Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 11135
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

እስክንድር ነጋ የእውነት የፍትህ ዐርበኛ - ለጥምር የኢትዮጵያ ጠላቶች ወያኔ እና ኦነግ የጎን እሾህ፤ ሆድ አደሮችን የሃፍረት ሻማ ያጎናጸፈ - የዘመናችን ጀግና።

Post by Abere » 06 Mar 2022, 18:42

እስክንድር ነጋ የእውነት የፍትህ ዐርበኛ - ለጥምር የኢትዮጵያ ጠላቶች ወያኔ እና ኦነግ የጎን እሾህ፤ ሆድ አደሮችን የሃፍረት ሻማ ያጎናጸፈ - የዘመናችን ጀግና።
ተከፋይ ደሞዝተኛ የኦነግ ብልጽግና ወይም የሆድ አደር ብ አደን ልቅሶ እና ጩኸት የእስክንድርን የእውነት መሰረት አያናውጥም። ትግል በጽናት እና በእውነት አለት ላይ እንደ እስክንድር ሲመሰረት እንጅ በካድሬነት ከሚገኝ የዳቦ ፍርፋሬ የባንክ አካውንት መጠን አይደለም። እስከ አሁን በአይናችን እንደምናየው እስክንድ እነዚህን ጣምራ ጠላቶች በብዕር እና በአስተሳሰብ በጽናት እያሸናፋቸው ነው - ውሸታቸው አቅልሎ አቅልሎ የ5 ሳንቲም ቂቤ ያህል አሳንሶ እያቀለጣቸው ነው። ቁመን እናስተውል ከዛሬ ሶስት አመት በፊት ዐብይ አህመድ የተናገረው እና የነካው ሁሉ እውነት ነው ተብሎ በብዙ ኢትዮጵያዊያን ዘንድ ቅቡል ነበር። እስክንድር ግን አብይ አህመድ አምሳለ ዳግም ወያኔ የውሸት ቁንጮ ነው ብሎ እስከ እስር ቤት ወርዶል። በሂደት ግን ያየነው የአብይ ወይም ኦነግ ብልጽግና ውሸት በዐደባባይ ተከስቶ እርቃኑን ሲሄድ ነው። ይህ ትውልድ እየሞተ የማያምን ድንጋይ ነው - ወይም በሆዱ ብቻ የሚገዛ ነው። እስክንድር የእውነተኛዋ ኢትዮጵያ ድምጽ ነው - የታፈኑ ድምጾች የሚያወጣ የነጻነት ማጉሊያ ነው። የነጻነት የመስዋዕት በግ አድርጎ እራሱን ያሳለፈ ነው እርሱ የአሳማዎች አቻ አይደለም።


Abere
Senior Member
Posts: 11135
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: እስክንድር ነጋ የእውነት የፍትህ ዐርበኛ - ለጥምር የኢትዮጵያ ጠላቶች ወያኔ እና ኦነግ የጎን እሾህ፤ ሆድ አደሮችን የሃፍረት ሻማ ያጎናጸፈ - የዘመናችን ጀግና።

Post by Abere » 08 Mar 2022, 15:46

የእስክንድር ነጋን የጫማ ማሰሪያ ለመፍታት የማይበቃ ፋንድያ - ታዲያለሁ ይባላል።
[size=150 wrote:Tadiyalehu[/size] post_id=1279262 time=1646614179 user_id=43007]
ቂጥ-አፍ :lol:
አራም!

Post Reply