Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የጎሳ ከበርቴዎች የስልጣን ክፍፍል

Post by Horus » 16 Mar 2022, 21:00

Wedi
Member+
Posts: 7994
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: የጎሳ ከበርቴዎች የስልጣን ክፍፍል

Post by Wedi » 16 Mar 2022, 21:38

የትግሬ ወያኔ ከስልጣን ሲባረረ እየሮጠ ወደ ትግርይ ሂዶ በመደበቅ ቢያን ቢያንስ ህይወቱን ለማትረፍ በቅቷል!! እንደ ስዮም ተሾመ፣ ደረጀ ሀብተወልድ እና ጋላ አብይ አህመድ ያለው ሆዳም ከስልጣን ሲባረር የት አባቱ ሂዶ እንደሚቀደበቅ ግዜ ያሳያናል፡፡ የግዜ ጉዳ ነው እንጅ ሁሉ ዋጋውን ያገኛል!!

Sam Ebalalehu
Member
Posts: 3639
Joined: 23 Jun 2018, 21:29

Re: የጎሳ ከበርቴዎች የስልጣን ክፍፍል

Post by Sam Ebalalehu » 16 Mar 2022, 21:56

Wedi a person who hates TPLF does not necessarily hate or doubt Seyoum Teshome. To TPLF cadres this is a difficult thing to differentiate. But here I am the unpaid rescuer of the TPLF clueless cadres.

Horus
Senior Member+
Posts: 30924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የጎሳ ከበርቴዎች የስልጣን ክፍፍል

Post by Horus » 16 Mar 2022, 22:47

ወዲ፣
አቢይን መቃውም መብትህ ሆኖ ሳለ ግን ለማለት የምትፈልገው ነገር ስሜት መስጠት አለበት ። ስዩም ተሾመና ደረጀ አብተወልድ እንደ ሰማይና ምድር የተለያዩ ነገሮች ናቸው። ስዩም ተሾመ ኣቢይ አሀመድን ብቻ ደግፎ የቀሩት እኔ የጎሳ ቡርዡዋ የምላቸውን እሱ ኢህአዴግ ይላቸዋል። ደረጀ ዝም ብሎ አገር ወዳድ አቢይ አፍቃሪ እንጂ ጥልቅ የፖለቲካ ሆነ ፍልስፍናዊ እውቀት የለውም። በብዙ ነገር እኔ ከስዩም የቀረበ አመለካከት አለኝ። አቢይ ሰብስቦ ሲያናግራቸው እንደ ካድሬ ጸጥ ብለው አዳምጠው ከመሄድ በተቀር የሕዝብ መሪ አይመስሉም፣ ካድሬዎች ናቸው። ነጻነታቸው የተሰለበ፣ በራሳቸው እግር የማይቆሙ የመሪነት ባህሪና ወኔ የሌላቸው ተከታዮች ናቸው ። ፈሪዎች ስለሆኑ አዳራሽ ውስጥ ዝም ብለው ወጥተው ከዚያ ሳቦትታዥ ማድረግ ይገባሉ ።

አቢይም እንደ አኩል መሪዎች ሳይሆን እሱ እንደ አንድ ፓስተር ወይም የክፍል አሰማሪ ቁጭ አድርጎ ሌክቸር ያደርጋቸዋል ። ስለዚህ ዲስኢምፓወረድ የሆኑ የራሳቸው ኤጀንሲ የሌላቸው ዲፔንደንት ጥገኛ አንጎሎች ናቸው ። ስለሆነም ብልጽግና እጅግ መሰረታዊ የመሪነት፣ የእውቀትና የፍልስፍና ችግር ያለው ፓርቲ ነው። የዚህን ፓርቲ ድክመት ለመዶገም አቢይ ከኢህአፓ፣ ኢሴፓ እና ሚኢሶን ጋራ እያወዳደረ ከፍ ከፍ ሊያደርጋቸው ይሞክራል፤ እዚያ ላይ ዞሮ ሌቦች ይላቸዋል ። ይህ ያቢይ የራሱ ግዙፍ በራስ የመተማመን ችግር ነው። ብልጽግናን ከፍ ለማድረግ ሌባ የሚላቸውን የጎሳ ጥርቃሞ እንደ ኢሃፓና ሚኤሶን መሰል የምሁራና የጀግንነት ጥግ ፓርቲዎች ጋር ራሱን ባያወዳድርና ያለፉት በነበሩበት አውድ ቢለኩ ፣ እሱ ደሞ አሁን ባለበት አውድ ቢለካ ነው እንደ መሪ የሚከበረው!

