Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30928
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ጠቅላይ ሚኒስትር ሳይሆን ቀዳማዊ ሚኒስትር ወይም ርዕሰ ሚኒስትር ነው መባል ያለበት!

Post by Horus » 24 Feb 2022, 15:52

ይህን ፍጹም የተሳሳተ ቃል ማለትም ጠቅላይ ሚኒስትር ማን እንደ ፈጠረው አይታወቅ። ፕራይም የሚለው አፍሮ ኤሲያዊና ላቲን ቃል ቀዳሚ፣ አንደኛ፣ሁሉም ቀድሞ ያለ በደረጃው ማለት እንጂ ፕሪይም ማለት በፍጹም ጠቅላላ ማለት አይደለም ። ጠቅላላ ጄኔራል ማለት ነው ። ፕራይም ቀዳማዊ ማለት ነው። እንዲያውም ጠቅላይ ሚኒስት ማለት ሁሉንም ሚኒስትሮች የጠቀለለ ማለት ነው። ስለዚህ ወደ ፊት ሕገ መንግስቱ ሲሻሻል ይህን የቃል ግድፈ ታርሞ ቀዳምዊ ሚንስትር መባል ነው ያለበት እንጂ ጠቅላይ ሚኒስትር ትርጉም አልባ ነው ። የተፈለገው የሚኒስሮች ሁሉ አዣዥ ለማለት ከሆነ ጠቅላይ የሚለው አይገልጸውም እንዲያውም ቀዳማዊ የሚለው ነው አዛዥ ለሚለው ትርጉም የሚጠጋ።

ሌላው ቀርቶ ፕሬዚደንት የሚለው ቃልም ከሁሉም ቀድሞ ከፊት የተቀመጠ፣ ርዕስ፣ ራስ ማለት ነው ። ፕራይም ሚኒስትም ፕሬዚደንት ያላቸው ትርጉም ቀዳሚ፣ ቀዳማዊ፣ ርዕስ፣ ርዕሰ መንግስት ማለት ነው ። ጠቅላላ ሆነ ጠቅላይ ፍጹም የተሳሳቱ ጽንሶች ናቸው !

ሆረስ ነኝ
Last edited by Horus on 24 Feb 2022, 16:23, edited 1 time in total.

Sam Ebalalehu
Member
Posts: 3639
Joined: 23 Jun 2018, 21:29

Re: ጠቅላይ ሚኒስትር ሳይሆን ቀዳማዊ ሚኒስትር ነው መባል ያለበት!

Post by Sam Ebalalehu » 24 Feb 2022, 16:05

I agree with you “ teklay” is not the correct choice of word. As for its replacement, I am open to suggestions.

Abere
Senior Member
Posts: 11135
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: ጠቅላይ ሚኒስትር ሳይሆን ቀዳማዊ ሚኒስትር ወይም ርዕሰ ሚኒስትር ነው መባል ያለበት!

Post by Abere » 24 Feb 2022, 16:20

ችግሩ ስያሜው አይደለም። ቦታውን የሚይዘው ሰው ዐቅም አለወይ ነው? ሁሉ በሬ ይባላል ግን እርሻ ፈር ላይ የሚወድቅ በሬም በሬ ይባላል እኮ። የኢትዮጵያ ጉዳይ እስከ አሁን ከዚህ ግባ የሚባል ቀዳሚ ሚንስትር የላትም። ለነገሩ ይህ ጠቅላይ ሚንስትር የሚባል ነገር የፈጠረው መለስ ዜናዊ ስልጣን በመኖፓል ለመያዝ ነው - ምንም ዲሞክራሲያዊ አካሄድም መልክም የለውም። ፕሬዚዳንት ይሻላል። ሁሉም ዜጋ የሚሆነውን ለይቶ የመምረጥ እድል ይሰጣል። ጠቅላይ ሚንስትር የሚለው መጥፋት አለበት በፕሬዚዳንት መተካት አለበት። ለበሻሻ ወይም ለአድዋ ወይም ለወላይታ ሶዶን መንደር ተመርጦ ምን በፈረደበት ነው ባልመረጠው ሰው ሌላው ኢትዮጵያዊ በማፊያ የሚመራው- ተገዶ ያለፈቃዱ።

Horus
Senior Member+
Posts: 30928
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ጠቅላይ ሚኒስትር ሳይሆን ቀዳማዊ ሚኒስትር ነው መባል ያለበት!

