Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abe Abraham
Senior Member
Posts: 14412
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Abe Abraham » 10 Mar 2023, 15:40

Horus wrote:
10 Mar 2023, 15:16
Abe Abraham wrote:
10 Mar 2023, 14:36
Horus wrote:
10 Mar 2023, 14:00
Abe,
አንድ ነገር ብቻ ባስቸኳይ ልበል። ቆወል የሚለው ክወል፣ ክወር፣ ሃወር፣ ሃውርር፣ አውርር እያለ ይረባል ። ወ ድሮ ድሮ አፍ ማለት ነበር፤ ምልክትና ትርጉም አንድ በነበሩበት ዘመን ከ/ቀ ፕሪፊክስ ቅጽል መሆን አለበት ። እኛ መናገር ስንል ሃውር፣ አውር። አውርር ነው የምንለው። ወሬ የነገር ስም ነው ። ዜና/ዝና ስሩ ሌላ ነው ። አንደ ነገረ መንገር (ቱ ቴል) አውድ እንለዋለን በጉራጌ፤ ባማርኛ አውጋ የሚባለው ማለት ነው። ስለዚህ ሃወር እና አውድ/አውጋ ካየህ ሁለቱም ወ አላቸው! ኤቲማ ማለት ያ ነው። ከ/ገ/ ቀ ከፊትና ከኋል ሲቀጠል ታያለህ ።

ረዋ ማስተላልፈ ያው መንገር ማለት ነው ። መረዋ ማለት ነው። ግን ወ እዚያም አለ ።

ኬር!
ዜና ያነሳሁት ለሚነገር ነገር ምሳሌ ለመስጠት ነው ። በኣረብኛ رَوَى الأَخْبارَ ( ረዋ ኣል-ኣኽባራ ...) ዜናውን ኣስተላለፈ ማለት ነው ።

ኣረቦች ከረዋ ያወጡት ሪዋያ ( story) የሚል ቃል ኣላቸው ኣንተ የጠቀስከው " መረዋ " መሰረቱ ከየት ነው ? ግእዝ ?

-
"ረዋ ማስተላልፈ ያው መንገር ማለት ነው ። መረዋ ማለት ነው። ግን ወ እዚያም አለ ።"

ረዋ ላልከው ምሳሌ ነው የሰጠሁህ (መረዋ) ማለት ድምጽ ማስተላለፍ ስለሆነ መረዋ/በረዋ ከላይ ያለው 'ወር ነውኮ!
Thanks.

Abe Abraham
Senior Member
Posts: 14412
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Abe Abraham » 10 Mar 2023, 16:11

I have discovered something with regard to ጋረደ in Arabic but I want to know whether the meaning of ጋረደ in Amharic includes ከለለ. We know that Geez does.
GEEZ DICTIONARY

ጋረደ

አንጦለለ ፣ ከለለ ፣ ጠውለለ ፣ ጸለለ ፣ ቀመረ ፣ ከተረ

-

Abe Abraham
Senior Member
Posts: 14412
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Abe Abraham » 10 Mar 2023, 18:39

  • እዛ ኣብ ላዕሊ ትርእይዋ ዘለኹም ናይ ቪድዮ ጸብጻብ ብዛዕባ እስራኤላውያን ብናይ ጸጥታ ስግኣት ኣመኽንዮም ንዐዖምን ንፍልስጤማውያንን ክፈሊ ዝሰርሕዎ " ኣል-ጂዳር ኣል-ዓዝል " ትዛረብ ። ሕጂ ንሕና ኣድህቦና ኣብ ፖለቲካ ዘይኮነ ኣብ ቋንቋ እዩ ። ማለት ብፍላይ ኣብ " ጂዳር " ዝብል ቃል ። ከምቲ ኣብ ዓረብ " ጀመል " ክበሃል እንከሎ ኣብ ትግርኛ ድማ " ገመል " ዝበሃል ብኡ መሰረት ን " ጀ " ብ " ገ " ተኪእና ኣብ ቦታ " ጂዳር " ጊዳር ይህልወና ። ተማም ዶ ? ግርም !! ናይ " ጊዳር " ፊደላት ገግእዞም(ቀዳማይ ፊደሎም) እንተ ወሲድና " ገደረ " ይህልወና ። ነቲ ፊደላዊ ኣሰራርዓ ናይ " ገደረ " ኣብ ክንዲ " 123 " ናብ " 132 " እንተቀየርናዮ ኸ እንታይ ንረክብ ? መልሲ ፥ ገረደ !! ካብ ገረደ ኣብ ትግርኛ እንታይ ይወጽእ ? መልሲ ፥ ጋረደ !!! እስራኤል ንፍልስጤማውያን ንመሬቶም ብስግንጢር ዝገማምዕ ፈላላዪ ጋራዲ መንደቕ ምስ ሰርሑሎም " ኣል-ጂዳር ኣል-ዓዝል " ዝብል ስም ኣውጺኦም ንዓለም ኣውያቶም ከስምዑ ጽዒሮም ። ስጋዕ ሕጂ ድማ የእውዩ ኣለዉ ።

-
  • ዓቢ ፍልስጤማዊ ገጣማይ ነፍስ-ሄር ማሕሙድ ደርዊሽ !!!!!

Horus
Senior Member+
Posts: 30657
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Horus » 10 Mar 2023, 21:17

Abe,
" ጋረደ
አንጦለለ ፣ ከለለ ፣ ጠውለለ ፣ ጸለለ ፣ ቀመረ ፣ ከተረ"

ጋራደ፣ ጋረጠ፣ ጋሬጣ (ከፊት ለፊት ሆኖ እንዳናይ እንዳናልፍ የሚገታን ባሪየር ወይም ኮንስትሬይንት! ጋረደ መጋረዳ፣ መጋረጃ። አንጦለለ (=አን(ኮ)ለለ፣ ከለለ)፣ ጠውለለ (= ጠ(ው)ለለ፣ ጸለለ፣ ጥላ፣ ከለላ ። በጉርጌኛ ጥላል (shade, shadow)፣ ጥላ (ዣንትላ አምበሬላ) ነው ። ስለዚህ ጋረደና ከለለ ትርጉማቸው ይለያያል ።

ቀመረ = ከመረ፣ ሰበሰበ ። ዉሃ ስንከትር ስንገድብ ዉሃ እንከምራለን፣ እንሰበስባለን!

ከተረ ( = የጥምቀት ከተራ!) እዚህ እንዴት እንደ ተጠቀሙበት ተመልከት ። ከተረ (ገተረ) ፣ አቆመ፣ ገታ፣ ከለከለ ሲሆን የጥምቀት የሚሆን ዉሃ በገንዳ ወይም በወንዝ ገድቦ መያዝ ማለት ነው። ዛሬ የታቦቶች አንድ ላይ መሰብሰብ ብለውም ይተረጉሙታል ። ሰለዚህ ከተረ ፣ ገተረ፣ ገደበ ማለት ነው ። ለምሳሌ የአባይ ዉሃ ሙሌት የአባይ ከተራ ቢባል ነው ። ከተረ= ገደበ!

