎትን የሚጠይቁ ቢሆኑም ሚስጥራዊ እና ለመረዳት አስቸጋሪ ስለሆኑ ህዝብ ታላቅነታቸዉን ቢረዳም ዝናን ግን አይቸራቸዉም። ከመሳፍንት ደግሞ ዝናን የሚያገኙት በጦር ሜዳ ድልን የተቀዳጁት ናቸዉ። እናም ታላቅ ሰዉ በህዝብ ዘንድ ታዋቂ የሆነን ሙያ ሊመርጥ ይገባዋል። ይህ ሁሉም እንዲያዩት እና እንዲተባበሩት ሲያደርግለት፤ የህዝቡ ድምጽ ደግሞ ዘላለማዊ ያደርገዋል።

68. ሰዎች እንዲገባቸዉ አድርግ። ሰወችን እዲረዱ ማድረግ እንዲያስታዉሱ ከማድረግ የበለጠ ነዉ። ይህ የሆነዉ ማስተዋል ከማስታወስ የበለጠ በመሆኑ ነዉ። አንዳንዴ ሰዎች እንዲያስታዉሱ ጥረት አድርግ ሌላ ጊዜ ደግሞ ነገርን ይረዱ ዘንድ ምከራቸዉ። አንዳንድ ሰዎች ልብ ስለማይሉ ብቻ ጉዳይን ለመፈጸም ምቹ ጊዜ አግኝተዉ እያለ እድሉን ያሳልፉታል። ለነዚህ ሰዎች ምክርህን ለግሳቸዉ። ከታላላቅ ስጦታዎች አንዱ ነገሮችን በፍጥነት መረዳት ነዉ። ይህ ችሎታ በሌለበት ብዙ ስኬቶች ይኮላሻሉ። ስለዚህ ብርሃን ያየዉ ሰዉ ብርሃን ላላዩት ብርሃንን ያሳይ። ብርሃንን ያላየ ደግሞ ብርሃንን ይፈልጋት። ይህ ሲሆን ብርሃን ያየዉ ሰዉ ብልህነትን ይከተል፤ ብርሃንን ያላየዉ ደግሞ ማስተዋልን ይከተል። ሰዎችን ስትመክር ጥቂት ምልክቶችን ካሳየህ በቂ ነዉ። በተለይ ይህን መርህ መከተል ያለብህ ጉዳዩ አንተንም የሚመለከት ከሆነ ነዉ። ምክርን ስትለግስ ግልጽ መሆን ያለብህ የአግቦ ንግግር በቂ ያልሆነ ጊዜ ብቻ ነዉ። ይህም ቢሆን ከልክ ማለፍ የለብህም።

69. የስሜትህ አሽከር እንዳትሆን። ታላቅ ሰዎች ለተለዋዋጭ ሀሳቦች አይንበረከኩም። የማስተዋል አንዱ ገጽታ ዉስጥን መረዳት መቻል ነዉ። ይህም ራስህን እና ባህሪህን እንድታዉቅ ያደርግህ እና የረጋ ባህሪን ያላብስሃል። ራስን ማረም የሚጀመረዉ ራስን ከማወቅ ነዉ። እነሆ ባህሪያቸዉን በትንሽ ነገር የሚለዋዉጡ ስድነት የተሰቀላቸዉ አዉሬ ግለሰቦች አሉ። እናም በዚህ ባህሪያቸዉ ምክንያት የሚፈጽሙት ነገር ሁሉ በራስ ተቃርኖ የተሞላ ነዉ። ይህ ባህሪያቸዉ ደግሞ የማድረግ ፍላጎታቸዉን ይደፈጥጠዉ እና የማመዛዘን ችሎታቸዉን ያሳጣቸዋል። ይህም ፍላጎታቸዉን እና የመረዳት ችሎታቸዉን ችግር ላይ ይጥለዋል።

70. እንቢታን እወቅበት። ሁሉንም ነገር ለሁሉም ሰዉ መስጠት አትችልም። በተለይ በአመራር ቦታ ላይ ላሉ ሰዎች የእንቢታ ጠቀሜታ የይሁንታን ያህል ነዉ። ሰዎች ልብ የሚሉት የመልስ አሰጣጥህን ነዉ። የአንዳንድ ሰዎች እንቢታ ከሌሎች ሰዎች እሽታ የበለጠ የተወደደ ነዉ። ይህ የሆነዉ ወርቃማ እንቢታ ደረቅ ከሆነች እሽታ የበለጠች በመሆኗ ነዉ። እንቢታ ከናፍራቸዉ ላይ የተለጠፈባቸዉ የሚመስሉ ነገርን የሚያበላሹ ግለሰቦች አሉ። እንዲህ አይነት ሰዎች ቶሎ እንቢ ማለት ይቀናቸዋል። በመጨረሻ እሽ ሊሉ ቢችሉም ሲጀመር ነገሩን ስላበላሹት በሰዎች ዘንድ ምስጋናን አያገኙም። ሰዎች ተቃዉሞህን ቀስበቀስ እንዲያላምጧት አድርግ እንጅ እንቢታህን ባንዴ መወርወር የለብህም። እንዲሁ ሰወች ያንተ ጥገኛ ይሆኑ ዘንድ ደግሞ አንድን ነገር ስትከለክል ፍጹማዊነትን እንዳትከተል ይሁን። የእንቢታህን መራራነት ማጣፈጫ ይሆን ዘንድ ተስፋን ስጥ። ነገሩ ከፍትፍቱ ፊቱ ስለሆነ እሽታን ስትነፍግ ትህትና ይኑርህ። እነሆ “እንቢ” እና “እሽ” ምንም አጭር ቃላት ቢሆኑ እንኳ በደንብ ማሰብ የሚጠይቁ ቃላት ናቸዉ።

ጎበዝ፣ በብልህነት መንገድ እንጓዝ፣ ብልሆችም እንሁን! :mrgreen:

Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ‘የብልህነት መንገድ’ - ምርጥ መጠሓፍ በምርጥ ተርጓሚ - ይዘቷን እንካችሁ አጣጥሙ!

Post by Meleket » 11 Apr 2019, 09:39

በኤርትራ ህዝብና በኢትዮጵያ ህዝብ የተቀናጀ ትግል፡ በዓለም አደባባይ “የታላቋ ትግራይ ሕልም” ጠንሳሾችና አራጋቢዎች እያዩና እየሰሙ ከነ ህይወታቸዉ በመቐለዉ አኽሱም ሆቴል የተቀበሩበትን 1ኛ ዓመት የድል በዓል በደማቅ ሁኔታ በማክበር ላይ እያለንም የሟቿ ሕውሓት ቀንደኛ አጋሮችንና አምባገነኖችን የሚያሳፍር የድል ዜና ከበስተ ሱዳን እየሰማን እንገኛለን። :lol: ለዛሬ፡ “ ‘ያይናችሁ ቀለም አላማረንም’ በሚል እኩይ የፖለቲካ ፈሊጥ ግፍ ለደረሰባቸዉ፣ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ለሚገኙ፡ ለፖለቲካ ፍጆታ ሲባል ብቻ ስማቸዉ ለሚነሳዉ፡ ምንም እንኳ ሰላም ከሰፈነ 1 ዓመት ቢቆጠርም እስከአሁን ድረስ ቅንጣት ታህል በኢትዮጵያ መንግስት ላልተካሱት ንጹሐን 70 ሺ ኤርትራዉያን” ክብርና በታሪክም ተመዝግቦ ለመጪዉ ትውልድ ይተላለፍ ዘንድ፡ የዛሬዎቹን 10 የብልህነት መንገዶች እዚህ እናጣጥማለን። :mrgreen:

71. በባህሪህ ሆነ በአስመሳይነትህ ምክንያት ተለዋዋጭ ወይም ወፈፌ እንዳትሆን። አስተዋይ ሰዉ በሚሰራቸዉ ነገሮች ሁሉ ባህሪዉ ተለዋዋጭ አይደለም፤ ይህም የጥበበኝነቱ መገለጫ ነዉ። ጠቢብ ሰዉ ፀባዩን ሲለዉጥ በምክንያት እና በማሰብ ነዉ። ወደ አስተዋይነት የመጣን እንደሆን አፍለኛነት በጣም መጥፎ ነገር ነዉ። አንዳንድ ሰዎች የሚለዋወጡት በየእለቱ ነዉ። የእንዲህ አይነት ሰዎች እድል ሆነ የማድረግ ፍላጎት በዚያዉ ልክ በየእለቱ እንደተቀያየረ ነዉ። ለነዚህ ሰዎች ትላንት ነጭ የነበረዉ ነገ ጥቁር ሲሆን፤ የትላንቱ እሽታቸዉ ደግሞ የነገ እንቢታ ነዉ። ታዲያ ይህ ተቀያያሪ ባህሪያቸዉ ሰዎችን ግራ ስለሚያጋባ በሰዉ ዘንድ ከበሬታን ያሳጣቸዋል።

