Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

የደጃዝማች ባህታ ሓጎስ - “አባ ጥመር” ታሪክ፣ በኤርትራዊው እይታ!

Post by Meleket » 02 Mar 2022, 03:54

ከዓድዋ ድል በፊት፡ አስቀድመው ገድል የፈጸሙትን ኤርትራዊ ጀግና ስንዘክር፡ ተልባ ባንድ ሙቀጫ እየወቀጥን ነው፡ ኤርትራዉያን የመስመርና የመሃል ዳኞች :mrgreen:
Meleket wrote:
05 Sep 2018, 00:25
ኤርትራ ውስጥ ሰሞኑን “ተጋዳላይ ሃይለስላሴ ወልዱ” የተባለ ዜጋ፣ መስከረም በደረሰ ቁጥር የምናስታውሰውን የአርበኛውን የሓምድ እድሪስ ዓዋተን ታሪክ 500 ገጾች ባሉት ደጎስ ያለ መጸሐፍ አቅርቦልናል። ጅግና ተጋዳላይ ሃይለስላሴ ወልዱ ንስለ ምርምራዊ አበርክቶካ ነመስግነካ!!! ይህን አዲስ መጸሐፍ አንብበን ታሪኩን በወጉ እስክናጣጥም ድረስ እስኪ የደጃዝማች ባህታን ታሪክ እንኮምኩም።

በእውቀቱ ሥዩም የደጃዝማች ባህታን ታሪክ “ከአሜን ባሻገር” በተሰኘው መጽሐፉ ለመዳሰስ እንደሞከረ ይታወቃል። ተስፋዬ ገብረአብም እንዲሁ “የኑረነቢ ማኅደር” በተሰኘው መጸሐፉ የደጃዝማቹን ታሪክ በእይታው ለመዳሰስ ሞክሯል። የሚከተለውን ታሪክ ደግሞ አንድ ስምኦን ኣማኑኤል የተባለ ኤርትራዊ በከፊል የኤርትራን ታሪክ በዳሰሰት መጸሐፉ የደጃዝማቹን ታሪክ በዚህ መልኩ እይታውን አቅርቦልናል። እንደ ኤርትራውያን የጋራ እይታ እውነተኛ ታሪክ የሚባል ድልህንም ሽንፈትህንም ሁሉን ከታሪክ አኳያ የሚገልጽ እንጂ፣ መልካም ብለህ የምታስበውን ብቻ ኳኩለህ የምታቀርበው እንዳልሆነ ግልጽ ነው። ያም ሆነ ይህ የስምዖንን የታሪክ እይታ የምታጣጥሙ በሉ እስቲ እነዚህ ታሪካዊ ሓቆችን ማወራረጃ እያደረጋቹ ኮምኩሙ።

1.) በአጤ ሚኒሊክ አመራር ዓድዋ ላይ በጣልያን ላይ ከተደረገው ድል በፊት፣ ደጃዝማቹ ጣልያንን ብቻውን የተጋፈጠ ኩሩ ሓበሻ መሆኑን
2.) የትግራዩ ራስ መንገሻ ሥዩም ኾዓቲት ላይ ከጣልያን ሰራዊት ጋር ተዋግተው ከመሸነፋቸው በፊት፣ ይህ ደጃዝማች ብቻውን ከጣልያን ጋር ተዋግቶ መስዋዕትነትን የመረጠ ሰው መሆኑን
3.) ደጃዝማቹ ከጣልያን ጋር ተፋልሞ መስዋዕት በሆነ ማግስት፣ የትግራዩ ራስ መንገሻ ለጣልያኖች እንኳን ደስ አላቹ የሚል “የደስታ መግለጫ” መልዕኽት ልኮ እንደነበረ፤ ይህንና ይህን የመሰሉ ታሪካዊ ሓቆችን ልባችን ውስጥ አትመን፣ የ ስምዖንን መጸሐፍ ይዞታ እስቲ እንኮምኩም።

በዚህ ጽሑፍ ስር የሰፈረውን ታሪክ ብዙ የተለያዩ ኣዛውንቶች ለኣባ ፍስሃጽዮን የተረኩላቸው ታሪክ እንዲሁም ኣዝማች ገብረሚካኤል ግርሙ “ደግያት ባህታ ሓጎስ ሰገነይቲ” በሚለው መጸሃፋቸው ላይ ያሰፈሩትን ያጠቃልላል። በተጨማሪም በ 1893 ሩፌሎ ፐሪኒ የተባለው ጣሊያናዊ ጸሃፊ ደጃዝማች ባህታ ሓጎስን በአካል ካገኛቸው በኋላ ያሰፈረውን እማኝነት ያጠቃልላል።

“ግርማ ሞገስ ያለው ደስ የሚል አለባበስ የሚያዘወትር ስለሆነ አክብሮት እንደሚገባው ገና ለመጀመሪያ ግዜ ስታየው ይገለጽልሃል። ወንድሙን ስለገደለ ወትሮም ፊቱ ትልቅ ሓዘን ይነበብበታል። ለበርካታ ስነምግባር ብልሹ ለሆኑ ጣሊያናዊ ወጣቶች ምንም የማይበገር ሰው ነው። በአከለጉዛይ ውስጥ ብዙ ጠላቶች ነበሩት ይህም ደግሞ ለመጀመሪያ ግዜ በወታደራዊ ቁጥጥር ስር በኃይል ስለመጣባቸው ከቅናት የተነሳም ሊሆን ይችላል” ይላል ሩፌሎ ፕሪኒ በመጸሃፉ።

በተጨማሪም ደጃዝማች ባህታ ሓጎስ ሃይማኖታዊ ትእግስተኛ አስተዋይና ደፋር ለወዳጆቻቸው ጠቃሚ ለጠላቶቻቸው ደግሞ ሃያል ተቃዋሚ ነበሩ። ነገር ከመጀመራቸው በፊት ደባቂ ረጋ ብለው የሚያስቡና አንድን ነገር እፈጽመዋለው ብለው ካሰቡ ደግሞ መደምደሚያው ላይ ሳይደርሱ የማይተው የማያወላውሉ፣ የወንድማቸውን የሰንጋልን ምክር ካልሆነ በስተቀር የሌላ ሰው ምክር የማይቀበሉ፣ ፈሪሓ እግዚኣብሔር ያላቸው፣ በሄዋን ልጆች ወይ በሴቶች ፈጽመው የማይታለሉ ነበሩ። ሲፎክሩም “እኔ የግምጁ ወንድም” ይሉ ነበር። የፈረሳቸው ስም “አባ ጥመር” ይባል ነበር። የሳሆን ቋንቋ በደንብ አድርገው አቀለጣጥፈው መናገርም ይችሉ እንደነበር ይነገርላቸዋል።

ደጃዝማች ባህታ የተራ ገበሬ ልጅ ሲሆኑ፣ በልጅነታቸው አባታቸው በአምባጓሮ መካከል ህይወታቸው አለፈች። ከእለታት አንድ ቀን ለሰርግ ማዕረባ ወደተባለችው ቀየ እንደሄዱ፣ በአካባቢው ባህል መሰረት በሰርግ ወቅት ሴት ልጆች በዘፈን አማካኝነት እንደፈለጉት መሳደብ ስለሚችሉ እነ ባህታ ሓጎስን “አየ የሓጎስ ልጆች አየ የሮማይ ልጆች ፣ ከአባታቸው ገዳይ ጋር ወሃ ጠጪወች” በማለት ወደ ባህታ ሓጎስ ያነጣጠረ ስድባቸውን አወረዱ። ሊበላ ተቀርቦ የነበረውን ገበታም በቦታው በመተው፣ አባቴን ገድሎት ይሆናል ብለው ይጠረጥሩት የነበረውን ሰው ወደ በረሃ በመሄድ ገደሉት። በዚህ ሁኔታም ሰለድ ወደ ተባለው ቦታ በመሄድ ሸፈቱ።

በአንድ ወቅት ፊተውራሪ እምባየ የተባለ የራስ አርአያ ልጅ ማለትም የአጼ ዮሃንስ የእህታቸው ልጅ ለዝርፊያና ለወረራ ወደ የቡር ምድር መጣ። ሴት ልጆችንም የተደበቀ ንብረታቸውን ያመጡ ዘንድ ጡታቸውን በፈረስ ጭራ እያሰረ ያሰቃያቸው ነበር። ወንዶችንም የፊጥኝ በማሰር በጀሮዎቻቸውም የዓተር ቆሎ በማስገባት የደበቃችሁትን መሳርያ አምጡ እያለ ከፍተኛ በደልና ግፍ ይፈጽም ነበር። በዚህ ሁኔታ እያለም በእገላ ሓመስ በተባለ ቀየ አንዳንድ ሰዎች “ሂድ በኃያሎች እጅ ያውድቅህ” በማለት ረገሙት።

በጥቅምት ወር በ1876 ፊተውራሪ እምባየ ወደ ሰገነይቲ እንደገባ እንደ አመሉ ግፍና በደል መፈጸሙ ሳይበቃው በተጨማሪም የሰባ ፍሪዳና ቆንጆ ሴት እንዲያቀርቡለትም አዘዘ። የቀየዋ ሽማግሌዎችም ከሁሉ ሁሉ የሴት ነገር ጨነቃቸው፣ ከመካከላቸችው ግን አንዲት እራሷን ለመስዋእትነት ያዘጋጀች ቆንጆ መርቁኝ እንጂ እኔ እሄዳለው በማለት፣ ይጠላት ዘንድም መላው አካላቷን በቅቤ ታጥባ ወደ ፊተውራሪ እምባየ ፊት ቀረበች። ፊተውራሪ እምባየም ተቆጥቶ አባረራት። እርድ አቅርቡልኝ ብሎ አዝዞ ስለነበረም የሰባ ፍየል አረዱለት። በተጨማሪም ውሃ ለመቅዳት ወደ ወንዝ ይወርዱ የነበሩትን ሴቶች የሱ ሰራዊት እንደፈለጉት ሆነው ስላልተገኙላቸው በሸቁ። በማግስቱም ፊተውራሪ እምባየ ተቆጥቶ እኔ ፈንጣጣ አመመኝ ብያችኋለው እንዴ ያልተቀጠቀጠ ወጠጤ የምታርዱልኝ በማለት አረመኔነቱን ገለጸ።

ይህን አይነት ትዕቢትና ማን አለብኝነት በጣም ያናደዳቸው የሰገነይቲና ያካባቢው ህዝቦችም፣ ሆ በማለት በዱላና በጦር ብቻ መሳርያ ካነገቡት ከፊተውራሪ እምባየ ሰራዊት ጋር ጦርነት ገጠሙ። ይህ በእንዲህ እንዳለ የህዝቡን መከታ ሊቆጣጠሩት ያልቻሉ ወራሪዎችም የቀረባቸውን ሰው በጥይት እያወደቁ ወደ ደቡብ አቅጣጫ ሸሹ።

