Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30841
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Horus » 14 Mar 2023, 22:11

ያመጣሃው ጉዳይ ረጅም ስለሆነ አንድ ሁለት ነገር ብዬ ላቁም ።

ከዚህ በላይ ስለ መሬትና ካርታው ምሳሌ አንስቼ ነበር። ይህ ምሳሌ በሰው ልጅቾ ማህበረሰብ ውስጥ እንዴት ነው የሚሰራው? (በነገራችን ላይ ሴሚዮቲክስና ሄርሚዩነቲክስ አንድ አይደሉም)።

በሰው ልጅ አለም ውስጥ ያለው ሰውና ባህሪው ብቻ ናቸው ። ማለትም ሰዎች እንደ ፊዚካል ምድር ቢሆኑ ምንድን ናቸው ካልክ ያለው ሰው በአካለ ስጋ እና ሰው በባህሪው ናቸው ። በቃ! የሰው አካል ካርታ ዛሬ በብዙ አይነት ባዮኬምስትሪና አናቶሚ ተጽፎ ከሞላ ጎደል ፊዚካል አካላችንን የሚገልጽ ካርታ (እውቀት) አለ። ያ ሳይንስ ስለሆነ የሃይማኖት ንትርክ አያስነሳም ።

ሌላኛው የሰው ፊዚካል ሪያሊቲ (ምድር) የሰው ባህሪ ነው ። የሰው ባህሪ በአንድ ቃል የሰው ተግባር ነው! የሰው ተግባር የሰው ንቅናቄ ነው ።ፊዚካል አቲቪቲ ነው (የሚታይም የማይታይም አክቲቪቲ)። ይህን ፊዚካል ባህሪ በካርታ ለመግለጽ ሃይማኖት፣ ፊሎሶፊ፣ ሶሲዮሎጂ፣ ሳይኮሎጂ ወዘተ የሚባሉ እውቀቶች (ካርታዎች) ተሰርተዋል፣ ይሰራሉ ። እኔ እነዚህ ካርታዎች በሙሉ ካልቸር እላቸዋለሁ ። ከሃይማኖት እስከ ስነጽሁፍና ሌላም ካልቸር ናቸው፣ ትልቁ ካልቸር ቋንቋ ነው።

ስለዚህ አንድ ሰው አንድን ባህሪ ለምን ያደርጋል? ስንል (ሃማኖትና ፊሎሶፊ) ጥያቄ ነው ። የባህሪው ኮዝ ፣ ፈጣሪ ምንድን ነው ማለት ነው። የአንድ ሰው ባህሪ ምንድን ነው? ምን እያደረገ ነው ስንል (ኤፒስቲሞሎጂ ጥያቄ ነው)? ተግባሩን እንዴት አድረገው ስንል ኢትዮሎጂ ወይም ሜትዶሎጂው ነው? ተግባሩ ትክክል ነው ወይ? ተግባሩ ጥሩ ነው ውይ? መጥፎ ነው ወይ ስንል ኤቲክስ ወይም ሞራሊቲ ይባላል። ያ የስነ ምግባር (የተግባር ሳይንስ) ነው በሃይማኖት ውስጥ በብዛት ያለው ። ሌላው የኦንቶሎጂ ማለት አላህ አለ ወይ የሚለው ንትርክ ነው ።

ስለዚህ አንድ የሰው ልጅ ባህሪ (ቢሄቪየር) በማየት፣ በመስማት፣ በመንካት፣ በማሽተት፣ በመቅመስ (በመሳም) መለካት ካልቻልክ ለሺ ዘመን በተጻፈ ወይም በተሳለ ቴክስት ወይም ምልክት ላይ በመከራከር፣ በመተርጎም (ሄርሚነቲክስ) ወደ እውነት መድረስ አይቻልም ። እውነት ማለት መሬቱ የሰውዬ ተግባር፣ የሰውዬ ፊዚካል አክት ስለሆነ ። በቃ !!

በወረቀት ላይ ያለ የስነ ምግባር መመሪያ፣ ለምሳሌ ከዋሸ ምላሱን ቁረጠው የሚለው ካርታ ትክክል ነው ይቀጥል (ኮንሰርቫቲቭ)፤ ስህተት ነው ረፎርም ይደረግ የሚሉት ሁለቱም የሚዳኙት በሚቆረጠው ፊዚክል ምላስ ነው ። የአንድን ሰው ምላስ በቢላ መቁረጥ የሰው ባህሪ ነው፣ ፊዚካል ተግባር ነው ። ምላስ ለሰው ልጅ አስፈላጎ ኦርጋን ስለሆነ አይደለም በሞራል ፕሪንሲፕል በሜዲካል ሳይንስም ክልክል ነው ። ግን ሰዎች ያን መሰል ስከፎ ባህሪ ለመተው ወይም መጥፎነቱን ለመቀበል ከፍ ያለ የስነምግባር ወይም ሞራል ፕሪንሲፕል ላይ መድረስ አለባቸው ። ያ እንዴት የመጣል? ስዎች ከፍተኛ ሞራሊቲ የሚያገኙት እንዴት ነው የሚለው ሌላ የኮግኒቲቭ ሳይንስ ጥያቄ ነው ።

ይህ ነው የችግሩ አፈታት ። ከእምነት፣ ከካልቸር ፣ ከፊሎሶፊ ወጥተን ባህሪን እንደ መሬት ይቀሩት እውቀቶች ሁሉ እንደ ካራታ መመልከት ስንጀምር ነው ከጉንጭ አልፋ የምንወጣው ።

Abe Abraham
Senior Member
Posts: 14412
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Abe Abraham » 15 Mar 2023, 00:27

Horus wrote:
14 Mar 2023, 22:11

Source: internet

Nasr Hamid Abu Zayd as a Modern Muslim Thinker

NUR ZAINATUL NADRA ZAINOL, LATIFAH ABD MAJID &
MUHD NAJIB ABDUL KADIR1

ABSTRACT

Nasr Hamid Abu Zayd is a thinker who has produced works in the fields of theology,
philosophy, law, politics and humanities.Abu Zayd’s thought, partly on the Quran
and its hermeneutics has stirred controversy in Egypt and the Muslim world.

This research focuses on the controversy surrounding Nasr Hamid Abu Zayd which led to the declaration of his apostasy by the Supreme Court of Egypt in 1995, as well as his controversial thoughts on the Quran, its method of exegesis and certain fiqh (Islamic jurisprudence) issues such as the hijab (veil) and polygamy.

This paper serves as a literature review which employs the content analysis as a methodology to elaborate on Abu Zayd’s controversial thoughts based on his books, as well as through the views of Muslim and Western scholars on those thoughts.

Keywords: hermeneutics, modernism, Nasr Hamid Abu Zayd, Quranic exegesis
ኣንተን ለመጥቀስ " በመተርጎም (ሄርሚነቲክስ) ወደ እውነት መድረስ አይቻልም " ስትል ዶክተር ነስር ሓምድ ኣቡ ዘይድ በችግር የገባው hermeneutics በቁርኣን ኣፕላይ ለማድረግ ስለ ሞከረ እኮ ነው !

