************
By Yared Estifanos Yumura
1/ ጀነራል ባጫ ደበሌ ጦሩ ከመቐለ ተሸንፎ ሲወጣ ህወሃት ወደ ራያ፣ ሁመራ እና ወልቃይት የሚንቀሳቀስ ከሆነ ውጊያ እንደሚያደርግ ገልፆ ነበር ።
2/ በተባበሩት መንግስታት የኢትዮዽያ አምባሳደር ታዬ ከጋዜጠኛ ጥያቄ ቀርቦላቸው ሲመልሱ ወልቃይት እና ራያ የአማራ ርስት እንደሆኑ በመጥቀስ የፌደራል መንግስት አከባቢዉ በአማራ ሚሊሻና ልዩ ሃይል ስር መሆኑን እንደሚደግፍ ተናግረዋል።
3/ እነ ታዬ ደንደዓ አምባሳደር ታዬ ወልቃይትና ራያ የአማራ ርስት ነው ያሉበትን ንግግር በመውሰድ በድጋፍ መልክ አራግበዋል።
ከዚህ የምንረዳው ከአሁን በኻላ የሃገር መከላከያ ሰሜን ላይ ጦርነት የሚያደርግ ከሆነ ዋነኛ ምክንያቱ የአማራ ሊህቅ ርስቴ የሚለውን መሬት ለማስጠበቅ ነው።
(በርግጥ ከዚህ በፊት በነበረው ጦርነትም "ርስት ማስመልስ" አንዱ የተዋጊ ሃይሎች አላማ ነበር ። )
የመከላከያ አባል የሆነ ኦሮሞ ፣ሲዳማ፣ ወላይታ ፣ ጋሞ፣ ሶማሌ፣ አፋር፣ ወዘተ ለአንድ ወገን ወግኖ መዋጋት ፈፅሞ የለበትም።
ስለዚህ ከተለያዩ አከባቢዎች የተሰባሰባቹ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እናንተ አደራ የተሰጣቹ የሃገሪቱን ዳር ድንበር ከውጭ ወረራ ትጠብቁ ዘንድ እንጂ በድንበር ጦርነት ለአንድ ወገን ወግናቹ እንድትዋደቁ አይደለም። የናንተ ተልዕኮ ይህ አይደለም።
እናም አዲስ ምልምሎችም ሆናቹ ውስጥ ያላቹ የመከላከያ አባላት በዚህ ጦርነት የምትሳተፉ ከሆነ ደምና ላባቹ የሚፈሰው በከንቱ ይሆናል ።
በውነቱ ህይወታቹንም ባልተገባ መልኩ መስዋት አታድርጉ።
የወታደር ቤተሰቦችም ልጆቻቹ በዚህ ከንቱ ጦርነት ህይወታቸውን እንዳይገብሩና በተለያየ መልኩ ከውጊያ እንዲርቁ ምከሯቸው። ፖለቲከኞች የፖለቲካ ልዩነታቸውን አሁን ዳር ዳር እያሉ ባሉበት መንገድ በሰላማዊ ደርድር ይፍቱ።
የአንድም መለዮ ለባሽ ወንድም/እህታችን ህይወት በከንቱ አይለፍ።