አስቀድሞም እርዱን የሚል መልእኽት በሁሉም አቅጣጫ ተልኮ ስለነበረም፣ ባህታ ሓጎስ የሚገኝባቸው ብዙዎችም ሰለድ ከተባለው የሰገነይቲ አካባቢ (አንዳንዶች እንደሚሉት ደግሞ ከባህታ ሓጎስ የእናቱ ቀየ ከሆነችው ከደግራ ልብኤ) በመነሳት ለእርዳታ መጡ። በጦርነቱ ወይም በግጭቱም ተክሉና ጓንጉል የሚባሉ የባህታ ሓጎስ የአጎቶቹ ልጆች የሚገኙባቸው ሰባት ሰዎች በወራሪዎች ተገድለው ቆዮዋቸው። በዚህ የተበሳጩት ባህታ ሓጎስም በሳሆ ቋንቋ “ረዘንቲ መሓቢንያንየ መርዓዊ መሓቢንያንየ፣ ጓንጉል ደራኪንያየ” እያሉ ማለትም “ሹመኛውንም ቢሆን ፊተውራሪ እምባየንም ቢሆን አትማሩት፣ ጓንጉል እንደሆነ ሞቷል” እያሉ ዓረኮሮ ወደ ተባለ የደግራ ልብኤ መሬት ማለትም ከሰገነይቲ በስተደቡብ እዋነት በተሰኘ ቀየ አቅጣጫ ሲደርሱ ዓርብ ዕለት ፊተውራሪ እምባየን ገደሉት። የፊተውራሪ እምባየ ሰራዊትም በመሸሽ መረብን ተሻገሩ።

ደጃዝማች ባህታ ሓጎስ ፊተውራሪ እምባየን የገደሉት ወንድሞቻቸውን በትዕቢት ተወጥሮ ስለገደለባቸው እንጂ፣ ለሹመት ወይም የሰው ገንዘብ ለመዝረፍ ብለው አልነበረም። እሱ ጥይት ሲተኩስባቸውና ሲያቆስላቸው፣ እሳቸው ግን በጦር ነበር ሆዱን ቦድሰው የገደሉት። ፊተውራሪ እምባየ ከሞተ በኋላም የወይራ ቅጠል አምጥተው በማልበስ ካህናትና ንዋየ ቅዱሳትን በማምጣት በፍትሃትና በክብር ነበር ዓደንጎፎም በተባለው ቀየ ውስጥ በሚገኘው የደብረ ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስትያን የቀበሩት። ሲቀበርም ከመሳሪያው በስተቀር ከነሙሉ ትጥቁ ነበር የቀበሩት። መቃብሩንም እንከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ብዙ ሰው ያውቃት ነበር።
ደጃዝማች ባህታ ፊተውራሪ እምባየን እንደገደሉ አቶ ምሑር የተባሉ የወርሒ ለይቶ የተባለ ቀየ ገዛ መከዳ ማዕረባ ተወላጅ እንዲህ በማለት ሙሾ ደረደሩላቸው፦

ለመቅጠን ለመቅጠን ባህታ ይቀጥናል፣
የንጉሥ ልጅ ሲገል መች ይፈራል፣
ጀግና ባህታ ሓጎስ ለሃገሩ መከታ፣
ምን ያጋጥመው ይሆን የማታ የማታ፣
ሚሆነውን እንጃ የማታ የማታ።
የንጉስ ሰራዊት በጥይት እየተኮሰ ቃታ፣
ጀግናው ባህታ ሓጎስ ግን በጦርና ዋልታ፣
ወራሪን ግፈኛን ድል የመታ።
በማለት ገጠሙላቸው። (ይቀጥላል)

Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የደጃዝማች ባህታ ሓጎስ - “አባ ጥመር” ታሪክ፣ በኤርትራዊው እይታ!

Post by Meleket » 02 Mar 2022, 05:03

"ተልባ እየወቀጥን" ትረካችንን እንቀጥላለን ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች። :mrgreen:
Meleket wrote:
07 Sep 2018, 00:27
ራስ አሉላ እንደ አሸን የፈላ ሰራዊቱን መርቶ በምድሪ ባሕሪ ብዙ ቦታዎች አስከፊ ዘረፋን አድርጎ ነበር። ያኔም ግፉ ያንገሸገሻቸው ሰዎች “የአሉላ ሰራዊት ከአንበጣ የከፋ ነው፣ አንበጣ እንደሆነ ጎተራ ውስጥ ዘው ብሎ ገብቶ እህልህን አይበላብምህም።” እስከማለት ደርሰው እንደነበር እያጣጣምን። አሁን ወደ ስምዖን እይታ፦

ደጃዝማች ደበብ የአባቱን መሀላ በመጣስ የወንድሙን የፊተውራሪ እምባየን ደም ለመበቀል ከትግራይ በመምጣት፣ የደጃዝማች ባህታ ሓጎስን ቤተሰብ ቤት በማቃጠል፣ ቤቱ ሰፍሮበት የነበረውን ቦታ ሳይቀር በበሬ በማረስ ድምጥማጡን ለማጥፋት ሞከረ። ልክ ወንድሙ ያደርገው እንደነበረም የሰገነይቲን ህዝብ ዘረፈ። ደጃዝማች ባህታ ግን ቤተሰቦቻቸውን ይዘው ዱርቤቴ በማለት በበረሃ ሰፈሩ፣ ደጃዝማች ደበብም አዘናግቶ ሊገድላቸው ስለፈለገ ማድባቱን ቀጠለ። ሁለቱ ተጻራሪዎች ይተዳደኑ በነበረበት ወቅትም የአካባቢውን ህዝብ ጥበብና ልቦና እንዲሁም ምስጢራዊነት የሚገልጽ የአንድ ቀን ፍጻሜን የሚያወሳ ታሪክ እናገኛለን።

ደጃዝማች ባህታ ሚስታቸው በእናታቸው ሔቦ ከተባለው ቀየ ተወላጅ ነበሩ፣ ስለሆነም በቀየዋ ውስጥ የነዚህ ቤተሰቦች የተያያዙ አምስት ቤቶች ነበሯቸው እስከ አሁን ድረስም አሉ። ደጃዝማች ባህታ ወደ ሔቦ እንደገቡ ደጃዝማች ደበብ ደግሞ ደጃዝማች ባህታን ለመፈለግ ወደ ሔቦ መጣ። የቀየዋ ሰዎችም ደጃዝማች ባህታን በስተሰሜን፣ ደጃዝማች ደበብን በስተደቡብ አቅጣጫ በአንድ ቤት ውስጥ አስገብተው አብልተውና አጠጥተው በማዋል ሸኟቸው። የማታ ማታም ደበብ ወደ ሰገነይቲ ሄደ፣ አንዳንድ ሰዎችም “ባህታን እኮ ደብቀውህ ነው እንጂ እዛ የዋልክበት ቤት ውስጥ እኮ ነው የነበረው” በማለት ነገሯቸው። ደጃዝማች ደበብም በድንጋጤ “ምን አይነት ሁለት እሳትን በአንድ ቤት ጥላ ስር ሊያውሉ የሚችሉ ጀግኖች ናቸው! ምናለ ሃገሬ ቢሆኑ፣ አንዳችንን ለመግደል ቢፈልጉ ኖሮስ ማድረግ በቻሉ ነበር እኮ ወይ ጉድ” አለ፣ በማለት የሔቦ ታላላቅ አባቶች ይህን የመሰለውን በራስ የመተማመንን እውነተኛ ታሪክ ያወሱ ነበር።

በኋላም ደጃዝማች ባህታ ‘ደግዓ’ በተባለው ‘የቶርዓ መሬት’፣ ‘ዓጉምቦሳ’ በተባለው ‘የባህሪ መሬት’ እንዲሁም የደጃዝማች ባህታ ምሽግ በተባለው ‘በዓጋመዳ’፣ ‘በዓላ’ ‘በአፈልባ’ መሬት እየተዘዋወሩ፣ ከነ ቤተሰባቸው እየተዘዋወሩ ሊያጠፏቸው ከተነሱት ከነ ደጃዝማች ደበብ ሰራዊት ጋር በየተመቻቸው ቦታ እየተጋጠሙ በርካታ መሳርያ ማረኩ። ራስ አርአያ በራስ አሉላ እንደተተካም አንዳንድ የአካባቢው ሰዎች የደጃዝማች ባህታ ከብቶች ከባሕሪ ወደ የዓላ መሬት እንደገቡ ለአሉላ ነገሩት። ራስ አሉላም ስፍር ቁጥር ያልነበረውን ሰራዊቱን በሙሉ ይዞ በአካባቢው ሰዎች እየተመራ ማንም ሳያውቀው በለሊት በእገላ ሓመስ አድርጎ የዓላን ሜዳ ወረረው። የራስ አሉላ ሰራዊትም ያገኘውን ፍየልና ከብት በሙሉ አንድ ሳያስቀር ዘረፈ።

ሰራዊቱም የዘረፈውን ሁሉ ተከፋፈለ፣ ከብቶቹም በማይ ዕዳጋ በኩል በቴድረር በኩል እንዲሁም በሃዘሞ በኩል ወደ ትግራይ ተሻገሩ። የመጀመሪያዎቹ ከብቶች ማይ ዕዳጋ እያሉ የኋለኞቹ ደግሞ ሃዘሞ ደርሰው ነበር። 50ኪሎሜትር የሚሆን መንገድ በአቧራ ተሞልቶ ነበር ይባላል። የተቀሩት ደግሞ በሰሳሕ በደቂናዞ በወቀርቲ መሬት በኩል ወደ አብረንታንቲ አወጧቸው። ያሻቸውን እየመረጡም ይመገቡ ነበር። የተቀሩትን ደግሞ አንድ ከብት በአንድ ወይም ሁለት የማርያ ተሬዛ ገንዘብ ይሸጧቸው ነበር። አቶ ብርሃነ አብርሃ ‘የሰገነይቲው ደጃዝማች ባህታ ሃጎስ’ በሚለው መጸሃፋቸው እንዳሰፈሩት በዚህ ዝርፊያ የተነሳ አብረንታንቲ በተባለው ስፍራ ሳይታሰብ የከብት ገበያ ተቋቁሞ ነበር። ይህ በዓላ ላይ የተፈጸመው ዘረፋ እስከ አሁን ድረስ “ዘመነ ዓላ” እየተባለ ይጠቀሳል።

ከዚህ በኋላም የደጃዝማች ባህታ ጓደኞች ከብቶቻቸውን ተንቤን እንደወሰዷቸው ሲነግሯቸው፣ ደጃዝማች ባህታም ተዎቸው ይውሰዷቸው በዝተው እንጂ ጎድለው እንደሆን አይመለሱም በማለት የሚከተለው ሙሾ ደረደሩ፦
አሻህ ላሜ አንቺ አሻሕ ላሜ፣
ደህና ሁን አትይኝም ወይ አንቺ አለሜ።
ብኖርማ እኔ ባጠገብሽ፣
እኮ ማን ሊደፍርሽ ሊዳፈርሽ፣
የፈለገው ሆኖ ደሜ ቢፈስልሽ።
አንገብርም ስላልን ዘረፉሽ ወይ፣
ተንቤኖች ቀማኞች ዘረፉሽ ወይ፣
ድል እንዳደረግነው ይህን አባይ፣
አንድ ቀን አይቀርም ሳንተያይ።
ወዘተ በማለት ሙሿቸውን ደረደሩ።