ከዚያም በላይ ቁርኣን " ለሁል ጊዜና ቦታ ነው / ሊኩሊ ዘማኒን ዎ መካን " እየተባለ በኣቀራረቡ ለቴክስቱ ጊዜ ሊያስገባለት ሞከረ ። ጊዜ ማስገባት ማለት ፥ በቴክስቱ ኣንዳንድ ኣስቸጋሪና ኮንትሮቨርሻል ነገሮች ካገኘህ " ለዛ ጊዜ እንጂ ላለንበት ጊዜ ኣይመለከትም " ብለህ ልታልፈው ትችላለህ ማለት ነው ። ኮንሰርቫቲቮች ኣፕሮቹ ኣንዳንድ ጊዜ ሊጠቅማቸው ቢችልም ኣይወዱትም ምክንያቱ ባንዳንድ ነጥቦች በተለያዩ ምክንያቶች ኮንሰሽን ካደረግን ቀስ በቀስ ጠቅላላው የእምነት ህንጻ ሊፈርስብን ይችላል የሚል ፍርሃት ስላላቸው ።

" ሊጠቅማቸው ቢችልም " ምን ማለት ነው ? መልስ ፥ የሚልክ ኣል-የሚን ጉዳይ ለመፍታት ። በሚልክ ኣልየሚን ፕሪንሲፕል ኣንድ ሙስሊም በህግ ባንድ ጊዜ እስከ ኣራት ሴቶች ኣግብቶ ከባሮቹ ( በእጁ ቁጥጥር ካሉ ስለይቭ ዊመን) ደሞ ያልተገደብ ቁጥር ሊጨምር ይችላል ። ኣሁን የጊዜ ጉዳይ ካስገባህ በድሮ እንጂ በዘመናችን ሚልክ ኣልየሚን ኣይሰራም ብለህ ማምለጫ ለማግኘት ትችላለህ ። ኮንስርቫቲቮቹ ግን በፍርሃት ጉዳዩን ሊገጥሙት ኣይወዱም ። ይህ የ ክሊር ስታንድ ኣለመውሰድ በኣል-ኣዝሃርና መሰልቶቹ ለነዳዕሽ/ኣይሲስ ሴቶች እየዘረፉ ሚልክ የሚን በዒራቕና ሶርያ ፕራክቲስ እንዲያደርጉ ዕድል ይሰጣቸዋል ።

-

Horus
Senior Member+
Posts: 30841
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Horus » 15 Mar 2023, 01:06

ወንድሜ አቤ አብርሃ፣
መጀመሪያ አንተ እራስህ የተጠመድክበት የሃሳብ አላማ በግልጽ ዲፋይን ማድረግ አለብህ ! ከጊዜ እና ከሁኔታ፣ ከቦታና ከማህበረሰብ ጋር የሚለዋወጥ ካልቸር እንጂ እምነት አይደለም ። እምነት ማለት ድንቁርና ማለት ነው። የዚያ ተጻራሪ እውቀት ይባላል ። ሳይንስ ማለት እውቀት ወይም ኖውሌጅ ማለት ነው። እምነት አንድን ነገር እንደ ወረደ መቀበል ነው። እውቀት ማለት ከላይ እንደ ነገርኩ በኤክስፔሪያን ወይም በፋክት የተረጋገጠ ካርታ ማለት ነው ።

ግዜ ማስገባት ማለት ሬላቲቪዝም ይባላል። ፊዚክስ ነው ። አንድ ነገር፣ አንድ ፋክት፣ አንድ ኢቬንት ከግዜና ቦታ ውጭ ሊሆን አይችልም ። አቤ ምሳ በላ የሚለው ፋክት አይደለም ። መቼና የት የሚሉት (ግዜ ማስገባት፣ ቦታ ማስገባት) ነው እውነት እና እውቀት የሚያደርገው ። ያን ሳታደርግ ብዙ ብትጽፍ ምናብ አብስትራክት ይባላል ። በኮግኒቲቭ ሳይንስ አንድ ትልቅ ሕግ አለ፣ እሱም 'በቋንቋ የፈለግነውን ነገር መፍጠር እንችላለን' ይባላል ። ለምሳሌ 'ሰማይ እሳት ነው ' ብዪ በቋንቋ ብፈጥረው አንተ ልታምነው ትችላለህ!!!!!!!! ሰማይ ግን እሳት አይደለም !

ስለዚህ እምነት ያለ እውቀት አንድን ነገር መቀበል መሆኑን ካላወቅህ እዚህ ውይይት ውስጥ ብዙ ጥቅም አታገኝም!

ያ ሄርሙኒቲክስ እየተጠቀመ ቁርአንን ሊተች የሚፈልገው ምሁሩም በእምነትና በእውቀት፣ በሳይንስና ሚቶሎጂ መሃል ያለውን ልዩነት ያልተገነዘበ ሰው ነው!

Abe Abraham
Senior Member
Posts: 14412
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Abe Abraham » 15 Mar 2023, 15:19

Horus wrote:

ያ ሄርሙኒቲክስ እየተጠቀመ ቁርአንን ሊተች የሚፈልገው ምሁሩም በእምነትና በእውቀት፣ በሳይንስና ሚቶሎጂ መሃል ያለውን ልዩነት ያልተገነዘበ ሰው ነው!
ዶክተር ዓብድሰቡር ሻሂን

"ሄርሞነጢቓ'' በየቑርኣን ቴክስት ( ኣል-ነሱ ኣል-ቕሩኣኒ ) ኣይገባም ብሎ ኣጥብቆ የተቃወመ ሰውና ዶክተር ነስር ሓምድ ኣቡ ዘይድን ኣገሩን ትቶ ወደ ኤውሮጳ እንዲ ኮበልል ካደረጉ ዋና ሰዎች ዶክተር ዓብድሰቡር ሻሂን ነበር ። የሰጠው ምክንያት ፥ ዶክተር ነስር ሓምድ ኣቡ ዘይድ ነጮች በጽሁፋቸውና ትራዲሽናቸው የተጠቀሙትን ዘዴ በቁርኣን ተጠቅሞ በ " መታሃት " ( labyrinth) ሊያገባን ይፈልጋል ። (ስለዚህ ሰውየውን ሩቅ ሳይሄድ ማቆም ኣለብን!!)

ዶክተር ዓብድሰቡር ሻሂን ዘዴው (ሄርሞነጢቓ) የሚያመጣው ችግር ኣስቀድሞ ተገንዝቦ ነበር ማለት ነው ። ዶክተር ነስር ሓምድ ኣቡ ዘይድ ግን ስራው መነሻውና መድረሻው ችግር ለመፍጠር ሳይሆን ችግር ለመፍታት ያለመ ነው የሚል በኤቪደንስ የተደገፈ ኣቋም ነበረው ።

የዶክተሩ ኣሰራር ፥ የማይነኩ የእምነቱ መሰረቶች ( ኣል-ሰዋቢት ) እንዳሉ ትተህ ልቀየሩ በሚችሉት ( ሙተቐይራት ) ኣትኩረህ የምታገኛቸው ችግሮች ( ሃይማኖትን በሚገባ ለመረዳትና ፕራክቲስ ለማድረግ " በተለምዶ " ችግር የሚፈጥሩ " ነሶች " /ቴክስቶች ) ተንትነህ (በኣእምሮኣዊ ዘዴ/ ዝም ብለህ ከኪስህ ያላወጣሀው!! ) ለማሻሻል ። ለምን ? የሃይማኖት(የምስልምና) ዋና ኣላማው የሰው ንሮ በኣለም በጭንቀት ለማስገባት ስላልሆነ ።

ስለዚህ ኣንተ " ያ ሄርሙኒቲክስ እየተጠቀመ ቁርአንን ሊተች የሚፈልገው ምሁሩም በእምነትና በእውቀት፣ በሳይንስና ሚቶሎጂ መሃል ያለውን ልዩነት ያልተገነዘበ ሰው ነው! " ያልከው ለዶክተር ነስር ሓምድ ኣቡ ዘይድ ቢቀርብለት ኖሮ " በኔ ኣፕላይ ኣያደርግም ፡ እምነት እምነት መሆኑን ኣውቃለሁ ። እኔ እምነቴን ኣልካድኩም ። ሙስሊም ነኝ ።" ብሎ በመለሰ ነበር ።