ብልጽግና ገና ሰላም እንኳ አስፍኖ በውስጡ አንድ ያልሆነን ፓርቲ ያፍርካ ምንትስ ቅብጥርስ ፕሮፓጋንዳ ነው የሚሆነው። 11 ሚሊዮን አባል አለው የሚባለው ፓርቲ በውስጡ እከሌ የሚባል ምሁር፣ ፈላስፋ ሊቅ ቲኦረቲሻን የለበትም ፣ ሁሉም የጎሳ ኮታ ለመሙላት የተቀመጡ ካድሬዎች ናቸው ።

አብዮያዊ ዴሞክርሲ የሚባል ሶሺያል ሳይንስ፣ ፖለቲካል ሳይንስ የለም! መደመር የሚባል ሶሺያንስ ሳይንስ፣ መደመር የሚባል ፖለቲካል ሳይንስ የለም የለም ! እነዚህ ነጠላ የጽንሰ ሃሳብ ፍሬምወርኮች ናቸው። ትናንሽ ለፕሮጀክት ሃሳብ ማደራጃ ሰው ካንጎሉ የሚወልዳቸው ምሳሌዎች፣ ሜትፎሮች ናቸው እንጂ አንድ ግዙፍ ማህበረ ሰብ አንድ ግዙፍ የፖለቲካ ኦርደር ማደራጃ ፍልስፍናም ሆነ ቲኦሪዎች አይደሉም!

ለምሳሌ አቢይ በፍጹም ስለ ዴሞክራሲ፣ ስለ ሰው ልጅ ነጻነት፣ ስለ ፖለቲካዊና ሾሺያ ጀስቲስ አውርቶ አያቅም ። ስለ ባህል እና የጎሳ መብት ሲያነሳም አንዴም ስለ ዘመናዊ ካልቸር፣ ስለ ፍጠራ፣ ስለማንኛው ሳይንሳዊ የሰው ልጅ እድገት አያነሳም ። ስለዚህ ነገሮች ሁሉ እጅግ ያስፈራሉ! የጆርጅ ኦውርዌሊያን አኒማል ፋርም እንዳንሆን እፈራለሁ!

Wedi
Member+
Posts: 7994
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: የጎሳ ከበርቴዎች የስልጣን ክፍፍል

Post by Wedi » 17 Mar 2022, 05:42

Horus wrote:
16 Mar 2022, 22:47
ወዲ፣
ስዩም ተሾመና ደረጀ አብተወልድ እንደ ሰማይና ምድር የተለያዩ ነገሮች ናቸው። ስዩም ተሾመ ኣቢይ አሀመድን ብቻ ደግፎ የቀሩት እኔ የጎሳ ቡርዡዋ የምላቸውን እሱ ኢህአዴግ ይላቸዋል። ደረጀ ዝም ብሎ አገር ወዳድ አቢይ አፍቃሪ እንጂ ጥልቅ የፖለቲካ ሆነ ፍልስፍናዊ እውቀት የለውም።
Horus ከላይ አንተ ስለ ደረጀ ሀብተወልድ የጻፍከው ትክክል ነው፡፡ እገር ቤት እያለን ከደረጀ ጋር ለበርካታ አመታት አብረን በአንድ መስርያ ቤት የሰራንብ ሰዎች ነን፡፡ ደረጀ ሀብተወልድን አንተ ከምትገምተው በላይ አውቀዋለሁ ለማለት ነው፡፡ የጉማሬ ስዮም ተሸኦመን ነገር ተወው፡፡ ጉማሬ ስዮም ያነው ጉማሬ ነው፡፡ በነገራችን ላይ ስዮም ተሾመ አቅጣጫ ከመቀየሩ በፊት የወያኔ አሽከር ነበር፡፡ የእነ ዳንኤል ብርሃኔ ተቀጣሪ እና ቁሚ ደንበኛ የነበረ ሰው ነው፡፡
Please wait, video is loading...

