Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Dawi
Member
Posts: 4311
Joined: 30 Aug 2016, 03:47

ኤርምያስ አመልጋ ከደረጀ ኃይሌ ጋር -ክፍል ሁለት - METEC indirectly bankrupted Access Real-estate :)

Post by Dawi » 18 Apr 2022, 11:42

In this interview we learn METEC indirectly bankrupted Ermias's Access Real-estate. This revelation is more than the known "Hotel" transaction.

Yeah! Tell us something we don't know....! :cry:




Ethoash
Senior Member+
Posts: 26144
Joined: 20 Apr 2013, 20:24

Re: ኤርምያስ አመልጋ ከደረጀ ኃይሌ ጋር -ክፍል ሁለት - METEC indirectly bankrupted Access Real-estate :)

Post by Ethoash » 19 Apr 2022, 10:48

ትራፕን ስሙት ስለኤርማስ ያሉትን ስዋችን እንዴት መጠበቅ እንዳለብን ሲናገር ።



እንደ ኤርሚያስ ያለ ስው በአንዲ ሺህ አመት አንዴ የሚመጡ ናቸው። ይልቁንም አንድም ሳንጠቅምበት እንዳይሞት ብቻ ነው የምፈራው። ኤርሚያስ ስለኢትዬዽያኖች ምቀኝነት አላወቀም እሱ አሜሪካዊ ነው ጥቁርም ቡሆንም በሐቅ ነው መሄድ የሚፈልገው። ግን ኢትዬዽያ ውስጥ የመንሺያ ፣ የመታያ ፣ አብላኝ ልብላ የሚባል ነገር አለ። ይህንን ስላላደረገ ስለሞን የሚባል የወያኔ ተላላኪ ገንዘብ ስርቆ ጠፋ ብሎ በአዲስ ፎርቹን ጋዜጣ ላይ አሳተመ ስው ደነገጠ ሁሉ ነገር ተበላሽ። አዲስ ፎርቹን ብዙ ስዋችን ነው ገደል የከተቱት በጣም መጥፎ ጋዜጣ ነው።

አብይ ከመጣ በኋላ አመልጋን እዳውን ከፍሎ ለአማልጋ ስጥቶ ቤቱን ጨርስ ማለት ነበረበት ። ኦባማ እኮ በትሪሊዬን ነው ለአሜሪካን ድርጅቶች ስጥቶ ከኪሳራ ያዳናቸው። መንግስት ምንድነው ይህንን ማረግ ካልቻለ።

እኔ ብዙ ነገር በዚህ ኢንተርቪው ላይ እንዳማራጭ የማቀርበው አሳብ አለኝ ግን ይህንን በሌላ ግዜ።

Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ኤርምያስ አመልጋ ከደረጀ ኃይሌ ጋር -ክፍል ሁለት - METEC indirectly bankrupted Access Real-estate :)

Post by Meleket » 19 Apr 2022, 11:16

"ነብይ በሃገሩ አይከብርም!" የተባለው ለእንዲህ ኣይነቱ ሃቀኛ ሰው ሳይሆን ይቀራልን?

Ethoash
Senior Member+
Posts: 26144
Joined: 20 Apr 2013, 20:24

Re: ኤርምያስ አመልጋ ከደረጀ ኃይሌ ጋር -ክፍል ሁለት - METEC indirectly bankrupted Access Real-estate :)

Post by Ethoash » 21 Apr 2022, 11:46

በድጋሚ ኤርሚያስ አመልጋን ቃልምልልስ ስማሁት ። ያለው ዋናው የዶላርን ፍላጎታችንን ማርካትና ዋጋውን ማወረድ መቻል አለብን ብሎ የሱን መፍት ሄ አቅርቦዋል።

እኔ ደግሞ ሶስት አራት ትላልቅ ወድ አገር ውስጥ የምናስገባው እቃዎች ስላሉ እነሱን ማስገባት ማቆም ወይም መቀነስ ብንችል ታላቅ የዶላር ብክነትን እናቆማለን።

