Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Tintagu wolloye
Member
Posts: 1474
Joined: 02 Sep 2016, 16:59

ሕዝብ አንቅሮ የተፋው ህወሓት ሲጨልምበትና መውደቂያው ሲደርስ የሶማሌ ክልልንና ጭካኔ፣ጠባብ ብሔርተኝነትና ጥላቻ አጥብቶ ያሳደገውን የበኩር ልጁን አብድሌን የሙጥኝ ያለባቸው ምክንያቶች (ትንታጉ ዘወሎ)።

Post by Tintagu wolloye » 22 Dec 2017, 07:42

ህወሓት ህዝብና ሃገርን በመክዳቱ፣የሚያደርሰው ግድያና እስር፣ጭቆናና ዝርፊያ ሞልቶ በመፍሰሱ ሲጠላና ሲወገዝ ኖሯል።ውግዘትና የእርምት ትችት አልበግር ያለው ህወሓት በሕዝብ ተተፍቶ፣የመሰረተው ዘረኛና ኢ-ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ተመንቅሎ ሊወድቅ በቅዋፍ ላይ ነው።ታዲያ ዛሬም እንደልማዱ እኩሉን የእሱ ጠላት ሌላውን የእሱ ወዳጅ አድርጎ ለማሳየትና በዚህም የተለመደ ህዝብን ከህዝብ የማቃቃርና የማጋጨት ተግባሩን ሊገፋበት ተንሰስቷል።ኦሆዲድና ብአዴን በሕዝብ ተገድደው ሌላ የፖለቲካ አቅጣጫ ይዘዋል በሚል ህዝብን በመበቀል የረዳውን የሶማሌ ክልል ሹመኛውንና ልዩ ኃይሉን በመሳሪያነት ለመጠቀም መርጧል።

ይህ ያለምክንያት አይደለም።አንደኛው ምክንያት የመከፋፈል ማጋጨት አባዜው ተቀጥያ ነው።ጎሳን ከጎሳ፣ብሄርን ከብሄር ሲያጋጭ ወያኔ ዛሬ የመጀመሪያው አይደለም። 26 ዓመት በስልጣን ያቆየ ዋስትናው እሱ ነበር፣ሆኖ መቀጠሉ ግን ማጠራጠሩ ሲበዛ ነው።ሁለተኛው ምክንያት የህወሓት ጀነራሎች የኮንትሮባንድ ንግድ ገቢ መውጫና መግቢያ፣መምሪያና ማሽከርከሪያ መዘውሩ ያ ክልል ነው።ሶስተኛው ምክንያት ለአሜርካኖቹ የሚሸጠውን ወታደራዊ ግልጋሎት (ሽብርተኞችን እዋጋለሁ በሚል) የሚያከናውነው በእዚህ ክልል አልፎ ነውና ከኮንትሮባንድ ንግዱ በላይና ባሻገር ለህልውናው ይህን ክልል ይፈልገዋል።እናም ህወሓት ለኢትዮጵያ ሶማለውጭ አዝኖ ሳይሆን የህልውናው መሰረት ያን ክልል በመቆጣጠር የተመሰረታ ጭምር በመሆኑ ነው።ህወሓት በአብድላና በልዩ ኃይሉ በኩል በሶማሌ ወገኖቻችን ላይ የፈጸመውን ግፍና ጭፍጨፋ ዓለም ያወቀውና በዓለም አቀፍ ደረጃ የተመዘገበ በመሆኑ የዛሬው የአዞ እምባ ከምንም አያድነውም። ሀውዜን ላይ የተጫወተውን ድራማ ሐረርጌ ላይ መድገሙ ያስወግዘዋል እንጂ አያስመሰግነውም።

ኦብነግን ደግፋችሁ በሚል መንደር ሙሉ ሰው ሲፈጅ ድምጻቸው ያልተሰማው የህወሓት ኩብኩባወች ሳይቀሩ ከወደ አሜሪካ ያሰሙትን ማላዘን ሰምተነዋል።ህዝቡ የሚያውቀው እውነታ በማንም ማላዘን አይቀየርም።ህወሓት ድራማውን እንዴት እንደደረሰና እንደተጫወተው እናውቃለን። መጀመሪያ ኦሮሞ ወገኖቻችንን በሶማሌ ልዩ ኃይል ስም ፈጀ፣አፈናቀለ።በዚህ ንዴትና ቁጭት እንደሚፈጠር ሳያውቅ ይህን አላደረገም።የተፈናቀሉት እንዳይመለሱ መደረጉም የቦካው ኩፍ እንዲል፣ነገሩ እንዲብላላና የኦሮሞውም ሆነ ሌላው ኢትዮጵያዊ የንደትና ቁጭት ቴርሞሜትር ከፍተኛውን ሙቀት እስክያስመዘግብ ድረስ ነው። ህወሓት በአንድ በኩል ግድያውና መፈናቀሉ እንዲቀጥል አድርጎ በሌላ በኩል አስጥለን ብለው ያልጠየቁ ሶማሌ ወገኖቻችንን አስጥላለሁ በሚል ዋርድያ ቆሞ ኢላማ የማመላከት ሥራ ሰራ።ነገሩ “መበቀል ያማረው እዚህ አለለት” አይነት ነበር። በዚህ ሁኔታ በኢላማነት ያዘጋጃቸውን ሶማሌ ወገኖቻችንን ድንገት ጥሎ በመሄድና ጥሎ መሄዱም እንዲታወቅ በማድረግ ልጁን፣ሚስቱን፣ወድሙን፣ አባቱን ወገኑን በህውሃት ልዩ ኃይል ያጣውና በዚህም የተቆጨው ቁጫኑን ተወጣ። ህወሃትና አሜሪካ ነዋሪ ቡችላወቻቸው “አረመኔው ኦሮሞ ሶማሌን ፈጀ” ሲሉ በእሳት ላይ በንዚን ለማርከፍከፍ ሞከሩ። ህወሓት የቀረው የተቆረጠ አንገት በእጁ የያዘ ሃውልት ማሰራትና በሁለቱ በሄረሰቦች መካከል ቅዋም የጥላቻ መሰረት ማቆም ነው።ይህ እኩይ ስራው በእየቦታው ይቀጥላል።ጉጅና ወርጅ አካባቢ እንዲህ አይነት ሃውልት መስራቱ ከህወሓት የሚጠበቅ ነው።

