Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
-
Revelations
- Senior Member+
- Posts: 33873
- Joined: 06 Jan 2007, 15:44
Post
by Revelations » 19 Apr 2024, 21:23
And it has been quite a while since we exposed the PP "cyber army" aka a few devoted cadres right here on this forum!
Please wait, video is loading...
Last edited by
Revelations on 19 Apr 2024, 22:02, edited 1 time in total.
-
Revelations
- Senior Member+
- Posts: 33873
- Joined: 06 Jan 2007, 15:44
-
Revelations
- Senior Member+
- Posts: 33873
- Joined: 06 Jan 2007, 15:44
-
Revelations
- Senior Member+
- Posts: 33873
- Joined: 06 Jan 2007, 15:44
-
Revelations
- Senior Member+
- Posts: 33873
- Joined: 06 Jan 2007, 15:44
Post
by Revelations » 19 Apr 2024, 22:30
አበል የሚታሰብላቸው ተቀጣሪ ‘የሚዲያ ሠራዊት’ አባላት
ከ15 ዓመታት በላይ በፌደራል መንግሥት ተቋማት የኮሚዩኒኬሽን ኃላፊነት የሠሩ አንድ ምንጭ፤ የፓርቲ አባላትን በመጠቀም በዘመቻ መልክ የመንግሥትን ፕሮፓጋንዳ በፌስቡክ ላይ የማሠራጨት ሀሳብ የቀድሞው ገዢ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) በመጨረሻዎቹ የሥልጣን ዓመታት ላይ በዕቅድ ደረጃ ተዘጋጅቶ የነበረ ጉዳይ እንደሆነ ለቢቢሲ ገልጸዋል።
መንግሥት ላይ የሚደረጉ ተቃውሞዎች እየበረቱ በመጡበት በ2008 ዓ.ም.፤ የቀድሞው የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ይህንን የተመለከተ ሥልጠና ለመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ባለሙያዎች ሰጥቶ እንደነበር አስታውሰዋል። ይሁንና ኢሕአዴግን የመሠረቱት አራት ፓርቲዎች ተቃውሞዎቹን በተመለከተ ያላቸው አቋም እየተለያየ በመምጣቱ በታሰበው ልክ ዕቅዱን መተግበር አለመቻሉን ምንጩ አስረድተዋል።
በአሁኑ ጊዜ የሚታየው የፌስቡክ ዘመቻ አተገባበር ከስምንት ዓመት በፊት ተዘጋጅቶ ከነበረው ዕቅድ ጋር ተመሳሳይነት እንዳለው የሚያነሱት ምንጩ፤ ብልፅግና ፓርቲ እና የመንግሥት አመራሮች በወቅቱ የተዘጋጀው ዕቅድ መተግበር ላይ “ተሳክቶላቸዋል” ብለው እንደሚያምኑም ጠቅሰዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መንግሥት ወደ ሥልጣን ከመጣ እና ብልፅግና ፓርቲ ከተመሠረተ በኋላም የቀጠለው የሚዲያ ሠራዊትን ተጠቅሞ ፕሮፓጋንዳ የማሠራጨት ዕቅድ ብቻ አልነበረም። የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀምን እና ሥርዓተ ቀመርን (አልጎሪዝም) የተመለከቱ ሥልጠናዎች አሁንም በብልፅግና ፓርቲ የተለያዩ መዋቅሮች ይሰጣሉ።
ለፓርቲ አባላት እና የኮሚዩኒኬሽን ባለሙያዎች የሚሰጡት የእነዚህ ሥልጠናዎች አንዱ ትኩረት “በሀገሪቱ የሚከናወኑ የልማት ፕሮጀክቶቻችንን” የተመለከቱ “መረጃዎችን ለሕዝብ ማድረስ” የሚል ነው።
የብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅህፈት ቤት ለቢቢሲ በሰጠው ምላሽ ላይ “የማኅበራዊ ሚዲያ ምንነትና ፋይዳ፣ የመተግበሪያዎቹ አሰራርና በመተግበሪያዎቹ ሃሳብን እንዴት ለብዙኃን ማድረስ እንደሚቻል” ለአመራሮቹ እና ለአባላቱ ሥልጠናዎችን እንደሚሰጥ ጠቅሷል።
ፓርቲው፤ “ይህ ደግሞ በየትኛውም የዓለም ክፍል ያለ የፖለቲካ ማኅበር ሁሉ ሊያደርገው የሚችልና የሚገባ እንደሆነ ያምናል” ሲል ይህንን ዓይነቱ ጉዳይ የተለመደ አሠራር መሆኑን ገልጿል።