ስለዚህ ሶስቱም ጋረደ፣ ጠለለ፣ ከተረ የተለያዩ ቃላት ናቸው ። ከለለ እና ጋረደ በተልምዶ በተለዋዋጭነት ተጠቅመንባቸዋል ። ግ ን ልብ በል 3ቱም ከ2 ተመሳሳይ ድምጾች ነው የተቀመሩት ...
ጋረደ (ካ ራ ካ)
ጠለለ (ካ ራ ራ)
ከተረ (ካ ካ ራ)
የድምጾቹ ሺፍትና የቦታዎቹ መቀያየር ተመልከት! አልጎሪዝሙን እያስጨበጥኩህ ነው

ሰላም

Abe Abraham
Senior Member
Posts: 14412
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Abe Abraham » 11 Mar 2023, 00:24

Horus wrote:
10 Mar 2023, 21:17

ጥላል በትግርኛ ጽላል ነው ። ምግታር በትግርኛ ለመቆምና ኣቋም (negatively) ነው የምንጠቀመው ። ገታ ( ገትአ= to stop an enemy, a challenge). ክትራ ከከተረ በትግርኛ ለውሃና ለሰው ( ባሁኑ ጊዜ በመቀሌ የሚታየው ሰዎች በመንገድ ኣቁሞ መዝረፍ ) እንጠቀምበታለን ።

በጋረደ ያተኮርኩት ምክንያት ኣረቦች ጂዳር የሚል ቃል ስላላቸው ነው ። ከጂዳር ---> ጊዳር ---> ገደረ ----> ገረደ --->ጋረደ እናገኛለን ። ለምሳሌ እስራኤል ለሰራችውን separation barrier ኣል-ጂዳር ኣል-ዓዝል ብለው ይጠሩታል ።

ወደ ጥላል ስንመለስ ሰይድ ቑጥብ " ፊ ላል ኣል-ቑርኣን "/ In the shadows of the Qur'an የሚል መጽሓፍ ጽፎ ነበር ። ኣረብኛ በየቃል መጀመርያ ሳድስ ኣያፈቅድም !

ጥላ (ዣንትላ አምበሬላ) ነው።
ኣረቦች ለፓራሹት ሚዘላ(ሚ ተጨማሪ ፊደል ነው ) ብለው ይጠሩታል ።

-
Last edited by Abe Abraham on 11 Mar 2023, 12:14, edited 1 time in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 30657
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Horus » 11 Mar 2023, 01:34

Abe,

ከለለ የሚባለው ቃልማ ይህው ሌት ተቀን የሚያስጨንቀን ክልል የሚባለው ጉድ ነውኮ ! የቃሉ ስር 'ክል' ነው (ክልክል)! ኬላ፣ ክልል። በጉራጌኛ በጣም ተራ ቃል ነው ። ክላ አቤ ማለት ወዲያ ወግድ ምለት ነው። ኳ ምኝት ከላዬም ስል እሱ እንቅልፍ ከልክሎኛል ማለቴ ነው ።

ገደረ፣ ገታ! የሚገርመው በጉራጌ ገታ (ታ ይለሰልሳል) የሳር አይነት ነው ። ባማርኛ ሰርዶ የሚባለው ትልፍልፍ አስቸጋሪ ሳር ገታ እንለዋለን ። ገደረ ከሚለው የተጠጋ ትልቅ ቃል አለ በጉራጌኛ፤ ግድር ይባላል፤ ታላቅ ማለት ነው ። ለሰው ነው ጥቅሙ ። ግድር ሰብ ማለት ታላቅ ሰው ማለት ነው ። በታሪክ ውስጥ አጼ ኢዛና ከተዋጋቸው ነጋሲዎች ውስጥ ነጋሲ ግድር የሚባል ሰው አለ በዶሮሴ መጻፍ ውስጥ ! ዛሬ ላይ ግድር የሚለው ቃል ያለው በጉራጌኛ ውስጥ ብቻ ነው ። ታላቅ ሰው ለማለት ጉራጌ ሁለት ቃላት አሉን፣ አንዱ ማለቅ ይባላል፣ (ማለቅ ሰብ) ሌላው ግድር ነው፣ (ግድር ሰብ)

Abe Abraham
Senior Member
Posts: 14412
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Abe Abraham » 11 Mar 2023, 12:11

Horus wrote:
11 Mar 2023, 01:34
Abe,

ከለለ የሚባለው ቃልማ ይህው ሌት ተቀን የሚያስጨንቀን ክልል የሚባለው ጉድ ነውኮ ! የቃሉ ስር 'ክል' ነው (ክልክል)! ኬላ፣ ክልል። በጉራጌኛ በጣም ተራ ቃል ነው ። ክላ አቤ ማለት ወዲያ ወግድ ምለት ነው። ኳ ምኝት ከላዬም ስል እሱ እንቅልፍ ከልክሎኛል ማለቴ ነው ።

ገደረ፣ ገታ! የሚገርመው በጉራጌ ገታ (ታ ይለሰልሳል) የሳር አይነት ነው ። ባማርኛ ሰርዶ የሚባለው ትልፍልፍ አስቸጋሪ ሳር ገታ እንለዋለን ። ገደረ ከሚለው የተጠጋ ትልቅ ቃል አለ በጉራጌኛ፤ ግድር ይባላል፤ ታላቅ ማለት ነው ። ለሰው ነው ጥቅሙ ። ግድር ሰብ ማለት ታላቅ ሰው ማለት ነው ። በታሪክ ውስጥ አጼ ኢዛና ከተዋጋቸው ነጋሲዎች ውስጥ ነጋሲ ግድር የሚባል ሰው አለ በዶሮሴ መጻፍ ውስጥ ! ዛሬ ላይ ግድር የሚለው ቃል ያለው በጉራጌኛ ውስጥ ብቻ ነው ። ታላቅ ሰው ለማለት ጉራጌ ሁለት ቃላት አሉን፣ አንዱ ማለቅ ይባላል፣ (ማለቅ ሰብ) ሌላው ግድር ነው፣ (ግድር ሰብ)
1_በትግርኛ ደስ የማይለህና ያልሆነ ነገር ስትሰማ " ክላእ " የሚል ቃል ትጠቀማለህ ። " ወዲያ ወግድ " ነው የሚያሰማው ። ለምሳሌ ኣንድ ሰው መጥቶ " በ300 ብር የፕለይን ትኬት ወደ ኣሜሪካ እየሸጡ ነው " ሲልህ " ክላእ ንስኻ ድማ ሱቕ ኢልካ ዝኾነ ትኣምን ! / ኣንተ ደሞ ወግድ ዝም ብለህ ያልሆነውን ታምናለህ ! " ብለህ ልትመልስለት ትችላለህ ። ጥያቄ ፥ ከለከለ ከ ከለለ ግኑኝነት ኣለው ወይ ? ኣንተ የተጠቀምከውን በጣም ኣስፈላጊ ቃል ተጠቅሜ ከለከለ በይዞታው ከ ከለለ የተጠጋ ነው ወይ ? ( ስለ ቃላት ጉንኙነት ስትናገር ሁል ጊዜ መነሻህ 100% መሆን ጥሩ ኣይደለም ማለቴ ነው ። )

ሌላ በትግርኛ ከ ከልከለ ( ከለከለ) በስተቀር ከልአ / refuse to give something; deny / የሚባል ቃል ኣለ ።