ከዚህ ከዘመነ ዓላ ተለይቶ የማይታይም በአንድ ወቅት “ሽፍቶች ሰገነይቲ ውስጥ ተሰባስበው ለማጥቃት እየተዘጋጁ ናቸው” የሚል የውሸት ወሬ ስለሰማ ራስ አሉላ ሰራዊቱን በሙሉ ይዞ ወደ ሰገነይቲ አመራ። ሁሉም ህጻናትና እናቶች ሳይቀሩም ሰርክዓት ወደተባለው በመተተን ተራራ ወደ ሚገኘው ብርቱ ቦታ በማምራት ሸሹ። ይህ ቦታ በጣም የደስ ደስ ያለውና በከብቶችና በፍየሎች ጸጋ በጣም የተሞላ ብዙ አባጣና ጎርባጣ ሰርጦች የተሞሉበት ቦታ ነው።

ራስ አሉላም ፈረሰኞቹን ሁላ በማሰማራት ያገኘውን ከብትና ፍየል በሙሉ ዘረፈ። ራሱ ራስ አሉላም መተተን ወደተባለው ተራራ በመውጣት በጦር መሳርያ መነጸር እየተመለከተ የተደበቁ ፍየሎችንና ከብቶችን ሁሉ ሙልጭ አድርጎ ዘረፈ። እስከ አሁን ድረስም እሱ የወጣባት ጫፍ የራስ አሉላ ጫፍ እየተባለችም ትጠቀሳለች። ለምሳሌም ማይ ሓራሳት በተባለችው ቀየ ነዋሪ በነበሩት አቶ ሓይለአብ በተባሉ ግለሰብ ሰባት በትር ፍየሎችን ወደ ሓላይ ደርዓም አርቀው እንዲሸሹ ለማድረግ ቢሞክሩም እንኳን ተዘረፉ ወይ ተወረሱ። (በትር ማለት የ100 ከብቶች/ፍየሎች መጠሪያ የወል ስም ነው)። በዚህ ዝርፊያ ወቅት ከአንድ አቅጣጫ ብቻ የተዘረፉት ከብቶችና ፍየሎች የኋለኞቹ ማይ ሓራሳት በነበሩበት ወቅት የፊተኞቹ ደግሞ ገዛ ሓውያ ሰገነይቲ ድረስ ማለትም ግምቱ 25ኪሎሜትር የሚሆን መንገድ ይሸፍኑ ነበር።

ራስ አሉላና ደበብ ራሳቸው እንዲሁም ሰላዮችንና ልኡካንን በመላክ የደጋና የቆላውን የኤርትራ ህዝብ ያስጨንቁበት በነበረ ወቅት፣ ደጃዝማች ባህታ “እንደ አራዊት በወጥመድ፣ ልክ እንደ ከብት ደግሞ በነ አሉላ ቀንበር ከምገባ፣ አምላኬን አምኜ ለግዜው አርቄ ወደ የሃባብ ምድር ብሄድ ይሻላል” በማለት ከአራት አመት መንከራተት በኋላ፣ 150 የሚሆኑ ተከታዮቻቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ይዘው ወደ ሃባብ አመሩ። ከጥንት ከጠዋቱ የምድሪ-ባሕሪ ጀግኖች ከመረብ ወዲያ ከሚመጡባቸው አንዳንድ ወራሪ መሳፍንቶች የሚጠለሉበት የሓባብ ምድር ነበር። ደጃዝማች ባህታም በዚህ በሃባብ ምድር ለሰባት አመታት ከከንቲባ ሓምድ ጋር ተስማምተው በሓባብ ተቀመጡ። ወንድማቸው ደጃዝማች ሰንጋልም ዓይሻ የተባለች የሓባብ ተወላጅ አገቡ።

በዚህ ቦታም ቢሆን ከራስ አሉላና ከደበብ ክትትል ሊያመልጡ አልቻሉም። ለምሳሌነት የሚጠቀስም ራስ አሉላ ለስዊዘርላንዳዊው የግብጽ መንግስት ልኡክ ሙሲንጀር ፓሻ “ባህታ ሓጎስ የተባለ በግዛታችሁ ውስጥ ያለ ሰው አስረህ አስረክበን” በማለት የምስጢር መልዕክቱን ላከ። ሙሲንጀርም በበኩሉ “እኔ ራሴ እጁን አስሬ ላስረክብህ አልችልም። ነገር ግን ከቻልክ በጥበብና በመላ አድርገህ ከያዝከው እኔ ምንም አልልህም፣ እንዳላየሁ ሆኘ ነው የምሄደው” በማለት መልስ ላኩለት። ይህን መልዕክት ያስተላልፉ የነበሩት ደግሞ ባሻ ተስፋይ ደብረጽዮን የተባሉ የሰሰወ መረታ ሰበነ ተወላጅ የሆኑ አስተዋይ ሰው ነበሩ። እሳቸውም በዚያን ወቅት ላዛሪስት በተባሉት ካቶሊካዉያን ሚሲዮናውያን ጋር ሓልሓል በተባለ ቦታ ይኖሩ ስለነበሩ፣ ይህን ሚስጢር ለባህታ ሓጎስ ነገሯቸው።

ሰላዮችም ሰራዊት አስከትለው የደግለልን ከብቶች ለመዝረፍ በመጋርህ በኩል የነበሩትን የደጃዝማች ባህታ ከብቶች ዘረፉ። እሳቸው ግን ይጠራጠሩ ስለነበሩ በርቀት ይመለከቱ ነበር። ሙሲንጀርም ልክ አስቀድሞ እንደተባባለው እንዳላየ ሆኖ ከብቶቹ ሲዘረፉ ዝም አለ። ደጃዝማች ባህታም በሙሲንጀር ሁኔታ በጣም ስለተበሳጩ በእልህ ተነሳስተው ከደግለል ጋር በመተባበር እስከ የሓማሴን ወሰን ድረስ በመሄድ ከብቶቻቸውን ከዘራፊዎች አስመለሱ።

በዚህ ወቅትም እንደነ ባላምባራስ ካፍል ጎፋር፣ ደጃዝማች ሓድገምበስ ጉልወት፣ ተድላ አባ ፈርጃ የተባሉና ሌሎችም ኤርትራዉያን የምድረባሕሪ ጀግኖች ከራስ አሉላ ሸሽተው በሓባብ ምድር እንደነበሩ ይታወቅ ነበር። አንድ ቀንም በጋራ ሆነው ሲጫወቱ አንዳንዶቹ “አጼ ወይም አሉላ አሸነፈ ብለው ከሚነግሩኝ ድርቡሽ ወይም ቱርክ ወይም ግብጽ አሸነፈ ቢሉኝ እመርጣለው” ይሉ ነበር። ደጃዝማች ባህታ ግን “እኔ እንኳን እዝችው ያለሁበት ቦታ እሞታታለው እንጂ ቱርክ ወይም ግብጽ አሸነፈ ከሚሉኝ አጼ አሸነፈ ቢሉኝ ነው የምመርጥ።” አሉ። (ይቀጥላል)

Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የደጃዝማች ባህታ ሓጎስ - “አባ ጥመር” ታሪክ፣ በኤርትራዊው እይታ!

Post by Meleket » 02 Mar 2022, 08:06

ከዚህ በፊት እዚሁ መረጃ ውስጥ Open Forum ላይ ዱለነው የነበረውን የደጃዝማቹን ታሪክ፡ ተልባ ባንድ ሙቀጫ እየወቀጥን፡ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች ትኮመኩሙ ዘንድ ጋብዘናል። :mrgreen:
Meleket wrote:
08 Sep 2018, 00:57
እንደሚታወቀው ለማወራረጃነት እነዚህን ሓቆች እየተጎነጨን የደጃዝማቹን ታሪክ በስምዖን እይታ እንቀጥል፦
1) ባህታ ቆቅ ከመሆኑ የተነሳ “አሽንዃይ ንጉሥ ተምቤን ንፋስ ተምቤን አይልኸኻ” የሚል ብሂል ያዘወትር እንደነበረ፣ ትርጓሜውም “ከተንቤን የመጣ ንጉሥ ይቅርና ከተንቤን አቅጣጫ የነፈሰ ንፋስ አይንፈስብን” የሚል አባባል በማዘውተር ከመረብ ማዶ ይመጣበት የነበረን ተጽዕኖ በአባባሉ ይገልጽ እንደነበረ።
2) ባህታ ሆነ ሌሎች የምድሪ ባሕሪ አርበኞች በሓባብ ምድር መመሸግ የጥንት የጥዋቱ ስትራቴጂ እንደነበረ፣ አሁንም በዘመናችንም ኤርትራውያን ታጋዮች ይህን ሓቅ እንደደገሙ።
3) ባህታ ሆነ ሌሎች የምድሪባሕሪ አርበኞች ሲሻቸው ከጣልያን ጋር ይቀላቀሉ የነበሩት ስልታዊ በሆነ መንገድ መሳርያ ሆነ ሞራላዊ ድጋፍን ለማግኘት እንደ ነበረ። (ልኽ እንኳን ጠቅላይ አብይ ግቡ ከማለቱ በፊት እዚ ኤርትራ ውስጥ እንደነበሩት የጦቢያ ተቃዋሚዎች ማለት ነው፣ ነጭ ነጩን እናውጋ ከተባለ። አሁን የስምዖንን እይታ እንቀጥል፦

በዚህ ወቅትም እንደነ ባላምባራስ ካፍል ጎፋር፣ ደጃዝማች ሓድገምበስ ጉልወት፣ ተድላ አባ ፈርጃ የተባሉና ሌሎችም ኤርትራዉያን የምድረባሕሪ ጀግኖች ከራስ አሉላ ሸሽተው በሓባብ ምድር እንደነበሩ ይታወቅ ነበር። አንድ ቀንም በጋራ ሆነው ሲጫወቱ አንዳንዶቹ “አጼ ወይም አሉላ አሸነፈ ብለው ከሚነግሩኝ ድርቡሽ ወይም ቱርክ ወይም ግብጽ አሸነፈ ቢሉኝ እመርጣለው” ይሉ ነበር። ደጃዝማች ባህታ ግን “እኔ እንኳን እዝችው ያለሁበት ቦታ እሞታታለው እንጂ ቱርክ ወይም ግብጽ አሸነፈ ከሚሉኝ አጼ አሸነፈ ቢሉኝ ነው የምመርጥ።” አሉ።

ይህች ንግግራቸው ወደ ራስ አሉላ ስለደረሰች ራስ አሉላ ደስ ብሏቸው “የሓጎስ ልጅ ወደኔ ቢመጣ እኮ የአከለጉዛይን ምድር በሙሉ እንዲያስተዳድር በሰጠሁት” በማለት በተሰበሰቡ ሰዎች መካከል ተናገረ። አንዳንድ ሰዎችም ወደ ደጃዝማች ባህታ በማምራት ኑ እንሂድ ወደነ አሉላ እንግባ ብለው ሲለምኗቸው “ፈጽሞ አይታሰብም እነዚህ እንደሆኑ መሃላ መጣስ አመላቸው ነው፣ መሀላን ለማፍረስ ወደ ኋላ የማይሉ ትውልዶች ስለሆኑ እኔ አላምናቸውም፣ በነሱ ስር ደግሞ ፈጽሜ አልሆንም።” አሉ።