በመንግሥት እና ፓርቲ የፌስቡክ ገጾች ላይ ተከታይ እና ተሳታፊዎችን የማብዛት ጥረት፤ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ሁለት ቢሮዎች ላይክ፣ ኮሜንት እና ሼር የሚያደርጉ ሰዎችን እስከመቅጠር እንዳደረሰ ሁለት የቢሮዎቹ ምንጮች ለቢቢሲ ገልጸዋል።
በዚህ ዓይነት መልኩ የፌስቡክ ገጻቸውን ተሳትፎ ለማብዛት እየሞከሩ እንደሆነ የተጠቀሱት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ እንዲሁም ፐብሊክ ሰርቨስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ናቸው። ቢቢሲ በሁለት ቢሮዎች የፌስቡክ ልጥፎች ላይ ያደረገው የዳታ ትንተና ከምንጮች ከተገኘው መረጃ ጋር ተመሳሳይ ነው።
ይህንን ጉዳይ አስመልክቶ ቢቢሲ ጥያቄ ያቀረበለት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ፤ በቢሮው የፌስቡክ ገጽ ላይ ተሳትፎ ለማድረግ “የተቀጠሩ እና ክፍያ የሚያገኙ ግለሰቦች አሉ” መባሉን አስተባብሏል።
ቢሮው የሶሻል ሚዲያ አጠቃቀምን በተመለከተ ለወጣቶች ሥልጠና እንደሚሰጥ ለቢቢሲ የተናገሩት የቢሮው የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ መሃሪ ተመስገን፤ ይህንን ሥልጠና የወሰዱ ግለሰቦች በቢሮው ገጽ ላይ ተሳትፎ እንዳላቸው ገልጸዋል።
አቶ መሃሪ፤ “ከእኛ ቢሮ ጋር የሚሠሩ ወጣቶች እና የስፖርት ቤተሰቦች የተቋሙን ፔጅ በመከታተል የሚለቀቁ መረጃዎች ላይ የራሳቸውን ላይክም፣ ኮሜንትም እንዲያደርጉ የተለያዩ ሥልጠናዎችን እንሰጣለን። ሥልጠናውን ከወሰዱ ሰዎች ውስጥ አንዳንዶቹ በተደጋጋሚ [ኮሜንት] እያደረጉ ሊሆን ይችላል” ብለዋል።
ተመሳሳይ ጥያቄ የቀረበላቸው የፐብሊክ ሰርቨስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ጣሰው ገብሬ ደግሞ ይህ ዓይነቱ ተግባር ስለመኖሩ “መረጃ እንደሌላቸው” ተናግረዋል። ኃላፊው ጉዳዩን አጣርተው መረጃ እንደሚሰጡ ቃል የገቡ ቢሆንም፣ ከዚያ በኋላ ከቢቢሲ የተደረገላቸውን ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ አልመለሱም።
ቢቢሲ ከምንጮች ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ይህንን ተግባር ለመፈጸም "የተቀጠሩት" 11 ግለሰቦች ተሳትፎ የሚያደርጉት በሁለቱም ቢሮዎች የፌስቡክ ገጾች ላይ ነው። ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው አንድ ምንጭ ግለሰቦቹ የብልፅግና ፓርቲ አባል የሆኑ እንዲሁም በወረዳዎች እና በክፍለ ከተሞች ላይ የኮሚዩኒኬሽን ባለሙያ ሆነው መደበኛ ሥራ የሚያከናውኑ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ምንጩ ጨምረውም “አንድ ሰው እስከ ስምንት እና አስር የፌስቡክ አካውንት አለው። በቀኑ የሚከታተሉት የእኛን ገጽ ነው። ኮሜንት፣ ሼር ሲያደርጉ የተጻፈውን ያነቡትና በእሱ ላይ ተመርኩዘው የቢሮውን ሥራ የሚደግፍ ኮሜንት ይሰጣሉ። የእኛን ልጥፍ ወስደው በአስሩ ፔጃቸው ላይ ሼር ያደርጉታል ማለት ነው” ይላሉ። ግለሰቦቹ ለዚህ ተግባራቸው “በአበል መልክ” ክፍያ እንደሚያገኙ ምንጮቹ ገልጸዋል።
ቢቢሲ፤ የፌስቡክ ይዘቶች መከታተያ የሆነውን “ክራውድ ታንግል” ተጠቅሞ ያገኘው ዳታ እንደሚያመለክተው ከኅዳር እና ታኅሣሥ ወራት ጀምሮ የሁለቱ ቢሮዎች ገጾች ልጥፎች ላይ የሚሳተፉ አካውንቶች እና ገጾች ቁጥር በከፍተኛ መጠን ጨምሯል። ይህ ወቅት ምንጮች የግለሰቦቹ ቅጥር እንደተፈጸመ ከገለጹት ጊዜ ጋር ተመሳሳይ ነው።
አብዛኛውን ጊዜ በገጾቹ ልጥፎች ላይ ኮሜንት የሚያደርጉት ተመሳሳይ አካውንቶች ሲሆኑ፣ እነዚሁ አካውንቶች በሁለቱም ቢሮዎች ገጽ ላይ እንደሚሳተፉ ቢቢሲ አረጋግጧል። ቢቢሲ በዚህ ተግባር ላይ የሚሳተፉ እና ከሁለት ግለሰቦች ጋር ግንኙነት ያላቸውን 16 አካውንት እና ገጾች ለይቷል።