2_ በትግርኛ በ ገ+ደ+ረ የቆመ " ዳርጋ " የሚባል ቃል ኣለ ። " መዳርግቲ ዘይብሉ " ስንል " incomparable ማለት ነው ። እብራይስጦች " ጋዶል" ሲሉ ትልቅ (በመጠን መሰለኝ) ማለታቸው ነው( በትግርኛ ክንዲ ገደል = ግዙፍ) ። በትግርኛ " ይከኣሎ/omnipotent " የምንለው በኣረብኛ " ቐዲር/ገዲር '' ነው !! በትግርኛ " ከኣለ " ስንል ኣማርኛ በ"ከ" ምትክ "ቸ" መርጦ "ኣ" ን ኣስወግዶ " ቻለ " ይላል ። ድሮ በኤርትራ " ይቻላል " የምትለውን ቃል የሚወድ መጠርያ ስሙ ኣድርገን የወሰድነው ኢትዮጵያዊ የፋሚሉ ፍሬንድ ነበረን ። የድሮ ሰዎችን ስላነሳሁ ሌላው ምስርን የማይወድ የጉራጌ ተወላጅ ፋሚሊ ፍሬንድ ደሞ በትግርኛ " ብርስን የራስን / ብርስን ሙቀት(ደስ የማይል) ይዞ ይመጣል " ብሎ ያስቀን ስለ ነበር የሱን ማስታወቅያ ሆነች!

በጉራጌኛ " ማለቅ "/ታላቅ ሲባል ኣረቦች ደሞ ኣድንቆታቸው ለመግለጽ " ዒምላቕ " /huge,gigantic,super/ የሚል ቃል ይጠቀማሉ ። በኣረቦች ኣነጋገር ሰው በኣካሉ ይሁን በስራው ዒምላቕ ተብሎ ሊጠራ ይችላል ። ለምሳሌ ቴዲ ኣፍሮ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ዒምላቕ ነው ልትለው ትችላለህ ።

Horus
Senior Member+
Posts: 30657
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Horus » 11 Mar 2023, 14:24

በቋንቋ ሳይንስ ውስጥ በተለያየ ቦታና ካልቸር ውስጥ የሚኖሩ ሕዝቦች በስረ ግንዳቸው ዝምድና ወይም ትስስር እንዳላቸውና እንደሌላቸው መፈተሻው አንዱ ዘዴ (ሜትዶሎጂ) እነዚህን መሰል ግዙፍ ግዜ የማይለውጣቸው ቃላቶች ላይ አንድ መሆናቸውን በመመርመር ነው ። ለምሳሌ የአባት ስም፣ የእናት ስም፣ የፈጣሪ ስም፣ የምድር፣ የሰማይ ፣ ስም ወዘተ ።

ስለዚህ በእብራይስጥ ጋዶል (ጋዶር/ግድር)፣ በትግርኛ ገደል (ገደር/ግድር)፣ በአረብኛ ቀዲር፣ ከዲር፣ ገዲር ሁሉም አንድ ትርጉም ነው ያላቸው ። ታላቅ ኅያል ማለት ነው ። ግን ከግዜ ብዛት ትርጉማቸው ሊሰፋና ሊጠብ ይችላል ። ለምሳሌ ማለቅ (የአረብኛው ማሊክ ድሮ ንጉስ ማለት ነበር በጉራጌም ቢሆን። ዛሬ ሰው ላልሆነ ነገር ሁሉ ማለቅ እንላለን፤ ለምሳሌ ማለቅ ምካት ስንል ትልቅ ችግር ማለታችን ነው ።

ኢምላቅ፣ ማለቅ ፣ ሊቅ (የላቀ፣ ሊቀ ሊቃውንት!)

ከለለ ከለከለ ማለት ነው ። በኢትዮፒክ አንድን ቃል ለማጥበቅ ቃሉን እንደግመዋለን (ኢንቴንሲቭ ለማድረግ) ። ስለዚህ ክልል/ከለለ ማለት ወሰን አበጀ፣ ለየ ማለት ሲሆን (ይህ ክላ የሚለው ነው) ክልክል የከለለ ማጥበቂያ ነው ። ክልክል ወደን ብቻ ሳይሆን ወሰኑን አለማለፍ አለት ነው።

ስለዚህ የኢትዮጵያ ክልል ሲስተም የሰሩት አላዋቂ ጎሬላዎች በጣም ኔጌቲቭ የሆነ ቃል ነው የተጠቀሙት ።

Horus
Senior Member+
Posts: 30657
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Horus » 11 Mar 2023, 20:30

Abe,
የዛሬ ሳምንት ከዚህ በታች ያለውን ነግሬህ ነበር ። በለቅሶ ሙሹ ከቀብር በፊት ሴቶቹ ሲያቦሱ ተመልከት! አቦሰ (ታቦስሕ ታበጽህ) ማለት ያ ነው!

"ለምሳሌ ሌላ ግዕዝ ልጥቀስልህ!

ኢትዮጵያ ታበጽህ እደዊሃ አበ አግዚአብሄር ይባላል ። ሁሉም ሰው እድ (እጅ) እንደ ሆነ ያውቃል ። ለምሳሌ ተግባረ እድ ሰለሚባል ። ነገር ግን አቦሰ፣ ዋቡስ፣ አቡስም የምንለው ጉራጌዎች ብቻ ነን። አቦሰ፣ ዋቡስ አብስህ (ጸ(ን) በ ሰ ሺፍት አድርገን ማለት አነሳ፣ ማንሳት፣ እጆች ወደ ሰማይ መዘርጋት ማለት ነው ።

ለምሳሌ በጉራጌ የባህል ለቅሶና ሙሾ ሴቶች ለብቻ ፣ ወንዶች ለብቻ በሰልፍ ሆነው ሁለት እጆቻቸውን ወደ ሰማይ በማንሳት በዋቡስ የኦፈን ያሉ በዜማ ሙሾ ያዜማሉ ! ያ በብሸ (በለቅሶ) ዋቡስ፣ ዋቦስ ይባላል ። ያ ነው ግዕዝ ታበጽህ (ታበስህ) የሚለው ። ይህ ቃል ከችግር፣ ከምህላ ከሃዘን ጋር ስለተያያዘ ይመስለኛል አበሳ (ጣጣ) ወይም መከራ ከቃሉ ጋራ የተያያዘው !!"

Abe Abraham
Senior Member
Posts: 14412
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Abe Abraham » 12 Mar 2023, 02:14

Horus wrote:
11 Mar 2023, 20:30
Abe,
የዛሬ ሳምንት ከዚህ በታች ያለውን ነግሬህ ነበር ። በለቅሶ ሙሹ ከቀብር በፊት ሴቶቹ ሲያቦሱ ተመልከት! አቦሰ (ታቦስሕ ታበጽህ) ማለት ያ ነው!

"ለምሳሌ ሌላ ግዕዝ ልጥቀስልህ!

ኢትዮጵያ ታበጽህ እደዊሃ አበ አግዚአብሄር ይባላል ። ሁሉም ሰው እድ (እጅ) እንደ ሆነ ያውቃል ። ለምሳሌ ተግባረ እድ ሰለሚባል ። ነገር ግን አቦሰ፣ ዋቡስ፣ አቡስም የምንለው ጉራጌዎች ብቻ ነን። አቦሰ፣ ዋቡስ አብስህ (ጸ(ን) በ ሰ ሺፍት አድርገን ማለት አነሳ፣ ማንሳት፣ እጆች ወደ ሰማይ መዘርጋት ማለት ነው

ለምሳሌ በጉራጌ የባህል ለቅሶና ሙሾ ሴቶች ለብቻ ፣ ወንዶች ለብቻ በሰልፍ ሆነው ሁለት እጆቻቸውን ወደ ሰማይ በማንሳት በዋቡስ የኦፈን ያሉ በዜማ ሙሾ ያዜማሉ ! ያ በብሸ (በለቅሶ) ዋቡስ፣ ዋቦስ ይባላል ። ያ ነው ግዕዝ ታበጽህ (ታበስህ) የሚለው ። ይህ ቃል ከችግር፣ ከምህላ ከሃዘን ጋር ስለተያያዘ ይመስለኛል አበሳ (ጣጣ) ወይም መከራ ከቃሉ ጋራ የተያያዘው !!"

