Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Assegid S.
Member
Posts: 936
Joined: 11 Aug 2013, 07:11
Contact:

ጨረቃው መንግስታችን

Post by Assegid S. » 09 Feb 2022, 18:40

https://www.eaglewingss.com/

ጨረቃው መንግስታችን

አነሳሴ "ፀሐዩ መንግስታችን" በመባል የሚታወቀውን የቀድሞውን የቀዳማዊ ኃይለስላሴን አገዛዝ ከዘንድሮው ንጉሣዊ-መሰል ሥርዓት ጋር ለማወዳደር አይደለም። የእኔ ጨረቃ በተለምዶ "የጨረቃ ቤት" "የጨረቃ ምርጫ" ወዘተ እየተባለ እንደሚጠራው "ህገ-ወጥነትን" የሚጠቁም ለዛም የላተም። የዚህ ጽሑፌ "ጨረቃ" ትርጓሜ፦ ልማደ-ወጥ እውነታን ለማሳየት ሳይሆን ባሕሪ-አልባ ገፅታን ለማጉላት ነው።

ድቅድቅ ባለው ጨለማ ውስጥ ድንገት ፍንትው የምትለው ጨረቃ - እንደ ድሮ ልጃገረድ ገፅታ ቀልብን ትገዛለች፤ ኧረ ኣንዳንዴም ልብን ትስርቃለች። እውነታው ግን፦ አማላይዋ ጨረቃ … "ዕድሜ ለፀሐይ!” ትበል እንጂ … በውስጡዋም ይሁን በላይዋ የእኔ ነው የምትለው ቅንጣት (0.0001 lumens ) ብርሃን የላትም። ታዲያ ያ ማራኪ ውበት፣ ብሩህ ብርሃን ከየት መጣ? ለሚለው ጥያቄ መልስ የgoogle search box አለና … እኔ ወደ ጨረቃው መንግስታችን ልመለስ።

ብልፅግና፦ ልክ እንደ ጨረቃ … መንግስት ያልሆነ ነገር ግን መንግስታት ነን ከሚሉ ሀገራት የመንግስትን ስነ-ባህሪ ተቀብሎ መልሶ በማንፀበረቅ መንግስት ለመምሰል የሚሞክር የግብዞች ስብስብ ብቻ ሳይሆን፤ ልክ እንደ amoeba (አሜባ) የእራሱ የሆነ ቅርፅና መጠን ኣልባ አካልም ጭምር ነው። ከዚህም የተነሳ፦ ነብዩ ኤልያስ ወደ ምድር ቢመለስ እንኳ … የነገን የብልፅግና አቋም መተንበይ ቀርቶ ዛሬ ላይ ያለውን ባህሪም ቢሆን በቅጡ መናገር የሚችል አይመስለኝም። ከኣፍ እስከ ገደፉ "አማኞች ነን" በሚሉ እምነት-ናቂ ዘረኞች ለተሞላው መስተዳድር ... "ኣንድ ሺህ ዘመን እንደ ኣንድ ቀን፥ ኣንድ ቀንም እንደ ኣንድ ሺህ ዘመን" ነው። በየሰከንዱ ለመቀያየር ከበቂ በላይ ጊዜ አለው።

ብልፅግና፦ ከውጭ ወደ ውስጥ ለምንመለከተው ባይተዋር ዜጎች ብቻ ሳይሆን፥ ከውስጥ ወደ ውጭ ለሚያዩት ቤተኛ አባላቱም ቢሆን እንዲሁ ወጥ-አልባ (abstract) ድርጅት ነው። ለዛም ነው፦ ኣንዱ ባለስልጣን tweeter ላይ የነገረንን ... በዛው ቅፅበት ሌላው telegram ላይ ወጥቶ የሚሽረው። ፓርቲው፦ እንኳን ለሚመራቸው ዜጎች … ለሚመሩትም ዘገምተኞች ቢሆን የጋር መግባቢያ ሆኖ የሚያገለግል ምስልም ሆነ ባህሪ የለውም።