DefendTheTruth
Member+
Posts: 9924
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

Re: የጎሳ ከበርቴዎች የስልጣን ክፍፍል

Post by DefendTheTruth » 17 Mar 2022, 08:37

Horus wrote:
16 Mar 2022, 22:47
ወዲ፣
አቢይን መቃውም መብትህ ሆኖ ሳለ ግን ለማለት የምትፈልገው ነገር ስሜት መስጠት አለበት ። ስዩም ተሾመና ደረጀ አብተወልድ እንደ ሰማይና ምድር የተለያዩ ነገሮች ናቸው። ስዩም ተሾመ ኣቢይ አሀመድን ብቻ ደግፎ የቀሩት እኔ የጎሳ ቡርዡዋ የምላቸውን እሱ ኢህአዴግ ይላቸዋል። ደረጀ ዝም ብሎ አገር ወዳድ አቢይ አፍቃሪ እንጂ ጥልቅ የፖለቲካ ሆነ ፍልስፍናዊ እውቀት የለውም። በብዙ ነገር እኔ ከስዩም የቀረበ አመለካከት አለኝ። አቢይ ሰብስቦ ሲያናግራቸው እንደ ካድሬ ጸጥ ብለው አዳምጠው ከመሄድ በተቀር የሕዝብ መሪ አይመስሉም፣ ካድሬዎች ናቸው። ነጻነታቸው የተሰለበ፣ በራሳቸው እግር የማይቆሙ የመሪነት ባህሪና ወኔ የሌላቸው ተከታዮች ናቸው ። ፈሪዎች ስለሆኑ አዳራሽ ውስጥ ዝም ብለው ወጥተው ከዚያ ሳቦትታዥ ማድረግ ይገባሉ ።

አቢይም እንደ አኩል መሪዎች ሳይሆን እሱ እንደ አንድ ፓስተር ወይም የክፍል አሰማሪ ቁጭ አድርጎ ሌክቸር ያደርጋቸዋል ። ስለዚህ ዲስኢምፓወረድ የሆኑ የራሳቸው ኤጀንሲ የሌላቸው ዲፔንደንት ጥገኛ አንጎሎች ናቸው ። ስለሆነም ብልጽግና እጅግ መሰረታዊ የመሪነት፣ የእውቀትና የፍልስፍና ችግር ያለው ፓርቲ ነው። የዚህን ፓርቲ ድክመት ለመዶገም አቢይ ከኢህአፓ፣ ኢሴፓ እና ሚኢሶን ጋራ እያወዳደረ ከፍ ከፍ ሊያደርጋቸው ይሞክራል፤ እዚያ ላይ ዞሮ ሌቦች ይላቸዋል ። ይህ ያቢይ የራሱ ግዙፍ በራስ የመተማመን ችግር ነው። ብልጽግናን ከፍ ለማድረግ ሌባ የሚላቸውን የጎሳ ጥርቃሞ እንደ ኢሃፓና ሚኤሶን መሰል የምሁራና የጀግንነት ጥግ ፓርቲዎች ጋር ራሱን ባያወዳድርና ያለፉት በነበሩበት አውድ ቢለኩ ፣ እሱ ደሞ አሁን ባለበት አውድ ቢለካ ነው እንደ መሪ የሚከበረው!

ብልጽግና ገና ሰላም እንኳ አስፍኖ በውስጡ አንድ ያልሆነን ፓርቲ ያፍርካ ምንትስ ቅብጥርስ ፕሮፓጋንዳ ነው የሚሆነው። 11 ሚሊዮን አባል አለው የሚባለው ፓርቲ በውስጡ እከሌ የሚባል ምሁር፣ ፈላስፋ ሊቅ ቲኦረቲሻን የለበትም ፣ ሁሉም የጎሳ ኮታ ለመሙላት የተቀመጡ ካድሬዎች ናቸው ።

አብዮያዊ ዴሞክርሲ የሚባል ሶሺያል ሳይንስ፣ ፖለቲካል ሳይንስ የለም! መደመር የሚባል ሶሺያንስ ሳይንስ፣ መደመር የሚባል ፖለቲካል ሳይንስ የለም የለም ! እነዚህ ነጠላ የጽንሰ ሃሳብ ፍሬምወርኮች ናቸው። ትናንሽ ለፕሮጀክት ሃሳብ ማደራጃ ሰው ካንጎሉ የሚወልዳቸው ምሳሌዎች፣ ሜትፎሮች ናቸው እንጂ አንድ ግዙፍ ማህበረ ሰብ አንድ ግዙፍ የፖለቲካ ኦርደር ማደራጃ ፍልስፍናም ሆነ ቲኦሪዎች አይደሉም!