72. ቆራጥ ሁን። ከሚንቀሳቀሱ ነገሮች ይልቅ የረጉ ነገሮች ስለሚገሙ ወስኖ በደንብ አለመፈጸም ካለመወሰን የተሻለ ነዉ። እንዲሁ በራሳቸዉ መወሰን ስለማይችሉ ከሌላ ሰዉ ግፊትን የሚሹ ሰዎች አሉ። እንቅፍቶችን መለየት ጉብዝና ቢሆንም፤ ችግሮቹን በዘዴ ማምለጥ መቻል የበለጠ ጉብዝና ነዉ። ሌሎች ደግሞ ላቅ ያለ የማመዛዘን ችሎታ እና ቆራጥነት ሲኖራቸዉ የፈለጉትን ከማድረግ የሚገታቸዉም አንዳች እንቅፋት የለም። እንዲህ አይነት ሰዎች ወደዚህ አለም የመጡት ለታላቅ ተግባር በመሆኑ ላቅ ያለዉ የማገናዘብ ችሎታቸዉ ስኬትን በቀላሉ ይቀዳጁ ዘንድ ይረዳቸዋል። ነገርንም የሚፈጽሙት በተናገሩበት ፍጥነት ልክ ነዉ። እድለኛ እንደሚሆኑም እርግጠኛ ስለሆኑ በራሳቸዉ ተማምነዉ ወደፊት ይገሰግሳሉ።

73. ማድበስበስን ቻል። ይህ አስተዋዮች ከችግር የሚያመልጡበት ብልሃት ነዉ። እነዚህ ሰዎች ለዛ ባላት ቀልድ ተጠቅመዉ ከከባድ አጣብቂኝ ዉስጥ ራሳቸዉን ማዉጣት ይችላሉ። ብርቱ ከሆነ ፍጥጫም በፈገግታ እና በግርማሞገስ ይወጣሉ። እናም ይህ ብልሃት የታላላቅ ሰወች የስልጣን መሰረት ነዉ። የመነጋገሪያ ርዕስን መቀየር ትህትና የተሞላበት እንቢታ ሲሆን፤ ያልገባህ መምሰል ደግሞ የበለጠ የትህትና ተግባር ነዉ

74. ሰዉ ሊቀርብህ የምትከብድ እንዳትሆን። በጣም አረመኔ የሆኑት አዉሬወች የሚገኙት ህዝብ በሚበዛበት ቦታ ነዉ። ሰዉ አላስጠጋ ባይነት ራሳቸዉን የማያዉቁ ሰዎች የእርኩሰት ተግባር ነዉ። ሌሎችን ማስቀየም የሰዎችን መልካምነት አያስገኝም። አስቡት እንዲህ አይነት አዉሬወች ስድነታቸዉን እና ሰዉ በላነታቸዉን ለማሳየት የተዘጋጁ ናቸዉ። ላልታደሉት የበታቾቻቸዉ እነዚህን ሰወች መቅረብ ከነብር ጋር ትግል የመግጠም ያህል በመሆኑ ብርቱ ትእግስት እና ፍርሃትን ይጠይቃቸዋል። እነዚህ አዉሬ የሆኑ ሰዎች ወደስልጣናችዉ ለመድረስ ሁሉንም አስደስተዋል፤ ስልጣኑን ከጨበጡት በኋላ ግን የድሮዉን ባህሪያቸዉን ለማካካስ ይመስል ሁሉንም ያስቀይማሉ። ስልጣናቸዉ ሁሉንም ሰዎች ያስተናግዱ ዘንድ ግድ ቢላቸዉም እብሪተኛነታቸዉ ይህን እንዲያደርጉ ያግዳቸዋል። እነዚህን ሰዎች የምንቀጣበት የጨዋ መንገድ መራቅ ነዉ። ይህ ደግሞ ራሳቸዉን ለማረም ያላችዉን እድል እና ደጋፊወቻቸዉን ያሳጣቸዋል።

75. ታላቅ ሰዎችን እንደ ምሳሌ ውሰድ። እነዚህን ሰዎች ለመምሰል ሳይሆን ለመብለጥ ጥረት አድርግ። እነሆ የታላቅነት ምሳሌወች እና የክብር መድብል የሆኑ ሰዎች አሉ። ስለዚህ እያንዳንዱ ሰዉ በሙያዉ ታላቅ የሆነዉን ሰዉ ይለይ እና እርሱን ከመከተል ይልቅ ለመብለጥ ጥረት ያድርግ። የሌላዉን ሰዉ ዝና እንደመስማት የመንፈስ ጉጉትን የሚጨምር ነገር የለም። ይህ ስሜት የቅናተኝነትን ስሜት ግብአተ መሬት ፈጽሞ መልካም መንፈስን ያነቃቃል።

76. ሁሌም አትቀልድ። አስተዋይነት የሚለየዉ በኮስታራነቱ ነዉ። ኮስታራነት ደግሞ ከወገኝነት ይልቅ ከበሬታን ያስገኛል። ሁሌ የሚቀልድ ሰዉ ከበሬታን ሊያገኝ አይችልም። የሚያወራዉ ነገርም በሰዉ ዘንድ የታመነ ስላልሆነ እንደ ዉሸታም ይቆጠራል። ይህ የሚሆነዉ አንድም በሰዉየዉ መጭበርበርን ሌላም አፌያዥነቱን ስለምንፈራ ነዉ። ወገኞች የማመዛዘን ችሎታቸዉን እንዳልሳቱ ማወቅ አንችልም፤ አብዛኛዉን ጊዜ ደግሞ የማመዛዘን ችሎታቸዉ ዝቅተኛ ነዉ። ሁሌ መቀለድን የመሰለ ተራ ተግባር የለም። አንዳንዶች በወገኝነታቸዉ ይታወቁ እና የአስተዋይነት ዝናቸዉን ያጣሉ። ሳቅ የራሱ ጊዜያት ቢኖሩትም የተቀረዉ ጊዜ ግን ለኮስታራነት የተገባ ነዉ

77. ከሁሉም ጋር መግባባት ቻል። ከምሁር ጋር ምሁር ከጻዲቅ ጋር ጻዲቅ መሆን መቻል ጠቢብነት ነዉ። ተመሳስሎ ማደር የሰዎችን የቅንነት ስሜት ስለሚቀሰቅስ መልካም ፈቃዳቸዉን ለማግኘት ይረዳል። የሰዎችን ባህሪ አስተዉል እና እነሱን ለመምሰል ሞክር። እናም የተጠጋህዉ ሰዉ ኮስታራ ሆነ ፍልቅልቅ የነገሮችን አዝማሚያ ተከትለህ ራስህን ቀይር። በተለይ እንዲህ አይነት ባህሪ በጣም አስፈላጊ የሚሆነዉ የሰዎች ጥገኛ ለሆነ ሰዉ ነዉ። ይህ ታላቅ ችሎታን የሚጠይቅ ስትራቴጂ በማስተዋል ዉሎ ለማደር ጠቃሚ ነዉ። ይህን ማድረግ ደግሞ ብዙ ነገር ላሳለፈ እና ለአዋቂ ከባድ አይደለም።

78. የአፈፃጸም ክህሎት ይኑርህ። ሁሉም ቂሎች በድፍረት የተሞሉ ስለሆኑ አንድን ነገር ለመፈጸም ሁሌም ችኩል ናቸዉ። ታዲያ ቂልነታቸዉ አደጋን ቀድሞ ለመለየት ስለማያስችላችዉ ከፊታቸዉ የሚጠብቃቸዉን ዉርደትም ልብ አይሉም። ጠቢብ ግን ጉዳዩን በጥንቃቄ ስለሚያከናዉን ያለምንም አደጋ ጉዳዩን እንዲፈጽም ይረዳዋል። አስተዋይነት ችኩልነትን ለውድቀት ብትፈርድበትም አንዳንዴ እድል ምህረቷን ታወርድለታለች። የያዝከዉ ጉዳይ ጥልቀቱ የሚያስፈራ ከሆነ እርጋታ ይኑርህ። ዘመኑ የሰዉ ቀረቤታ የከፋበት ስለሆነ የምታደርገዉ ነገር ሁሉ በማስተዋል የተሞላ ይሁን።

