Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

የትኛው ጥቅም ... ኢህአዴግና ብልፅግና ምንና ምን ?? | ጫናው የመጣው "አንድን ህዝብ መጨፍጨፍ መብታችን ነው" ብለው በሚያስቡ ደመኛ ሰዎች ሀገሪቷ በመመራቷ ነው።

Post by sarcasm » 20 Feb 2022, 10:38

የትኛው ጥቅም ... ኢህአዴግና ብልፅግና ምንና ምን ??
By Finfinne Times


ባሻዬ ጫናው የመጣው "አንድን ህዝብ መጨፍጨፍ መብታችን ነው" ብለው በሚያስቡ ደመኛ ሰዎች ሀገሪቷ በመመራቷ ነው።


ከሀበሻ የፖለቲካ አመለካከት የሚገርመኝ ከአለምአቀፉ ማህበረሰብ ጋር መጋጨት የሀገር ወዳድነት ወይም ጥቅምን አሳልፎ ያለመስጠት ተምሳሌት ተደርጎ ይወሰዳል። ይህ ጭፍን አመለካከት ሀበሻ ከጥንት ጀምሮ ይዞት የመጣው የፖለቲካ ብሂል ነው።

ከአለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር መጋጨት እንደ ጀግንነት ይወሰዳል .. አሜሪካንን ጉድ አደረጋት ተብሎ መሪው ይደነቃል። በስሙ ስለት ይገባለታል። አይዞህ ግፋ ቀጥል ... ይባላል።

በእርግጥ አለም የምታራምደው የጥቅም ፖለቲካን ነው። ኢትዮጵያ በኢህአዴግ ዘመነ መንግስት ከምዕራባውያን ጋር የጥቅም ተቋዳሽ ነበረች። በአፍሪካ ቀንድ በደህንነት በፀጥታ ጉዳዮች ላይ በጋራ ይሰሩ ነበር። ቀጠናውን አሜሪካንና ምዕራባውያን በሚፈልጉት መልኩ ትዘውረው ነበር።

ኢኮኖሚን አስመልክቶ ኢህአዴግ ያራመደው አቋም ለምዕራባውያን ምቹ አልነበረም። የመንግስት ተሳትፎ በኢኮኖሚ ላይ መኖር ከሀያላኑ ጋር የቅራኔ ምንጭ ነበር። በኢኮኖሚ ጉዳዮች ኢህአዴግና ምዕራባውያን በአጠቃላይ ሆድና ጀርባ ነበሩ።

በዘመነ ኢህአዴግ በሌሎች በፖለቲካ በማህበራዊ .. በአህጉራዊ በአለምአቀፋዊው ጉዳዮች ላይ ሰጥቶ በመቀበል መርህ አንፃራዊ ጥሩ የዲፕሎማሲ ግንኙነቶች ከአለም ሀገራት ጋር ነበረን። ምንአልባትም የቻይና የኢኮኖሚ ተሳትፎ ከፍተኛ ተፅዕኖ እስኪፈጥር ድረስ ኢህአዴግ የሚጥላቸው ዲፕሎማሲ ካርዶች ስኬታማ ነበሩ።

በዘመነ አብይ የተለየ ጥቅም የሚባለው ምንድነው ?? .... በጂኦፖለቲካ በኢኮኖሚ ጉዳዮች በፖለቲካ ርዕዮት .. በሀገሪቱ ብሔራዊ ጥቅም ወይስ .. በህዳሴው ግድብ ??

ኢኮኖሚዋ ዜሮ የገባች ሀገር ፣ ውስጣዊ የፖለቲካ ትኩሳቷ ወደ እርስ በርስ ጦርነት የተቀየረባት ፣ ወታደራዊ ሀይሏ የተንኮታኮተባት ሀገር ፣ በአፍሪካ ቀንድ የነበራትን ሃያልነት ያጣች ሀገር ..