መጀመሪያ መንገድ መንግስት መስራት አለበት ፣ ያለመንግስት ማንም መንገድ መስራት አይችልምና መንግስት ይህ መንገድ ላይ ብዙ የውጭ ምንዛሪ ያጠፋል ለምሳሌ የአስፋልት መንገድ የሚስራው በሬጅ ነው ሬንጅ ደግሞ ከውጭ ነው የሚመጣው በውጭ ምንዛሪ ታድያ ይህንን በአንድ ደቂቃ ማቆም እንችላለን አስፋልት መጠቀም ብቻ ነው። የኮንክሬት መንገድ ወድ ነው መጀመሪያ ሲስራ ግን ለስልሳ አመት ጥቅም ይስጣል ። የአስፋልት መንገድ በሁለት አመቱ መበላሽት ይጀምራል ፓላስቲ ነው ። በሙቀት ግዜ ይስፋል በቅዝቃዜ ግዜ ይጠባል በመሀሉ ይሽረሽራል አለቀ ነገሩ ። ሲሚንቶ ግን በሙቀት ግዜ እየጠነከረ ነው የሚመጣው አንዱ ዜደው በመሐል በመሐል ክፍት ቦታ ይተውለታል ለሙቀት ማስተንፈሻ ስለዚህ ለስልሳ አመት ልክ እንዳዲስ ሆኖ ነው የሚያገለግለን።

አሜሪካኖች መንገዳቸውን በኮንክሬት ሲስሩ ፣ የኮንክሪቱን ዋጋ ለመቀነስ የድንጋይ ከስል አመድ ይጠቀማሉ። የድንጋ ከስል አመድ ሲሚንቶ ፋብሪካዎች ጋ ይገኛል ይህ አመድ ከሲሚንቶ ጋራ ተደባልቆ ቆንጆ መንገድ ይስራል።

ሁለተኛ ነዳጅ የምናስመጣውን በጣም መቀነስ እንችላለን። በመጀመሪያ ደረጃ በጃጆች ለነዳጅ ሁለት ቀን ሙሉ ይስለፋሉ ከዚያም ነዳጅ አለቀ ሊባሉ ይችላሉ ። በጃጆችን ብቻ ወድ ኤሌትሪክ በጃጅ መቀየር ብቻል ወይም የኤሌትሪክ በጃጅ ያለቀረጥ ቢገባ ይህ ታላቅ ጥቅም አለው።

ሶስተኛ ውጭያችን ማዳበሪያ ነው ። ይህ ኬሚካል ማዳበርያ አላስፈላጊና ምርታችንን ዋጋ የሚያሳጣ መሬታችንንም የሚያቃጥል ነው ። ግን የተፈጥሮ ማደበሪያ እዛው አገራችን ውስጥ መስራት እንችላለን ። ባንችል ደግሞ እስራሔሎች ሊረዱን በጣም ደስተኞች ናቸውና አስገብተን የአረንጎዴ ምርታችንን ማልማት ነው።

አራተኛ በጣም የሚቆጨኝ ነገር ቢኖር አስሩ የሱካር ፋብሪካዋች ምን ላይ ደረሱ ። አስተዳደሩን በፋንኪሎ ብሎ ሌላ ቀጥሮ በአጭር ግዜ መጨረስና የወጭ ምንዛሪ ማስገባት መቻል አለብን።

አምስተኛ የሐይል ማመንጫችን ግድብ ከአባይ ቀጥሎ አሁን ስሙን የረሳሁት ገና አላለቅም እሱንም ማፋጥን ነው ። ይህ ከሆነ ብዙ ችግራችን ይቃለልናል

ስድስተኛ ዘይት አገራችን ውስጥ መጭመቅ። ብርቱካን ልኮ የብርቱካን ጭማቂ መግዛት ማቆም አለብን

ስባተኛ የምግብ እርሻ በብዛት በጥራት መገንባት ለምሳሌ የዶሮ እርባት በጣም በዘመናዊ መንገድ መጀመርና ለግለስቦች መሽጥ፣ የወተት ላሞችንን እርሻ እንዲሁ። መንግስት እነዚህን ኢድስትሪዎች ጀምሮ ወድ ግል እያዞረ መሄድ አለበት።

ሌላም ይቀጥላል

Post Reply