79. ደስተኛ ባህሪ። ባግባቡ ከተጠቀምክበት ደስተኛነት ድክመት ሳይሆን በረከት ነዉ። ቀልደኛነትም በጥቂቱ የሆነ እንደሆን ነገሮችን ያጣፍጣል። ታላላቅ ሰዎች አንዳንዴ ቀልደኛ ሊሆኑ ይችላሉ፤ ይህም ታዋቂነታቸዉን ይጨምርላቸዋል። እነዚህ ሰዎች ሁሌም አስተዋይነትን ስለሚከተሉ ከልካቸዉ አያልፉም። ሌሎች ሰዎች ደግሞ ቀልድን ከአደጋ ለማምለጥ ይጠቀማሉ። ምንም ሌሎች ሰዎች ቢያመሩባቸዉ እንኳ አንዳንድ ነገሮች እንደቀልድ መታየስ አለባቸዉ። ይህ ደግሞ እንደ ትሁት ስለሚያስቆጥርህ በሰዎች ዘንድ ተወዳጅነት ያተርፍልሃል።

80. መረጃን ስትሰበስብ በጥንቃቄ ይሁን። አብዛኛዉን የህይወታችን ዘመን የምናሳልፈዉ መረጃን እየሰበሰብን ነዉ። እንዲሁ በራሳችን የምናየዉ ነገር በጣም ጥቂት በመሆኑ ሌሎች የሚነግሩንን እያመንን እንንኖራለን። ጆሮ ለእዉነት የጓሮ በር ለቅጥፈት ደግሞ የፊት በር ነች። እዉነት ብዙዉን ጊዜ በአይን ቢታይም በጆሮ የሚሰማዉ ግን አልፎ አልፎ ነዉ። እዉነት ሳይቀየጥ የምትደርሰን በጣም አልፎ አልፎ ሲሆን፤ ይህ ደግሞ የባሰ የሚሆነዉ እዉነት ከሩቅ ቦታ የመጣች እንደሆን ነዉ። እዉነት ሁሌም የምትጓዘዉ በሰዎች ስሜት እየተቀየጠች ነዉ። ስሜታችን ደግሞ ያገኘዉን ነገር ሁሉ መጥፎ ወይም በጎ ገጽታን ያላብሰዋል። ስሜት በማንኛዉም መንገድ ትኩረትን ለማግኘት ትጣጣራለች። በተለይ ከሚነቅፍህ ይልቅ የሚያሞግስህን ሰዉ ተጠንቀቅ። ይህ አይነቱ ሰዉ ከማን ጋር እየተመሳጠረ እንደሆነ አጥና፤ አቅጣጫ እና አካሄዱንም በደንብ ለመረዳት ሞክር

ጎበዝ፣ በብልህነት መንገድ እንጓዝ፣ ብልሆችም እንሁን!
:mrgreen:

Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ‘የብልህነት መንገድ’ - ምርጥ መጠሓፍ በምርጥ ተርጓሚ - ይዘቷን እንካችሁ አጣጥሙ!

Post by Meleket » 12 Apr 2019, 10:46

ለዛሬ፡ ወንድማማች በሆኑት በኤርትራና በኢትዮጵያ ህዝቦች መካከል፡ በተደረጉት የተለያዩ ጦርነቶች፡ 'ፖለቲከኛ ነን' በሚሉ አንዳንድ ብልጣብልጦች ምክንያት የጦርነት ሰለባ ሆነዉ ህይወታቸዉን ላጡ (ለተሰዉ)ና የአካልና የመንፈስ ጉዳተኞች ለሆኑት የዋህ የአፍሪካ ቀንድ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ክብር እንዲሁም ለወላጆቻቸዉ ክብር የዛሬዎቹን 10 የብልህነት መንገዶች እዚህ እንጋራቸዋለን። የተሰዉ ወንድሞቻችንና እህቶቻችንን እየዘከርንም አፈንጋጯና ብልጣብልጥ ነኝ ብላ የምታስበዉ ህወሓት ላንዴና ለመጨረሻ ግዜ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ምህዋር እንደልቧ የምታሾርበት ግዜ በአስገራሚ ሁኔታ የተገባደደበትን 1ኛ ዓመት የድል በዓላችንን ኤርትራዉያንና ኢትዮጵያዉያን በደመቀ ሁኔታ ማክበራችንን እንቀጥላለን። :mrgreen:

81. አንፀባራቂነትህን ማደስ ተለማመድ። ይህ የፎኒክስ ልዩ ተሰጠኦ ነዉ። እንደ ዝና ሁሉ ታላቅ ችሎታም ያረጃል። አንድን ነገር ስንላመደዉ ስለነገሩ ያለን አድናቆት ይቀንሳል። እናም በጣም ያረጀን ታላቅ ሰዉ አልባሌ የሆነ አዲስ መጤ ሊበልጠዉ ይችላል። ስለዚህ በእዉቀትህ፣ በደስታህ፣ በድፍረትህ፣ እና በሌሎች ነገሮች እንደገና ተወለድ። አንጸባራቂነትህን እንደ ፀሀይ በተደጋጋሚ ለማደስ ሞክር። በሰወች እንድትናፈቅ ራስህን ቁጥብ አድርግ፣ ከዛም በአዲስ መልክ ቅረብ እና አስደስታቸዉ።

82. መልካምን ሆነ መጥፎን ነገር አተላ እስኪወጣዉ ድረስ አትጭመቀዉ። አንድ ብልህ ሰዉ የጠቢብነትን መንገድ በዝች ወርቃማ አባባል አስቀምጧታል። ትክክለኛነትን ሙጭጭ ብትልበት ስህተትን ይወልድልሃል። እንዲሁ ብርቱካንን እስከመጨረሻዉ ብትጨምቀዉ የሚወጣዉ መራራ ነዉ። ስትደሰትም ከልክ አትለፍ። መንፈሳችንንም ከልክ በላይ ያስጨነቅነዉ እንደሆን በድን ይሆናል። ላምንም ከልክ በላይ ብታልባት የሚወጣት ደም ነዉ

83. ይቅርታ ሊደረግለት የሚችል ስህተት ይኖርህ ዘንድ ተዘጋጅ፤ ምክንያቱም አንዳንዴ ድክመት ብርቱ የጉብዝና ምልክት ሊሆን ስለሚችል ነዉ። እነሆ ላቅ ማለት በቅናት አይን የተወገዘ ነገር ስለሆነ ምንም እንከን የማይወጣልህ ከሆንክ ለሰዎች የቅናት መንፈስ የተጋለጥክ ትሆናልህ። ቅናተኞች ላቅ ካሉ ነገሮች ሁሉ ራሳቸዉን ለማጽናናት ይረዳቸዉ ዘንድ እንከንህን እያነፈነፉ ይፈልጓታል። ስለዚህ ቀናተኞች እርር ድብን እንዳይሉ የማስተዋል ሳይሆን የሌላ ነገር ጉድለት እንዳለብህ ለማመልከት ሞክር። ይህ ከቀናተኞች ጥቃት ይጠብቅሃል።

84. በጠላቶችህ መጠቀምን እወቅበት። ነገሮችን በስለታቸዉ ብትይዛቸዉ ስለሚጎዱህ በእጀታቸዉ ያዛቸዉ እና መከላከያ ይሆኑሃል። ቂል ከጓደኞቹ ከሚያገኘዉ ጥቅም ይልቅ፣ ጠቢብ ከባላንጣወቹ ብዙ ይጠቀማል። አንዳንዴ በቅንነት የሚፈራ የችግር ተራራ በክፉ ሀሳብ ወደ ደልዳላ ሜዳነት ይቀየራል። ብዙ ሰዎች በጠላቶቻቸዉ ሀያልነት ጠቀሜታን አግኝተዋል። ሽንገላ የሸፋፈናቸዉን ድክመቶች ለማስተካከል ስለሚረዳ ነዉ። አስተዋይ ሰዉ የጥላቻን እውነትነት ስለሚረዳ ድክመቶቹን ለማስተካከል ጥላቻን እንደምስታወት ይጠቀማል። እንዲሁ ጥንቁቅነታችን የሚጎለብተዉ ባላንጣ ጎረቤት ያለን እንደሆን ነዉ