እነ ዶክተር ዓብድሰቡር ሻሂን የቑርኣን ነስ/ቴክስት ለማብራርያ " ተፍሲር / መግለጫ/ትንተና " ልታደርግልህ ትችላለህ በ " ሄርሞነጢቒያ " ና " ቴክስት ኣናሊሲስ " ተጠቅመህ ግን ቁዱስነቱን ( ቑድሲያ ) ልትነካ በፍጹም ተገቢ ኣይደለም ባዮች ሲሆኑ ( በዶክተር ሻሂን ኣነጋገር " በመታሃት ( labyrinthes) እንገባለን )ዶክተር ነስር ሓምድ ኣቡ ዘይድ ደሞ ነሱ/ቴክስቱ እንዳለ ትቶ በውስጡ ያለውን ትርጉም መርምሮ ያሉ ታላላቅ ችግሮችን ለመፍታት ለመሞከር " ቑድሲያ " የሚባለውን ለጊዜ በጎን መተው ኣለብን የሚል ኣስተያየት ነበረው ።

ባጭሩ በዶክተር ነስር ሓምድ ኣቡ ዘይድ ኣስተያየት ምንም ሊደረግ ኣይቻልም ክልክል ነው( የነሱ/ቴክስቱ ቑድሲያ -
ለበእምነት መሰረታውያን ላልሆኖ ኣርእስቶችም ጭምር - ፍጹም ነው! ) ብለህ ባለህበትን ከቆምህ ያሉ የነሱ/ቴክስቱ ችግሮች - ኣንተን እንደ የእምነት ሰው - በኣደጋ ሊያስገቡህ ይችላሉ ።

ኤቪደንስ ፥ በታች በምታየው ቪድዮ ኣንድ ግብጻዊ ሞሮኮ ሄዶ ኣንዲት ሴት ኣምጥቶ ከስዋ ጋር " የሚልክ የሚን " ጋብቻ"/ሴክሳዊ ትስስር! " ኣደረገ ። ለምን ተብሎ ሲጠየቅ " ሃይማኖቴ ያፈቅድልኛል " ብሎ መለሰ ።

(የፕሮግራሙ ኣቅራቢ ታላቁ " ዋኢል ኣል-ኢብራሺ " በ 9 ጃንዋሪ 2022 በኮረና ታሞ ሞተ ።)

-

Horus
Senior Member+
Posts: 30841
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Horus » 15 Mar 2023, 16:03

አቤ
የዘረዘርካቸው ምሳሌዎች አዲስ አይደሉም። በክርስትና ውስጥም አሉ ። ያሉት ንትሮክ ሁለት አይነት ናቸው ። አንዱ የዶግማ (መለኮታዊ) ልዩነት ነው ። አንድ እምነት መሰረታው መርሆች አሉት፣ ያ የእምነቱ ዶክሪን ወይም ዶግማ የምንለው ነው ። ለምሳሌ በኦርቶዶክስ ክርስትናና በጴንጤኮስቴ ክርስትና መሃል ያለው የዶክትሪን፣ የዶግማ ልዩነት ነው ። ግን እንዳትረሳ ሁለቱም ክርስቲያ (የክርስቶስ) አምላኪዎች ናቸው ። ልዩነታቸው የክርስቶስ ባህሪ፣ ፍጥረት፣ ኃይል ምንድን ነው በሚለው ነው ። ስለዚህ ሁለት ሙስሊሞች ሁለቱም የአላህ አምላኪ ሆነው ግን የአላህ ባህሪ ምንድን ነው በሚለው ከተለያዩ አንዱ ሺዓ ይሆናል ሌላው ሱኒ ይሆናል ማለት ነው። ወይም ሌላ አይነት ሙስሊም ይሆናል ማለት ነው ።

ሁለተኛው የንትርክ አይነት ዶግማና ቀኖና ባላቸው ልዩነት ላይ አለመስማማት ነው ። ቀኖና (መቀኒያ፣ መከነያ፣ መፈጸሚያ) ማለት ነው ። ሜትድ፣ ቴክኖሎጂ፣ መሳሪያ ፣ ባንድ ቃል አፈጻጸም ሪቿል ስነ ስርዓት ማለት ነው ። ለምሳሌ ኦርቶዶክስ ውስጥ ከበሮ እንጂ ፒያኖ ጊታር መጠቀም ክልክል ነው የሚሉ አሉ። ጾም መጾም ። የተከለከሉ ምግቦች ወዘተ ላይ የሚለያዩ አሉ ። ብዙ ብዙ ግዜ ንትርክ የሚነሳው በነገረ መለኮት (nature of God) ላይ ሳይሆን (differences of rituals) ላይ ነው ።

ሌላ ቦታ እንዳልኩት ፈጣሪ ምንድን ነው የሚለው እምነት ነው ። በሱ ላይ የማይስማሙ አንድ እምነት አይኖራቸው ። ነገር ግ ን በነገረ መለኮት አንድ ሆነው በተለያየ ካልቸርና ባህል የሚተገብሩ ሁሉም የዚያ ሃይማኖት አባላት ናቸው ።

Abe Abraham
Senior Member
Posts: 14412
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Abe Abraham » 15 Mar 2023, 17:10

Horus wrote:
15 Mar 2023, 16:03

የዘረዘርካቸው ምሳሌዎች አዲስ አይደሉም። በክርስትና ውስጥም አሉ ።

ኣዎ ኣዲስ ኣይደሉም ግን ኣዲሱ በምስልምና ነጮች በተከተሉትን የቋንቋና ምርምር ዘዴዎች ኣንገባም የሚል ፍጹም ኣስተሳሰብ ነው ።

በሌላ ኣነጋገር ሙስሊሞች ፥ እኛና እነሱ ኣንድ ኣይደለንም ። መጽሃፋችን ከሰማይ እንዳለው ስለ ወረደ ከመውረዱ በጓላ ደሞ ምንም የጎደለበት ስላልሆነ እንደማንኛውም ነስ/ቴክስት ልንወስደው ኣንችልም ። ወደ ጥርጥርና ኢልሓድ/atheism ሊመራ የሚችል መንገድ ልናመራ ኣንፈልግም ። የነጮችን ለነጮች እንተዎው !! ወደ የክርስትና መንገድ ኣትውሰዱን !!! ምዕራባውያን እስልምናን ሪፎርም ምናምን ብለው ወደ ክርስትና የሄደውን መንገድ ወስደው " ሪችዋል " ብቻ ኣድርገው ሊያስቀሩት ይፈልጋሉ ። ኣልዲያናት ኣል-ኢብራሂምያ/ኣብራሚክ ረሊጅዮንስ የሚባለው ኣዲስ ፋሽን የክፋቱ ኣንድ ገጽ ነው ።

https://www.timesofisrael.com/uae-inter ... -thursday/
-

Abe Abraham
Senior Member
Posts: 14412
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Abe Abraham » 15 Mar 2023, 23:03

Horus wrote:

....ስንጀምር ነው ከጉንጭ አልፋ የምንወጣው ።
ጉንጭ በእንግሊዘኛ ትርጉሙ cheek ከሆነ ፥

ከየኣረብኛ ዚቕን( chin ) ተነስተን ---> ዚግን--->ጭግን--->ጨገነ-->ገነጨ--->ጉንጭ (cheek)!!!