ዛሬ ላይ እንደምናየው፦ ኣፋር ተወረረ - ኣማራ ተለቀቀ፣ ኣማራ ተለቀቀ - ኣፋር ተወረረ … እያልን እንዲህ በፈረቃ የማበዳችን ሚስጥርም ይህንን የብልፅግናን ጨረቃዊ ባህሪ ካለመረዳት የመጣ ችግር ነው። ይህ ብቻም ደግሞ አይደለም፦ ሀገር ... ዕውቀት ስልጣን በሰጣቸው ምሁራን ሳይሆን፥ ስልጣን ኣዋቂ ባስመሰላቸው መኃይማን ስትመራ የምትጓዘው እንዲህ በሦስት ማዕዘን ጎማ ነው። እየተነሱ መውደቅ፣ ከፍ እያሉ ዝቅ ማለት የየሰከንዱ አደጋ ይሆናል፤ መንገጫገጩ ይበዛል።

እርግጥ ነው መፅሐፉም ቢሆን "ጥበብን (ዕውቀትን) ገንዘብህ አድርጋት" ይላል፤ እየመነዘርክ እንድትጠቀማት ብቻ ሳይሆን ሌላውንም እንድትጠቅምባት። የጥበብ ገንዘብን የመሆን ምሳሌ ግን ማንም ያለ ሥራ ቀብድ እንዲወስዳት አያደርጋትም። በዚህ በጨረቃው የብልፅግና መንግስት የምናየው እውነታ ግን ይኼንኑ ነው። በየሚንስቴር መስሪያ ቤቱ ብቻ ሳይሆን - ከእምነቱ ቡራኬ እስከ ፖለቲካዊው ትንታኔ በሚዘጋጁት ህዝባዊ መድረኮች ላይ ያዙኝ ልቀቁኝ የሚሉት ... እንደ ጨረቃዋ የራሳቸው ብርሃን (ዕውቀት) የሌላቸው፥ ነገር ግን ብሩህ መስለው ለመታየት የሚሞክሩ ግብዞች ናቸው። ዲግሪ ዲፕሎማና ሥልጣን በቀብድ የተቀበሉ ዘረኛ እብዶች።

ከእነዚህ በላይ የሚገርሙት ደግሞ፦ ነጮቹ እንደሚሉት "የተቀደደ ጫማ አድርገው ታዋቂ ጫማ ሰፊዎች ነን" በማለት እግር ይዘው አላራምድ የሚሉት ብልፁግ "የማህበረሰብ አንቂዎቹ" ናቸው። ከጥቂት ዓመታት በፊት በድንገት የሰማሁት ኣንድ ድምፃዊ ይህን መሳይ እውነት በዘፈን ስንኝ ሲገልፀው እንዲህ ነበር ያለው፦

"የዘንድሮ ዐዋቂ ... ጨዋ በኣደባባይ
ፀሐይ ልሁን ይላል ... የጨለመበት ሲያይ
"

ገራሚ ትዝብት! ኣራት ፍሬ ቤተሰባቸውን በትነው ... መቶ ሚልዮን ህዝብ በኣንድ ጣሪያ ስር ለማኖር የሥነ-ልቦና ምክር ካልሰጠን ብለው ከግሩቭ ጋርደን የሚያጓጉሩት የብልፅግና ካድሬዎች ይህን ግሩም ዘፈን ሰምተው ይሆን?

አጭር ጽሑፌን ከማጠቃለሌ በፊት ግን፥ የዚህን መንግሥት ጨረቃዊ ስሪት ለተረዳ አእምሮ እንዲህ በየሰዓቱ ብልጭ ድርግም ማለቱ አረማመዱን ከእንቅፋት ብቻ ሳይሆን እምነቱንም ከተስፋ መቁረጥ እንደሚታደገው ማስገንዘብ እወዳለሁ። መንግሥት ያልሆነውን መንግሥት መሳይ፦ ኣፋርን ከህወሃት - ኣማራን ከኦህዴድ ተከላከል እያለ ነጋ ጠባ እሰጣ-ገባ ውስጥ ከመግባት ይታደጋል። መሆን ያለበትን በጊዜ መክሮ ከዚህም በላይ እጅግ ሳይረፍድ ወደ ተግባር ለመግባት ያነቃል። ይሰማል? ደግሞስ መንግስት ከተግባሩ መች ቦዘነ? ከተናገረውስ ምን አጎደለ? እንኳን ቃሉን ትንቢቱንም በትጋት ፈፅሟል፥ ነገም ይፈፅማል። ለዚህም መከራከሪያዬ ብዙ ነው። ትዝ ይላችኋል? በኣንድ ወቅት ጨረቃው ጠቅላይ ሚንስትር "ግዴለም ትንሽ ታገሱ እንጂ እጃችሁን በኣፋችሁ ላይ አስጭናችኋለሁ" ብለው ሊያስገርሙን ትንቢት እንደተናገሩልን? የእናንተን ባላውቅም እኔን ግን በግርምትም ባይሆን በሀፍረት እጄን በኣፌ ላይ ካስጫኑኝ ሰነባብተዋል። ይኼ ብቻም አይደለም፦ "ድላችን ሰበር ዜና አይሆንም" ብለውንም ነበር እኮ። ታዲያ መቼ ዋሹ? ከኣፋር እስከ ኣማራ በሴራ ረግፈው፣ ከህፃን እስከ መንኮሴ በስድ ተደፍረው፣ ህዝቡ ከቅልጥም እስከ ቅስሙ ተሰባብሮ እንክትክቱ ከወጣ ቦኃላ "ህወሃት ጠፋ" ቢባል እንኳ ሰበር ዜና የሚሆነው ለማን ነው? ለነገሩ መንግስት ህወሃትን ሊያጣፍጣት እንጂ ሊያጠፋት ፍላጐትና ዕቅድ ያለው አልመሰለኝም። ጄነራል ባጫ ደበሌ "መቀሌን ቀስ እያልን ሹርባ እየሰራናት ነው" ሲሉን ሊደልሏት እንጂ ሊድሯት … እንዲህ በድርድር አስውበው ሊሞሽሯት እንዳሰቡ ማን ጠረጠረ?