ጣልያኖች የምጽዋን ከተማ እንደተቖጣጠሩም “እራት የፈለገ እንግዳ ህጻንን ከነ ንፍጡ ይስማል” እንደሚባለው፣ ጣሊያኖች ይዘውት የመጡትን የማሪያ ተሬዛ ገንዘብ ላገኙት ሁሉ ማደል ተያያዙት። ይህን ያዩ ገራገሮችም፣ ጣሊያን እንደሆን ገንዘብ ይሰጣል እንጂ እንደሌሎች የሰውን ገንዘብ አይዘርፍም አይወርም አይቀማም፣ መንግስት ማለት ይህን ነው አሉ።ብዙዎችም ክርስትያኖችና እስላሞች ሁሉም ከየቀያቸው ይሁን ሸፍተውበት ከነበረ በረሀ እየወጡም ወደ ምጽዋ በማምራት ከጣሊያኖች ጋር ታጠቁ። በዚህ ወቅት ደግሞ መጥፎ ወረርሽኝና ህመም እንዲሁም ረሃብ ተስፋፍቶም ነበር።

ደጃዝማች ባህታም “ጣሊያን ና ወደኔ የሀገርህን ግዛት እሰጥሃለሁም እያለኝ ነዉና ምን ባደርግ ይሻላል?” በማለት ከጓደኞቻቸው ጋር ተመካከሩ። ጓደኞቻቸውም ይህን ሁሉ አመታት በበረሃ እንደ አራዊት ስንኖር ቆይተንስ አሁን ና እንሹምህ የሚል ተገኝቶስ እሽ እንበላቸው እንጂ አሏቸው። ደጃዝማች ባህታ ግን “እናንት ሰዎች እነዚህ ትግራዮችንና ፈረንጆችን አላምናቸውም። ሙሲንጀር ፓሻ እንኳን ሳይቀር አሳልፎ ለራስ አሉላ ሊሰጠኝ የነበረ፣ አሁንም ይህ ጣሊያን የሚባል አሳልፎ እንዳይሰጠንና እንዳይከዳን እጠራጠራለው። አይ የግድ መግባት አለብን ካላችሁ ግን እሽ በሉ ይሁንላችሁ” በማለት ከነተከታዮቻቸው ጋር በመስማማት ወደ ምጽዋ በመውረድ ከጣሊያኖች ጋር ተቀላቀሉ። በዚህ ተግባራቸው ደስተኛ እንዳልነበሩ የምትገልጽ ራሳቸው የደረደሯት ሙሾም እስከ ዛሬ ድረስ ትደገማለች፦

ሰንጋል ወንድሜ ሆይ ብዙም አትሞኝ፣
ገብረመድኅን ልጄ ብዙም አትሞኝ፣
ብላታም ብትሆን ብዙም አትሞኝ፣
ልቤ ተሰብሮ ነው ይህንን ስቀኝ።
አስተውል አስተውል አስተውል ልብ አርገህ፣
ነጭ እባብ እንደሆን አንዴ ከነከሰህ፣
ፈውሱ አይገኝም ፈልገህ ፈላልገህ።
እግሩ ግብጽ ላይ፣
ትራሱ አሰብ ላይ፣
አምላክ ፈልጓል ወይ ይህን ጉድ እንድናይ!
አሉ።

ምንም እንኳን በብዙ መጻሕፍቶች ላይ ይህን ሙሾ የደረደረው ሰንጋል ወንድማቸው ነው ቢባልም ፣ ብዙ ታላላቅ ሰዎች የሚስማሙበት ግን ይህ ሙሾና በርካታ ሙሾዎችን በመደርደር ልቦና የሞላው ጥበባዊ መልእኽትን በማስተላለፍ የሚታወቁት ራሳቸው ደጃዝማች ባህታ እንደሆኑ ነው።

አባ ቪካር የተባሉ አንድ ካህን “ የቁልቋል ፍሬ(በለስ) ና ጣልያን እያደር ይወርስሃል” እንዳሉት፣ ደጃዝማች ባህታም የጣሊያን ተግባር አስቀድሞ ቢታያቸውም እንኳን፣ በጓደኞቻቸው ግፊትና ጠላቶቻቸውን ለመጠራረግ ይህን ዕድል ለመጠቀም ሲሉ ወደ ደኾኖ በመሄድ ከጣሊያን ጋር ተስማሙ። ነሓሴ 3 1889 ጣሊያን አስመራ ገብቶ መላ ኤርትራን እንደተቆጣጠረም፣ ደጃዝማች ባህታን የአድግና ተገለባ ማለትም የአከለጉዛይ ምስለኔ በማለት ሾሞ በሰገነይቲ ቀያቸው እንዲቀመጡ አደረገ። ከጣሊያን ጋር በደኾኖ በተገናኙበት ወቅትም ደበብን እዛው ስላዩት በማዶ እየተያዩ ተለያዩ። የኋላ ኋላም ነገሩን ሲያሰላስሉት በህይወት ዘመኔ ከሰራሁት ሶስት ትልልቅ ስህተት መካከል “ደበብን እያየሁ የተውኩበት ቀን፣ ከዓሳሊሰን ጋር በብርኩታ (የእረኛ ምግብ) ምክንያት ደም የተፋሰስኩበት ቀን እንዲሁም ወንድሜ ካሕሱን የገደልኩበት ቀን ነው” በማለት በማንም ሰው የሌለ የግልጽነትና ስህተትን የማመን ጠባያቸውን እንደሚገልጽ ይነገርላቸዋል።

በዚያን ወቅት አጼ ዮሃንስ በድርቡሾች ተሸንፈው እንደሞቱ፣ ይህ አካባቢ በተለይም ትግራይ በረሃብ ተሰቃየ፣ ትልቅ እልቂትም አጋጠመ። ይህ ረሃብና ድርቅ በተለይ ትግራይ ውስጥ እንደነበረ የሚያስረዳም ባሻ ገብረእዝጊ ወደንገዘ የተባሉ በትውልድ የመረታ ሰበነ ተወላጅ መሆናቸውን የሚያምኑ የትግራይ ተወላጅ፣ እናቶቻቸው የሞቱባቸው 60 የሚሆኑ ህጻናትን በማሰባሰብ አሳደጓቸው። እስከ አሁን ድረስም እነዚህ ልጆች “ገብረዝጊ ይሙት” በማለት ይምላሉ። ይህ በጣም በሁሉ መአዘናት ችግርና እልቂት የበዛበት ዘመን ነበር። “ዘመን አካሂዳ” ወይም “የመካካጃ (የመካካድ) ዘመን” በመባልም ይታወቃል። ይህም የሚያስረዳን ህዝብ ምን ያህል ተጨንቆና እርስ በራሱ ተካክዶ እንደነበረ ነው። በዚህ የተነሳም አቶ ዕንዳይ የተባሉ በጽንዓደግለ የአዅሩር ተወላጅ እንዲህ ብለው ነበርም ይባላል፦

ምን ዓይነት ዘመን ነው ዘመነ ገጣጣ፣
ሁሉ ሚመጣብን እየያዘ ጣጣ፣
ምጽዋ ብንሄድ ጣልያን መጣ፣
ወደቆላ ብንወርድ ድርቡሽ መጣ፣
ቀያችንን ለቀን ታድያ የት እንውጣ፣
ማርያም ራስሽ አውጭን ከዚህ ከጋሬጣ፣
በፍቅር በሰላም በድል እንድንወጣ።


ይህን ሁኔታ ወደ ጥቅሙ ለመቀየር የፈለገው ጣሊያንም ለፖለቲካው ሲል በመርከብ እህል ጭኖ አስገባ። በዚህ ወቅትም ነበር የእርዳታ እህልን ለፖለቲካ አላማ መሳርያነት በሀገራችን ውስጥ መጠቀም የተጀመረው። የዚህን ምስጢር ጠንቅቆ ያላወቀ ዜጋም፦

ባቡር(መርከብ) መጣች ጢስ እያቦነነች፣
የእህል ክምር ይዛልን ነጎደች(ከነፈች)፣
ጎበዝ ሁሉ ሄደ እህል ሊከፋፈል፣
አሁንስ አክትሟል በእርዛት መቁሰል።

በማለት ተቀኘ።

የጣልያን መንግስት በረሃብ ተሸንፎ የነበረውን ህዝብ እህል ያድለው በነበረበት ወቅት ደጃዝማች ባህታ ሓጎስ ሰራዊታቸውን ወደ ዓድሮሶ በመላክ በኩባያ አስራት ይሰበስቡ ስለነበሩ “ዘመነ ኩባያ” እየተባለም ይታወቃል። በዚህ ወቅት ብዙ የተሰቃዩት ደግሞ ከትግራይ ይመጡ የነበሩት እርዳታ ጠባቂዎች ነበሩ። የምድሪ ባሕሪ ህዝብ ግን ያ ይፈጽሙ የነበሩትን ግፍና በደል በመርሳት ይተባበራቸው እንደነበረ ይነገራል። ከዚህ በኋላ ግን በደጃዝማች ባህታ አምስት የአስተዳደር ዘመናት ችግርና ረሃብ ተወግዶ ህዝባቸውን በሰላምና በጥጋብ እንዳስተዳደሩ ይነገራል። በዚህ ወቅትም አንድ የቶርዓ አዝማሪ በሳሆ ቋንቋ እንዲህ በማለት ሙሾ ደረደረ፦

ልቦክ ዳልተ ዳጊራቶ፣
ሕያው ናጋዶ ዛዛዕቶ፣
ክሳብ ገደም ክሳብ ሮብቶ።
ወዘተ አለ። ትርጓሜውም

አንበሳ ወለደች የደግራዋ እናት፣
በሰላም ሚገዛ ሁሉንም በሙላት።
ከገደም እስከ ሮብቶ ሃገር ሚያስተዳድር
ነጋዴ እንዲነግድ ህዝብም ሳያማርር
በሰላም የሚያኖር ያላንዳች መቃቃር
ይህን ነው መሪ ማለት ተቆርቋሪ ላገር።
እንደማለት ነው።

ይህን በደጃዝማች ባህታ ላይ የነበረውን የህዝቡን አመኔታ ጣሊያኖች እንዳዩም ደስ ስላላላቸው ተልንቲ ሳንጉነቲ የተባለ ተቆጣጣሪ ላኩባቸው። (ይቀጥላል)

Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የደጃዝማች ባህታ ሓጎስ - “አባ ጥመር” ታሪክ፣ በኤርትራዊው እይታ!