-

Abe Abraham
Senior Member
Posts: 14412
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Abe Abraham » 16 Mar 2023, 14:02

جزمة

المصطلح أصله تركي (بالتركية: Cizme)‏ ومعناه الحذاء عالي الساق إلا أنه بات يعني الحذاء بشكل عام في دول عديدة خصوصاً في المنطقة المغاربية

ጀዝማ የሚለውን የኣረብኛ ስም መሰረቱ " ጂዝመ/ቡት " ከሚለውን የቱርክ ቃል የተወሰደ ነው ። ኣሁን ግን ከጊዜ ጀዝማ - በብዙ የኣረብ ኣገሮች - ለቡት ያልሆነ ሌላ ጫማ መጠርያ ሆነዋል ።

ጂዝመ (በቱርክ) ---> ጀዝማ (ኣረብኛ) ---> ጫማ ( ትግርኛ/ኣማርኛ/...)

-

Abe Abraham
Senior Member
Posts: 14412
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Abe Abraham » 17 Mar 2023, 14:22

"International Monetary Fund " በኣረብኛ " ሰንዱቕ ኣል-ነቕድ ኣል-ደውሊ " ተብሎ ይተረጎማል

"ሳንዱቕ" በትግርኛ "ሳንዱቅ" ደሞ ባማርኛ የምናውቃቸው ቃላቶች ናቸው ። ነገርን ለማስቀመጥ ደሞ እንጠቀምባቸዋለን ።

ኣሁን ኣትኩሮኣችን በ " ሰንዱቕ " ሳዮይሆን በ " ነቕድ " ነው ። ለምን ? መልስ ፥ በትግርኛና ኣማርኛ ከገንዘብና እቃ መለዋወጥ የተሳሰረ " ንግድ " የሚባል ቃል ስላለን ። ድምዳሜ ፥ ነቕድና ንግድ ግንቹነት ስላላቸው መሰረታቸው ኣንድ ሳይሆን ኣይቀርም

-

Abe Abraham
Senior Member
Posts: 14412
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Abe Abraham » 19 Mar 2023, 23:59

القيراط (كوحدة قياس لمساحة الأراضي) في مصر هو جزء من 24 جزء من الفدان، أي ما يعادل 175 متر مربع.

ቒራጥ/ጊራጥ የሚባል ቃል በግብጽ የእርሻ መሬት ስፋት መለክያ ሆኖ በስፋቱ ሃያኣራተኛ ክፋል የ 'ፈዳን ' ወይም 175 ሜትር ካሬ ነው። በትግርኛ የ "ቒራጥ/ጊራጥ'' ዘመድ " ግራት " ይባላል ።

የፕረዚደንት ኢሳያስ ኣፈወርቂ ኣብራሃም የትውልድ መንደር በሓማሴን ለምሳሌ ከጥንት ጀምሮ በእኩልነት የተመሰረተ በ " ዴሳዊ " የመሬት ኣከፋፈል ስለሚገዛ እያንዳንዱ የመንደሩ ገበሬ እኩል ቁጥር ግራቶች ያገኛል ። "በዋሬዳ" የሚባል ሲስተም ደሞ በየ ስድስት ዓመቱ ሌላ ግራቶች ይሰጠሃል ። ግራቶቹ ከመንደሩ የራቁና የቀረቡ ሊሆኑ ይችላሉ ። ድርሻህን በምትቀበልበት ጊዜ እንደ እድልህ ማለት ነው ።

ኣሁን በመንግስት ኣሰራር መሬት የመንግስት ነው ስለሚባል የሓማሴን ህዝብ ከዋና ከተማው ኣስመራ በትልቅ ችግር ይገኛል ።

--
በምድረ ትግርኛ " ዓዲ ግራት " የሚባል ንኡስ ከተማ ኣለ ። ምስኪን ቶሚ ወዲ ሓጎስ " ዓዲ ግራት " የሚባለውን ስም ኤርትራውያኖች በትግርኛ የሰጡት ስያሜ ሳይሆን በኦሮምኛ ከተራራ ጋር የተሳሳረ መጠርያ ነው ሲባል ከሰማ በጓላ ኣብዶ/ተጸሊሉ ኦባማ ኬንያ ኬንያ ኦባማ እያለ ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ ሲያመልጥ በሞያሌ ተይዞ ወደ የኣእምሮ ሆስፒታል ተወሰደ ። እዛም ኣንድ ኤርትራዊ ዶክተር ኣግኝቶ '' ዓዲ ግራት '' ስያሜው በትግርኛ ሆኖ " ግራት " የእርሻ መሬት ከነስፋቱ ነው " ዓዲ " ደሞ የምታውቀው ዓዲ ነው ስላለው ኣሁን ወዲ ሓጎስ በጥሩ ሁኔታ ይገኛል !!!

የሚገርመው ዛሬ በየሶርያ ኣረብኛ የ " ዓዲ " ትርጉም የያዘ " ደይዓ " የሚባል ቃል ኣለ ። ደይዓ በ ደ+ይ+ዓ የቆመ ሆኖ ረዘም ያለ ቫወል '' የ " ን ከቃሉ ከቀንስክ ደ+ዓ ይዘህ ትቀርና በግልባጩ " ዓዲ " ታገኛለህ !!!

-

Horus
Senior Member+
Posts: 30841
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Horus » 20 Mar 2023, 00:29

በሶሪያ አረብኛ ደይዓ ምን ማለት ነው? በትግርኛ ዓዲ ማለትስ?

ስለ...
ሰንዱቅ
ዱቅ
ነቅጅ
ንግድና መንግጅ
ጫማም እንዲሁ ሌላ ግዜ ።

Naga Tuma
Member+
Posts: 5523
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Naga Tuma » 23 Mar 2023, 15:59

አቤ አብረሃም

የምያስተምር ርዕስ ነዉ።

ከኣሁን በፊት የቦረና እና የግዕዝ ቃላት ዲክሽነሪ ቢወጣ ብዬ ተመኝቼ ነበር።

የለጠፍካቸዉ የመጀመርያ ሶስት ቃላትን ሳነብ እና ትርጉማቸዉን ሳስተዉል የተመኙሁት ዲክሽነሪ ይሄ ነዉ ኣስባለኝ።

የኣንተ እና የሆረስ ዉይይት ለጥልቅ የቋንቋ ትምህርት የምያመራ ነዉ። ከዓመታት በፊት ኣንድ ታዛቢ ኢትዮጵያዊያን ለጥልቅ እዉቀት ዝንባሌ የላቸዉም ብሎ ለህትመት ያበቃዉን ተሳስተሃል እያላችሁት ነዉ።

ኣሁን ወደ ቃላቱ ልመለስ እና ቃል በቦረና ቋንቋ ቃሊ ከሚባለዉ ጋር ኣንድ መሠረት እንዳላቸዉ ነዉ የሚገባኝ። ቃሉም ከዛ ጋር የተያያዘ ይመስለኛል። ሎሬቱ ቃሉ የማይቀለበስ ቃሉ ያለዉ ይህን ለማመልከት ይሆን ብዬ እራሴን እጠይቃለሁ።

ከቃል ጋር የተያያዙ ሌሎች ቃላት ኣሉ። ቃል ከሚወጣበት ቆንቆ ወይም ጉሮሮ ጀምሮ። ቆንቆ ኣንድም ቋንቋ ነዉ።

ጸዋሬ ከጦረ ጋር ተመሳሳይ ትርጉም ኣለዉ ስትሉ ሰሞኑን ለብቻዬ ሳስብ የነበረዉን ኣስታወሳችሁኝ። ጡሪ ስት ሃተኡ ማለት ጡር ይሁንብህ ወይም ይሁንብሽ ማለት ነዉ። እምማን ኮ ጡሪ ስት ሃተኡ ማለት እንባዬ ጡር ይሁንብህ ወይም ይሁንብሽ ማለት ነዉ።

እኔ የማዉቃት የድሮ ኢትዮጵያ ዉስጥ ሰዉ እንደዚህ መባልን ይፈራ ነበር። ስለዚህ ሐቀኛ እና ጨዋ፣ የሌላ ስዉን ጥረት በመግፋት ወይም ግፍ በመስራት ወደ እራሱ ኣያመጣም ነበር። የሰዉ ልጅ ስልጣኔ ኣንድም ይህ ማለት ነዉ።