Post by Horus » 24 Feb 2022, 16:20

Sam Ebalalehu wrote:
24 Feb 2022, 16:05
I agree with you “ teklay” is not the correct choice of word. As for its replacement, I am open to suggestions.
ትክክለኛ ቃሉ 'ርዕሰ ሚኒስትር' ነው

Sam Ebalalehu
Member
Posts: 3639
Joined: 23 Jun 2018, 21:29

Re: ጠቅላይ ሚኒስትር ሳይሆን ቀዳማዊ ሚኒስትር ወይም ርዕሰ ሚኒስትር ነው መባል ያለበት!

Post by Sam Ebalalehu » 24 Feb 2022, 16:34

I know “ reesa memeher” is a director of a school. It vibes with prime minister. Unless someone comes up with a better alternative, Horus, you have a leg up on the name change which should happen.

Abere
Senior Member
Posts: 11135
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: ጠቅላይ ሚኒስትር ሳይሆን ቀዳማዊ ሚኒስትር ወይም ርዕሰ ሚኒስትር ነው መባል ያለበት!

Post by Abere » 24 Feb 2022, 17:00

እረ ጎበዝ ሃሳቡ ቃጤ አንሁን። ኮከብ በመቁጠር ስማ ማውጣት ጥሩ መሪ ያመጣል ብለን እያሰብን ነው ወይስ ሰዎቹን መቀየር ሲያቅተን ስማቸውን ሆነ?

Horus
Senior Member+
Posts: 30928
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ጠቅላይ ሚኒስትር ሳይሆን ቀዳማዊ ሚኒስትር ወይም ርዕሰ ሚኒስትር ነው መባል ያለበት!

Post by Horus » 24 Feb 2022, 17:05

Abere wrote:
24 Feb 2022, 17:00
እረ ጎበዝ ሃሳቡ ቃጤ አንሁን። ኮከብ በመቁጠር ስማ ማውጣት ጥሩ መሪ ያመጣል ብለን እያሰብን ነው ወይስ ሰዎቹን መቀየር ሲያቅተን ስማቸውን ሆነ?
አበረ
ምስማርና ዶማ ብቻ ባሉበት ዩኒቨርስ የሁሉ ነገር መፍትሄ መዶሻ ይሆናል ይባላል! በፖለቲካ ተቃዋሚነት አዲስ ሰው ትመስላለህ! እዚህ ያለው ውይይት አንተም ነገር ርዕሰ ሚኒስትር ብትሆን የሚነሳ ሃሳብ ነው ። በምድርና ሰማይ መሃል ላሉ ነገሮች መልሱ አቢይን መቃወም አይደለም ! ተረጋጋ :idea:

Abere
Senior Member
Posts: 11135
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: ጠቅላይ ሚኒስትር ሳይሆን ቀዳማዊ ሚኒስትር ወይም ርዕሰ ሚኒስትር ነው መባል ያለበት!