85. እንደ ጆከር ካርድ እንዳትሆን ተጠንቀቅ። እጅግ ላቅ ያሉ ነገሮች አግባብ ላልሆነ ጥቅም ለመዋል የተጋለጡ ናቸዉ። አንድ ነገር በሁሉም ዘንድ ተፈላጊነት ካለዉ በሁሉም ዘንድ መጠላትን ያስከትልበታል። ለምንም ነገር የሚጠቅም አለመሆን ከንቱነት ሲሆን፤ ለሁሉም ነገር ጠቃሚ መሆን ደግሞ የባሰ ከንቱነት ነዉ። አንዳንዶች በጣም ይፈለጉ እና በተፈለጉበት ልክ ይጠላሉ። እነዚህ በሁሉም ዘንድ የሚፈለጉ ካርዶች በብዙ ዘርፎች ይገኛሉ። እንዲህ አይነት ካርዶች በመጀመሪያ ልዩ በመሆናቸዉ ዝናን ቢያገኙም አመሻሹ ላይ ግን እርካሽ እየተባሉ ይወረፋሉ። እናም ለዚህ መድሀኒቱ ችሎታህን ስታሳይ ከልክ አለማለፍ ነዉ። በችሎታህ ከልክ በላይ የላቅክ ሁን፤ ሆኖም ግን በጣም እየተንቦገቦገ የሚበራዉ ሻማ በቶሎ ቀልጦ ስለሚያልቅ ችሎታህን ስታሳይ በመጠኑ ይሁን። በሰዎች ዘንድ ከበሬታን ማግኘት ብትሻ ተናፋቂ ሁን

86. አሉባልታን ተከላከል። መንጋዎች ብዙ አይኖች ለጥላቻ ብዙ ምላሶች ደግሞ ለስድብ ያላቸዉ ባለብዙ ጭንቅላት ጭራቆች ናቸዉ። አንዳንዴ አሉባልታ ታላቅ ዝና ያላቸዉን ሁሉ ስለሚያረክስ አንተ ላይ የተጣበቀብህ እንደሆነ ዝናህ ወደ ኣንጦሮጦስ ይወርዳል። መንጋዎች ብዙዉን ጊዜ ሙጭጭ የሚሉት ለማነብነብ ከሚያመቻቸዉ እንደ ታላቅ ድክመት ወይም አስቂኝ እንከን ላይ ነዉ። አንዳንዴ እነዚህን አሉባልታወች የሚፈጥሩብን ብልጣብልጥ የሆኑ ባላንጣዎች ናቸዉ። አንዳንድ መርዘኛ ምላሶች ደረቅ ዉሸት ከመትፋት ይልቅ በቀልድ ታላቅ ዝና ያለዉን ሰዉ ማዋረድ ይችሉበታል። መጥፎ ስም በቀላሉ ስለሚታመን እና ለማጥፋትም አስቸጋሪ በመሆኑ መጥፎ ዝናን ማትረፍ ቀላል ነዉ። እናም ታሞ ከመማቀቅ አስቀሞ መጠንቀቅ በመሆኑ አስተዋይ የሆነ ይህን የህዝብ ብልግና ይከላከል።

87. ጨዋ ሁን፤ የታረመ ጸባይም ይኑርህ። ሰዉ ሲወለድ አረመኔ ነዉ። ከአዉሬነት እንዲወጣ የሚያደርገዉ ጨዋነት ነዉ። ጨዋነት እዉነተኛ ሰዉ ስለሚያደርገን፤ ታላቅነታችን በጨዋነታችን መጠን ነዉ። ድንቁርና ሸካራ እና ባለጌ ነዉ። የእውቀትን ያህል ስብእናን የሚኮተኩት ነገር የለም። ሆኖም ግን ጠቢብነት በራሷ በደንብ ካልተገራች ሸካራ ትሆናለች። እናም በደንብ መገራት ያለበት ማስተዋል ብቻ ሳይሆን ፍላጎታችን እና ንግግራችን ጭምር ነዉ። አንዳንድ ሰዎች በተፈጥሮ ዉስጣቸዉ እና ውጫቸዉ፤ ሀሳባቸዉ ሆነ ንግግራቸዉ የጨዋ ነዉ። ሌሎች ደግሞ እጅግ ያልታረሙ ስለሆኑ የነኩትን ነገር ሁሉ፤ የራሳቸዉን መልካም ጎን ሳይቀር ቀፋፊ በሆነዉ አረመኔነታቸዉ ያረክሱታል

88. ከሰዎች ጋር የምታደርገዉ መስተጋብር ታላቅነትን የተሞላ ይሁን። ታላቅ ሰዉ በስራዉ ታናሽ ሊሆን አይገባም። በተለይ ርእሱ አስጠሊታ ከሆነ ንግግርህ ፀጉር ስንጠቃ መሆን የለበትም። ነገሮችን አስተዉል ግን ይህን ስታደርግ በግድየለሽነት መልክ መሆን አለበት። ከሰዉ ጋር የምታደርገዉን ንግግር ወደ መስቀለኛ ጥያቄ መለወጥ ተገቢ ስላልሆነ ነገርህ ትህትና ባለዉ እና ጠቅለል ባለ መልኩ ይሁን። ይህ ደግሞ የታላቅነት ተግባር ነዉ። የአስተዳዳሪነት ታላቅ መርህ ቢኖር ሆደ ሰፊ መሆን ነዉ። እናም በጓደኞችህ ሆነ በጠላቶችህ ዘንድ ስለሚከናወኑ ነገሮች ብዙዉን ጊዜ እንዳላየህ ሆነህ ማለፍ አለብህ። ከልክ በላይ ጥንቁቅ መሆን በጣም አናዳጅ ነዉ፤ በባህሪህ ጭምር እንዲሁ ከሆንክ ደግሞ በሌሎች ሰዎች ዘንድ ነገሩ በጣም አናዳጅ ነዉ። ባንድ ነገር ላይ ደግሞ ደጋግሞ መመላለስ ከአስጠሊታነቱ በላይ የእብደት ምልክትም ሊሆን ይችላል። የእያንዳንዱ ሰዉ ባህሪ ልቡንና የችሎታ ማንነቱን እንደሚገልጽ ተረዳ

89. ራስህን እወቅ፤ ጸባይህን፣ እዉቀትህን፣ የማመዛዘን ችሎታህን እና ስሜትህን እወቅ። ራስህን ካላወቅክ ራስህን ልትገዛ አትችልም። ለፊታችን መስታዉት ቢኖርም ለመንፈስ ግን መስታውቱ ጠቢብነት የታከለበት ከራስ ጋር መምከር ነዉ። ዉጫዊ ዉበትህን መዘንጋት ምንም ላያስከትል ቢችልም ውስጥህን ግን ሁሌም መንከባከብ እና ማረም እንዳለብህ አትዘንጋ። ነገሮችን በጠቢብነት ለመፈጸም ብትሻ የአስተዋይነትህን እና የችሎታህን ልኬታ ማወቅ አለብህ። እናም ላንድ ጉዳይ ያለህን አቅም በደንብ መዝን፤ ችሎታህን እና ያሉህን አቅርቦቶችም በደንብ ገምግም።

90. የረዥም እድሜ ሚስጥር ሕይወትን በመልካም ሁኔታ መምራት ነዉ። ሕይወትን ባጭሩ ከሚቀጯት ነገሮች ዉስጥ አንደኛዉ ደደብነት ሲሆን ሌላኛዉ ጋጠወጥነት ነዉ። አንዳንዶች ሕይወታቸዉን የሚያጧት እንዴት ማዳን እንዳለባቸዉ ስለማያዉቁ ሲሆን ሌሎች ደግሞ ማዳን ባለመፈለጋቸዉ ነዉ። ግብረገብነት መልካም ነገርን እንደምታስከትል ሁሉ መጥፎ ምግባር ደግሞ መጥፎ ነገርን ታመጣለች። እናም ሕይወቱን በመጥፎ ምግባር የሚመራት ሁሉ በፍጥነት ያሳጥራታል፤ ሕይወቱን በግብረገብነት የሚመራት ደግሞ ያስረዝማታል። ስለዚህ በመልካም ሁኔታ የምትመራ ህይወት ምሉእ እና ረዥም እድሜን ታወርሳለች።

ጎበዝ፣ በብልህነት መንገድ እንጓዝ፣ ብልሆችም እንሁን! :mrgreen:

Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ‘የብልህነት መንገድ’ - ምርጥ መጠሓፍ በምርጥ ተርጓሚ - ይዘቷን እንካችሁ አጣጥሙ!