ጡሪ የሚለዉን ቃል ያስታወስኩኝ ከቃናት በፊት ለሆረስ ጊዜ ሳይሆን ወይም ከጊዜ በላይ ጥረት ብዙ ያሳያል ብዬ ከመለስኩለት በሁዋላ ነበር። ጥረት የሚለዉን ቃል ከተጠቃምኩ በሁዋላ ነዉ የጥረት፣ ጡረታ፣ ጣሩ፣ ጦሩ፣ ጡሪ ቃላት መዛመድ የተገለጠልኝ።

ድባብ ደግሞ ድባባ እና ድባቤ የሚሉ ስሞችን ያስታዉሱሃል።

አይን ደግሞ የኢንግሊዘኛዉ ኣይ ወይም የቦራናዉ እጀ ከሚሉት ጋር ተመሳሳይነትን ብያንስ ከአስር ዓመታት በፊት ኣስተዉዬ ኣቅርቤ ነበር። አከባቢን ማያ የተፈጥሮ ስጦታ ሰለሆነ በቀላሉ የማይዘነጋ ቁልፍ ቃል ነዉ። ከሁሉም የገረመኝ የቻይና ቋንቋ ዉስጥ ተቀራራቢ ቃል መኖሩ ነዉ።

ሌላ ቁልፍ ቃል ነዉ ብዬ ይዤ የነበረ ኣለ። ብያንስ የአስር ሺህ ዓመታት እድሜ ያለዉ እና ኢትዮጵያ ዉስጥ ዕፅዋትን ከማላመድ ጋር የተገናኘ ነዉ ተብሎ የሚታሰብ። ስር ከ ጂዝር የመጣ ሊሆን ይችላል ያልከዉ ስር እና ጅዳን ኣስታወሰኝ። ስር እና ጅዳ የትርጉማቸዉ መሠረት ኣንድ ሊሆን ከቻለ ጅዳ እና ጂዝርን ልያገናኛቸዉ የሚችል ተዓምር ሊኖር ይችላል? በአረብኛ ስር የሚሉት የምናዉቀዉ ሀረግስ ሊሆን ይችላል?

ሆረስ፣

በትክክል ኣእምሮ የብርሃን ምንጭ መባል ይችላል። ችግሩ የነበረዉ እኮ የዛ ብርሃን ምንጭ ዉስጣዊ ይሁን ዉጫዊ መሆኑን በቅጡ መለየቱ ላይ ነበር። ናቹራል የሆነዉን ከኣእምሮ በላይ ስለሆነ ሱፐርናቹራል ብቻ መልስ መስጠት የሚችል ነዉ የሚል ክርክር። ይህ ጥያቄ ኣይዴለም ዘ ክንግደም ኦፍ ጎድ ኢዝ ዊዝእን ዩ ወደሚለዉ ኣስተሳሰብ ኣምርቶ ትራንስፎርሜሽንን ያስጀመረዉ? ይህ ግንዛቤ ኣይዴለም እንላይትመንትን ያቀጣጠለዉ?

በተረፈ ሁለታችሁንም ኣንድ ነገር መንገር ያስፈልጋል። ያ ሰዉ እንድሆን ፍቀዱልኝ።

ሁለታችሁም የቀያችሁን ትታችሁ ወደ ማዶ የምታዘንብሉ ይመስላል። ወደ ሴሜቲክ። ከሆነ ወደ ዴድ ኤንድ የምትጓዙ ምሁራን ኣትሁኑ እባካችሁ። በኣንድ በኩል ጥንታዊ ግብጥ እያላችሁ በሌላ በኩል ሴሜቲክ ኢትዮጵያዊያን ማለት ምን ማለት ነዉ ብላችሁ መልስ አግኙ። ከስደት ወይም ኤክሶደስ በፊት ከነበረዉ ታሪክ ነዉ ወይስ ከዛ በሁዋላ ከነበረዉ ታሪክ ነዉ መነሻችሁ? ከስደት ወይም ኤክሶደስ በፊት በነበርችዉ ጥንታዊት ግብጥ ዉስጥ የሴሜቲክ እና ኩሺቲክ ክፍፍል ነበረ? ዶናልድ ኤን ለቪን ይህን ኣስተዉሎ ነዉ ከእንደዚህ አይነት ትግል ብትላቀቁ ይሻላችሁ ነበር ያለዉ።

በመጨረሻም እናንተ ስለቋንቋ ብዙ ጥናት ያካሄዳችሁ ቢሆንም ቋንቋዎችን ስንናገር የኖርን ዉቅያኖስ ዉስጥ የኖረን ሻርክ ዋና ማስተማር እንዳይሆንባችሁ። እንደ ሰብመሪን ባያቀላጥፍም ሻርክን መሠረታዊ ዋና ኣያስተምሩትም።

ለምሳሌ እርባተ ወይም እራት ሲመገብ የሚኖር ሰዉ ምን እንደሆን ኣይስትም።

Abe Abraham
Senior Member
Posts: 14412
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Abe Abraham » 24 Mar 2023, 20:42

Naga Tuma wrote:
23 Mar 2023, 15:59

1_ለቋንቋ ምርምር ለሚወድ ሰው -- ባለሞያ ይሁን ተራ ሰው -- መዝገበ-ቃላቶች በጣም ኣስፈላጊ ናቸው ። ለማንበብ በሚመች ኣገባብ ክተጻፉ ቃላቶችን እያነበብክ በውቅያኖሳቸው ራስህን ረስተህ ልትንሳፈፍ ትችላለህ ።

2_የቃላቶች መሰረትና ከሌሎች ቋንቋዎች ያላቸው ግኑኝነቶች ስትመረምር ኣንዳንድ ጊዜ ቃላቶቹ በገዛ ራሳቸው "ና ውሰደን " ሊሉህ ይችላሉ ። ይህ ግን ሁል ጊዜ ኣይደለም ። ያ ስል መስራትና ለብዙ ጊዜ ማሰብ ካስፈለገ ተሰፋ ባለመቁረጥ መስራትና ማሰብ ኣለብህ ማለት ነው ። በሌላ ኣነጋገር ቃላቶች ሁል ጊዜ እንደ ቃል እና ቃሊ ወይም ቆንቆና ቋንቋ ተቀራርበው ኣይጠብቁህም ።

በትግርኛና ኣረብኛ ዓይኒ/ዓይን ባማርኛ ደሞ ኣይን ሆና ያገኘሀው ቃል በቦራና እጀ ከሆነ ትንሽ ወደ ጀርመነኛ ሄደህ የን ወደ " " መቀየር ሚስጥርን ለማወቅ ትችላለህ ። ጀርመኖች ለኣይን " auge " ስለሚሉት በቦረና " እጀ " ሆኖ ስታገኘው ኣስገራሚ ላይሆን ይችላል ። ክርክሬ ጀርመንኛና ቦራና ይገናኛሉ ማለቴ ሳይሆን መሰረታቸው ኣንድ የሆኑ ቃላቶች በተለያዩ ቋንቋዎች የፊደልና የ "ሳውንድ " መቀያየር ሊያደርጉ እንደሚችሉ ለማብራራት ነው ።

3_ በኣረብኛ " ደባብ " /mist,fog,haze,smog,blurs ያሰማል ። ከማየትና ከሚታይ ነገር የተያያዘ ። ኣረቦች ኣንድ ጉዳይ " ደባቢያ " ኣለው ሲሉ ብሩህ ኣይደለም ማለት ነው ። ምሳሌ ፥ ባሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ሁኔታ " ደባቢያ " ኣለበት !!