1_I find the video and its solemnity very moving.

2_ In Tigrigna too we have ተብጽሕ( ታብጽህ በግእዝ ) in the sense of to drive to, to arrive at and visit ( ምብጻሕ)። All of thems words related to movements with a direction. For unknown reason many Tigrayans ( who didn't get opportunity and help to develop their language skills ) have trouble using ምብጻሕ . They resort too quickly to ጎብንዩ ( የኣማርኛ ጎበኘ ).

3_" እድ " በትግርኛ " ኢድ " በኣረብኛ ደሞ " የድ " ነው ። ሆኖ ግን በኮሎኲያል ኣረብኛ እንደ ትግርኛ " ኢድ " ነው ። በኣሜሪካ የሚኖር ዋኢል ሰዲቒ የሚባል ግብጻዊ ከኣንዲት ሴት ሆኖ " ሲብ ኢዲ / እጄን ልቀቅ " የሚል ስም ያላት ቪድዮ ክሊፕ ከነዘፈንዋ ስለ ሰራ በየግብጽ መንግስት የኣንድ ኣመት የእስር ቅጣት ተበየነለት ። ለሴትየዋም( ስምዋ፥ ሪዳ ኣልፉሊ ) እንደሱ ! ምክንያት፥ ስራው ኣጸያፊና ለኣጸያፊ ነገር ስለሚያበረታታ!!!

ሲብ ኢዲ !! ( ሪዳ ኣልፉሊ " እጄን ልቀቅ " ትለውና ዋኢል ሰዲቒ " እኔ ኣልቀረብኩሽም/ እንኳን ልነካሽ ኣጠገብሽህም የለሁም " ብሎ ይመልስላታል )

-
Last edited by Abe Abraham on 12 Mar 2023, 18:41, edited 1 time in total.

Abe Abraham
Senior Member
Posts: 14412
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Abe Abraham » 12 Mar 2023, 15:30

ፈሪ ( ኣማርኛ ) ና ሃዳሚ ( ትግርኛ ) !

1_ በኣረብኛ ፈራ ትርጉሙ ( to flee, run away,run off escape ) ሲሆን ኣማራ ከውግያ ይሁን ኣንድ ፈታኝ ሁኔታ courage ሳያሳይ ran away የሚያደርግ ሰው ፈሪ ይሉታል ።

2_ ሃዘማ in Arabic ( active form ) ትርጉሙ " to defeat " ሲሆን the passive form of the word is ሁዚማ ( Arabic passive uses change of vowel while in Tigrigna and Amharic ተ at the front of the word is used. Example ፥ ሰዓረ/ተሳዕረ ፡ ኣሸነፈ/ተሸነፈ ) ። The Tigrigna word " ሃዳሚ '' is related to " ሁዚማ ( got defeated = ተሳዕረ/ተሽነፈ ) and ሃዚማ ( defeat) in the sense of the defeated ( ኣል-ማህዙም) runs away ( ይሃደም) then he becomes ሃዳሚ !!

እንደ ሓላፊ መንገዲ የመሳሰሉ ትግርኛ ተናጋሪዎች ሲፎክሩ ባማርኛ " ሓቦ " የሚባል ቃል የለም ይላሉ !! የጀርመኖች Heimat ( ሃይማት ) በውስጡ ብዙ ስሜት የያዘ ስለሆነ በሌሎች ቋንቋዎች በቀላሉ ሊተረጎም ኣይቻልም ይባላል ። እንደ የኤርትራ ዓዲ ዓድና ( where you really feel at home in a special way ) ማለት ነው ።

ጊዜው የሁለተኛ የኣለም ጦርነት ነው ። ሰውየው ከልጆች ጋር በመኪናው ኢያለ ኣንድ የእንግሊዝ ፖይሎት ( የጦር) ተመትቶ ወድቀዋል ስለ ሰማ መኪናዋን ኣቁሞ ለጓደኛው ሞተሩን መልሶ እንዳያነሳ ነግሮ ወደ ጫካው ያመራል ...watch what happened then. I watched Heimat I and II long time ago when it was aired by the BBC. I recommend that you watch it. It is about the lives of Thomas,Matthias,Simon, Maria .....their village, church, war-time suffering, family life, love, missing eachother ....

_
Last edited by Abe Abraham on 12 Mar 2023, 18:14, edited 3 times in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 30657
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Horus » 12 Mar 2023, 16:08

Abe
ሃዘማ የሚለው አረብኛ ዘማች፣ ዘመቻ፣ አዝማች ከሚባሉት የኢትዮፒክ ቃላት አንድ መሰለኝ። የቃሉ ስር ካ፣ ጋ፣ ጋስ፣ ጋዝ፣ (ዘመቻ በጉራጌኛ)፣ አጋዚ (ጦረኛ) ማለት ነው ። ካዘ ከሚለው ነው አረብኛው ሃዘማ የመጣው ። ማ = ኛ (ሰፊክስ)። አዝማች ማለት አጋዝ (አባ ጋዝ) የጦር አዛዥ ማለት ነው ።

የትግርኛው ተሳዕረ ተሻዕለ ፣ ተሻለ ፣ በለጠ ፣ አሸነፈ የሚለው ነው ። የቃሉ ስር ቻለ (ካረ) የሚለው ነው፤ ለምሳሌ ጠነ(ከረ)፣ ጠን(ካራ) ወዘተ።

ኬር!

Abe Abraham
Senior Member
Posts: 14412
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Abe Abraham » 12 Mar 2023, 18:00

Horus wrote:
12 Mar 2023, 16:08
Abe
ሃዘማ የሚለው አረብኛ ዘማች፣ ዘመቻ፣ አዝማች ከሚባሉት የኢትዮፒክ ቃላት አንድ መሰለኝ። የቃሉ ስር ካ፣ ጋ፣ ጋስ፣ ጋዝ፣ (ዘመቻ በጉራጌኛ)፣ አጋዚ (ጦረኛ) ማለት ነው ። ካዘ ከሚለው ነው አረብኛው ሃዘማ የመጣው ። ማ = ኛ (ሰፊክስ)። አዝማች ማለት አጋዝ (አባ ጋዝ) የጦር አዛዥ ማለት ነው ።

የትግርኛው ተሳዕረ ተሻዕለ ፣ ተሻለ ፣ በለጠ ፣ አሸነፈ የሚለው ነው ። የቃሉ ስር ቻለ (ካረ) የሚለው ነው፤ ለምሳሌ ጠነ(ከረ)፣ ጠን(ካራ) ወዘተ።

ኬር!
1_Any exploration which leads into a plausible direction is worthy of investigation.
2_ We take from them and others also take from us. Some of our words by the admission of Quranic scholars are in the Quran itself.

