Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum

Wedi
Member+
Posts: 7996
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: ዋልታና ፋና የብልጽግና ሚዲያ ናቸው! ኢሳት የኢዜማ ሚዲያ ነው! ኢሳት አለማቀፍ የማን ሚዲያ ነው?

Post by Wedi » 27 Mar 2022, 05:08

ከኢዜማ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ “ESAT International” aka የብልጽግና/የኦሮሙማ ሚዲያን በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ


የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ - ኢዜማ Ethiopian Citizens for Social Justice

ከኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (#ኢዜማ) ብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ


መጋቢት 14 ቀን 2014 ዓ.ም ከኢሳት የተለዩ ጋዜጠኞች ከሚዲያ ተቋሙ ጋር የተለዩበትን ምክንያት ለህዝብ ይፋ ባደረጉበት ወቅት በተደጋጋሚ የፓርቲያችንን ሥም በሐሰት በመወንጀል ጠቅሰዋል።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ሥም ከሚድያ ባለቤትነት እንዲሁም ለኢሳት የተሰበሰበ ገንዘብን ከመውሰድ ጋር ተደጋግሞ ተነስቷል፡፡
ፓርቲያችን በጋዜጠኞቹ የቀረበበትን ሥም ማጥፋት ፈፅሞ አይቀበልም፡፡ ኢዜማ የትኛውም የፖለቲካ ፓርቲ የሚድያ ተቋምን በባለቤትነት ከያዘ ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ትልቅ እንቅፋት እንደሚፈጥር የሚያምን ሲሆን ይህ በአገራችን ህግም በግልፅ የተከለከለ ነው። ስለሆነም ኢዜማ በእንዲህ ያለ ድርጊት ውስጥ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎችንም በጥብቅ ይታገላል፡፡

ለኢሳት የተሰበሰበ ገንዘብ ለፓርቲያችን ኢዜማ ተላልፏል የተባለውም የፈጠራ ክስ ነው። ገንዘቡ በማን አካውንት እንዳለ የቦርድ አባላቱ እና አሁን በኢሳት ውስጥ ያሉትም ሆነ ተለየን የሚሉት ጋዜጠኞች በሚገባ የሚያውቁት ሃቅ ነው።

እንዲህ አይነት አሉባልታዎች የፖለቲካ ባህል እየሆኑ የመጡበትን ሁኔታ የምንገነዘብ ቢሆንም የሙያ ስነ-ምግባር አላቸው ብለን ከምናምናቸው እና ሰፊ ልምድ ካካበቱ ጋዜጠኞች ያልጠበቅነው በመሆኑ ሀፍረት እንደተሰማን ለመግለፅ እንወዳለን።

በመጨረሻም ኢዜማን በግልፅ በከሰሳችሁበት የሚድያ ባለቤትነት ጉዳይ፣ እንዲሁም ለኢሳት ተሰብስቦ ለፓርቲያችን ተላልፏል ስላላችሁት ገንዘብ ያላችሁን ማስረጃ ለህዝብ በግልፅ እንድታቀርቡ፣ ያለዚያ እውነቱን እያወቃችሁ የዋሻችሁት ህዝብ ፊት ፓርቲያችንን በይፋ ይቅርታ እንድትጠይቁ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡

ኢዜማ በጠንካራ የድርጅት ባህል እና ሀላፊነት በሚሰማው የፖለቲካ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ዘመን ተሻጋሪ ፓርቲ ሆኖ ይቀጥላል፡፡

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ብሔራዊ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ

መጋቢት 18 ቀን 2014 ዓ.ም.
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ


Please wait, video is loading...

Right
Member
Posts: 2833
Joined: 09 Jan 2022, 13:05

Re: ዋልታና ፋና የብልጽግና ሚዲያ ናቸው! ኢሳት የኢዜማ ሚዲያ ነው! ኢሳት አለማቀፍ የማን ሚዲያ ነው?

Post by Right » 27 Mar 2022, 08:18

Wedi,
This is what you call FACT CHECKING.

Some people just write something rabbis based on assumptions.

Horus
Senior Member+
Posts: 30933
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ዋልታና ፋና የብልጽግና ሚዲያ ናቸው! ኢሳት የኢዜማ ሚዲያ ነው! ኢሳት አለማቀፍ የማን ሚዲያ ነው?