ለምሳሌ አቢይ በፍጹም ስለ ዴሞክራሲ፣ ስለ ሰው ልጅ ነጻነት፣ ስለ ፖለቲካዊና ሾሺያ ጀስቲስ አውርቶ አያቅም ። ስለ ባህል እና የጎሳ መብት ሲያነሳም አንዴም ስለ ዘመናዊ ካልቸር፣ ስለ ፍጠራ፣ ስለማንኛው ሳይንሳዊ የሰው ልጅ እድገት አያነሳም ። ስለዚህ ነገሮች ሁሉ እጅግ ያስፈራሉ! የጆርጅ ኦውርዌሊያን አኒማል ፋርም እንዳንሆን እፈራለሁ!
This could be true, or we can assume so for a while.

The next most important question then will be, why you (your camp) failed to defeat such a weak and "unfit" party?

Unless you are able to answer this follow-up question properly, you can keep writting 1000s of lines of critiques but that will remain inconsequential in the end effect.

The other important issue is that ጎሳ in Ethiopian context is an issue that needs to be addressed for us to move forward and progress effectively. You keep criticizing those who took up the issue without providing your own alternative means of addressing the issue itself. This is also another indication of your (plural) failure. Here you are effectively shooting the messengers instead of the message.

You are good at criticizing but next to nothing when it comes to providing any better alternative.

These points are not my personal views but emprically proven dogmas, you can leave it or take it.

Abere
Senior Member
Posts: 11132
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: የጎሳ ከበርቴዎች የስልጣን ክፍፍል

Post by Abere » 17 Mar 2022, 10:39

እንደ ውታፍ ነቃዮች እና የሞት ነጋዴዎች(merchant of death) ጎሳ ለአንድ ሰው በህይወት ለመኖር ኦክስጅን አየር፤ ውሃ፤ምግብ ፤መጠለያ ነው። ማንም ሰው ጎሳ ካልሆነ መኖር አይችልም - ተወርውሮ ወደ እሳት ይጣላል። የዳቦ ወይም የምግብ ችግር ጊዜ ይሰጣል ጎሳ ግን ኦክስጅን ነው - ለመኖር እጅግ አስፈላጊ። ወይ ጉድ! በዚህ የሞት ነጋደዎች ፍልስፍና መሰረት - ጎሳ የሌላቸው ሰዎች በኢትዮጵያ መኖር አይችሉም። ደግሞ አንድ ግለሰብ ከ7 ጎሳዎች በላይ የተወለደ ቢሆን ይህ ሰው ጎሳው ማን ሊባል - አገሩስ የት ነው? ለመሆኑ ኢትዮጵያ ጎሳ ነው ቋንቋ ያለው? የተሻለ ዕውቀት ያለው ሰው ቢያብራራልኝ ( እንደ ሆረስ አይነት) አመሰግናለሁ - ውታፍ ነቃይ አለፈልግም።

Horus
Senior Member+
Posts: 30924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የጎሳ ከበርቴዎች የስልጣን ክፍፍል

Post by Horus » 17 Mar 2022, 11:52

DTT
ፍሬ ከዛፉ ርቆ አይወድቅም ይባላል! ብልጽግና የኢሃድግ ውላጅ ነው! በመደመር ጠርሙስ ውስጥ የተሞላ የውያኔ ትግሬ ቅራሬ ነው! ስልጣን ይዘናል ምን ይጠበስ? ምን ታደርጋለህ የሚለው የባለተራዎች እብሪት ምን እንደ ሚያስከትል ትግሬዎችን ጠጋ ብለህ ጠይቃቸው!!! እኔ አንተን የፖለቲካ ሳይንስ ማስተምርበት ግዜ የለኝም ። ምን አማራጭ መፍትሄ ላልከው ወደ ኋላ ተመለስና ላለፈው 10 አመት ያደረገነውን ክርክር አንብብ! ወያኔዎች ሽቅብ ይቀዝኑ በነበረ ግዜም ትቃወመኝ ነበርኮ አትርሳ!

Post Reply