Post by Meleket » 02 Mar 2022, 09:19

የመጨረሻው ክፍል የስምዖን ትረካ እዚህ ላይ ሲቋጭ፡ ደህና አድርገን በአንድ ሙቀጫ የወቀጥነው ተልባ፡ ለጦሙ ግዜ ሊያገለግላችሁ ስለሚችል፡ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ ልናካፍላችሁ ፈቃዳችን መሆኑን በኤርትራዊ ጭዋነት እንገልጣለን። :mrgreen:
Meleket wrote:
10 Sep 2018, 00:55
ጥር 1893 ጣሊያኖች መሬትን ዶሚናለ በማለት የህዝቡን የሰባ የሰባ መሬት መውረስ ጀመሩ። በተጨማሪም ኢትዮጵያን ለመውረር ያስቡ ስለነበሩና እንዴት አድርገን ነው ኢትዮጵያን ልንቆጣጠራት የምንችለው ብለው ሰፊና ጥልቅ ጥናትም ያደርጉ ስለነበሩ፣ በርካታ ኤርትራዉያን ወጣቶችን መለመሉ። እንዲሁም በርካታ ወጣት ሴቶችንም ልክ የጭን ገረድ ሆነው ያገለግሏቸው ዘንድ መመልመል እንደሚያስፈልጋቸውም ተግባቡ። አመንዝራነትም የተዘወተረ ተግባር ስላልነበረ የተለመደ ቀላለ ነገር ነው ይባል ዘንድ ሴቶችን ራቁታቸውን አድርገው ፎቶ በማንሳት በየቦታው መለጠፍ ጀመሩ።

ከዚህ በኋላም ወንድና ሴት ወጣቶችን በኮታ አስረክቡን ወደ ጣሊያን ሃገር ወስደን ልናስተምራቸው ስለፈለግን ነው በማለት እኩይ ተንኮላቸውን በአዋጅ መልክ አስተጋቡት። ትልንቲ ሳንጎንቲም በበኩሉ ሁሉም ወረዳዎች የተባሉትን ያህል ኮታ ወጣቶችን አስረክበውናል አንተ ብቻህን ነው የቀረሀው በማለት በተለያየ መልኩ ደጃዝማች ባህታን ለማሳመን ሞከረ።

ደጃዝማች ባህታ ግን የተልንቲ ሳንጎንቲን ተንኮልና ድፍረት ሊቋቋሙት ስላልቻሉ፣ ጆሮግንዱን በጥፊ በመምታት ከነተከታዮቹ አሰሩት። ከተከታዮቹ መካከል አስተርጓሚው የነበሩትንና በጣም ይወዷቸው የነበሩትን ብላታ ገብረእግዚአብሄር ጊላይ የተባሉትን የጻዕዳ ክርስትያን ተወላጅ ግን አላሰሯቸውም ነበር።

አስመራንና ሰገነይቲን ያገናኝ የነበረውን የቴሌፎን መስመርም ነሓሴ 14 ቀን 1894 በመበጠስ አቋረጡት። ጆሮግንዱን በጥፊ መተው መሬት ላይ የዘረሩት ተልንቲ ሳንጎንቲንም ደጃዝማቹን ማሩኝ ማሩኝ ለማለት “ቫቤነ ባህታ፣ ቫቤነ ባህታ” እያለ በመማጸኑም “በቃኝ በቃኝ” እስኪል ድረስ ለተሸነፈ ሰው መገለጫነት እስከ ዛሬ ድረስም “ባቤነ ባህታ ሓጎስ ሰገነይቲ ይላል ጣልያን” እየተባለ ይነገራል።

ከዚህ ጋር ሊጠቀስ የሚገባው ደግሞ ደጃዝማች ባህታ ለሚስታቸው “ጣልያኖች እኮ ወጣቶችን ስጠን በማለት ጠየቁኝ” በማለት ውሏቸውን አጫወቷቸው። ሚስታቸውም ወጣት ታድያ ሞልቶ እያለ ምን ቸገረዎ ቢሏቸው “እሽ በይ መስጠት ከጀመርን መጀመሪያ ከሴቶች ትምኒት ልጃችንን ከወንዶች ደግሞ ገብረመድህን ልጃችንን ነው የምንሰጠው” አሏት። ሚስታቸውም እንዲያማ አይደረግም፣ እነዚህ ምን ምን የመሰሉ ልጆቸንማ ለምን ብለን ነው የምንሰጠው በማለት መለሱላቸው። ደጃዝማች ባህታም “አይ ያንች ነገር ሁሉም ደግሞ ለየ እናቶቻቸው እንደዚያ ሆነው ነው የሚታዩዋቸው ገባሽ፣ ስለሆነም ባህታ ሞተ ይባላታል እንጂ እኔ የወገኖቸን ልጆች አሳልፌ ለጣሊያን አልሰጥም።” በማለት ተናገሩ። ቀጥለውም፦

“ከአሁን በኋላ ሞትን እመርጣለው እንጂ እኔ እንደሁ የሚበላ አላጣሁ የሚጠጣ አላጣሁ - - -ለህዝብና ለወገኔ ስል ደግሞ መብታችንን ለመጣስ መሬታችንን ለመውረስ እርሻችንን ለመቀማት ጫካችንን ለመቀማት በባህር በኩል ከመጣ መንግስት ነጻ አወጣሃለው፣ በማለት በሰገነይቲ መሃል ባለው ሜዳ ጦራቸውን እየሰበቁ ፎከሩ። አጋራቸውና ጓደኛቸው የነበሩትን የአኵሩር ተወላጅ የሆኑትን ባሻ ምስጉን ሃብተማርያምንም ና ፎክር ሲሏቸው፣ ባሻ ምስጉንም “ኣየ ጓዴ መች ከመፎከር ሆነና ቁምነገሩ ከመተግበር እንጂ” በማለት መለሱላቸው” ይላል የሰገነይቲው ተወላጅ ባሻ የዕብዮ ትኩእ አተራረክ።

ደጃዝማች ባህታ ይህ ዓይነት ተንኮልና ችግር እንዳጋጠማቸውም አስቀድመው በጋብቻ ተሳስረዋቸው የነበሩትን የኤርትራ መኳንንት መልእክትና ግብዣ ላኩላቸው። ያም ሆኖ ግን ሁሉም መኳንንት ለየግል ጥቅማቸውና ለእርስ በእርስ ውድድራቸው ይራኮቱ ስለነበሩ ግብዣቸውን የተገበረ ሰው አልነበረም። ራስ መንገሻም ቢሆኑ በበኩላቸው ለይስሙላ እስከ ሰንዓፈ ደርሰው ነበርም ይባልላቸዋል።

ደጃዝማች ባህታ በጋብቻ የተሳሰሯቸው መኳንንትም ለመጥቀስ አንድ ልጃቸውን ከባላምባራስ ንጉሰ ማለትም ከማዕረባው ከንቲባ አስመሮም ወንድም ጋር ሲያጋቧት፣ ባሏ እንደሞተባትም ከዓረዛው ራስ ኪዳነማርያም ጋር አጋቧት። ልጇም ከደጃዝማች በላይ ማለትም ከደጃዝማች ንጉሰ ባረክናሃ ማለትም ከሽመዛና እንዳዳሽም ተወላጁ ጋር አጋቧት። አንዲት ልጃቸውንም ከእምባደርሆ ካርነሽም ተወላጁ ከደጃዝማች ሚኒሊክ ማለትም የደጃዝማች ስብሃቱ ልጅ ጋር አጋቧት። ሌላ አንዲት ልጃቸውንም በትግራይ ከደጃዝማች ወልዴ የሹም ሰባጋድስ ልጅ ጋር አጋቧት።

ደጃዝማች ባህታ እላይ እንደጠቀስነው አካባቢያቸው በጎበዝ አለቃ ማለትም በህዝብ ምርጫ ይተዳደር የነበረውን ስርአት በመጣስ ለመጀመሪያ ግዜ በኃይል ሊያስተዳድሩ ስለሞከሩ ይህ ያልተዋጠላቸው አንድ አንድ የቀያቸው ሰዎች እንቅልፍ ነሷቸው። በዚህ የተነሳም እነዚህን ሰዎች በመያዝ ለጣሊያን አስረከቧቸው። ጣሊያኖችም አስረው ወደ ዓሰብ በመውሰድ በዛው ደብዛቸውን አጠፏቸው። የኋላኋላ ግን ደጃዝማች ባህታ በተግባራቸው ተጸጽተውና አዝነው በትካዜ መንፈስ እንዲህ በማለት አንጎራጎሩ፦

ሰብ ዓሰመ አንቱም ሰብ ዓሰመ
አጥፋእናኩም ከብዲ ምስ ሓሰመ
ደለናኩም ጊዜ ምስ ጸገመ።
በማለት እየተከዙ ሙሾ ደረደሩ። ትርጓሜውም፦

እናንት የዓሰቦች የዓሰቦች፣
እናንት ዘመዶቸ ታሳሪዎች፣
ጨኽኜ እያለሁ ሳጠፋችሁ፣
አሁን በችግሬ ፈለግኋችሁ።
በማለት እየተቆረቆሩና በቀድሞ ድርጊታቸው እየተጸጸቱ አስታወሷቸው።

በመጨረሻም ታማኝ ተከታያቸው ሻለቃ ሰለሞን ከንቲባ ዘርኡ የሰገነይቲ ሓድጎማ ተወላጅና አቶ ባርናባስ ወልደስላሴ የሚገኙባቸው ሰዎች የባህታ ሓጎስን ቤተሰቦች በመያዝ ከሰገነይቲ በማይሰራው በኩል በጸሮና አድርገው ቤት ሰማእት ለጎሳርዳ በኩል ወደ ትግራይ ወሰዷቸው። ቤት ሰማእት አካባቢ እንደደረሱም ሻለቃ ሰለሞን ትቷቸው ሲመለስ የቀሩትን ግን ከንቲባ ሓድጉ የተባሉ የመስሓል ወደከለ ተወላጅ ማይዝጊ በተባለ ትልቅ ወንዝ ዳርቻ አስጠልለው በጣም ምስጢራዊ ወደሆነ ደጊዐን ወደ ተባለ ቦታ በመውሰድ ሸሸጓቸው። ከዚያም በመቀጠል ወደ የዳሞ መሬት በማስገባት ወደ ተምቤን በመውሰድ ሩባ ኩሳ በተባለ የራስ መንገሻ መሬት አስቀመጧቸው።

ደጃዝማች ባህታ 1600 የሚሆኑ ሰራዊታቸውን አክትተውም / አሰማርተውም ለጦርነት ተዘጋጁ። የቴሌግራም መስመርን ከቆረጡ በኋላም በሳልስቱ በማጆር ቶሰሊ የሚመራ በርካታ የጣሊያን የሰራዊት ኃይል ከአስመራ በመነሳት ማዕረባ አካባቢ ደረሰ። በሕርጊጎና በጊንዳዕ የነበረ ሌላ የሰራዊት ክፍልም በበኩሉ ወደ ሰገነይቲ አመራ።

ደጃዝማች ባህታ ሓጎስም ይመጣባችው የነበረውን የጣሊያን ሰራዊት ይመቸኛል ብለው ባሰቡት ቦታ ለመግጠም በሰገነይቲ ጥቂት ዘቦችን /ቃኝዎችን በመተው ሓላይ ወደ ተባለችው ቀየ አመሩ።
በጉብጣን ካስተለዚ የሚታዘዝና የሚመራ በሓላይ መሽጎ የነበረውን የጣሊያን ሰራዊትም ታሕሳስ 18 ከቀትሩ ሰባት ሰዓት ተኩል ላይ ጥቃት ፈጸሙበት። የደጃዝማች ባህታ ሰራዊት ከፍተኛ እልቂት በጣሊያኖች ላይ ካደረሰ በኋላም ልክ አስራ አንድ ሰዓት ላይ በውጥረት ላይ የነበረውን ሰራዊት እጁን እንዲሰጥ ዕድል ሰጡት። ልክ በዚህ ሰዓትም በሰገነይቲ ለጥቃት ትተዋቸው የነበሩት ሰዎች በመክዳት የጣሊያንን ሰራዊት በነጻ ያለ ምንም ተቃውሞ አሳለፉት። ደጃዝማች ባህታም ባልጠበቁትና ባላሰቡት ሁኔታ ከበስተጀርባቸው ጥቃት ተሰነዘረባቸው።