በኛ ድባብ የጸሓይ ብርሃንና ዝናብ ሊከለክል የሚችል ነገር ብቻ ሳይሆን ሃይማኖታዊ ትርጉምም ኣለው መሰለኝ ።
  • ተወዳጅዋና ታላቅዋ የኤርትራ ኣርቲስት በኺታ ዓሊ ፥ ድባብ ( ኤርትራ ኣገሬ ድባቤ ነሽ! )

4_ ከጂዝር --->ጂዝ--->ጂዳ is plausible because to the change of sound there could also be addition or deduction of letters. Example : ኣፍንጫ ---> ኣፍን+ጫ ---> ኣፍን ---> ኣንፍ ( nose in Arabic ! ) . Therefore continue with your search without abandoning some routes too quickly.

5_ " ሰሞኑን ለብቻዬ ሳስብ " ! That is the right way to learn. While thinking you could get a solution to your problem totally unexpected. Your brain could tell you : look at this or look at it this way. Sometimes when that happens it could be really scary, at least in my case in both language and mathematics.

-

Abe Abraham
Senior Member
Posts: 14412
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Abe Abraham » 25 Mar 2023, 13:33

Horus wrote:
20 Mar 2023, 00:29
በሶሪያ አረብኛ ደይዓ ምን ማለት ነው? በትግርኛ ዓዲ ማለትስ?

ስለ...
ሰንዱቅ
ዱቅ
ነቅጅ
ንግድና መንግጅ
ጫማም እንዲሁ ሌላ ግዜ ።

" ዓዲ " በእንግሊዘኛ ሲተረጎም " ቪለጅ " ቢሆንም በኤርትራ " ዓዲ " እንደ የጀርመኑ " ሃይማት " ልዩ ስሜት ይጨመርበታል ። ለምሳሌ እኔ እንደ ኣንድ መሰረቱ ገበሬና ከመሬትና ርስት የተሳሰረ ሰው የኣባቶቻቼና ኣያቶቻቼ " ዓዲ " special sense of being at home ይሰጠኛል ። በሌላ ኣነጋገር " ዓዲ " የሚትኖርበት ቦታ ብቻ ሳይሆን ባንተ ወስጥም የሚኖር ማለት ነው ። ላንተ ለምሳሌ የጉራጌ ህብረተ-ሰብ ቤተ-ሰቦችህን የሚኖሩበት ቦታ (ዓዲ) ስትሄድ ቋንቋው ባህሉ ሃይማኖቱ ተራራውና እርሻው የ " home coming " ና " back to the roots " ስሜት of "ዓዲ " ሊሰጥህ ይችላል ። By extension the whole country - in your case Ethiopia - could be your ዓዲ.

ባማርኛ " መንደር " የሚል ቃል ኣለ ። ካልተሳሳትኩ ትርጉሙ " ቪለጅ " ነው መሰለኝ ። በኣረብኛ "መ " ን በ " በ" ተክተህ " በንደር " የሚባል ቃል ኣለ ። የድሮው ትርጉሙ ፥ sea-town,commercial town. ከሱ የተሳሳረ " ሻህ በንደር " የሚል ስያሜ ኣለ ። ትርጉሙ ፥ የነጋዴዎች ስብስብ ሃላፊ ። በዘመናችን በግብጽ " በናት ኣል-በንደር " / " የከተማ ልጆች/ሴቶች " ሲሉ የ " በንደር " ትርጉም ወደ " ከተማ " የሚለውን እንደ ተራመደ ያመለክታል ። ሁላችን እንደምናውቀው ከተማ የንግድና ሌሎች " ኣክቲቪቲስ " ማእከል ነው ። እንደሚመስለኝ የጉራጌ ነጋዴዎች በኣዲስ ይሁን ሌላ ቦታዎች የራሳቸው " ሻህ በንደር ኣል-ቱጃር " ሳይኖራቸው ኣይቀርም ።

ኬር/ሰሰናዩ !!

-

Horus
Senior Member+
Posts: 30841
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Horus » 25 Mar 2023, 14:22

አቤ፣
በጉራጌኛ ...

አንፉና = አፍንጫ (አባባል፤ አፍ ዪሳተ ባንፉናን ታተ! አፍህ የት እንዳለ ከሳትክ ያለው ካፍንጫ በታች ነው ማለት ነው ! በደደብ ሰው ላይ የሚተረት ነው ።
ታተ = ታች (ታህታይ በግዕዝ)
ገንዳ (ጌኧንዳ) = ጎረቤት
ጌዲ/ጌኧዲ = ቤቴ
ኧዲ/አዲ = እኔ
ነግዳ (ነ ጌ ኧዳ) = እንግዳ (የገንዳ/ጎረቤት ተቃራኒ)
መንደር፣ ወተደር፣ ጌኧየት (ጌያት) = ቪሌጅ
ደር በአረብኛ ደር ነው! ደር/ዱር ሱልጣን ። ምድር ማለት ነው

በነገራችን ላይ ጌ (ጌህ) የጥንታዊ ግብጽ ቃል ነው። መሬት ኧርዝ ማለት ነው ፣ የዛሬ ጂኦ (ጂኦግርፊ) ። ግ ን በአሲሪያ ኢምፓየር ዘመን አስሪያጌ ነበር የሚሉት ዘ ላንድ ኦፍ አሱር/አሲሪያ ማለት ነው ። ቤት አዲስ ቃል ነው ። ነጠላው ባ/ቤ ነው ፣ ከተማ ማለት ይሆናል ። ለምሳሌ ባባ ዋና ከተማ እንደ ማለት ነበር ድሮ ። ቤት የቤ ብዙ ነው ልክ መጻፍ፣ መጻፍት እንደ ምንለው ። ዛሬ ግ ን ቤት የጥቅል ስም ነው ።

Abe Abraham
Senior Member
Posts: 14412
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Abe Abraham » 28 Mar 2023, 16:16

Horus wrote:
25 Mar 2023, 14:22
አቤ፣
በጉራጌኛ ...

አንፉና = አፍንጫ (አባባል፤ አፍ ዪሳተ ባንፉናን ታተ! አፍህ የት እንዳለ ከሳትክ ያለው ካፍንጫ በታች ነው ማለት ነው ! በደደብ ሰው ላይ የሚተረት ነው ።
ታተ = ታች (ታህታይ በግዕዝ)
ገንዳ (ጌኧንዳ) = ጎረቤት
ጌዲ/ጌኧዲ = ቤቴ
ኧዲ/አዲ = እኔ
ነግዳ (ነ ጌ ኧዳ) = እንግዳ (የገንዳ/ጎረቤት ተቃራኒ)
መንደር፣ ወተደር፣ ጌኧየት (ጌያት) = ቪሌጅ
ደር በአረብኛ ደር ነው! ደር/ዱር ሱልጣን ። ምድር ማለት ነው