There is a famous word in the Arabic and Islamic culture and tradition which is borrowed from us(Eritrea and Ethiopia). I do not know whether we should be proud of it. We will come back to it. :lol: :lol: It is something which is keeping you busy these days !!!

-

Horus
Senior Member+
Posts: 30657
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Horus » 12 Mar 2023, 20:05

Abe

የኢትዮጵያ አሻራ በቁርአን ውስጥ ቢገኝ ለምን ትገረማለህ ሁሉም ከዚህ በፊት እንደ ነገርኩ ክርስትናም እስልምናም የብርሃን አምላኪዎች ናቸው። አንድ በጸሃይ ሌላው በጨረቃ ። ጥንታዊ ግብጾች ካ ፈጣሬ ወይም ዲቫይን ሃይል ነው፣ ካራ የዚያ ሃይል ጸሃይ ነው ብለው ያምኑ ነበር ። ከዚያ ካራ ማለት ሃይል ብቻ ሳይሆን ህግ ማለት ሆነ ። ያ ቃል ዛሬ ሙስሊሞች ሸሪአ ይሉታል ። ጉራጌ ሴራ ይለዋል። ግዕዝ ሰርዕ (ነጠላ) ስርዓት (ብዙ) ይለዋል ። ስለዚህ እግጅ ግዙፉ የቁራ ቃል ሸሪአ ሕግ፣ ሴራ፣ ስርዓት ማለት ነው ። አንድ ነገር የምንለው ።

Abe Abraham
Senior Member
Posts: 14412
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Abe Abraham » 12 Mar 2023, 21:26

Horus wrote:
12 Mar 2023, 20:05
Abe

የኢትዮጵያ አሻራ በቁርአን ውስጥ ቢገኝ ለምን ትገረማለህ ሁሉም ከዚህ በፊት እንደ ነገርኩ ክርስትናም እስልምናም የብርሃን አምላኪዎች ናቸው። አንድ በጸሃይ ሌላው በጨረቃ ። ጥንታዊ ግብጾች ካ ፈጣሬ ወይም ዲቫይን ሃይል ነው፣ ካራ የዚያ ሃይል ጸሃይ ነው ብለው ያምኑ ነበር ። ከዚያ ካራ ማለት ሃይል ብቻ ሳይሆን ህግ ማለት ሆነ ። ያ ቃል ዛሬ ሙስሊሞች ሸሪአ ይሉታል ። ጉራጌ ሴራ ይለዋል። ግዕዝ ሰርዕ (ነጠላ) ስርዓት (ብዙ) ይለዋል ። ስለዚህ እግጅ ግዙፉ የቁራ ቃል ሸሪአ ሕግ፣ ሴራ፣ ስርዓት ማለት ነው ። አንድ ነገር የምንለው ።
1_ኣዎ ሸሪዓና ስርዓት ተዛማጅ ቃላቶች ናቸው ። እኔ በገዛ ራሴ ድሮ በመደምደምያው ደርሼ ነበር ። መስርዕ በትግርኛ row (ስርዓቱ ይዞ በመስመር የቆመ) ማለት ነው ። ስርርዕ ደሞ some kind of an organizational system ነው።

2_ለምን ትገረማለህ ? ጥያቄውን ለመመለስ መጀመርያ " መገረም " የሚለውን ቃል መተንተን ኣለብን ። ለምሳሌ ኣንተ " ጥላል " ና " ካራ " የሚባሉ ቃላቶች በጉራጌኛ ኣሉ ስትለኝ ስለ our common shared heritage እያወቅኩ ሁለቱ ቃላቶች በትግርኛም ስላሉ " ልገረም " እችላለሁ ። መገረሙ ከ " እንዴ ብሎ ? " የሚል ጥያቄ የተሳሰረ ሳይሆን የደስታ ነው ። " ፋንታስቲክ! '' እንደማለት ቁጠረው ። Discovery is always a discovery. It brings with it setiments.

3_ቁርኣንን በሚመለከት ግን " መገረሙ " ለኔ ብቻ ሳይሆን ለተማራማሪዎችም ጭምር ምክንያት ኣለው ። ከዚህ በፊት እንደ ነገርኩህ ቑርኣን " ብብሩሕ ልሳነ-ኣረብ " የቐረበ መልእክት ነው ስለሚባል ተመርምሮ የኣጎራባች ቃላቶች ይዞ መገኘቱ ለብዙ ኣነጋጋሪ እስከሚሆን ደረሰ ። ኣነጋጋሪ ነጥቡ ፥ በቁርኣን የ " ባእድ " ቃላቶች መገኘታቸው " ቢሊሳኒን ዓረቢዩን ሙቢን " የሚለውን contradictory ያደርገዋል ወይ ? In other words is there a contradiction between " the claim " and the " discovery " ? There are two schools of thought who try to solve the " problem " ( it is not a minor issue for serious scholars who are used to reading various arguments on various texts in the Qur'an, the Sunnah and the Hadith) :

First : The words were already part of the language at the time of the " revelation of the Qur'an " .
Second : The second groups puts a question mark and considers the issue unresolved.

-

Selam/
Senior Member
Posts: 11549
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Selam/ » 12 Mar 2023, 22:34

እራሱ ነቢዩ መሀመድ የአማርኛ ዕውቀት እንደነበረው፣ ከረጅም ጊዜ በፊት አንብቤ ነበር። ለዚህ ምስክርነት ሊሆን የሚችለው: ደቡብ አረብያ ለረጅም ጊዜ በኢትዮዽያ ስር ስለነበረች፣ ነቢዩ ኢትዮዽያዊ ሰራተኛ ስለነበረው፣ ተከተዮቹን ወደ ኢትዮዽያ ስለላከ፣ የመጀመሪያው ቢላል የኛው ሰው መሆኑ።

Horus
Senior Member+
Posts: 30657
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Horus » 13 Mar 2023, 03:14

Abe,
እሺ ያልከውን እቀበላለሁ! ሁሉም ነገር ሚራክል ነው!

አሁን ከፍ ወዳለ ጉዳይ ልንገባ ነው ። እኔ በእምነቴ (አምልኮዬ) ኦርቶክስ ክርስትና ቢሆንም ባይምሮዬ ሳይንቲስት ነኝ ማለትም የእውቀት አማኝ ነኝ ። ስለሆነም እኔ በህይወቴ አንድ ኮርስ የስላሚክ ፊሎሶፊ የሚል ነው የወሰድኩት ፣ ቁራን ነበረኝ ግ ን አላጠናሁትም። ስለዚህ በቁራን ዶግማ ውስጥ ስላለ ክርክር እውቀት የለኝም ።

እኔ ከላንጉጅ ጋር ካለኝ ዝምድና በመነሳት ቁር አን የሚለው ቃል ዲኮድ አድረጌዋለሁ። ማየት፣ በብርሃን መመልከት፣ ማንበብ ማለት ነው ። አንድ ነገር በብርሃን አማካይነት ስናይ አዲስ ነገር መፍጠራችን አይደለም ! ያለን ነገር፣ የበረን ነገር ማየታችን ነው ። ይህ ትርጉሙ ደግሞ ማየት ማለት ነው።

በኦርቶዶክስ እራሱ የኦርቶዶክስ ስረ ቃል ዴክማ (ዶግማ) ይባላል ። መልሶ ማየት፣ ደግሞ ማየት ማለት ነው ። ስለዚህ የሙስሊም ደራሳም (ድርሰት ማለት ነው) ደጋሚ ነው ። የኦርቶዶክስ ምሁር በለው ተመሪ ደጋሚ ነው ። ዳዊትም ቅዳሴም ሁሉም ዶግማ ነው ።

ስለዚህ ቁራንን የደረሱ ሰዎች ነቢያት (ወደ ፊት ትንቢት ተመልካቾች) የተገለጸላቸው ቁርአን ብርሃነ ራዕይ ከድሞ የነበረ እንጂ እነሱ አልፈጠሩትም የሚለው ክርክር ነው ትክክል !