ወዘተ በእጅግ ብዙ ቀውሶች ውስጥ ያለች ሀገር የምዕራባውያን የተለየ ትኩረት የተደረገባት ወይም ጫና የበዛባት ምክንያት በእርግጥም ግራ ያጋባል።

ኢህአዴግ በኢኮኖሚ ጉዳዮች እድሜ ልኩን የውጭ ጫና ነበረበት። ነገር ግን አንድም ቀን ሲያለቃቅስ ታይቶም አይታወቅም። አረ ስለጉዳዩ ድምፅ እራሱ አይሰማም ነበር።

ኢህአዴግ የህዳሴው ግድብን ሲጀምር በትከሻው እጅግ ብዙ ጫናዎችን ተቋቁሞ ነበር። በወታደራዊ ስጋት አንፃር የታጀበ ነበር ስጋቱ። ነገር ግን ይህንን ሁሉ ጫናዎች አንድም የጩኸት ድምፅ ሳያሰማ ተቋቁሞት ግድቡን አስጀምሮታል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በቀጠናው ጥቅም አስከባሪ የነበረውን የወታደራዊ ሀይልን በሀገር ውስጥ ጦርነት ማግዶ .. የህዳሴ ግድብ ድርድርን እነሱ በሚፈልጉት መልኩ እየተደራደረ ..

ኢኮኖሚውን ከመንግሥት እጅ አውጥቶ ለግል ሴክተር ለመሸጥ እንቅስቃሴ ጀምሮ ወይም በምዕራባውያን አይን የተቃኘ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ለመተግበር ተፍተፍ እያለ .... የውጭ ጫናዎች አሉብኝ ሲል ያስቀሃል።

ባሻዬ ጫናው የመጣው ፖለቲካ ዲፕሎማሲ ምን እንደሆነ በማያውቁ ደብተራዎች ቤተመንግስቱን በመሞላቱ ነው። አንድን ህዝብ መጨፍጨፍ መብታችን ነው ብለው በሚያስቡ ደመኛ ሰዎች ሀገሪቷ በመመራቷ ነው።

ባሻዬ ጫናው የመጣው መነጋገር መደራደር በማይችሉ መሃይሞች ምክንያት የመጣ ነው። ከአለምአቀፉ ማህበረሰብ ጋር እንዴት ተግባብቶ መስራት እንደሚቻል በማያውቁ ሰዎች በመሞላቱ ነው።

በዲፕሎማሲ መድረክ እኔ ብቻ ነኝ ትክክል ብለው በሚያምኑ ተረታ ተረቶችን ለቅመው በሚያወሩ .. ዘራፍ አረ ጎራው በሚሉ ፎክሮ አደሮች ሀገሪቷ በመመራቷ ነው።

የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመዷ ኢትዮጵያ በዚህ ሰአት አይደለም የሚሰጥ ጥቅም ሊኖራት ቀርቶ የሚበላ ምግብ እንኳን የሌላት ሀገር ናት ... ጦርነቱ ያመጣው ነበልባል በሁሉም አቀፍ ድርድር ካልተጠናቀቀ በስተቀር .. ባሻዬ አይደለም ስለ ግድብና ልማት ቀርቶ ስለ ምትበላው ምግብ እንኳን የምታስብበት ሰላም ላይኖርህ ይችላል !!

Finfinne Times



https://www.facebook.com/permalink.php? ... 1731586155

TGAA
Member+
Posts: 5626
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

Re: የትኛው ጥቅም ... ኢህአዴግና ብልፅግና ምንና ምን ?? | ጫናው የመጣው "አንድን ህዝብ መጨፍጨፍ መብታችን ነው" ብለው በሚያስቡ ደመኛ ሰዎች ሀገሪቷ በመመራቷ ነው።

Post by TGAA » 20 Feb 2022, 11:22

Ayatola jewar"s mouthpiece fineness times churning out its usuall Ant Amhara propaganda. It's not weyan"s night attack on Ethiopian National Defense forces the source of the destruction but Amharas who went in to rescue ENDF. Americans that came down hard and heavy to save their 30 year of poodle 🐩 that went to slaughter Somalis and used to send Ethiopians in every hot spot in Africa for pennies wanted to reimpose on Ethiopian people and according to Ayatola's mouthpiece finfine times ,Ethiopia should not resisted -so who is to blame for this ? Bloody Amharas and theirs Fukera. Enthusiastic servitude according to finfine times is a prelude to democracy and freedom, resisting to servitude is the conspiracy of the bloody Amharas. What time are we are living in?

Post Reply