ጀግናው ደጃዝማች ባህታም ከብዙ ታማኝ ጓደኞቻቸው ጋር በ56 ዓመት ዕድሜያቸው በ 7 ጥይት ተመትተው ዖና ቀራና በተባለ በሓላይ መሬት በጀግንነት ተሰው
። አቶ ብርሃነ አብርሃ የሰገነይቲው ደጃዝማች ባህታ ሓጎስ በሚለው መጸሓፋቸው ላይ እንዳሰፈሩት ደግሞ ከሳቸው ጋር በጀግንነት ከተሰውት እስከ 15 የሚሆኑትን አንድ በአንድ ስማቸውን መጥቀስም ይቻላል። የተቀረው 400 የሚሆን ሰራዊታቸውም በወንድማቸው በደጃዝማች ሰንጋልና በኮዓቲት ተወላጅ በፊተውራሪ ተስፉ እየተመሩ መረብን በመሻገር ወደ እንትጮ ትግራይ አመሩ። ሌሎች ሰራዊቶቻቸውም በልጃቸው በገብረመድህን እየተመሩ በጽንዓደግለ መሬት በኩል በማምራት ወደ የሳሆዎች መሬት በመግባትና በመጠለል እነኛ ክደው ጣሊያንን በመምራት ያስጠቋቸውን የአካባቢው ተወላጆች ቀስ በቀስ ደፈጣ ውስጥ እያስገቡ ቤቶቻቸውን አቃጠሉባቸው። በዚህ ሁኔታም ከጣሊያን ጋር የነበረው ጦርነት ተደመደመ። ለጀግናው ደጃዝማች ባህታም እንደሚከተለው ሙሾ ተደረደረላቸው፦

ባህታ ባህታ የሰገነይቲ ልጅ፣
አንበሳ ይወለዳል ወይ ከሰው ልጅ፣
ጣሊያኖችን ሁሉ ያደረግክ ፍሪዳ፣
እስኪ በል ይመችህ ያ የሓላይ ሜዳ።
በማለት የወደቁበት ሓላይ በተባለች ቀየ የሚገኘው ሜዳ ይመቻቸው ዘንድ ተቀኙላቸው።

እንዲሁም በዛው ጦርነት ወቅት በጀግንነት ለወደቁት ታማኝ የደጃዝማች ባህታ ሓጎስ ጓደኛ ለነበሩት ለባሻ ምስጉንም እንዲህ ተባለላቸው፦

በሓላይ ጦርነት ምን አለ ጣልያን?
ምሽግን ሰባብሮ ወራሪን ሲበትን፣
የስያሑ ጀግና ያ ባሻ ምስጉን።
ተባለላቸው።

ጓደኞቻቸው በደጃዝማች ባህታ ላይ በነበራቸው ጽኑ እምነት የተነሳም ታማኝ ጓዳቸው የድግሳው ሰቋር ባሕሮም የደጃዝማች ባህታን አስከሬን ቀበሩት።
በሓላዩ ተወላጅ በብላታ ብርሃነ አማን ቤት ማለትም የደጃዝማች ባህታ ልጅ ከሆነው ከደጃዝማች ገብረመድህን የሚስቱ እህት ቤትም አስፈላጊው መገነዝና ሓዘን ተደረገላቸው። ብላታ ብርሃነም በጦርነቱ ወቅት ዳብር ወደ ተባለው በመረታ ወደሚገኝ ቀየ ሄደው ስለነበሩ፣ ጦርነቱ እንደተካሄደ በቅጽበት ወደ ቀያቸው ሓላይ በመምጣት የደጃዝማች ባህታን የመቃብር ቦታ በሰቋር ባሕሮ ተነገሩ። አስከሬናቸው ከወደቀበት ቦታ በይፋ እስከተነሳበትና በቀያቸው በሰገነይቲ በክብር እስከተቀበሩበት እስከ 1963 ድረስ የመሬት መከፋፈል በተደረገ ቁጥር “ይህች ቦታ አንድ ትልቅ ሰው አለባት” እያሉ የደጃዝማች ባህታን መቃብር በአደራ ይጠብቋትና ይከላከሉላትም ነበር። ከዚህ ሁሉ ዓመታት በኋላም እንደ መምህር ሃብተማርያም ሃይለማርያም ማለትም የብላታ ብርሃነ የልጅ ልጅ አገላለጽም የደጃዝማች ባህታ አስከሬን በክብር ወደ ቀያቸው ሲሄድም ከነ እራሳቸው ላይ ይታሰ ከነበረው ጨርቅ ጋር (ቀይሕ ቋረ) ቆዩዋቸው።

የጣሊያን መንግስትም ሬሳቸውንም ይሁን መቃብራቸውን ለማግኘት ያላሰለሰ ጥረት ቢያደርግም ሊያገኘው ስላልቻለ መላውን የአከለጉዛይን ህዝብ በመሰብሰብ ማን ነው ባህታን የቀበረ በማለት ጠየቀ። የድግሳው ሰቋር ባሕሮም “እኔ ነኝ” በማለት መለሱለት። “ባህታ ጌታየ ስለሆነ ቀብሬዋለው፣ እናንተም ጥሩ ነገር የምታደርጉ ከሆናችሁ ደግሞ ልክ እንደ ደጃዝማች ባህታ ሞት ካጋጠማችሁ በክብር እቀብራችኋለው” በማለት በድፍረት ተናገሩ። ጣሊያኖችም በሰቋር ባሕሮ ድፍረትና የአላማ ጽናት ተገርመው የእድሜ ልክ ደሞዝ አደረጉላቸው። ይህን አባባል የሰማ የጣሊያን የጦር ሰራዊት መሪም ለሰራዊቱ “እናንተም ልክ እንደዚህ ሰውየ ታማኞች ሁኑ” በማለት ተናገራቸው።

ደጃዝማች ባህታ የካቶሊክ እምነት በ 1852 በአካባቢያቸው መግባት ሲጀምር እምነቱን ተቀብለው ስለነበረ አባ ክፍለማርያም ወልደኢየሱስ በተባሉ ካቶሊካዊ ካህን የንስሓ ስነስርኣት ተፈጽሞላቸው ነበር። በዚህ ምክንያት አባ ክፍለማርያም ለምን ይህን አደረጉ ተብለው ናኩራ በተባለችው ደሴት ታስረው እንደነበረም ይነገራል።

(ይህ ጽሑፍ ስምዖን አማኑኤል “ኤርትራዊነት - ወራሪዎችን በጽናት የመመከት የዘመናት ገድል ውጤት” በሚል ርእስ እ.ኤ.አ 2001 ያሳተመው መጸሐፍ ውስጥ የሚገኝ ታሪክ ነው። ስምዖን ስለቲ ብዕላል ዝሰማዕኻዮ ታሪክ ምስናድኻን ምዝንታውካን ነመስግነካ።)

ይህ ምስል የኤርትራዊው ጀግና የደጃዝማች ባህታ ሓጎስ ነው።

Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የደጃዝማች ባህታ ሓጎስ - “አባ ጥመር” ታሪክ፣ በኤርትራዊው እይታ!

Post by Meleket » 02 Mar 2022, 10:54

እግረመንገዳችንን የትግራዩ (የሃውዜኑ ወይ የተንቤኑ) 'ሊቅ' የጻፉትን መጸሓፍ እናብጠልጥላ፡ እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ ባንድ ሙቀጫ የወቀጥነውን ተልባ፡ በዉሃ በጥበጥ አድርገን እየተጎነጨን። :mrgreen:
Meleket wrote:
20 Feb 2019, 05:04
“እዛ መሬተይ መሬተይ ኣሖይ መሬተይ ዋሕስ ክብረተይ” ዚብል ዜማ እናስተማቐርና!

የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ግጭት መንሥኤ እና መፍትሔ” በሚል ርእስ አንዳንድ ሓቆችን አዛብተውና መግለጥ የሚገባቸውን አንዳንድ ሐቆችን ችላ ብለው ታሪክን በተንሸዋረረ እይታቸው ለመጣፍ የቋመጡት ዶ/ር ደጃዝማች ዘውዴ ገብረ ሥላሴ፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ በሚል ጭምብል እውነቱን አዛብተው ቢጥፉም፣ እንዲሁም የዩኒቨርስቲውን ፕሬስ ሓቀኝነት ጥያቄ ውስጥ ቢያስገቡም፣ እኛ ኤርትራውያን ግን “ዶ/ሩ” በዚህ መጸሓፋችው (ገጽ 197-198) የጣፉትን የተዛባ ታሪክ እንዲህ አድርገን እናብጠለጥለዋለን።

ደጃዝማች ባሕታ ሓጐስ፦ በዶክተሩ ሸውራራ እይታ

የአከለ ጉዛይ ተወላጅ።

የዐፄ ዮሐንስ ዘመን መንግሥት ራስ አርአያ ድምፁ አከለ ጉዛይን ሲያስተዳድሩ ግብር አንከፍልም በማለት በተነሣ አንባጓሮ የራስ አርአያ ድምፁን ልጅ ፊተውራሪ አምባዬን ገድለው በሐባብ በረሃ በሽፍትነት ይኖሩ ነበር። (የራስ አርአያ ድምጡን ልጅና የጭፍሮቹን እኩይ ተግባሮች ግን ችላ ብለውታል’ሳ ጃል) በግብፆችና በኢጣልያ እየተረዱ በተለያየ ጊዜ ያስቸግሩ ነበር። (ማንን ነው ያስቸገሩት፣ አልገዛም እምቢ ለመሬቴና ለርስቴ ማለት ማስቸገር ነው እንዴ!) ከዐፄ ዮሐንስ ህልፈት በኋላ ኢጣልያ ከዐፄ ምኒልክ ጋር በውጫሌ ስምምነት በአንቀጽ ሦስት ላይ በተመለከተው መሠረት ከተሰጣት ወሰን አልፋ ስትይዝ ሰገነይቲ ድረስ የኢጣልያ ግዛት እንዲሆን ስለረዱ የደጃዝማችነት ማዕረግ ሰጥተው በክብር ይዘዋቸው ነበር። ቲኔንቲ (የመቶ አለቃ) ሴንጉኔቲ የተባሉ የኢጣልያ ተወላጅ ከርሳቸው በላይ ምስለኔ ሆነው በመሾማቸው ግን ቅሬታ ተሰማቸው። በአጠቃላይም በአገር ተወላጆች ላይ የኢጣልያ ሹማምንት የነበራቸው ንቀት በመመልከታቸው ልባቸው ከዳ። (ሴት ኮረዳ ልጆቻችንን ለጣልያን አልሰጥም ብለው፣ አሻፈረኝ በማለት ለሕዝባቸው ክብር ያላቸውን ቁርጠኝነትና የማያወላዳ አቋም ምነውሳ አልገለጡትም። ባሕታ ለነጭ ሆነ ለጥቁር እብሪተኛ አልገዛም ያለ ጀግና መሆኑን ማጤን አልቻሉም ማለት ነው ዶክተሩ!)።

ወንድማቸው ደጃዝማች ሰንጋል በግጥም እንዲህ ብለው እንደመከሩ ይነገራል፦ (በገጣሚነት የሚታወቁት ባሕታ እንጂ ወንድማቸው ሰንጋል አይደለም። ይህን ግጥምም የገጠሙት ባህታ እንጂ ሰንጋል አይደለም። ምክሩም ባህታ ለሰንጋል እንጂ ሰንጋል ለባህታ ኣይደለም። ከባለቤቱ ያወቀ ሆነ’ኮ ጉዳዩ። ታሪክን መሸራረፍ ማለት እንዲህ ነው፣ እቶም ደቂ መሬት ግን እናነቐስና ነቲ ሕንዚ ከነውጽኦ ኢና።)

ባሕታ ሀወይ እምብዛ ኣይትአሹ
ጻእዳ ተመን እንድሕር ነኺሱ
ደላሊኻ ኣይግነን ፈውሱ !!!!! (አቤት ባሕታስ ‘አይግነን’ አሉ! የማይመስልና ባሕታ በሚኖርበት ህብረተሰብ የሌለ ቅላጼ!)