በነገራችን ላይ ጌ (ጌህ) የጥንታዊ ግብጽ ቃል ነው። መሬት ኧርዝ ማለት ነው ፣ የዛሬ ጂኦ (ጂኦግርፊ) ። ግ ን በአሲሪያ ኢምፓየር ዘመን አስሪያጌ ነበር የሚሉት ዘ ላንድ ኦፍ አሱር/አሲሪያ ማለት ነው ። ቤት አዲስ ቃል ነው ። ነጠላው ባ/ቤ ነው ፣ ከተማ ማለት ይሆናል ። ለምሳሌ ባባ ዋና ከተማ እንደ ማለት ነበር ድሮ ። ቤት የቤ ብዙ ነው ልክ መጻፍ፣ መጻፍት እንደ ምንለው ። ዛሬ ግ ን ቤት የጥቅል ስም ነው ።
የጉራጌው " ታተ " የኣማርኛው " ታች" የ ትግርኛው " ታሕቲ " የኣረብኛው ደሞ " ታሕት " ነው ። በትግርኛ " ታሕታይ" ትርጉሙ " lower" ሲሆን " upper " ለማለት ከተፈለገ ደሞ " ላዕላይ '' እንጠቀማለን ። ስለሆነም በኤርትራ በኣንድ መንደር - እንደ ኣንድ ህንጻ - ለምሳሌ የፕረዚደንት ኢሳያስ ኣፈወርቂ ኣብራሃም የኣባቶቹና ኣያቶቹ መንደር "ጸሎት" በኣስመራ/ሰሓርቲ/ሓማሴን ( ከደብረ ቢዘን የኣቡነ ፊሊጶስ ብዙ ያልራቀ ) " ጸሎት ታሕታይ ፡ ጸሎት ላዕላይ " ተብሎ ይጠራል ። ፕረዚደንት ክሊንተን በኣሜሪካ ለከፍተኛው ስልጣን ሲወዳደር ስለ ኦሪጅኑ/መበቆሉ ኣንስተው " The Man From Hope " በሚል ስያሜ ቪድዮኣዊ የሂወቱ ትረካ ኣቅርበውለት ነበር ። በተመሳሳይ በኤርትራ ፕረዚደንት ኢሳያስ ኣፈወርቂ ኣብራሃም " The Man From The Village Called PRAYER " ነው ለማለት እንችላለን ። " ኣፈወርቂ " በሚመለከት ምንጩ በታች የሚከተለውን ታሪክ መሆኑን እንደምታውቅ ምንም ጥርጥር የለኝም ፥

https://en.wikipedia.org/wiki/John_Chrysostom
John Chrysostom (/ˈkrɪsəstəm, krɪˈsɒstəm/; Greek: Ἰωάννης ὁ Χρυσόστομος; Ge'ez[citation needed] :ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ c. 347 – 14 September 407)[5] was an important Early Church Father who served as archbishop of Constantinople.

በጉራጌኛ " ታተ " ባማርኛ " ታች " በትግርኛ " ታሕቲ " በኣረብኛ " ታሕት " ኣንስተን ስለ " ላይ "(ኣማርኛ) ና " ላዕሊ/ የኣረብኛ ዓሊ(high) ዘመድ " ( በትግርኛ) ሳንናገር ዝም ለማለት ኣንችልም ። ስለሆነም " ፈውቕ " በኣረብኛ የ " ታሕት " ተቃራኒ እያለ በኣማርኛ " ፎቅ " የሚለው ቃል ሰዎች ለሌላ ተመሳሳይ ሃሳብ ይጠቀሙበታል ወደሚለውን ትርክት ይወስደናል ። ከዚያም ወደ ጣፋጭ ህጻንነትን የሚያስታውስ ቪድዮ ፥
ኣስተውል ፥ በሶርያ ግብጽ ሌባኖንና ፍልስጤም የመሳሰሉ የኣረብ ኣገሮች በ " ኮሎኰያል " ኣነጋገር " ቐ " ን እንደ " ኣ" ኣድርጎ የማድመጽ ልምድ ኣለ ።

-

Horus
Senior Member+
Posts: 30841
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Horus » 29 Mar 2023, 00:22

አቤ፣
ትክክል፤ ጉራጌም ላለ (ለዕለ) ነው የምንለው ። በጉራጌኛ ሰሜንና ደቡብ ብዙ አንጠቀምም ። ሰሜን ለማለት ላለጌ/ላሊጌ እንላለን። ደቡብ ለማለት ታተጌ/ታቲጌ ነው የምንለው። ለምሳሌ የሰሜን ሰው ለማለት ዬላለጌ ሰብ ፣ ዬታተዴ ሰብ እንላለን ። ለምሳሌ ዝነኛው የጉራጐ ዘፈን ሁሉ አዝማች የሆነው ላሌ ዪቦ ላለ ድሮ የሃይማኖት መወድስ የነበረ ይመስለናል ! ትርጉሙ የባሉ ሁን በላይ! የበላይ በላይ ሁን፣ ግነን ታላቅ ሁን ማለት ነው ። ዛሬ ግ ን ከፍተኛ ደስታ ይሁን እንደ ማለት ነው። በዚህ የተነሳ ነው ከብዙ ሰዎች ጋራ ስለ ላሊበላ ትርጉም የማልስማማው ! እነሱ ንብ በላ ማለት ይላሉ፣ በአገውኝ ላሌ ንብ ስለሆነ። እኔ ግ ን ላሊበላ የግዕዙ ላለበላይ የበላይ በላይ፣ ንጉሰ ነገስት ማለት ነው ብዬ የማምነው! ምን ይመስልሃል?

በተረፈ ከላይ ባነሳናቸው ቃላት ላይ ... በጉራጌኛ ...
ሳጥ = ደብቅ ሳጥን ከዚያ የመጣ ነው
ውስጢር = ምስጢር
መንግጅ = ንግድ
ሽካ = ሙያ፣ የጅ ጥበብ
ሸክት = ስራ፣ ገምባ። ፍጠር
ሸቀጥ = በጅ የተሰራ ቁሳቁስ ስኬት የሚለው ቃል ከዚያ የመጣ ነው
ሰንዱቅ = አነስ ያለ የሸቀጥ መያዣ ሳጥን ነው እንጂ ቤት ውስጥ ልብስ የሚቀመትበት አይደለም እኛ !

Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Meleket » 29 Mar 2023, 05:58

ባናቱ ሲጀምር "ግእዝ ቃላት" ማለት ስህተት ነው። "ቃላት ግእዝ" ነው ዬሜባለው። ሲቀጥል ትምህርቱ መልካም ነው ምንም ኣዪል. . . :mrgreen:
Abe Abraham wrote:
03 Mar 2023, 15:18
ግእዝ ቃላት
እንደገና ሲቀጥል ኣጭቤው Abe Abraham እንዲህ ብለሃል፦
Abe Abraham wrote:
28 Mar 2023, 16:16
የጉራጌው " ታተ " የኣማርኛው " ታች" የ ትግርኛው " ታሕቲ " የኣረብኛው ደሞ " ታሕት " ነው ። በትግርኛ " ታሕታይ" ትርጉሙ " lower" ሲሆን " upper " ለማለት ከተፈለገ ደሞ " ላዕላይ '' እንጠቀማለን ። ስለሆነም በኤርትራ በኣንድ መንደር - እንደ ኣንድ ህንጻ - ለምሳሌ የፕረዚደንት ኢሳያስ ኣፈወርቂ ኣብራሃም የኣባቶቹና ኣያቶቹ መንደር "ጸሎት" በኣስመራ/ሰሓርቲ/ሓማሴን ( ከደብረ ቢዘን የኣቡነ ፊሊጶስ ብዙ ያልራቀ ) " ጸሎት ታሕታይ ፡ ጸሎት ላዕላይ " ተብሎ ይጠራል ። ፕረዚደንት ክሊንተን በኣሜሪካ ለከፍተኛው ስልጣን ሲወዳደር ስለ ኦሪጅኑ/መበቆሉ ኣንስተው " The Man From Hope " በሚል ስያሜ ቪድዮኣዊ የሂወቱ ትረካ ኣቅርበውለት ነበር ። በተመሳሳይ በኤርትራ ፕረዚደንት ኢሳያስ ኣፈወርቂ ኣብራሃም " The Man From The Village Called PRAYER " ነው ለማለት እንችላለን ። " ኣፈወርቂ " በሚመለከት ምንጩ በታች የሚከተለውን ታሪክ መሆኑን እንደምታውቅ ምንም ጥርጥር የለኝም ፥

https://en.wikipedia.org/wiki/John_Chrysostom
John Chrysostom (/ˈkrɪsəstəm, krɪˈsɒstəm/; Greek: Ἰωάννης ὁ Χρυσόστομος; Ge'ez[citation needed] :ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ c. 347 – 14 September 407)[5] was an important Early Church Father who served as archbishop of Constantinople.