ሁለተኛው ተከራካሪዎች ችግራቸው በሃሳብና በቋንቋ መሃል ያልው ሳይንስ ስለማያውቁ ነው ። ሃሳብ ባይምሮ ውስጥ ያለ ምስል ወይም ስዕል ነው ። ቋንቋ (ድምጻችን ሳይሆን) ድርሰታችን ካይምሮ ውጭ ያለ ምልክት ነው። ስለዚህ መንጋጋችን የሚፈጥረውን ፊዚካል ድምጽ ወደ ጎን ትተን ባንጎላችን ውስጥ የምናየውን ሜንታል ኢሜጅ እና በምልክት፣ በፊደል የምንቀጸውን ምስል ላይ ብንመራመር ሁሉም ነገር ወለል ይላል ።

ያም ማለት ማንኛውም እውነትም ሆነ ምናብ መጀምሪያ ባይሮ ምስል (በአንጎል ብርሃን፣ ኢሜጅ) እናየዋለን! ያም ሃሳብ ይባላል!!!!! ያንን ውስጣዊ ፎቶ ብርሃን ውጭ አውጥተን በፊደል፣ በቴፕ፣ በቪድዮ፣ በሙዚቃ ስንገልጸው ድርሰት ደራሳ ይባላል ።

ስለዚህ ከብርሃን በፊት ቁራን የለም፣ ቃል የለም፣ ምስል የለም፣ ሃሳብ የለም !!!!!የማያይ ሰው ሃሳብ የለውም ። ስለሆነም ኩር ኣን የሙስሊም ዶግማ (መድገሚያ) ነው ። ልክ እንደ ኦርቶዶክስ ጸሎት ሃይማኖት ዶግማ (መደሚያ)።

ሁሉ ነገር ሃይማኖትን ጨምሮ የተሰራው ባይምሮ ውስጥ ካለ ምስልና ካይምሮ ውጭ ካለ ምልክት ነው !!!!

Abe Abraham
Senior Member
Posts: 14412
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Abe Abraham » 13 Mar 2023, 20:40

Horus wrote:
13 Mar 2023, 03:14

ስለዚህ በቁራን ዶግማ ውስጥ ስላለ ክርክር እውቀት የለኝም ።
1_የ interpretation ክርክር ኣለ ግን ክርክሩ ከመነሳቱ በፊት ጽሑፉ ምን እንደሚል መረዳት ኣለብህ ። ከ understanding በኋላ interpretation ይመጣል ። ከዝያም የ interpretation ልዩነት ወደ schools of theology ያመራል ። ስለሆነም በእስልምና ኣራት schools of jurisprudence ኣሉ ።

ኣሁን እኛን የሚመለከት እምነታዊ ጉዳይ ሳይሆን ቋንቋው ነው ። የድሮ ሙስሊሞች ቁርኣን በብሩህና የጠራ ኣረብኛ ቋንቋ ነው የቀረበው የሚል መልእክት ከደረሳቸው ቡጓላ በጽህፉ የተጓራባች ህዝቦች ቃላቶችና ትርጉማቸው በቀላል ልታውቃቸው የማትችል ሌሎች ቃላቶች ኣገኙ ። ችግሩ እንዴት ይፈታ ? መልስ ፥ በየተለያዩ የቋንቋ መስኮች ብቃት ያላቸው ሰዎች መሰብሰብ ።

ስራውን ለማከናወን የመጀመርያው ትልቁ ችግር ምን ነበር መሰለህ ? መልስ ፥ ጽህፉ ያለ መለያ ነጥቦችና diacrtical signs ተቀምጦ ስለ ነበር ጉድለቱን ለማስተካከል ስራ ኣስፈለገ ። ለምሳሌ " ሀረሰ የኣበሰ ለጀ ነወ ''( በራስህ ኣስተካክለህ፥ ሆረስ የኣበሻ ልጅ ነው!! tricky,right? ) እንዴት ታነበዋለህ ? እኔ በኣረብኛ በቅደም ተከተል ከቀኝ ወደ ግራ " በየነት بينت " ስጽፍልህ ማንበቡ ምንም ችግር የለበትም ሆኖ ግን በኣረብኛ የጻፍኩትን ያለ ነጥቦች ( ኣንድ በታች ፡ ሁለት በታች፡ ኣንድ በላይ ፡ ሁለት በላይ ) ሳቀርብልህ ከኮንቴክስቱና ኣስቀድሞ ካለህ ኢንፎርሜሽን እንጂ ከጽህፉ ምንም ለማንበብ ኣትችልም ።

ኣስቀድሞ ካለህ ኢንፎርሜሽን ስል ወንድምህ ስሙ በየነ ከሆነና ኣባትህ ደሞ ነብይ " ወንድሜ _ _ _ ይባላል ። ኣባቴ ደሞ _ _ _ " የሚለውን ኣረፍተ-ነገር ለማንበብ ኣትቸገርም ። Without prior knowledge or context sometimes issues could be ኣካራካሪ ! በተለይ በሃይማኖት !! ኣንዳንድ ሰዎች የነጥቦች ጉዳይ ኣንስተው በእጅግ ኣካራካሪ የሆኑ ጉዳዮች ይገባሉ ። ክርክሩ ፥ ቃሉ እንደዚህ ነው ስትል ሌላው ኣይደለም ይለሃል ፡ ለምን ስትለው ድሮ ነጥቦች ስላልነበሩ የኔ ኣነባብ ትክክለኛ ሊሆን ይችላል ይለሃል !!!

-------------------------

2_ ደርስና ዲራሳ በኣረብኛ ከትምህርትና ጥናት የተሳሰሩ ስለሆኑ ከየኛ ድርሰት ግንኙነት እንዳላቸው የሚያጠራጥር የለም ። ( ዳሪሳ /ሳ-ከባድ ሳ/ የሚለውን የኣረብኛ ቃል ግን ትርጉሙ ሌላ ነው ። ለምሳሌ ፥ ዳሪሰት ኣል-ናቓቱ / ግመልዋ በእርጅና ጥርስዋን ተሰበረ ። ባንዳንድ የኣረብ ኣገሮች ኮሎኲያሊ ሰዎች ለጥርስ(ባማርኛ) ዲርስ ሲሉ ይሰማሉ !!

