Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 11135
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

አንድ የዐድዋ ተወላጅ የሰጠኝ መልስ <በመጀመሪያ የዐድዋ ሰው ከጎንደር የመጣ ነው> አለኝ- ለእኔ ገረመኝ። ጥያቄየ < የዐድዋ ሰው አማርኛ የተሳካ ብቻ ሳይሆን አማርኛቸው ውስጠ ወይራ አለው>

Post by Abere » 25 Feb 2022, 14:57

አንድ የዐድዋ ተወላጅ የሰጠኝ መልስ < በመጀመሪያ የዐድዋ ሰው ከጎንደር የመጣ ነው> አለኝ። ለእኔ ገረመኝ። የጥያቄየ መነሻ ይህ ነበር። የዐድዋ ሰው አማርኛ የተሳካ ብቻ ሳይሆን አማርኛቸው ላይ ውስጠ ወይራ ያጋጥመኛል ብየ በመጠየቄ ነው።የሰውየን አገላለጽ ሙሉ በሙሉ ባላምነውም ምናልባት በአክሱም ዘመን አማራዎች ቤተ መንግስታቸውን ወደ ደቡብ ሲያዛውሩ ተቆርጠው የቀሩ ቅሪተ አማራዎች ሊሆኑ ይችላሉ ብየ ገመትኩ። ምክንያቱም ማንም ከጎንደር ወደ ትግራይ ፈልሶ የሚሄድ ይኖራል የሚል ግምት የለም። በድሮ ጊዜ ፍልሰት የተፈጥሮ ጸጋ እና ምግብ ወደ ሚገኝበት አካባቢ እንጅ እጥረት ወዳለበት አይሆንም። ብዙዎች አገጥሟችሁ ከሆነ የዐድዋ ሰዎች አማርኛ ሰዋሰው እና ዘይቤ የቤተ-አማራዎች ይመስላል።የመለስ ዜናዊ አማርኛ ለአብነት መውሰድ ይቻላል። ስራው ትግሬ ምላሱ አማራ የነበረ ነው።