ወያኔ መፍጨርጨሩ እንጂ ከገባበት ማጥ የሚያወጣው የለም። ሶማሌ ወገኖቻችን በህወሓት የደረሰባቸውን ግፍና በደል ከማንም መስማት ሳያሻቸው ጠንቅቀው ያውቁታል።በልዩ ኃይል ስም እነሱንም ሆነ ሌላውን የሚገድለው ማን እንደሆነ ጠንቅቀው ያውቁታል።በቅዋንቅዋ፣በሃይማኖት፣በስነልቡናና ከሁሉም በላይ በኢትዮጵያዊ አብሮነት ለዘመናት የሚያውቁትን ኦሮሞ ወገናቸውን ሊሞት ለምያጣጥረው ህወሓት ብለው ቂምና ቁርሾ አይፈጥሩም። ከትግራይ ይልቅ ባሌና አልሞት ባይ ተጋዳይነቱ ቀጥሏል።የቀረው አገርን አጥፍቶ የመጥፋት ሕልሙ ከሽፎ መርወቹ እንደናዚ ጦር ወንጀለኛ እየታደኑ ለፍርድ መቅረባቸው ነው።
Last edited by Tintagu wolloye on 24 Dec 2017, 06:24, edited 1 time in total.

Tintagu wolloye
Member
Posts: 1474
Joined: 02 Sep 2016, 16:59

Re: ሕዝብ አንቅሮ የተፋው ህወሓት ሲጨልምበትና መውደቂያው ሲደርስ የሶማሌ ክልልንና ጭካኔ፣ጠባብ ብሔርተኝነትና ጥላቻ አጥብቶ ያሳደገውን የበኩር ልጁን አብድሌን የሙጥኝ ያለባቸው ምክንያቶች (ትንታጉ ዘወሎ)።

Post by Tintagu wolloye » 23 Dec 2017, 06:27

ህወሀት የኮንትሮባንድ መነገጃውንና በሽብር መዋጋት ስም ከአሜሪካ ዶላር የሚቀፍለውን የሶማሌ ክልል በሰራዊቱ አዛዥ በመሀይሙ ሳሞራ የኑስ የበላይነት በስሩ ያደረገው ገና ድሮ ገና ነው።የህወሀት የወርቅ እርሻ ይባላል ክልሉ። ልዩ ትኩረት ሰጥቶ የፖለቲካ ባሮችና ለምን ብለው ከመጠየቅ ይልቅ ተኩሶ መግደል የሚቀላቸው አንጋቾች ፈጥሯል።

ህዝባዊ አመፁ ባያዉከው ኖሮ በምእራብ ቅማንትን በስሩ አድርጎና ባዶው ክልል የሚባለውን ቤኒሻንጉልን እስከ ጋምቤላ ለመጠቅለል እንዳሰበው ሁሉ በሂደት አዳክሞ የተቆጣጠረውን የአፋር ክልል መረማመጃ በማድረግ ከሶማሌ ክልል ጋር ለማቆራኘት እቅድ ነበረው። ትግራይ ምንም እንደሌለ ያውቃል። ትግራይን ቢገነጥል ውሎ አድሮ ህዝቡ ራሱ እንደሚበላው ይረዳል። እናም ጥገኛውን ክልል እመራለሁ የሚለው ጥገኛው ፓርቲ ሊሸከመው ፈቃደኛ በሆነው ላይ ሁሉ ራሱን ይጭናል።

Tintagu wolloye
Member
Posts: 1474
Joined: 02 Sep 2016, 16:59

Re: ሕዝብ አንቅሮ የተፋው ህወሓት ሲጨልምበትና መውደቂያው ሲደርስ የሶማሌ ክልልንና ጭካኔ፣ጠባብ ብሔርተኝነትና ጥላቻ አጥብቶ ያሳደገውን የበኩር ልጁን አብድሌን የሙጥኝ ያለባቸው ምክንያቶች (ትንታጉ ዘወሎ)።

Post by Tintagu wolloye » 24 Dec 2017, 06:26

ህዝባዊ አመፁ ባያዉከው ኖሮ በምእራብ ቅማንትን በስሩ አድርጎና ባዶው ክልል የሚባለውን ቤኒሻንጉልን እስከ ጋምቤላ ለመጠቅለል እንዳሰበው ሁሉ በሂደት አዳክሞ የተቆጣጠረውን የአፋር ክልል መረማመጃ በማድረግ ከሶማሌ ክልል ጋር ለማቆራኘት እቅድ ነበረው። ትግራይ ምንም እንደሌለ ያውቃል። ትግራይን ቢገነጥል ውሎ አድሮ ህዝቡ ራሱ እንደሚበላው ይረዳል። እናም ጥገኛውን ክልል እመራለሁ የሚለው ጥገኛው ፓርቲ ሊሸከመው ፈቃደኛ በሆነው ላይ ሁሉ ራሱን ይጭናል

Post Reply