3_ ኣማርኛ/ኣረብኛ ፥ a) ትንቢት/ንቡኣ፡ተነቡእ b) ነቢይ/ነቢይ
4_ በኣረብኛ ቢል ፊጥራ ሲባል ባማርኛ ትርጉሙ በተፈጥሮ ( by natural disposition)
5_ወሰጥ ( middle,centre, ...). ዊሳጣ ( mediation ...)
6_ ጸሎት ( ሰላ / ከሌላ ቃል ፥ ሰላቱ ኣል-ዒድ means " id prayer --- /

-

Horus
Senior Member+
Posts: 30657
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Horus » 14 Mar 2023, 02:00

አቤ፣
በቁጥር አንድ ያነሳሃው ጉዳይ ለብዙ ዘመን ሴሚዮቲክስ (የምልክት ሳይንስ) በሚባል የቋንቋ ክፍለ ምርምር ተጠንቶ ያለ ጉዳይ ነው ። ነገሩን በምሳሌ ባጭሩ ባሳይህ ይበልጥ የጠቅምሃል ። ለምሳሌ መሬት፣ ፊዚካል ምድር አለ ። ያ ምድር ሜዳ፣ ወንዝ፣ ተራራ፣ ሸለቆ፣ ጫካ፣ ቤቶች ቋጥኞች ፣ ዛፎች ወዘተ አሉበት ።

አንድ ሰው ሄዶ ይህን ምድር ተመለከትና ወደ ሌላ አገር ሄዶ ያየውን ላላዩ ሰዎች እሱ ያየውን ምድር ዘርዝሮ በቃል ይነግራቸዋል ። ይህ የሱ ታሪክ የዚያ ቦታ ካርታ (ማፕ) ነው ። ለብዙ ዘመን ማለት የሰው ልጅ ያየውን በምልክት (ፊዚካል ምልክትም ሆነ፣ የስዕል ፣ ፊደል) ምልክት ቴክኖሎጂ ከመፍጠሩ በፊት ያ የቃል ኦሪት ፣ ያ የቃል ወሬ የአለም ካርታችን ነበር።

ኋላ በምልክትና ፊደላት ቴክኖሎጂ የተዋበ ካራታ በድንጋይ ላይ፣ በቆዳ ላይ፣ በወረቀት ላይ መንደፍ ቻልን! ያ ቻርት፣ ካርት፣ ካራታ ማፕ እንለዋለን።

አሁን ወደ ቁም ነገሩ ላምጣህ!
ያ የመጀመሪያ ተመልካች ለቦታው ካርታ ሰርቶ ነበር ብለናል ። ይህ ካርታ (የመጀምሪያው ቁርዓን ኮፒ ማለት ነው) የያዘ ሌላ ወጣት ልጅ እዚያ ሄዶ በካርታው ላይ የተዘረዘሩት ዛፎት፣ ተራሮ፣ ወንዞች፣ ሜዳዎች ሲያመሳክር በምድር ላይ ያሉት ነገሮችና በካርታው ላይ የተመለከቱት ነገሮች አንድ አልሆን አሉት! (ይህ ወጣት አዲሱን ቁርዓን የያዘው ሙስሊም ነው) ።

አሁን ያነሳሃው ችግር መጣ ማለት ነው ። ወጣቱ ሙስሊም አሮጌ ካርታ ይዞ ለማመሳከር እንደ ሄደው ወጣት ውሰደው ። የቱ ነው ትክክል ወጣቱ የሚያየው ካርታ (ፊዚካል ቪዥን ሊሆን ይችላል) ወይስ በድሮ ካርታ (ጽሁፍ) የተቀመጠው?

ለዚህ እንቆቅልሽ የሴሚዮቲክስ ሳይንስ ያለው ድንቅ ሳይሳዊ መልስ "ካርታውና ምድሩ ካልተስማሙ ትክክለኛው ምድሩ ነው" ይላል! ማለትም አንዱ መጽሃፍ መንግስተ ሰማያት ያለው ጨረቃ ላይ ካለ። ሌላው አይ መንስተ ሰማያት ያለው ማርስ ላይ ነው ካለ !!! ይህ ችግር የሚፈታው አንድም ጨረቃ ላይ ሄዶ ወይም ማርስ ላይ ሄዶ በማረጋገጥ ነው !!!!!!!!

አይ ሁለቱም ካርታዎች ባለ ጨረቃውም ባለማርሱም ከመሬቱ ጋራ አመሳክሮ መበየን የማይቻል ከሆነ ያ ሱዶ ፕሮብሌም፣ ባዶ ችግር ይባላል። ዘዴ ስለሌለው ከእውቀት መደብ አይመደብም ። ጉንጭ አልፋ የምንለው ማለት ነው። ስለዚህ አንድ እስክሪፕቸር ትክክል አይደለም ከተባለ ወደ እምነቱ ይዘት እንሄዳለን ። የእምነቱ ይዘት ከጽሁፉ ለይቶ ማወቅ ወይም መመዘን ካልተቻለ ያ እምነት በምድር ላይ የለም ፤ የሚጨበጥም ሆነ የማይጨበጥ ማረጋገጫ የለውም ማለት ነው ፣ ከተጻፈ ቃላት ውጭ!!!

በዚህ ሁኔታ ትክክል ወይም ስህተተኛ የሚባል ሰው አይኖርም ። ሁለቱም ሰዎች የሚያሳዩት ሪያሊቲ ስለሌለ ማለት ነው ! ምድር ሳይኖር ካራታ ሊኖር አይችልም! ሪያሊቲ ሳይኖር ምልክት መስራት አይቻልም ! ያን ካደረግን እብዶች እንባላለን ! የሌለን ነገር የሚያዩ ስይኮቲክስ ይባላሉና !

ደራሲ ከላይ እንዳልኩት ጽህፈት ከመፍጠራችን በፊት ትምህርትም ድርሰት፣ ግጥም፣ ዘፈን፣ ዜማ ሁሉም በቃል (ኦራል) ስለነበር እና አንዱ ካንዱ የሚማረው አንዱ ሲል ሌላው በመድገም ሃ ሃ፣ ለ ለ እያለ ስለነበር ያን ነው ድርሰት የምንለው ።

በጉራጌኛ ማንኛውም መዝሙር፣ ዘፈን፣ ቀረርቶ ደርስ ነው የምንለው ። ለምሳሌ ቴዲ አፍሮ ባማርኛ ዘፋኝ ይባላል። በጉራጌኛ ደራሲ (ደርሳማ) ይባላል !

ጸሎት ማለትና ጽላት ማለት አንድ እንደ ሆኑ ልብ በል! ጽላት መጸለያት ማለት ነው ። አልባሳት እንደ ምንለው ማለት ነው ።

Abe Abraham
Senior Member
Posts: 14412
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Abe Abraham » 14 Mar 2023, 20:06

Horus wrote:
14 Mar 2023, 02:00

በቁጥር አንድ ያነሳሃው ጉዳይ ለብዙ ዘመን ሴሚዮቲክስ (የምልክት ሳይንስ) በሚባል የቋንቋ ክፍለ ምርምር ተጠንቶ ያለ ጉዳይ ነው ።

1_ በኣረብኛ ሊንጒስቲክስ ኣል-ሊሳይኒያት ወይም ኣል-ሉቓዊያት ተብሎ ይጠራል ። የኛ ልሳንና የኣረቦች ሊሳን ኣንድ ናቸው። ኣንተ በበለጠ እንደምታውቀው ከሲምዮቲክስ ጀምሮ ለቋንቋ ምርምር የሚጠቅሙ ሌሎች " ቱልስ " ኣሉ ። በ "ቱሎቹ " የሚመለከት በየቑርኣን ሓዲስና ( ብሂለ ነብይ መሓመድ) ሱና ( ታሪክና ኣንዋንዋር ዘነብይ መሓመድ ) ተማራማሪዎች በኩል ብዙ ክርክር ኣለ ።