Post by Horus » 27 Mar 2022, 11:34

wedi,
እኔ የባንክ ቁጥር ሰጥቼ ኢሳትን የረዳሁ ሰው ነኝ ። ኢሳት ሲጀመር የተቋቋመበትን አላማ ያሳካ ድርጅት ነው። አላማውም የሆነ ገለልተኛ የጋዜጠኝነት መሞላቀቂያ ሳይሆን መታገያ መሳሪያ ነበር ። ያ ተግባሩን በሚያስደንቅ ደረጃ የተወጣ ድርጅት ነው ። ሆኖም ኢሳት ግለሰቦች የተሰበሰቡበት ማህበር ነበር። ግለሰቦች የተለያዩ ናቸው ። ለምሳሌ ጋዜጠኝንትን ለነጻነት ትግል ሊያውሉ የተሰበሰቡት ስደተኛ ጋዜጠኞች የኢሳት ስራቸው የመኖሪያ ሙያ አድርገውት ከራሳቸው ኑሮና ህይወት ጋር ስለ ተሳሰረ የውስጠ ድርጅቱ ንትርክ የአገራዊ አላማ ሳይሆን የግልና ቡድን ስልጣን፣ ገንዘብ፣ ዝና፣ ክብር እና የጥቅም ትግል ሜዳ ሆነ። በኢትዮ360 የተጀመረው እንደ ሽንኩርት መላጥ እንደ ደረጀን ዘሎ ይሀው ኢሳት አለማቀፍ ደርሰናል ። ይህ ሁሉም የስልጣን፣ የገንዘብ፣ የዘና፣ የስም፣ የክብር፣ ወዘተ ትግል እንጂ ሁሉም አንድ ናቸው ። ስራቸው ወሬ መሰብሰባና ማውራት ነው። ሁሉም ችግር ውስጥ የገቡት ያገር ፖለቲካ ሲለወጥ ወደ ሚቀጥለው የፖለቲካ አላማ መሄድ ስላቃታቸው አሁን ሁሉም ግዜያቸው የሚያባክኑት ወይም ገንዘብ መለመኛ ዘዲያቸው እርስበራስ መሰዳደብ ነው ። ሕዝቡ ደሞ ይህን አንቅሮ ከተፋ ሰንብቷል። ስለዚህ ዛሬ የኢትዮጵያ ሕዝብ ኢሳት ምን አለ? ደሬ ምን አለ? ሲሳይ ምን አለ? አትዮ360 ምን አለ? ብሎ አንዳቸውንም የሚጠብቅበት ዘመን አይደለም! ከዚህ በኋላ በኢትዮጵያ የሚገንኑ ሚዲያዎች ከህዝቡ ኑሮና ትልግ ጋር ቀጥታ ግብዓት ያላቸው ብቻ ናቸው። ያ ማለት ደሞ ምድር ላይ ያሉት ናቸው ። አንድ ሚዲያ ላንድ ፓርቲ ሊያጋድል ይችላል፣ያ ምንም አዲስ ዜና አይደለም! ኢሳት የኢዜማ ደጋፊም ሆነ በኢዜማ ተደጋፊ ጉዳዩ ያ አይደለም! ጥያቄው ኢዜማ ምን አላማ አለው? ኢዜማ አፍቃሪው ኢሳት ምን እያደረገ ነው? ይህ ነው የህዝቡ መለኪያ እንጂ በገንዘብ የሚጣሉ ስደተኛ ጋዜጠኞች የሕዝባችን ጭንቀት አይደሉም!

ለማንኛውም የኢዜማው ኢሳት ይህን ጠየቀ፡

"በመጨረሻም ኢዜማን በግልፅ በከሰሳችሁበት የሚድያ ባለቤትነት ጉዳይ፣ እንዲሁም ለኢሳት ተሰብስቦ ለፓርቲያችን ተላልፏል ስላላችሁት ገንዘብ ያላችሁን ማስረጃ ለህዝብ በግልፅ እንድታቀርቡ፣ ያለዚያ እውነቱን እያወቃችሁ የዋሻችሁት ህዝብ ፊት ፓርቲያችንን በይፋ ይቅርታ እንድትጠይቁ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡"

መልሱን ከኢሳት አለማቀፍ የምናየው ይሆናል።

እንደ እውነቱ ከሆነ ሚዲያ መብዛቱ ጥሩ ነው ። ግን የማይረባው ነገር የጋዜጠኞች እርስበርስ የገንዘብ ንትርክ ያገር ዜና አድርጎ ማውራት ነው።

Post Reply