Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Tintagu wolloye
Member
Posts: 1474
Joined: 02 Sep 2016, 16:59

የአራዳ ልጆች ወግ።አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተከትሎ የተጣለበትን ብሄራዊ አደራ ለመወጣት ኮማንድ ፖስቱ ያሳለፈው ታሪካዊ ውሳኔ! (ትንታጉ ዘወሎ)

Post by Tintagu wolloye » 28 Feb 2018, 15:16የሚኒስትሮች ምክር ቤት፣የብሄራዊ ፀጥታው አካላትና አግባብ ያላቸው ጓዶች ተሰብስበዋል።

ሊቀ መንበሩ ሲራጅ ፈርጌሳ "ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ውጤት ጋር በተያያዘ ሁለት መሰረታዊ የህዝብ ፍጆታዎች መሟላታቸውን ማረጋገጥ አለብን።አንደኛው የሬሳ ሳጥኖችን ከትግራይ በስተቀር በአሉ ክልሎች በገፍ የማቅረቡ ጉዳይ ሲሆን ሁለተኛው እንደባለፈው በእየጦር ካምፑ በገፍ ለሚታሰሩ ፀረሰላሞች ቀለብ ማቅረብ ጉዳይ ነው።"

ጌታቸው አሰፋ " የገራፊወች፣ይቅርታ የአስተማሪወች የውሎ አበልም እንዳይረሳ እዚሁ ላይ ይካተት።"

ሳሞራ " በበኩሌ ሜቴክ ሳጥኖቹን በአጭር ጊዜ ለማቅረብ የሚያስችል የኢንዱስትሪ አቅም አለውና በሜቴክ ስር ይሁን።"

ስብሀት " አየ ድንቁርና! መቸው አንተና ድንቁርና ተመቻችታችኋል!"

ሳሞራ "ምነው አቦይ አጠፋሁ?"

ስብሀት" ኧረ አብርተሀል! አእምሮው የሚያዘግም ያንተ አይነት ካልሆነ በቀር ገዳዩ ወታደር፣የቀብር ቁሳቁስም አቅራቢ ወታደር ይሁን አይልም!"

ሲራጅ " እንደ መከላከያ ሚኒስቴር ተወካይ የሳሞራን ሀሳብ እደግፋለሁ።"

ስብሀት " ‘የአይጥ ምስክሯ ድምቢጥ!!‘ አሉ። ያ ሀይለማሪያም እሚባል ነጉላ ተገላግሎ አንተ ቀርተህ የለ በል በቆማጣህ ፈትፍት! ደሞስ ሰናወራ መስማት እንጅ ምን ጥልቅ አድርጎህ ሀሳብ ሰጭ ሆንክ?!በጠረጴዛው አናት በኩል ስትቀመጥ አገር የገዛህ መሰለህ?! ቀንህን ጠብቅ!ትናንት ለደህዴን ስትታጭ አይሆንም፣ ሌላ ፈልጉ የማለቴን ትክክልነት አሁን ነው ያወቅሁት! ለመሆኑ ገዳይና የቀብር ቁሳቁስ አቅራቢ አንድ ሚኒስቴር ሲሆን ‘ከሳጥን ሽያጭ የሚገኘውን ገቢ ለመጨመር ብሎ በርከት አድርጎ ጨፈጨፈ‘ አያስብልም? እኛ ፖለቲከኞቹስ እንዴት አድርገን ይህን የተመለከተ የአምነስቲና የምድረ ወዲ ሰበይቲ ትችት ምላሽ እንሰጣለን? ያለውን ሟቹን ሁሉ ገጭ በማስመሰል የፀጥታ ሀይሎች ጋር ተጋጩ፣ግጭቱ የተመጣጠ ነው ምንምን ስንል ከርመናል። ይህንን ገቢ ተኮር ጭፍጨፋ እንዴት እንግለፀው? ሳሞራ ምን ተግዱ ይገድላል እንጅ ለፈረንጅ መልስ ስጥ አይባል! እድሜ ለድንቁርናዉ!!"