_ኣቃቢዎች (ኮንሰርቫቲቭስ ) ምን ይላሉ ? ከ " ቱሎች " ያስፈለገንን ተጠቅመን የቱሎች ኣጠቃቀምና ማን ሊጠቅምባቸው እንደሚገባው ግን ገደብና ማሰርያ (ደዋብጥ) ሊደረግበት ይገባል ። ኣለበለዚያ ማንኛውም ሰው ( ከሰዋስው ጀምሮ በስፔሻላይዜሽን ደረጃ ተገቢ የቋንቋና ሃይማኖት ትምህርት የሌለው ) ጥንቃቄ በሚገባው ጉዳይ ገብቶ ሊጫወት ከተውነው ይሄ የማይባል ኣደጋ ሊያደርስ ይችላል ።

ኮንሰርቫቲቮች በሁለት ይከፈላሉ ፥ ኣንድ - ተገቢ ስጋት ያላቸው ። ሁለት - ምርምርን በፍጹም የሚከለክሉ ( ፈጽሞ ኣያስፈልግም)።

_ እናውቃለን (ግለ-ሰዎች ዶክተር እከሌ ምናምን) የሚሉሳ ምን ይላሉ ፥ በእስልምና ልዩ የሃይማኖት ሰዎችና ( ሪጃል ኣል-ዲን ) ልዩ የሃይማኖት ወንበር እንደ ቫቲካን ስለ ሌለ ማንኛውም የማንበብና የማሰብ ፍላጎት ሆነ ችሎታ ያለው ሰው በገዛ ራሱ ሊመራመር ይችላል ። ( ኣቃቢዎች ለነዚህ ሰዎች፥ " በቤትህ ሆነህ እንደፈለግህ ተመራመር በውጭ ወጥተህ ግን ህዝብን ኮንፍዩዝ ኣታደርግ ! )

የበራሳችን እናውቃለን ግለ-ሰዎች ሁለት ኣይነት ናቸው ፥

ኣንድ - ሃይማኖትን ወደ ኣእምሮኣዊ ( ራሽናል) ኣስተሳሰብ ሊያጠጉ የሚፈልጉ ። የሚሰጡት ምክንያት ፥ ከኣእምሮ የሚጻረርና " ሃርሽ " የሚመስሉ ነገሮች በመጨረሻ ሃይማኖቱን ሊያፈርሱ ይችላሉ ። ማለት ፥ እንደ ኣይሲስና ኣል-ቓዒዳ የመሰሉ ሃይማኖተኛ ነን ሲሉህና ኣል-ኣዝሃር ደሞ ከእምነት ልናባርራቸው ኣንችልም ስትል የማስተካከል ስራ በተደራጀ መልክ ይሁን በግለ-ሰብ ደረጃ እጅግ ኣስፈላጊ ይሆናል ።

ሁለት - በክርክሩ ቀዳዳ ገብተው በሃይማኖቱ ጥርጣሬ ለማሳደር የሚፈልጉ ሰዎች ። እነዚህ ሰዎች በግልጽ ጸረ-ሃይማኖት ሆነው ሊቀርቡና ላይቀርቡ ይችላሉ ።

ክርክሩ በቱሎች የተመሰረተ ሲሆን ይህ ሊመስል ይችላል ፥

ምሳሌ ፥ " ሀረስ የኣበሰ ልጀ ነወ ። ኣበተ በተነ ሰጠ ። የሀበረተ-ሰበ ሀገ የመየከበረ ገደለት ። "
ዶክተር ሆረስ(ፊክቲቭ!) ትንታኔ ሲሰጥ እንዲህ ይላል ፥ " ሆረስ የኣበሻ ልጅ ነው ሳይሆን ትክክለኛው " ሆረስ የኢቢሳ ልጅ ነው " ። " ኣባቱ ቤቱን ሸጠ " እንጂ " ኣባቱ ቤቱን ሰጠ " ትክክል ኣይደለም ። " የህብረተ-ሰቡ ህግ የማያከብር ግደሉት " ትክክለኛው " የህብረተ-ሰቡ ህግ የማያከብር ግደሉት/ቅጡት " ምክንያቱ ግደሉት የሚለው ቃል ከየጥንት ጉራጌኛ የተወሰደ ቃል ሆኖ ትርጉሙ ቅጡት እንጂ እንደ የዛሬው ኣማርኛ ኣተረጓገም ህይወቱን ኣሳጡት ማለት ኣይደለም ። በሌላም " ምላሱ ቁረጡት " የሚለው የህብረተ-ሰቡ ትእዛዝ እንደ ኣባባል " ኣፉን ኣስይዙት " እንጂ ቃል በቃሉ ምላሱን ቁረጡለት ማለት ኣይደለም ።

የደግ-ሰው ዶክተር ሆረስ ፐርፐዝ ምንድነው ? ሆረስ የኢቢሳ ልጅ መሆኑ ማሳወቅና ኣባቱ ደሞ ቤት (ርስት) ለሌላ ሰው እንደ ሸጠ ( ነገሩ irreversible ነው መጨቃጨቅ ኣያስፈልግም ለማለት ) ። ከዚያም በህብረተ-ሰቡ የመግደልና ምላስ የመቁረጥ ልምድ ለማስወገድ ። ( በቅርብ ጊዜ የሞተው ሶርያዊ መሃንድስ ሻሕሩር እንደ ደግ-ሰው ዶክተር ሆረስ ነበር ። )

(በኣረብኛ ጽህፉ " መሓመድ ሻሕሩር ታታሪ ነው ወይስ መንገዱ የሳተ ሰው ?)

የዶክተር ነስር ሓምድ ኣቡ ዘይድ ( ሊንጒስቲክስ ስለተማረ የሆረስ ጓደኛ እንበለው) ጉዳይ

( ዶክተር ነስር ሓምድ ኣቡ ዘይድ ከሚስቱ ጋር ። ሊፈታት ሊያስገድዱት የፈለጉት ምክንያት ፥ ሙስሊም ያልሆነ ከሙስሊማ ጋር በጋብቻ ሊኖር ኣይፈቀድም ። / ሚስቱ እየወደደችው ማለት ነው።//

ዶክተር ነስር ሓምድ ኣቡ ዘይድ ቁርኣንና የሃይማኖት ርስቶች እንደ ማንኛውም ጽሁፍ ለ " ቴክስት ኣናሊሲስ " ሳብጀክትድ መሆን ኣለባቸው ብሎ ተነስቶ ኣንድ ጥናት ካቀረበ በጓላ በየዩኒቨርስቲ ሽማግሌዎች ተጠርቶ ከምስልምና እምነት ወጥተሃል የሚል ክስ ስለ ተሰነዘረበትና ሚስቱን እንዲፈታ ፕረሸር ስለ በዛበት ኮብልሎ ወደ ኤውሮጳ ሄደ ። ሰውየው ኣስከሚሞት ድረስ ግን ስራውን ኣላቋረጠም ። ኢላማው ምን ነበር ስንል መልሱ ሪፎርም ይላል ። ብዙ ሰዎች በምስልምና ሪፎርም የሚባል ነገር የለም ይላሉ ።

---

በላይኛው የሆረስ ቴክስት በቀይ የተጻፉትን የሌላ ጊዜ ኣርእስት ይሆናሉ !!

--

Post Reply