የዲጂታል ሰብአዊ መብቶች ተመራማሪው ዶ/ር ዮሃንስ፤ ከመንግሥት ጋር በተያያዙ ልጥፎች ላይ በተደራጀ መልኩ በብዛት ኮሜንቶችን መስጠት “ሀሳብን በነጻነት መግለፅ ሳይሆን ሌሎችን ማሸማቀቅ ነው” ይላሉ። ይህ አይነቱ እንቅስቃሴ “ተቃዋሚዎችን ማፈን፣ በንቃት የሚጽፉ ሰዎችን ከመድረኩ እንዲወጡ ማድረግ እንዲሁም በነጻነት የመናገር እና መረጃ የማግኘት መብትን መገደብ” እንደሚያስከትል ጠቅሰዋል።

by Revelations » 19 Apr 2024, 23:00
በአዲስ አበባ ከተማ ከወረዳ እስከ ክፍለ ከተማ የሚገኙ አመራሮች በማኅበራዊ ሚዲያ ዘመቻዎች ላይ ይሳተፋሉ። በከተማዋ ከ500 በላይ የክፍለ ከተማ እና ከ3,500 በላይ የወረዳ አመራሮች አሉ።
![](https://ichef.bbci.co.uk/ace/ws/800/cpsprodpb/9e8a/live/39139270-f737-11ee-a9f7-4d961743aa47.jpg)
-
Revelations
- Senior Member+
- Posts: 33873
- Joined: 06 Jan 2007, 15:44
-
Revelations
- Senior Member+
- Posts: 33873
- Joined: 06 Jan 2007, 15:44
Post
by Revelations » 19 Apr 2024, 23:54
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፓርላማ በቀረቡበት ዕለት 93 የተዘጋጁ ኮሜንቶች ለዋትስአፕ ግሩፕ አባላቱ ተልከዋል። ከስብሰባው መጠናቀቅ በኋላ ደግሞ የጠ/ሚ ዐቢይን ምስል እና ንግግር የያዙ 26 ግራፊክስ ምሥሎችን በግሩፑ ላይ ተለቅቀዋል።
![](https://ichef.bbci.co.uk/ace/ws/800/cpsprodpb/6980/live/fc43e000-f738-11ee-97f7-e98b193ef1b8.jpg)
-
Revelations
- Senior Member+
- Posts: 33873
- Joined: 06 Jan 2007, 15:44
Post
by Revelations » 20 Apr 2024, 00:04
የዋትስአፕ ግሩፑ አስተዳዳሪ የላካቸው ፅሁፎች በአቶ ታዬ የፌስቡክ ገፅ ላይ ቢያንስ 365 ጊዜ በተለያዩ አካውንቶች ኮሜንት መደረጋቸው ቢቢሲ አረጋግጧል።
![](https://public.flourish.studio/uploads/1146796/ad9d893d-ba25-4b40-9e62-26b3b2fe679d.jpg)
-
Revelations
- Senior Member+
- Posts: 33873
- Joined: 06 Jan 2007, 15:44
Post
by Revelations » 20 Apr 2024, 00:15
በሁለት ሰዎች የተከፈቱት እነዚህ አካውንቶች በአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ እንዲሁም ፐብሊክ ሰርቨስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የፌስቡክ ገጾች ላይ በተደጋጋሚ ኮሜንት ያደርጋሉ።
![](https://public.flourish.studio/uploads/1146796/7ffd32b4-09e0-4d70-9b20-c60fe306a2ab.jpg)
-
Revelations
- Senior Member+
- Posts: 33873
- Joined: 06 Jan 2007, 15:44
-
Revelations
- Senior Member+
- Posts: 33873
- Joined: 06 Jan 2007, 15:44
Post
by Revelations » 20 Apr 2024, 07:46
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፓርላማ ውሏቸውን በፌስቡክ ገፃቸው ሲያሠራጩ ቢያንስ 43 ጊዜ አወዳሽ ኮሜንቶችን ሰጥቶ የነበረው ይህ አካውንት በሜታ ተወግዷል።
![](https://ichef.bbci.co.uk/ace/ws/800/cpsprodpb/6fb9/live/6a41b900-f73a-11ee-bba2-211f72935902.png)