ሳሞራ " ግደሉ ሳትሉ ሁሌስ አንገድል?መቸም በእኔ ላይ ሲሆን
የማይገን የለም እንጅ ለመግደልስ ቢሆን ጌታቸ ——"

ስብሀት " ኧረ አንድ በሉኝ ይኸን ነጉላ! ትሰሙታላችሁ?——"

ደብረፅዮን " አስታራቂ ሀሳብ አለኝ።ኤፈርት የሬሳ ሳጥን ምርቱንም ሆነ ዶማና አካፋ፣ድንኳን፣ለእድር የሚሆን የፕላስቲክ ኩባያና ሳህን ማምረቻ ትግራይ ውስጥ ለመክፈትና ለትግራይ ወጣቶች የስራ እድል ለመክፈት የገንዘብ አቅሙ አለው።ስለዚህ ኢፈርት ስራውን በሞኖፖል ይዞ ቢሰራው ወታደሩ በመግደሉ የሚመጣበት ቀጥተኛ ወቀሳ አይኖርም።አቦይ እንዳለው ገዳዩም፣ ከግድያው ገቢ የሚያገኘውም አንድ ተቋም ሲሆን ያስጠረጥራል!"

ስብሀት "ይሄ ነው ጭንቅላት!!የተማረ ይግደለኝ!!"

ጌታቸው " ኧረ ጠላትህ አቦይ ኩለና!! ሙሁር ተብየው መስሎኝ እያክቸለቸለ መሬቲቱን ሲኦል ያደረገብን! ለምን አንተን ይግደልብን? ከአንድ ብሶ!ያለውን ዳውን ዳውን እያለ ህፃኑ ሳይቀር የአፍ መፍቻው አድርጎናል።ይህ አንሶ——"

ስብሀት " በቃ!በቃ!የአወራሁት ስለጭንቅላት ነው።አንተ ጆሮ እንጅ ጭንቅላት ስላልሆንክ ከዚህ ከባለ ቦቴ፣ከባለ ከስክሱ አትሻልም። ምሁር ተብየው፣ እዚህም ሆነ ዲያስፖራ ያለውን ——"

በረከት ስምኦን" ——— የኒዮሊበራሊዝምና የጥገኛ አስተሳሰብ አቀንቃኝ ብለነዋል!!የአብዮታዊ ዲሞክራሲ አንጡራ ጠላት!"

ስብሀት "ተመልከት! መለስ ሞተ ብለን እናዝናለን?አናዝንም! እሱ ቢሞት ምላሱ አለ፣ማለቴ አንደበቱ! የተለየ ሀሳብ ያለው ባለመኖሩ ወደ ድምፅ መስጠት እናልፋለን!"

ደብረፅዮን "በገፍ ለሚታሰሩት መኖ የማቅረቡ ጉዳይ ሀላፊነቱ ለኤፈርት——"

ስብሀት " ሁሉም ለኢፈርት! ሁሉም በኢፈርት! ግን እህል ከሌሎች ክልሎች እንጅ ትግራይ አይገኝምና ልክ ለሬሳ ሳጥን ከጅማ መጫን እንዳለበት እንጨት እህሉም እየተሸመተ ይጓጓዝ።ተቃውሞ ያለው አለ?"

ሳሞራ ፈጥኖ እጁ ላይ ይቀመጣል።ያን ያየው ሲራጅ የሚፅፍበትን እስክርቢቶ አሽቀንጥሮ እንደ ሳሞራ አደረገ።

ስብሀት "እሽ! የምትደግፉ እጃችሁን አውጡ!"

ሳሞራ የተቀመጠባቸውን ሁለቱንም እጆቹን ከተቀመጠበት ቦትርፎ ያወጣል።በረከትና ሲራጅ አከታትለው ሲያወጡ ሁሉም በጎኑ አድርጎ ረስቶት የነበረውንና ያላወጣውን እጁን መዘረጠ!