Post by Abere » 24 Feb 2022, 17:16

እኔ ፓለቲካ አልወድም፤ ምንም እንኳን ፓለቲካ በሚንጣት አለም ውስጥ ብኖርም። ምክንያቱም ፓለቲከኞች ውሸታሞች ናቸው፤ በኢትዮጵያ ደግሞ መተዳደርያ የሌላቸው ዱርየዎች በቀላሉ የሚያድጉበት መናኛ ክፍት የስራ ቦታሰ ለሆነ። እንደ ነጻ ዜጋ እንጅ እንደ ተቃዋሚ ድርጅት አባል ወይም ደጋፊ ሁኜ አይደለም ከዚህ ሃሳቤን የምሰነዝረው - ይህ ይታወቅልኝ :!:

Horus wrote:
24 Feb 2022, 17:05
Abere wrote:
24 Feb 2022, 17:00
እረ ጎበዝ ሃሳቡ ቃጤ አንሁን። ኮከብ በመቁጠር ስማ ማውጣት ጥሩ መሪ ያመጣል ብለን እያሰብን ነው ወይስ ሰዎቹን መቀየር ሲያቅተን ስማቸውን ሆነ?
አበረ
ምስማርና ዶማ ብቻ ባሉበት ዩኒቨርስ የሁሉ ነገር መፍትሄ መዶሻ ይሆናል ይባላል! በፖለቲካ ተቃዋሚነት አዲስ ሰው ትመስላለህ! እዚህ ያለው ውይይት አንተም ነገር ርዕሰ ሚኒስትር ብትሆን የሚነሳ ሃሳብ ነው ። በምድርና ሰማይ መሃል ላሉ ነገሮች መልሱ አቢይን መቃወም አይደለም ! ተረጋጋ :idea:

Horus
Senior Member+
Posts: 30928
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ጠቅላይ ሚኒስትር ሳይሆን ቀዳማዊ ሚኒስትር ወይም ርዕሰ ሚኒስትር ነው መባል ያለበት!

Post by Horus » 24 Feb 2022, 17:30

ስለዚህ ወንድም አበረ፣ የእኔ ትሁት ምክር ምን መሰልህ? በማትወደው ነገር ላይ በፍጹም ወርቃማ ግዜህን፣ ሃሳብክን፣ ስሜትክን/ኢሞሽንክን አታባክን፤ ትርፉ እራስን መጉዳት ነው ። አንተ ባለህ መክሊት የቻልከውን ለውጥ ወይም መሻሻል በዚህ አለም ላይ ለመፈየድ እንጂ በቁጣና ንዴት ብትቃጠል ለአንተ ይሰማሃል እንጂ ምድር ላይ ለውጥ አያመጣም ። ትንሽም ሆነ ትልቅ አንድ ፕሮጀት የሚሰራ የሚሳካ መሆኑን በውል ገምተህ ነው ጉልበትና እውቀትህን ኢንቬስት ማድረግ ያለብህ! አምናለሁ በወሎ ሕዝብ ላይ የትግሬ ባንዳ የሰራው ግፍ እጅግ አስቆጥቶሃል! ሁላችንም እንዲሁ! ግን ልብ በል ደረጀ ሃብተ ወልድ ያለውን መንግስት እየደገፈ እንኳ ምን ያህል ተጨባጭ እርዳታና ልዩነት ለወሎ ሕዝብ እንዳደረገ! የእውነት ፖለቲካ የማይመችህ ከሆነ በሌላ መንገድ ሕዝብህን እርዳ! ኬር

Abere
Senior Member
Posts: 11135
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: ጠቅላይ ሚኒስትር ሳይሆን ቀዳማዊ ሚኒስትር ወይም ርዕሰ ሚኒስትር ነው መባል ያለበት!

Post by Abere » 24 Feb 2022, 17:47

ሆረስ፥

ፓለቲካ ቢያስጠላኝም ድምፄን ደግሞ ማሰማት የተፈጥሮ መብቴ ይመስለኛል። ሁሉ ሰው ፓለቲካኛ አይደልም፥ሁሉም ሰው ግን የብሶት ድምጽ ያሰማል ውሸትም ይሁ እውነት እንድ መርጥም ይበረታታል። መረጃ ፎረም የሚመጣው ሁሉ መቸም ፓለቲከኛ ወይም ለፓለቲካ ለመታጨት ነው ብየ አላምንም።
Horus wrote:
24 Feb 2022, 17:30

Post Reply