Post by Meleket » 13 Apr 2019, 04:52

የዛሬዎቹን፡ አስር የብልህነት መንገዶችን በኤርትራና በኢትዮጵያ ምድር በግብረገብነት ኮትኩተዉ ላሳደጉን፡ ብልግናን፣ ስግብግብነትን፣ ለኔብቻ ይድላኝ ባይነትን፣ ጎጠኝነትን፣ ‘እኔ ምን ቸገረኝ’ ባይነትን፣ ግዴለሽነትን፣ ሌብነትን፣ ስድ አደግነትንና የመሳሰሉትን እኩይ ድርጊቶች ሁሉ እንድንጠየፍ አድርገዉ ላሳደጉን ጨዋ ወላጆቻችን ክብር ስናጣጥም :lol:አንደኛዉን አመት ‘ህወሓት’ ከአፍሪካ ቀንድ ፖለቲካ መድረኽ አዳልጧት የተዘረረችበትን :lol: ወደ ኢምንትነትም የተቀየረችበትንና የተደመሰሰችበትን፡ የህዝቦቻችንን የድል በዓል ‘ሞቅ ደመቅ ሸብረቅ ’ ባለ ሁኔታ እያከበርን ነዉ። “ሞቶ”ኛ የብልህነት መንገድ ላይ ስለደረስንም፣ “አጣጣሚዎች” እየተመላለሳችሁ ከለስ በማድረግ ታመነዥኩት ዘንድ ትንሽ ፋታ እንሰጣችኋለን! :mrgreen:

91. ጉዳይህን ልብህ እያመነታ እያለ አትፈፅም። የሚያመነታ ልብ ለሌሎች ሰዎች በተለይም ለባላንጣዎቹ የልብ ማመንታቱ ግልፅ ሆኖ ይታያቸዋል። መልካምነቱን እየተጠራጠርክ የምትፈፅመዉ ጉዳይ አደገኛ ነዉ። በእንዲህ አይነት አጋጣሚ ምንም አለማድረግ ይመረጣል። አስተዋይ በአንፀባራቂ ምክንያታዊነት እንጅ በይሆናል ጉዳዩን አይፈጽምም። ስንጀምር ልቦናችን የተጠራጠረዉ ጉዳይ እንዴት መጨረሻዉ ሊያምር ይችላል? እንኳን እንዲህ አይነቱ ነዉ እና አምነንበት በሙሉ ልባችን የምንፈጽመዉ ጉዳይም ተኮላሽቶ ይቀራል። ምክንያታዊነትህ አጠራጣሪ ነዉ፤ አመዛዛኝነትህ ደግሞ በጣም ፈጥኗል ካለዉ እርምጃ ምን ዉጤት ትጠብቃለህ?

92. በሁሉም አጋጣሚ እጅግ ጠቢብ ሁኑ እላችኋላሁ። ይህ በምታደርጉት እና በምትሰሩት ጉዳይ ላይ የመጀመሪያዉ እና ዋናዉ ህግ ነዉ፤ በተለይ ደግሞ ከፍ ባለ ስራ ላይ ላላችሁት። አንድ ግራም አስተዋይነት ከአንድ ኪሎ ብልጣብልጥነት የበለጠች ነች። ይህ የሚያካትተዉ ስድ የሆነ ጭብጨባን ከመሳብ ይልቅ እርግጠኛ ሆኖ መራመድን ነዉ። በአስተዋይነት ታዋቂ መሆን ታላቅ ድል ነዉ። ማለፊያ የሆነዉን ነገር የሚያዉቁትን ብልሆችን ካረካህ ደግሞ በቂ ነዉ።

93. ሁለገብ ሰዉ ሁን። እንዲህ አይነቱ ሰዉ በሁሉም ነገር ሙሉ በመሆኑ የብዙ ሰወች ድምር እንደሆነ ይቆጠራል። ይህ ሰዉ በዙሪያዉ ላሉት ሁሉ ደስታን በመፍጠር ሕይወትን ያጣፍጣታል። ሁሉን አቀፍ መሆን የሀሴት ሕይወትን ይፈጥራል። በሁሉም መልካም ነገሮች መደሰት መቻል ታላቅ ጥበብ ነዉ። ተፈጥሮ ሰዉን የፍጥረት አለም ተምሳሌት አድርጋ ስለፈጠረችዉ፤ ሥነ-ጥበብ ደግሞ ምርጫዉን እና አእምሮዉን በመግራት ሁሉን አቀፍ ልታደርገዉ ይገባል።

94. የችሎታህን መጠን እንዳይታወቅ አድርግበሌሎች ዘንድ መከበርን የሚሻ አስተዋይ ሰዉ ቢኖር የእዉቀቱን እና የችሎታዉን ልኬታ ማሳወቅ የለበትም። ሰዎች እንዲያዉቁህ ፍቀድላቸዉ እንዲረዱህ ግን አትፍቀድላቸዉ። ሰዎች ቅር ሊሰኙ ስለሚችሉ የችሎታህን መጠን መግለጥ የለብህም። የፈለገ ታላቅ ችሎታ ቢኖርህ እንኳ ከበሬታን የምታገኘዉ ችሎታህን ገልጸህ በማሳየት ሳይሆን ሰዎች የችሎታህን ልኬታ ማወቅ ተስኗቸዉ ሲቸገሩ ወይም ጥርጣሬ ዉስጥ ሲገቡ ነዉ።

95. ተስፋ ስጥ። ሰዎች የበለጠ እንዲጠብቁ እና ተስፋ እንዲኖራቸዉ አድርግ። ታላቅ ስራን እየሰራህ ሰዎች የበለጠ ታላቅ ስራን እንዲጠብቁ አድርጋቸዉ። ያለህን ነገር ሁሉ ባንዴ ገልጠህ አታሳይ። ጨዋታዉ ያለዉ ጥንካሬህን እና እዉቀትህን መጠን በመጠን እየተጠቀምክ ወደ ስኬት ማምራቱ ላይ ነዉ።

96. የማመዛዘን ችሎታ ይኑርህ። ማመዛዘን የምክንያታዊነት ዙፋን፤ የአስተዋይነት ደግሞ መሰረት ነች እናም በእርሷ ብርሃን ከተመራህ ስኬት ቀላል ነዉ። የሰማየሰማያት የመጀመሪያ እና ዋና ስጦታ በመሆኗ ማመዛዘን ታላቅ ችሎታ ነች። የማመዛዘን ችሎታ ልክ እንደጥሩር በመሆኑ ይህን ችሎታ ካጣን ሰወች እንደጎደሎ ይቆጥሩናል። እናም አናሳ የሆነ የማመዛዘን ችሎታ ቢኖርህ በጣም ብዙ ታጣለህ። ሁሉም የህይወት እርምጃወች በእርሷ ተጽኖ ስር ስለሆኑ የእርሷን መልካም ፍቃድ ይጠይቃሉ። የማመዛዘን ችሎታ በተፈጥሮዋ የምትጠጋ ለምክንያት ተገዥ እና ላቅ ያለ ብቃት ያላቸዉ ሰዎች ነዉ

97. ታዋቂነትን አግኝ እና ጠብቀህ አቆየዉ። ታዋቂነትን በብድር መልክ ከዝና ታገኘዋለህ። ታዋቂነት የሚወለደዉ ከታላቅነት በመሆኑ ተራ ነገር የበዛዉን ያህል እርሷ ደግሞ ብርቅየ ነች። ተራ ነገር በየቦታዉ ቢገኝም ታዋቂነት ግን የሚወለደዉ ከታላቅነት በመሆኑ ዉድ እና ብርቅየ ነዉ። ታዋቂነትን አንዴ ካገኘህ በኋላ ጠብቆ ማቆየት ቀላል ነዉ። ታዋቂነት ብዙ ነገርን ብትጠይቅህም እንኳ ብዙ ነገርን ትሰጥሀለች። ዘላቂ የምትሆነው ደግሞ በችሎታ ላይ የተመሰረተች እንደሆን ነዉ

98. አላማህን ደብቅ። ስሜታችን የመንፈሳችን በር ነዉ። ጠቢብነት ተግባራዊ መሆንን ይጠይቃል። ካርዱን እያሳየ ካርታ የሚጫወት ለሽንፈት የተጋለጠ ነዉ። የሰዎችን ትኩረት በጥንቃቄ እና በቁጥብነት ተጠጋዉ። ለአድናቆት ሆነ ለነቀፋ እንዳይመች ሀሳብህን ከሰዎች ሰዉረዉ።

99. ነገሩ እና ነገሩ በሰዎች አይን ሲታይ። ነገሮች የሚገመቱት በእነሱነታቸዉ ሳይሆን በሰዎች አይን በሚፈጥሩት ስሜት ነዉ። ብዙ ሰዎች በነገሮች ዉጫዊ ገጽታ ብቻ እርካታን ስለሚያገኙ ጠጋ ብለዉ ነገሮችን የሚመረምሩ በጣም ጥቂት ሰዎች ናቸዉ። ስለዚህ የስህተተኛ እና የክፋተኛ ስሜት ይዘህ ትክክለኛ መሆን ብቻ በራሱ በቂ አይደለም።

100. በተሳሳተ ሀሳብ እና በራስ ማታለል የተቀፈደድክ ሳይሆን ጠቢብ እና ግብረገብነት ያለህ ፈላስፍ ሁን። ግን ይህን ስታደርግ በአስመሳይነት እና በግብዝነት መሆን የለበትም። ምንም የጠቢብ ሙያ ብትሆን እንኳ ፍልስፍና ክብሯን አጥታለች። ሴኔካ ለሮም ቢያስተዋዉቃትም መሳብ የቻለችዉ ልሂቁን ክፍል ብቻ ነበር። እነሆ አሁንማ እንደ እርባና ቢስ እና ችግር ፈጣሪ እየተቆጠረች ነዉ። ስህተትን ነቅሶ ማውጣት የአስተዋይነት ምግባር ሲሆን ለግብረገቦች ደግሞ የደስታ ምንጭ ነዉ

ጎበዝ፣ በብልህነት መንገድ እንጓዝ፣ ብልሆችም እንሁን!
:mrgreen:

Masud
Member+
Posts: 8502
Joined: 18 Jun 2013, 09:06

Re: ‘የብልህነት መንገድ’ - ምርጥ መጠሓፍ በምርጥ ተርጓሚ - ይዘቷን እንካችሁ አጣጥሙ!