ትርጉሙ፦
ባሕታ ወንድሜ አትሁን ተላላ
ነጭ እባብ አንዴ ከነደፈ
ተፈልጎም አይገኝ ፈውሱ

ደጃዝማች ባሕታ ከራስ መንገሻ ዮሐንስ ጋር በርሳቸውም አማካይነት ከዐፄ ምኒልክ ጋር ተላልከው ከአድዋ ጦርነት አንድ ዓመት በፊት ለመሸፈት ወሰኑ። (ራስ መንገሻ ግን ውስጥ ለውስጥ ከጣልያን ጋር ይጣጣፍ እንደነበረ አልነገሩንም’ሳ ዶክተሩ) የኢጣልያ ባለሥልጣኖች የባሕታን ታማኝነት መጠራጠር ሲጀምሩ ሊያሥሯቸው አቀዱ። ይህን ወሬ ደጃዝማች ባሕታ እንደሰሙ ቲኔንቲ ሳንጉኔቲን ከሁለት ሌሎች የኢጣልያ ተወላጆች ጋር ታኅሣስ 6 ቀን 1887 ዓ.ም. ይዘው አሠሩ።

ባሕታ ባሕታ ሰገነይቲ
በሐንቲ ጠመንጃ ቐታል ምእቲ

ትርጉሙ
የሰገነይቲው ባሕታ ባሕታ
በአንድ ጠመንጃ መቶ እሚመታ

ተብሎም ተገጥሞላቸዋል። ጣሊያኑን ጥለው ከደረቱ ላይ በእግራቸው ሲረግጡት፤ “ኢጣልያ ኃይል ናት” ብሎ ሲጮህ “ኢትዮጵያም ከኢጣልያ የበለጠች ኃያል ናት” ብለው ገድለውታል። (ይችን ቅመም እንዴት አድርገው ነው የጨመሯት’ሳ ዶክተሩ) ከዚያም ሐላይ ላይ መሽጎ ከነበረው 259 የኢጣልያ ጦር ጋር 1600 ሰው ያህል አሰባስበው ተዋጉ። ድል ለማድረግ ጥቂት ሲቀራቸው በማጆር ቶዜሊ የሚመራ ጦር ከማዕረባ ገስግሶ መጥቶ ከኋሊት ተኩስ በመክፈት የደጃዝማች ባሕታን ጦር ደመሰሰ እርሳቸውም በጦር ሜዳ ላይ ተገደሉ። (ይህ ሲደረግ ግን መንገሻ ተኝቶ ያንኮራፋ ነበር ወይስ ለድጋፍ ደረሰላቸው? ዶክተሩ ጤናም የለው እንዴ ወዲ ማይ ጠላሚት ኢዩ ግዲ፣ ባህታ “ኢትዮጵያም ከኢጣልያ የበለጠች ኃያል ናት” አሉ እንዳላለን፣ ጦራቸው ተደመሰሰ ይለናል፣ ተሸነፈና ተደመሰሰ እኮ ይለያያል፣ አፈገፈገ ወይ ብርቱ ጉዳት ደርሶበት ተበታተነ ወዘተም እኮ ይባላል፣ አይ ኣገላለጽ! “ኢትዮጵያም ከኢጣልያ የበለጠች ኃያል ናት” አሉ የተባሉት ባህታ “በጦር ሜዳ ላይ ተገደሉ” ይባላል “ተሰው” ያልተባለው ለምንድን ነው።)

ሽሕ እንተኾነ ህያዋይ አይትእመን ትግራዋይ!” የተባለው ለካ ለዚህ ነው! ታሪክን አዛብቶና አወላግዶ ማቅረብ ሊሞከር ይችላል፣ ደቂ መሬት ግን እየነቀስን እናወጣዋለን። ባህታ ለነጭም ለጥቁርም አልገዛም ያለ ጀግና ነው፣ ከዓድዋ ጦርነት በፊትም ብቻውን ፋሽስቶችን ከነ ሙሉ ትጥቃቸውና ስንቃቸው የተጋፈጠና የተዋጋ ለርስቱና ለህዝቡ ክብር የተሰዋ፣ የወንድ ቁና ነው። አከተመ ቢለናል።

Axumezana
Senior Member
Posts: 13214
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: የደጃዝማች ባህታ ሓጎስ - “አባ ጥመር” ታሪክ፣ በኤርትራዊው እይታ!

Post by Axumezana » 02 Mar 2022, 13:32

ባህታ፥ሀጎስ፤ ሲወለድ፥ትግረዋይ፤ሲሞትም፥ትግረዋይ፤ እንተስ?
Last edited by Axumezana on 02 Mar 2022, 20:01, edited 1 time in total.

Axumezana
Senior Member
Posts: 13214
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: የደጃዝማች ባህታ ሓጎስ - “አባ ጥመር” ታሪክ፣ በኤርትራዊው እይታ!

Post by Axumezana » 02 Mar 2022, 14:42

ባህታ፥ሀጎስ፤ ሲወለድ፥ትግረዋይ፤ሲሞትም፥ትግረዋይ፤

Assegid S.
Member
Posts: 936
Joined: 11 Aug 2013, 07:11
Contact:

Re: የደጃዝማች ባህታ ሓጎስ - “አባ ጥመር” ታሪክ፣ በኤርትራዊው እይታ!

Post by Assegid S. » 02 Mar 2022, 15:18

ወንድም Meleket ... ጊዜህን መስዋዕት አድርገህ አብዛኞቻችን ያልሰማነውንና ያላነበብነውን ታሪክ ስላካፈልከን ትልቅ ምስጋና እና አክብሮት አለኝ። ፅሑፉን በማነብበት ወቅትም ኣንዳንድ የትግርኛና የሳሆ ቃላቶች ሲያጋጥሙኝ "ታሪኩን ልስተው ነው" የሚል ስጋቴም ወዲያው በምታስከትለው የኣማርኛ ትርጉም ስለተቀረፈ ለዚህም ትልቅ ምስጋና ላቀርብ እወዳለሁ። ከማይረባ እንቶ ፈንቶ እንዲህ ያለ ታሪክ አንብቦ መግባባትም ሆነ መከራከር በረከት ነው። አእምሮን ያጠነክራል። ታሪክ በተልባ ሲወራረድ እንደሚመች ዛሬ አውቄያለሁ። የዩኒቨርሲቲ ጓደኞቼንም በማስታወስ … ጥናት በጫት ምንኛ ባከነ ብያለሁ። By the way ... ጥሩ ወቃጭ ነህ 8)

Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የደጃዝማች ባህታ ሓጎስ - “አባ ጥመር” ታሪክ፣ በኤርትራዊው እይታ!

Post by Meleket » 03 Mar 2022, 10:10

ወንድማችን Assegid S. እኛም በታላቅ ኣክብሮት ኣመሰግነናል። እውነት ነው፡ መረጃን በተቻለን መጠን ይህን መሰሉን ያልተነገሩ ታሪኮችን በመጋራት ወደ የመማማርያ የመወያያና በሰለጠነ መንገድ የመከራከርያ መድረክነት በማሳረግ፡ አእምሯችንን ማጠንከር የሁላችንም ብርቱ ጥረት ይጠይቃል። ታሪክን በተልባ ማወራረድ ጣዕሙን ስለምናውቀው ነው፡ ለወንድሞቻችንና እህቶቻችን የጋበዝነው፡ እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፣ ሁነኞቹ ተልባ ወቃጮች

አንድ ወንድማችን ባንድ ወቅት በዩኒቨርሲቲ ቆይታው “ለጥናት ጫት ቃም” ሲባል፡ “እኔ ፍየል አይደለሁም ያልበሰለ ቅጠል የምበላ!” በማለት “በሶና ተልባ በጥብጦ በመጠጣት” ጥናቱን በወጉ እንዳካሄደ አጫውቶን ነበር። እርሱ ነው “ታሪክ በተልባ” ማወራረድ ግሩም መሆኑን ያስተማረን፤ ባለበት አክብሮታችንና ሰላምታችን ይድረሰው።
:mrgreen:

Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የደጃዝማች ባህታ ሓጎስ - “አባ ጥመር” ታሪክ፣ በኤርትራዊው እይታ!

Post by Meleket » 03 Mar 2022, 11:24

ወዳጃችን Axumezana ተሳስተሃል።

ባህታ ሓጐስ ሲወለድ የምድሪባሕሪ (የኤርትራ) ሰው፡ ሲሰዋም ኤርትራዊ ነው።

አንተስ? ላልከው . . .

እኔማ “ስወለድ እኔ፡ ስኖር እኛ፡ ሳልፍ ደግሞ እኔ” ብየ ላስቅህ ኣይደል . . . ትላንትም ዛሬም ነገም ከነገ ወዲያም ኤርትራዊ!
:mrgreen:
Axumezana wrote:
02 Mar 2022, 13:32
ባህታ፥ሀጎስ፤ ሲወለድ፥ትግረዋይ፤ሲሞትም፥ትግረዋይ፤ እንተስ?

Axumezana
Senior Member
Posts: 13214
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: የደጃዝማች ባህታ ሓጎስ - “አባ ጥመር” ታሪክ፣ በኤርትራዊው እይታ!

Post by Axumezana » 03 Mar 2022, 12:10

Hagos Bahta was born as Tigrayan and died as a proud Tigrayan. Could you produce any Pre-Italy map that demarcates Axumite with Midri Bahri or Tigray with Midri Bahri that proves your claim?
By the way the name Eritrea is a fake name that was given by Italy and better to find an indigenous brand name

Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የደጃዝማች ባህታ ሓጎስ - “አባ ጥመር” ታሪክ፣ በኤርትራዊው እይታ!

Post by Meleket » 04 Mar 2022, 10:59

ወዳጃችን Axumezana በቅርቡ ስለአኽሱም በከፈትከው አርእስት ውስጥ፡ “ ኣዅሱም ምቕማጡ ሕሱም’ ለምን ተባለ? በማን ተባለ? መቼ ተባለ?” ብለን በኤርትራዊ ጭዋነት ለጠየቅንህ ጥያቄ፡ በቅንነት መልስ ስላልሰጠሀን፡ የዚህን ጥያቄህን መልስ በቅንነት ለመመለስ እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች አንገደድም! :mrgreen:
Axumezana wrote:
03 Mar 2022, 12:10
.. .. .. Could you produce any Pre-Italy map that demarcates Axumite with Midri Bahri or Tigray with Midri Bahri that proves your claim? .. .. ..

Axumezana
Senior Member
Posts: 13214
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: የደጃዝማች ባህታ ሓጎስ - “አባ ጥመር” ታሪክ፣ በኤርትራዊው እይታ!

Post by Axumezana » 04 Mar 2022, 12:21

I told you to go to Axum during ህዳር ጽዮን and get the answer for yourself. With regard to producing the pre-Italy map I know you will not be able to produce it! I hope we will work together toward the reconcilation of our people on the post Isaias Eritrea .