ስብሀት " ጥሩ! እኔ ቀኝ ትክሻየን ስላመመኝ አንድ እጀን አውጥቻለሁ። ‘በ 99.9 % ተደግፏል‘ ብለህ ፃፈው! ማነህ አንተ!አቶ ሲጃራ! አዎ አንተ ማነው ስምህ! ደቡብ!!።!"
Last edited by Tintagu wolloye on 02 Mar 2018, 19:13, edited 4 times in total.

Tintagu wolloye
Member
Posts: 1474
Joined: 02 Sep 2016, 16:59

Re: የአራዳ ልጆች ወግ።አስቸኳይ ጊዜ አዋጁና የኮማንድ ፖስቱ ጭነቀት።የእሬሳ ሳጥን ምርትና ሽያጭን ለማፋጠን እንዲቻል በማን ሞኖፖል ስር ይሁን?ምረቱስ በየትኛው ክልል ይከናወን?(ትንታጉ ዘወሎ)

Post by Tintagu wolloye » 28 Feb 2018, 17:48

በሞታችን ለማትረፍ ሲነሱ በመኖር እንበቀላቸዋለን!! ላለመገደል መታገል፣ላለመሞት መስዋእትነት ከፍሎ እንደነጎቤው ህያው መሆን!!!

Tintagu wolloye
Member
Posts: 1474
Joined: 02 Sep 2016, 16:59

Re: የአራዳ ልጆች ወግ።አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተከትሎ የተጣለበትን ብሄራዊ አደራ ለመወጣት የሬሳ ሳጥን ምርትና አቅርቦትን ለማሻሻል ኮማንድ ፖስቱ ያሳለፈው ታሪካዊ ውሳኔ! (ትንታጉ ዘወሎ)

Post by Tintagu wolloye » 01 Mar 2018, 05:40

ስብሀት " ጥሩ! እኔ ቀኝ ትክሻየን ስላመመኝ አንድ እጀን አውጥቻለሁ። ‘በ 99.9 % ተደግፏል‘ ብለህ ፃፈው! ማነህ አንተ!አቶ ሲጃራ! አዎ አንተ ማነው ስምህ! ደቡብ!!።!

Tintagu wolloye
Member
Posts: 1474
Joined: 02 Sep 2016, 16:59

Re: የአራዳ ልጆች ወግ።አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተከትሎ የተጣለበትን ብሄራዊ አደራ ለመወጣት ኮማንድ ፖስቱ ያሳለፈው ታሪካዊ ውሳኔ! (ትንታጉ ዘወሎ)

Post by Tintagu wolloye » 02 Mar 2018, 19:14

ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ውጤት ጋር በተያያዘ ሁለት መሰረታዊ የህዝብ ፍጆታዎች መሟላታቸውን ማረጋገጥ አለብን።አንደኛው የሬሳ ሳጥኖችን ከትግራይ በስተቀር በአሉ ክልሎች በገፍ የማቅረቡ ጉዳይ ሲሆን ሁለተኛው እንደባለፈው በእየጦር ካምፑ በገፍ ለሚታሰሩ ፀረሰላሞች ቀለብ ማቅረብ ጉዳይ ነው።"

Tintagu wolloye
Member
Posts: 1474
Joined: 02 Sep 2016, 16:59

Re: የአራዳ ልጆች ወግ።አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተከትሎ የተጣለበትን ብሄራዊ አደራ ለመወጣት ኮማንድ ፖስቱ ያሳለፈው ታሪካዊ ውሳኔ! (ትንታጉ ዘወሎ)

Post by Tintagu wolloye » 03 Mar 2018, 15:17

የአዋጁን አላማ ሸተግባር እያየን ነው! ሞት ዘርቶ የሚያጭደው ህወሀት መቀመቅ እንዲወርድ የማድረጉ የመጨረሻ ፍልሚያ እነሆ በትግሉ የልደት ከተማ በአምቦ ተጀምሯል!!! ተነስ!


Post Reply