Post by Masud » 13 Apr 2019, 05:51

Meleket,
I would like to thank you one more time for taking time to share this ‘የብልህነት መንገድ’! From you today's post the expression which says " ካርዱን እያሳየ ካርታ የሚጫወት ለሽንፈት የተጋለጠ ነዉ። የሰዎችን ትኩረት በጥንቃቄ እና በቁጥብነት ተጠጋዉ። ለአድናቆት ሆነ ለነቀፋ እንዳይመች ሀሳብህን ከሰዎች ሰዉረዉ።" is very interesting!

In recognition of your generosity I invite you this Oromo music by Saad Awwal and Magartu Werqina. Wallo Oromo to whom this music belong are under attack once again by Neftegnas.

Degnet
Senior Member+
Posts: 25078
Joined: 16 Feb 2013, 11:48

Re: ‘የብልህነት መንገድ’ - ምርጥ መጠሓፍ በምርጥ ተርጓሚ - ይዘቷን እንካችሁ አጣጥሙ!

Post by Degnet » 13 Apr 2019, 06:03

Meleket wrote:
03 Apr 2019, 09:32
በዚህ ርእስ ስር፡ ባልታሳር ግራሽያን የጻፈውን፡ የሐረማያ ዩኒቨርስቲው አያሉ አክሊሉ የተረጎመዉን ድንቅ መጣህፍ ይዘት እናጣጥመዉ ዘንድ በዝግታ ማለትም በኤሊ አካሄድ እንጎማለልበታለን። እዚህ የምንጋራዉ ጽሑፍ መታሰቢያነቱ “የሔጉን ውሳኔ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ እተገብራለዉ” ብለው በይፋ በኢትዮጵያ ህዝብ ፓርላማ ውስጥም ሳይቀር ቃል የገቡትን የኦሕዴዱ ወጣት ጠቅላይ አብይ ወደ ስልጣን የተፈናጠጡበትን፡ እንዲሁም አፈንጋጯ ሕወሓት መቐለ የተወሸቀችበትን፣ የኤርትራና የኢትዮጵያ ህዝብም ሰላም በመስፈኑና የድንበሩ ብይን ትግባሬ ላይ ይውላል ብለው ሙሉ ተስፋ የጣሉበትንና ልባዊ ፈንጠዝያ ያደረጉበትን አንደኛ ዓመት የድል በአል እያከበርን ነው። :mrgreen:

የብልህነት መንገድ ይዘቷ በዚህ ፎረም ወይ መድረክ ተጠቃሚ ዜጎች በሙሉ፡ በተለይ ደግሞ አንዳንድ ስድነትን የምናስተጋባና ምላሳችን ሆነ ልባችን ያልተገረዘ ዋልጌዎችን የስነምግባር ትምህርት የምትሰጥ በመሆኗ፡ እግረመንገዳችንን ወደዝች ገጥ ጎራ ባልን ቁጥር ይህችን በምርጥ አማርኛ የተቀነባበረች ምርጥ ሃሳብን የምትዘራ መጽሐፍ ይዘት እንድትጋሩ በአፍሪካዊ ትህትና እጠይቃችኋለሁ!!! መጸሓፊቱን በመግዛትም ተርጓሚዉን ታበረታቱ ዘንድም በኤርትራዊ ወኔ ላሳስባችሁ እወዳለው። :lol:

የመጸሐፏን ደራሲ እስፓኛዊዉ ባልታሳር ግራሽያን (1601-1658 እኤኣ)፣ በድንቅ አማርኛ እጅግ ዉብ በሆነ አገላለጽ የተረጎማትን የሐረማያ ዩኒቨርስቲዉን አያሉ አክሊሉ እንዲሁም ይህን መድረኽ እዉን አድርጎ መልካም አስተሳሰቦች 20 እጥፍ፣ 60 እጥፍ፣ 100 እጥፍ፣ ፍሬ እንዲያፈሩ የተጋዉን ኤልያስ ክፍሌን ከልብ እያመሰገንን፡ ብቀጥታ የመጸሐፊቷን ይዘት ከዛሬ ጀምሮ አንድ ሁለት ሶስት እያልን እንቀጥላል። ለዛሬ ሶስቱን እንሆ! መልካም ማጣጣም ያድርግልዎ!!!

1. ሁሉም ነገር እጅግ ልቋል፤ እናም ምልኡ* ሰው መሆን ከሁሉም የበለጠ የልቀት ደረጃ ነዉ። ዛሬ አንድ ጠቢብን ለመፍጠር ጥንት በግሪክ ዘመን የነበሩ ሰባት ጠቢባንን ለመፍጠር የሚያስፈልገዉን ግብአት ይጠይቃል።

ምልኡ= ባልታሳር ግራሻን እንደሚያምነዉ ከሆነ ማንኛዉም ሰዉ እንደ እዉነተኛ ሰዉ አይቆጠርም። አንድ ሰዉ እዉነተኛ (ምልኡ) ሰዉ የሚሆነዉ ለሞራላዊ ልቀት ጥረት በማድረግ ነዉ።

2. ባህሪ እና እዉቀት። እነዚህ የተፈጥሮ ስጦታህን ደግፈዉ የያዙት ዋልታዎች ናቸዉ። አንደኛዉ በሌለበት ሌላኛዉ ግማሽ ስኬትን ብቻ ነው የሚፈጥርልህ። እናም እዉቀት ብቻዉን በቂ ስላልሆነ መልካም ባህሪም ሊጨመርበት ይገባል። ሞኝ ዉድቀቱን የሚያመጣት ባህሪዉ ሁኔታዉን፤ በሰዉ ዘንድ ያለዉን ተቀባይነት እና ጓደኞቹን ያገናዘበ ባለመሆኑ ነዉ።

3. ነገሮችን አንጠልጣይ አድርጋቸዉ። ላቅ ያሉ ስኬቶች አድናቆትን ያተርፋሉ። በጣም ግልጽ መሆን ጣፋጭም ጠቃሚም አይደለም። በተለይ የያዝከዉ ቦታ በጣም ተፈላጊ ከሆነ እራስህን ቶሎ ግልጽ አለማድረግ የሰወችን ትኩረት ይስብልሃል። ማንኛዉም ሰዉ ዉስጥህን እንዲያዉቅ አትፍቀድለት። ራስህን ስትገልጽ እንኳ ሙሉ በሙሉ መሆን የለበትም። እነሆ ብልህነት የምትገኘዉ ጥንቃቄን መሰረት ባደረገች ዝምታ ዉስጥ ነዉ። ሀሳቦች አንዴ ግልጽ ከተደረጉ በኋላ ከበሬታን አለማግኘት ብቻ ሳይሆን ለነቀፋም የተመቻቹ ናቸዉ። እነዚሁ ሀሳቦችህ ግባቸዉን ሳይመቱ የቀሩ እንደሆን ደግሞ እጥፍ ጊዜ እንደከሰርክ ይቆጠራል። የሰወችን ትኩረት የምትሻ ከሆነ መለኮታዊነትን ተከተል።

ወዳጄ “በብልህነት መንገድ ተጓዝ ብልህም ሁን፤ አንቺም እንዲሁ!”!!!
:mrgreen:
To the same [deleted] about the two shefatus,the best time in Ethiopian political history,the last 6 months before derg came to power

Degnet
Senior Member+
Posts: 25078
Joined: 16 Feb 2013, 11:48

Re: ‘የብልህነት መንገድ’ - ምርጥ መጠሓፍ በምርጥ ተርጓሚ - ይዘቷን እንካችሁ አጣጥሙ!