Fiyameta
Senior Member
Posts: 12331
Joined: 02 Aug 2018, 22:59

Re: የደጃዝማች ባህታ ሓጎስ - “አባ ጥመር” ታሪክ፣ በኤርትራዊው እይታ!

Post by Fiyameta » 04 Mar 2022, 12:41

Tigray Oligarch Meleket,

It must be very traumatizing for you to see all your efforts of the last 30 years gone to waste, especially after having spent decades learning Eritrean history, albeit for all the wrong reasons. There's this thing about you agame that can only be summed up with the word "FRAUD," which never fails to amaze me how a single unforced error can remove the veil of ignorance you're donning to hide your agame identity. Even Stevie Wonder can see that you are an evil, conniving, ruthless, immoral, and bloodthirsty agame! Please save your drama for your agame mama! We all know you're an evil agame! :lol: :lol:



Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የደጃዝማች ባህታ ሓጎስ - “አባ ጥመር” ታሪክ፣ በኤርትራዊው እይታ!

Post by Meleket » 05 Mar 2022, 03:38

@Axumezana - ክልቲኡ ሕዝብታት ናብ “ዕርቀሰላም” ዜምርሕ ጸገም የብሎምን። ጸገም ዛሎ ኣብ ክልቲኡ ሕዝብታት ዛለዉ ሰ.ፍ.ረ (ሰብ ፍሉዪ ረብሓታት) ኢዮም፤ ጸገም ዘሎ ኣባኻን ኣብ ደቂ Hawzenን ኢዩ። :mrgreen:

@Fiyameta - ከም Hawzen ዋጽዕ ኤርትራዊ ሽም ኣይመረጽኪን እምበር፡ ኣጆኺ ናትና! :mrgreen: እዚ ብ‘ንጹሕ-ኅልና’ ትገብርዮ ጻዕርኺ፡ ኣብ ታሪኽ ኤርትራና ዓቢ ምዕራፍ ሒዙ ንወሉድ ወለዶ ኪዝንተወልኪ ኢዩ። ‘ሕድሪ ሰማእታት’ ተኽብሪ ዋዕሮ፡ ከምዡይ ኪበሃል ኣበዪ ነቢርኺ ኣይንብለኪን ኢና፣ ኤርትራዉያን ደያኑ ማእከልን መስመርን
:mrgreen:
Meleket wrote:
29 Apr 2019, 05:13
Abe Abraham wrote:
27 Apr 2019, 17:12
... ብደም ተዋህዶ ነጻ ዝወጽአት ሃገር ...
ኣንታ መን ክሓፍረልኻ ኢዩ! ወይ ነገር “ዲጅታል ወያነ” ብጨናኻ ትፍለጥ! ደቂ ኤለትረያ ደኣ በዅርን ሕሳስ ልደን ኣስላማይን ክስታናይን፣ ተውሓዶኡ ኮተሊኹ ኬንሽኡ እንደኣሉ “ሃገር ቢሉ” ብሓድነት መኪቱን ተዓዊቱን ንጸላእቲ ሃገረ ኤለትረያ ዘሕፍሮምን “ሕዚ’ዶ ሓይሽ ዉይዉይ” ዝብሎም ዘሎ!!! ወላሒ!!! :lol:

እንታይ’ሞ ኣጣቈስቲ መኣስ ልርደኣዅም ዀይኑ

“ከምዡይ ገቢሩሎም ወ ጎሚዳ ኣባ ብልሓቱ - - - ” ትብል ደርፊ ጋቢዘካ ኣሎኹ!
:mrgreen:
"ክቡር የኽብረኻ መጠን ነፍሱ፡" እናበልና፡ ዋዕሮና ነዛ ዜማ ኣያና ኣስተማቕርያ ኣይተስተዋህድያ!

እዙይ "የደጃዝማች ባህታ ሓጎስ - “አባ ጥመር” ታሪክ፣ በኤርትራዊው እይታ!" ዚብል ኣርእስቲ ዝሃብናዮ ጽሑፍ፡ ብቋንቋ ኣምሓርኛ ንኢትዮጵያዉያን ኣሕዋትና ዝዓለመ፣ ንጀጋኑ ኤርትራ ንዓለም ኣብ ምልላይ ንገብሮ ጻዕሪ ሓደ ኣካል ኢዩ። ምስ "ሕልሚ ዓባይ ትግራይ" ዘራኽቦ ወላ ሓንቲ ነገርከምዘየሎ ኣንባቢ ዝርድኦ ጉዳይ ኢዩ። ክንዲ ዝዀነ ድማ ሓፍትና Fiyameta ዘይኾነ ነገር ኣእቲኺ፡ ክትብልልዮ ምፍታንኺ፡ 'ንፈራዲ ይጭነቖ' ዘብል ኢዩ፤ 'ደለ'ኹን' ይብሉ ለባማትና፡ ንእንታይነትኺ ዜብርህ ምርጫኺ ምዃኑ ግን ኤርትራዉያን ደያኑ ማእከልን መስመርን ኣጸቢቕና ንፈልጥ

ታሪኽ ደግያት ባህታ ሓጐስ ኣባ ጥመር ንኢትዮጵያዉያን ኣሕዋትና ካብ ኣላለና፡ ዕላማ ጽሑፍና ሕርሕራይ ጌሩ ሸቱኡ ወቒዑ ኢዩ። ቀዳሞት ከየመጐስካ ዳሕሮት ምምጓስ ኣይሕርያናን ኢዩ። ንኤርትራ ብመስዋእቶም መሰረት ካብ ዘንጸፉ ጀጋኑ ታሪኾም ንዓለም እንተተላለዬ ቂር ዚብሎ ኣካል "ሱሳ አላታ" ቢልና እናገደፍና፡ ኣብ ካልእ ኣርእስቲ የራኽበና ቢልና ብኤርትራዊ ጭዉነት ንሰናበተኹም።

ትሕዝቶ ኣርእስቲ ክጽይቕ ክቕጽል ዚብል እንተሎ ድማ ኅርይኡ ኢዩ'ሞ . . . ኪቕጽል ይኽእል እናበልና፡ ወደሓንኹም ኣሕዋት ደቂ ቀርኒ ኣፍሪቓ ንብለኹም ኤርትራዉያን ደያኑ ማእከልን መስመርን!!!! :mrgreen:

ዘለዓለማዊ ዝኽሪ ንሰማእታት ኤርትራና!


ዓወት ንሓፋሽ!!!!
:mrgreen:

Axumezana
Senior Member
Posts: 13214
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: የደጃዝማች ባህታ ሓጎስ - “አባ ጥመር” ታሪክ፣ በኤርትራዊው እይታ!

Post by Axumezana » 02 May 2022, 01:02

I am still waiting for response on the below request science begining of March!


Could you produce any Pre-Italy map that demarcates Axumite with Midri Bahri or Tigray with Midri Bahri that proves your claim? .. .. .

Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የደጃዝማች ባህታ ሓጎስ - “አባ ጥመር” ታሪክ፣ በኤርትራዊው እይታ!

Post by Meleket » 03 May 2022, 02:49

Meleket wrote:
04 Mar 2022, 10:59
ወዳጃችን Axumezana በቅርቡ ስለአኽሱም በከፈትከው አርእስት ውስጥ፡ “ ኣዅሱም ምቕማጡ ሕሱም’ ለምን ተባለ? በማን ተባለ? መቼ ተባለ?” ብለን በኤርትራዊ ጭዋነት ለጠየቅንህ ጥያቄ፡ በቅንነት መልስ ስላልሰጠሀን፡ የዚህን ጥያቄህን መልስ በቅንነት ለመመለስ እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች አንገደድም! :mrgreen:
Axumezana wrote:
03 Mar 2022, 12:10
.. .. .. Could you produce any Pre-Italy map that demarcates Axumite with Midri Bahri or Tigray with Midri Bahri that proves your claim? .. .. ..

Axumezana
Senior Member
Posts: 13214
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: የደጃዝማች ባህታ ሓጎስ - “አባ ጥመር” ታሪክ፣ በኤርትራዊው እይታ!

Post by Axumezana » 03 May 2022, 03:45

Did you see the 1849 map? It was for that reason I told you ደቻዝማች፥ ባህታ፥ሐጎስ፥ ሲወለዱ፥ትግረዋይ፤ሲሞቱም፥ትግረዋይ፤ እንተስ? ብዬ፥ ዬጠየቅኩህ። ስለአክሱም፥ ሕዝብ፥ እንግዳ፥ ተቀባይነት፥ ማወቅ፥ ከፈለክ፥ ደግሞ፥ ህዳር፥ ፅዮን፥ ሂደህ፥ ማዬት፥ነው።

Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የደጃዝማች ባህታ ሓጎስ - “አባ ጥመር” ታሪክ፣ በኤርትራዊው እይታ!

Post by Meleket » 03 May 2022, 05:23

Axumezana wrote:
03 May 2022, 03:45
Did you see the 1849 map? . . .
ወዳጃችን 'ካርታ ብርቅህ ነው መሰል" አንተ ስለ የ1849A.D. ካርታ ታወራለህ፡ እኛ ደግሞ ለኤርትራዊ ካልሆነ በስተቀር ለማንም ኣካል የማናሳየውን ቅድመ 1849 B.C. የተሰራ ካርታችንን አዱሊስ ከስከሰ መጠራ እንዲሁም ጥንታዊቷ አሥመራ ላይ ማለትም በማይ-ተመናይና ዳዕሮ ጳውሎስ በዓዲባሮና በወዘተ ከነኮፒዉ አስቀምጠነዋል፤ ቅድመ ኣኵሱም ማለት መቼም ይገባሀል አይደል? ይህ ከነኮፒው የተቀመጠው ጥንታዊው ካርታችን በኤርትራዉያን አእምሮ ውስጥም እንዳለ ስንገልጽልህ በኤርትራዊ ጭዋነትና ኩራት ትህትናም ጭምር ነው። :mrgreen:

አንተ ግን ኣሁንም በቅንነትና በግልጽ ለዚህ ገናና ብሂል መልስ አልሰጠህንም፡ ታዝበንሃል እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች።
:mrgreen:
Meleket wrote:
03 May 2022, 02:49
Meleket wrote:
04 Mar 2022, 10:59
ወዳጃችን Axumezana በቅርቡ ስለአኽሱም በከፈትከው አርእስት ውስጥ፡ “ ኣዅሱም ምቕማጡ ሕሱም’ ለምን ተባለ? በማን ተባለ? መቼ ተባለ?” ብለን በኤርትራዊ ጭዋነት ለጠየቅንህ ጥያቄ፡ በቅንነት መልስ ስላልሰጠሀን፡ የዚህን ጥያቄህን መልስ በቅንነት ለመመለስ እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች አንገደድም! :mrgreen:
Axumezana wrote:
03 Mar 2022, 12:10
.. .. .. Could you produce any Pre-Italy map that demarcates Axumite with Midri Bahri or Tigray with Midri Bahri that proves your claim? .. .. ..

Axumezana
Senior Member
Posts: 13214
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: የደጃዝማች ባህታ ሓጎስ - “አባ ጥመር” ታሪክ፣ በኤርትራዊው እይታ!

Post by Axumezana » 03 May 2022, 08:32

አውቆ፥ የተኛን፥ ቢቀሰቅሱት፥ አይሰማም፥ ይመስላል፥ነገሩ፤ Ascari syndrome የምትለውን፥ የምርምር፥ ዉጤት፥ ማንበቡ፥ይጠቅማል።

Post Reply