ወደ ቁምነገሩ ስንሄድ ተወደ ጎንደር "ታች ቤት" "ላይ ቤት" የሚባል የትምህርት ክፍል እንዳለ ሲነገር እንሰማለን። ሁለቱ የትምህርት ክፍሎች የተለያዩበት የራሳቸው ምክንያት እንዳላቸውም ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የታላቁ የኢትዮጵያ መሪ የዶ/ር ዐብዪ ኣህመድ ዓሊ ኣማካሪ እንዲህ ኣስቀምጦት ነበር።

በጎንደር መምህር ኤስድሮስ የሚባሉ መምህር ነበሩ አሉ፡፡ መጻሕፍቱን ሁሉ መርምረው ትርጓሜ አቅንተው ሲያስተምሩ ኖሩና ‹ምናልባት ያልደረስንበት አዲስ ነገር ቢኖርስ› ብለው በዚያ በጣና ገዳማት ውስጥ ገብተው መጻሕፍቱን ሁሉ ሲያገላብጡ ኖሩ አሉ፡፡ እውነትም ያልደረሱበት ብዙ ነገር ቢያገኙ ተማሪዎቻቸውን እንደገና ጠርተው ‹እኔም ያላወቅኩት እናንተም ያልተማራችሁት አዲስ ነገር አግኝቻለሁና ኑ እንደገና እንማር› ብለው ሰበሰቧቸው፡፡ እሺ ብለው ለአዲስ ዕውቀት የመጡ አሉ፡፡ እምቢ ብለው በቀድሞው ብቻ የቀሩ አሉ፡፡ እሺ ብለው የመጡት የሄዱበት መንገድ ‹የታች ቤት ትርጓሜ› ተባለ፡፡ እምቢ ብለው የቀሩት የሄዱበት መንገድ ደግሞ ‹የላይ ቤት ትርጓሜ› ተባለ፡፡

እናማ ስለ "ላይ ቤት - ታችቤት ጸሎት" ከተነሳ ዘንድ "ላይቤት ታች ቤት" የተባለበት ምክንያት ምንድን ይሆን? :mrgreen: ከጸሎት ደብረቢዘን ለመድረስ አንድም ጕልዒን ከዚያም ነፋሲትን ማለፍ፤ በማይ ሓባር በኩልም ከሆነ የኤርትራ የጦር ጉዳተኞች ካምፕና ቴክኒካል ትምህርት ቤት የሚገኝበትን ማይ ሓባርንና ለዓዪተንንም ማለፍ ያስፈልጋል። ደብረቢዘን በትግርኛ በሳሆ እና በትግረ ተናጋሪዎች የተከበበች ድንቅ ገዳም ነች። ንጉሥ ባዜን የተባለ ኩናማም ኖሮባታል ይባላል፤ ስሙንም ከእርሱ ወይ ከባይዛንታይን ዬወሰደችው ሳይሆን ኣይቀርም። ለዚህ ማስረጃ የሚሆንም ከዬት እንዳነበቡት ባናውቅም ኣንድ የኬንሻ ቄስ እንዲህ ብለው ኣጫውተውን ነበር " ፈረንጆቹ በምጥዋ በኩል ወደ ኤርትራ ሲገቡ፤ የአሁኗ ጊንዳዕና ኣካባቢዋ ላይ ጸጉራቸውን እንደ የአሁን ኩናማዎች "በጭቃ ነገር" የሚቀቡ ማሀበረሰቦች ቆይተዋቸው ነበር፤ ይህ ማለትም ከላይኛው የንጉሥ ባዜን ትርክት ጋር ይስማማል። አጤ ኃይለስላሴም ትልቅ ቤተክርስትያን ሳይሰሩበት አልቀሩም ቢዘን ኣናቱ ላይ። በመሆኑም የጦብያ ኣንዳንድ ተስፋፊዎች "ርስታችን ነው" ሲሉ ይደመጣሉ።

ግእዝ የሚለው ቃል ሲነሳ "ሓወልቲ መጠራ" እንደሚነሳ ሁሉ፤ ደብረቢዘን ሲነሳ፡ የኤርትራ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ኣብሮ ይነሳል፡ የኤርትራ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ሲነሳም፡ የሕምብርቲው ቅዱስ ሰማእቱ ፓትርያርክ እንጥንዮስ ይነሳሉ። ሶስተኛው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ፓትርያርክ፤ በረከታቸው በኛ ላይ ይደር።

ኦ ብጹዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ እንጥንዮስ ለምንሉን!

Horus
Senior Member+
Posts: 30841
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Horus » 29 Mar 2023, 22:42

መለከት፣
የታች ጸሎት? የላይ ጸሎት ምንድን ናቸው? የምድር ጸሎት፣ የሰማይ ጸሎት ማለት ነው ። አንዱ ለስጋ ለዚህ ምድር ሕይወት ሌላው ለሰማያዊ ሕይወት የሚደረግ ጸሎት ነው ። አንዱ ለመንግስተ ምድር ሌላው ለመንግስተ ሰማይ የሚድረግ ጸሎት ነው ።

Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Meleket » 30 Mar 2023, 05:13

እንዲያ ኣይደለም ወንድማችን Horus፡ ጎንደሮች፡ ኣርማጭሆን “ላይ ኣርማጭሆ” እና “ታች ኣርማጭሆ” ብለው ደጋውንና ቆላውን ኣርማጭሆ ነው መሰል ለመለየት ሞክረዋል። ልክ በዚህ መልኩም “ጸሎት” ተብላ ከአስመራ ኣቅራቢያ የምትታወቅ ኣንዲት መንደር ኣለች። ይህቺ መንደር “ላይኛዋ ጸሎት” እና “ታችኛዋ ጸሎት” ተብላ “ቨርቺዋሊ” ከሁለት ትከፈላለች። የወቅቱ የኤርትራችን ብረዚደንት ከዚች መንደር የፈለቁ ናቸው ለማለት ነው እየሞከረ ያለው ኣጭቤው Abe Abraham። ኣጭቤው ነገሩን ስለዘበራረቀው እንጂ አንተ እንደገመትከውና እንደመሰለህ “ከመንፈሳዊው ጸሎት” ጋር ኣይደለም ግንኙነቱ። እኛ ደግሞ “ላይኛዋ ጸሎት” እና “ታችኛዋ ጸሎት” በምን ኣጋጣሚና ምክንያት ነው ‘ቨርቺዋሊ’ ከሁለት የተከፈሉት ብለን ጠየቅነው ኣጭቤውን Abe Abraham ቢዘንን ስላነሳ ደግሞ እኛም ሰማእቱን ኤርትራዊ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ፓትርያርክ እንጥንዮስን ዘከርን፡ በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።

ይሄው ደግመህ ኣንብበው

Horus wrote:
29 Mar 2023, 22:42
መለከት፣
የታች ጸሎት? የላይ ጸሎት ምንድን ናቸው? የምድር ጸሎት፣ የሰማይ ጸሎት ማለት ነው ። አንዱ ለስጋ ለዚህ ምድር ሕይወት ሌላው ለሰማያዊ ሕይወት የሚደረግ ጸሎት ነው ። አንዱ ለመንግስተ ምድር ሌላው ለመንግስተ ሰማይ የሚድረግ ጸሎት ነው ።
Meleket wrote:
29 Mar 2023, 05:58

Post Reply