Post by Degnet » 13 Apr 2019, 06:07

Bezaeba Ahbay kab zseme’e kab nature tesfa zygeber

Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ‘የብልህነት መንገድ’ - ምርጥ መጠሓፍ በምርጥ ተርጓሚ - ይዘቷን እንካችሁ አጣጥሙ!

Post by Meleket » 15 Apr 2019, 08:21

የዛሬዎቹን አስር የብልህነት መንገዶች በኤርትራና በኢትዮጵያ ዉስጥ ትዉልድን በስነምግባርና በዕዉቀት ለማነጽ ሳያሰልሱ ለተጉት፣ በህይወት መንገድ የሚያጋጥሙንን አንዳንድ አልባሌ የእርጎ ዝንቦችን ንቀን እንድናልፍ ትእግስትን እንድንላበስ በመምከር ለጣሩልን የበሰሉ መምህራኖቻችን ክብር እንጋራለን :lol: ይህን ስናደርግም ሕወሓት ትግራይ ውስጥ አለሁ ለማለት እየተንፈራገጠችም ቢሆን የእንደርታ ወጣቶችን ለማሸማቀቅ በምትጣጣርበት ነገር ግን ከትልቁ የኢትዮጵያ ስልጣን ኮረቻ በመውደቅ መቀሌ ላይ የተንደባለለችበትን 1ኛ ዓመት የድል በዓል እያከበርን ነዉ! :mrgreen:

101. ሁሉም በቂላቂልነት ቀንበር ስር ቢሆኑም ግማሹ ኮልኮሌ በሌላዉ ግማሽ ይስቃል። ሁሉም ነገር መልካም ወይም መጥፎ ሊሆን ይችላል፤ ይህ ግን የሚወሰነዉ እንደ አመለካከትህ ነዉ። አንደኛዉ የሚፈልገዉን ሌላኛዉ ይጠየፈዋል። ሁሉንም ነገር በራሱ አስተያየት ብቻ የሚመዝን ሰዉ እጅግ ቀፋፊ የሆነ ቂል ነዉ። ይህ የሆነዉ ልቀት ማለት አንድን ሰዉ ብቻ ማስደሰት ብቻ ስላልሆነ እና ምርጫ በሰዎች ቁጥር ልክ ስለሆነ እና እንደ ሰዉ ፊት ልዩነትም የተለያየ ስለሆነ ነዉ። ስለዚህ አድናቂ የማይገኝለት ድክመት የለም፤ እናም ብዙ አድናቂዎች ስለሚኖሩት እና እነዚህን አድናቂዎችም መኮነን ስለሚሆንብህ አንድ ነገር የተወሰኑ ሰዎችን አላስደሰተም ብለህ ልትንቀዉ አይገባም። እንዲሁ አንድ ነገር አድናቂ ቢያገኝ እንኳ ሌሎች ሊነቅፉት ስለሚችሉ በከንቱ እንዳትደሰት። የአንድ ነገር መልካምነት ሊዳኝ የሚገባዉ በየዘርፉ ባሉ አዋቂወች አስተያየት ነዉ። ስለዚህ የአንድ አመለካከት፤ የአንድ ባህል፤ ወይም የአንድ ዘመን ቁርኝት እንዳያጠቃህ ይሁን።

102. መልካም እጣ ፈንታን ማጣጣም ትችል ዘንድ ሆደ ሰፊ ሁን። አስተዋዮች ሆደ ሰፊ መሆን አለባቸዉ። ታላቅ ጠቢብ የሚሰራዉ ከታላላቅ ነገሮች ነዉ። ለታላቅ ነገር የተገባ ሰዉ የመልካም እድል ቁንጣን አይዘዉም። ላንዱ የሚያስመልሰዉ ነገር ለሌሎች የምግብ ፍላጎት መክፈቻ ሊሆን ይችላል። አንዳንድ እንደ አህያ ከአልጋ ቢሉት ከመሬት የሆኑ ግለሰቦች አሉ፤ እንዲህ አይነት ሰዎች ለታላቅ ነገር ስላልተወለዱ ከታላቅ ነገር ጋር መላመድ አይችሉም። እነዚህ ሰዎች ያለችሎታቸዉ ከፍ ያለ ቦታ የተቀመጡ እንደሆን ድንግርግር ይላቸዉ እና ናላቸዉ ይዞራል። እናም ታላቅ የሆነ ሰዉ ልቡ ለብዙ መልካም ነገር ዝግጁ መሆኑን ያሳይ፤ የጠቢብነት ምልክቶችንም እየነቀሰ ያጥፋ።

103. እያንዳንዱ በራሱ መንገድ እንደ ንጉስ ይሁን። ሁሉም ሰዉ ንጉስ ባይሆንም ሁሉም በየመስኩ እና እንዳቅሙ ምግባሩ የንጉስ መሆን አለበት። ታላቅነት የሚለካዉ በምግባር ስለሆነ ንጉስ ሆነህ ባትወለድ እንኳ ምግባርህ የንጉስ ይሁን። ራስህ ታላቅ ከሆንክ ደግሞ በታላቅነት አትቀናም። በተለይ ከዘዉድ አቅራቢያ ያሉ ሰዎች ታላቅነትን ሊላበሱ ይገባቸዋል። እነዚህ ሰዎች ዘዉዳዊዉን የታላቅነት በረከት መካፈል እንጅ ስም ለጥፈዉ በከንቱ ሊወጣጠሩ አይገባም።

104. እያንዳንዱ ስራ ምን እንደሚጠይቅ ጠንቅቀህ እወቅ። ስራወች ሁሉ የተለያዩ ናቸዉ፤ ይህን ልዩነት ለመረዳት ደግሞ እዉቀት እና የማገናዘብ ችሎታን ይጠይቃል። አንዳንድ ሙያወች ደግነትን ሲጠይቁ ሌሎች ደግሞም ብልጠትን ይጠይቃሉ። በጣም ቀላል የሆኑት ስራወች ታማኝነትን የሚጠይቁት ናቸዉ። ለመጀመሪያዉ አይነት ስራ የሚያስፈልገዉ የጨዋነት ተሰጥኦ ሲሆን፤ ለሁለተኛዉ ግን ብዙ ልፋት እና የእንቅልፍ እጦት እንኳ በቂ ላይሆን ይችላል። ሰውን ማስተዳደር ታላቅ ስራን ይጠይቃል፤ በተለይ ደግሞ ቂሎችን እና እብዶችን። ምክንያቱም ጭንቅላት የሌላቸዉን ማስተዳደር ታላቅ ጭንቅላትን ግድ ስለሚል ነዉ። ተለዋዋጭነት የሌለዉ እና ሰራተኛዉን ቀኑን በሙሉ ጠምዶ የሚይዝ ስራ በጣም ከባድ ነዉ። የማይሰለቹት ስራወች ደግሞ ተለዋዋጭነት እና አስፈላጊነትን አጣምረዉ በመያዝ አእምሯችንን የሚያድሱት ናቸዉ። በጣም የተከበሩት ስራወች ሰወችን በመጠኑ ወይም በከፍተኛ ሁኔታ ጥገኛ የሚያደርጉት ናቸዉ። እጅግ ከባድ የሆኑት ስራወች ላባችንን ጠፍ እስክናደርግ መንፈሳችንን እና ስጋችንን የሚያለፉት ናቸዉ።

105. አትንዛዛ። ባንድ ጉዳይ ወይም ርዕስ ላይ ሙጭጭ አትበል። ነገርን አጠር ማድረግ አስደሳች ከመሆኑም በላይ ብዙ ለማከናወን ይረዳል። ነገርን ማሳጠር በርዝመት የምናጣዉን በግብረገብነት ያካክስልናል። መልካም ነገር አጠር ካለ የበለጠ መልካምነት አለዉ፤ መጥፎ ነገርም ቢሆን አጠር ካለ በጣም መጥፎ አይሆንም። የተመረጠ ነገር ከአሰስገሰስ የተሻለ ነዉ። የቁመተረዥም ብልህ በጣም ጥቂት እንደሆነ ሁሉም ሰዉ ያዉቃል፤ ሆኖም ግን ከንግግር መርዘም ይልቅ የቁመት መርዘም የተሻለ ነዉ። አንዳንድ ሰዎች ዉበት ከመሆን ይልቅ የዚህ አለም እንቅፋት ይሆኑ እና ሰዉ ሁሉ ሲያገላቸዉ ይኖራሉ። አስተዋይ የሆነ ሰወችን ማድነቅ የለበትም፤ በተለይ ደግሞ በስራ የተወጠሩትን ታላላቅ ሰዎች። እነሆ ከታላላቆች አንዱን ከመረበሽ ይልቅ የተቀረዉን አለም በሙሉ መረበሽ የተሻለ ነዉ። አጠር ብሎ የተነገረ ንግግር በደንብ እንደተነገረ ይቆጠራል።

106. የይስሙላ ሰዉ አትሁን። ከራስህ ይልቅ በያዝከዉ ስልጣን መኩራራት በጣም አስቀያሚ ነዉ። ራስህን እንደተፈላጊ ሰዉ አድርገህ ማየት አስጠሊታ ሲሆን፤ ይህን ተከትሎ ደግሞ ሰዎች ስለቀኑብህ ልትኩራራ አይገባም። የሰዎችን ከበሬታ ለማግኘት ከተጣጣርክ ሰዎች ከበሬታን ይነፍጉሃል። ከበሬታ ከመሬት ተነስተህ የምታገኛት ነገር አይደለችም፤ እርሷን ለማግኘት መጀመሪያ ከበሬታ የሚገባህ ሰዉ መሆን አለብህ ከዛም በርጋታ ልትጠጋት ይገባል። አንዳንድ ታላላቅ ስልጣኖች ታላቅ ችሎታን ይጠይቃሉ፤ እነዚህ ቦታወች ያለ ታላቅ ችሎታ በመልካም ሁኔታ ሊተዳደሩ አይችሉም። እነዚህ ስራወች የሚጠይቁትን ግዳጅ በአግባቡ ትወጣ ዘንድ ደግሞ ተገቢዉን ክብር ልትቸራቸዉ ይገባል። ሁሌም ስራህ ከሚጠይቀዉ በላይ አትድከም። በጣም ብርቱ ሰራተኛ መስለዉ ለመታየት ጥረት የሚያደርጉት በሰዎች ዘንድ ለስራዉ እንደማይመጥኑ ተደርገዉ ይቆጠራሉ። በስራህ ስኬትን ማግኘት ከፈለክ በችሎታህ እንጅ ታጥቦ በመቅረብ መሆን የለበትም። ንጉስ እንኳ መከበር ያለበት ባለዉ የባህሪ ማንነት እንጅ በእጣ ፋንታዉ እና በስልጣኑ በመቆነን መሆን የለበትም።

107. በራስህ የረካህ አትምሰል። ፈሪነት ስለሆነ ሕይወትህን ቅር እየተሰኘህ አትምራት። በራስ መርካትም ደግሞ ደደብነት ስለሆነ በራስህ ልትረካ አይገባም። ብዙዉን ጊዜ በራስ መርካት የሚመጣዉ ከድንቁርና ሲሆን፤ ይህም ሰዉየዉን ወደ ቂላቂል ደስተኝነት ያመራዉ እና በሰዎች ዘንድ ከበሬታን ያሳጣዋል። እንዲህ አይነቱ ሰዉ የሌሎችን ታላቅነት መረዳት ስለማይችል በራሱ ስድ አልባሌነት ይደሰታል። ጥንቁቅነት ሁሌም ጠቃሚ ነዉ፤ አንድ ነገር ጉዳይ እንዲሳካልን ስለሚረዳን ሲሆን ሌላ ነገር ደግሞ ነገሮች የተበላሹብን እንደሆን ስለሚያጽናናን ነዉ። ቀድመህ የፈራኸዉ ችግር ከሆነ የፈለገዉን ያህል ከባድ ቢሆን ብዙም አያስገርምህም። ነገሮች እንደሁኔታዉ ይወሰናሉ። አንዳንዴ ይሳካሉ፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ ይከሽፋሉ። በዚህ ሁሉ መሀከል ግን በባዶነት የተሞላችዉ የጅላጅል የደስታ ምንጭ ታብብ እና ባዶ ዘሯን ትበትናለች።

108. ታላቅ ሰዉ ለመሆን አቋራጭ መንገድ ዙሪያህን በተገቢ ሰዎች መከበብ ነዉ። በዙሪያህ ያሉት ጓደኞችህ በብዙ ነገር ሊጠቅሙህ ይችላሉ። ለምሳሌ ወግ እና ስነስርአትን ያስተምሩሃል፤ ይህ ብቻ ሳይሆን እዉቀት እንኳ ሳይታወቀን የምንወርስ ከነዚህ ሰዎች ነዉ። እንዲሁ ብዙ ልፋት ሳያስፈልግህ ራስህን ለማሻሻል ስትፈልግ አንተ የሌለህን ባህሪ ከሌሎች ለመዉረስ ሞክር። ለምሳሌ አንተ ችኩል ከሆንክ ረጋ ያለዉን መቅረብ ሁለቱን ያማከለ ባህሪ እንዲኖርህ ይረዳሃል። ከሌሎች ጋር ተስማምቶ መኖር ታላቅ ችሎታን ይጠይቃል። ከላይ እንደተጠቀሰዉ የተለያዩ ነገሮች መፈራረቅ አለምን ዉበት ያላት እና ዘላቂ ያደርጋታል። የነገሮች መፈራረቅ ተፈጥሮ ላይ መልካም ዉጤትን ካመጣ በሰዎች ባህሪ ላይ ደግሞ የበለጠ ዉህደትን ይፈጥራል። ስለዚህ አገልጋዮችህን ሆነ ጓደኞችህን ስትመርጥ ይህን መርህ ተከተል። ተቃርኖ ያላቸዉን ነገሮች ስናገናኛቸዉ ስብስቦቹን ያማከለ ወርቃማ ዉህድ እንፈጥራለን።

109. ሰዎችን አትወርፍ። በስሜታዊነት ሳይሆን በተፈጥሯቸዉ ሁሉንም ነገር እንደወንጀል የሚቆጥሩ አንዳንድ ሰዎች አሉ። እንደዚህ አይነት ሰዎች ሁሉንም ይወነጅላሉ፤ አንዳንዶችን የሚወነጅሏቸዉ መጥሮ ነገር አደረጉ እያሉ ሲሆን ሌሎችን ደግሞ ገና መጥፎ ነገር ያደርጋሉ እያሉ ነዉ። እንዲህ አይነት ሰዎች እጅግ መጥፎ ተፈጥሮ ያላቸዉ እና ጨካኝ መንፈስ የተጠናወታቸዉ ናቸዉ። ነቀፋቸዉ ደግሞ እጅግ የተጋነነ ከመሆኑም በላይ ሰዎቹ እጅግ በክፋት የተካኑ ስለሆኑ ገነትን ወደ ሲዖል መቀየር ይቻላቸዋል። የስሜት ዥዋዥዌ ዉስጥ የገቡ ጊዜ ሁሉንም ነገር እስከመጨረሻዉ ዳር ያደርሱታል። መልካም ባህሪ ያላቸዉ ሰዎች ግን ለሁሉም ነገር ይቅርታ ማድረግ ይችላሉ። እናም በዚህ ባህሪያቸዉ ምክንያት ሌሎች አንድን ነገር ሲፈፅሙ ቢሳሳቱ ሳያስቡት ተሳሳቱ እንጅ ክፋት አስበዉ ተሳሳቱ አይሉም።

110. የምትጠልቅ ፀሀይ እስክትመስል አትጠብቅ። የጠቢቦች መርህ በሌሎች ከመተዋቸዉ በፊት ቀድሞ መተዉ ነዉ። አንድን ነገር ስታቋርጠዉ ማቋረጥህን ራሱ ድል ልታስመስለዉ ይገባል። ፀሀይ እንኳ አንዳንዴ በጣም እያንጸባረቀች እያለች መጥለቋ እንዳይታወቅባት በደመና ትሸፈን እና ፀሀይዋ አለች ወይስ ጠልቃ ይሆን እያልን እንድናስብ ታደርገናለች። በመጥፎ እጣ ፈንታ መጥለቅለቕን ማምለጥ ከፈለክ የምትጠልቅ ፀሀይ የመሆንን አደጋ አስወግድ። ሰዎች ጀርባቸዉን እኪሰጡህ ድረስ እንዳትጠብቅ፤ ይህ ከሆነ ሰወች ይንቁህ እና ከነነፍስህ ይቀብሩሃል። አንዳንዴ አስተዋይ ሰዉ በፈረስ ውድድር ሜዳ ላይ ወድቆ መሳቂያ ከመሆኑ በፊት ፈረሱ ለዉድድር በቂ አለመሆኑን ተረድቶ ፈረሱ ጋጡ ውስጥ እንዲቆይ ያደርጋል። እንዲሁ ቆንጆም ጊዜዉ ሳይመሻሽባት መስታወቷን ትስበር፤ በጣም የዘገየች እንደሆን ግን የሚከተለዉን እዉነታ መቋቋም ይከብዳታል።

ጎበዝ፣ በብልህነት መንገድ እንጓዝ፣ ብልሆችም እንሁን! :mrgreen:

Post Reply