የከርሞ ሰው ይበለን እንጂ በጨረቃው መንግስት ምን እውነት - ምንስ እምነት አለ? እዛው መስቀል አደባባይ ላይ ክብርት ከንቲባዋ … "ንግሥት ጉዲት ሁለተኛ" ተበለው ሲቀቡ፣ "ዳግማዊ ዮዲት" ሆነው ሲነግሱ እናይ ይሆናል። ገንዘብ ያጠረው መንግስት-መሳይ መንግስት ግንባር ለግንባር እየዞረ ፥ ወታደራዊ ሹመትን በወርሃዊ ደሞዝ ፋንታ እንደ ብር እየቆጠረ መክፈል ከጀመረ … ያኔ … anything is possible!

kibramlak
Member
Posts: 2155
Joined: 26 Sep 2013, 09:27

Re: ጨረቃው መንግስታችን

Post by kibramlak » 10 Feb 2022, 00:33

Assegid, thank you. I have been saying this for over two years after noticing each and every bits of his acts and the works of his tribal clans. I recently posted on who is benefiting and who is really losing from this war.

ስለ ሴረኛው የጨረቃ ምናምን ትዝብት ካነሳሀ ላይቀር የሚከተሉትን ልጨምርልህ፣

- ዱቄት ሆነዋል ብሎ በእጅ አዙር አስታጥቆ ህዝብ እና ንብረት ያስጨረሰ
- ዱቄትትን አሸባሪ ብሎ ከአሸባሪ ጋር ለመደራደር የተቀመጠ
- የኢትዮጵያ የከፍታ ማማ ብሎ የጎሳ ማማ እንዳይወርድ ቀን ተሌት የሚያሴር
- በኢትዮጵያ ጉዳይ አንገቴን እሰጣለሁ ብሎ በእንድ የስልክ ጥሪ ይፕሀግርን ጥቅም ጉዳት ላይ የሚጥል ስራ የሰራ
- አሸባሪወችን/ኦነግ ይለፈፀሙት ጭፍጨፋ ምንም የማይተነፍስ ግን እራሱን እና ህዝቡን የሚከላከልን ህዝብ መሳሪያ ጣሉና ታረዱ የሚል ጉድ (ለዛውም እራሱን ያዳነውን)

የጨረቃው ሴረኛ ጉድ ተዘርዝሮ አያልቅም

Assegid S. wrote:
09 Feb 2022, 18:40

Post by Assegid S. » 10 Feb 2022, 11:21

kibramlak wrote:
10 Feb 2022, 00:33

ሰላም Kibramlak; you're welcome, Bro. ለአስተያየትህ በጣም አመሰግናለሁ።

ጠቅላይ ሚንስትሩ ብዙ የማይባል ብለውን ስላበዙብን ማስታውስ ቢያዳግተን መልሰው እኛኑ "የማስታውስ ብቃታችሁ ውስን ነው" ሲሉ ዘለፉን። አንተም እንዳልከው ሁሉንም እንዘርዝረው ብንል በእርግጥም አስልቺ ይሆናል። እኔ ግን ዛሬም ድረስ ሰው አዕምሮውን ካልሳተ በስተቀር እንዲህ ብሎ ሊናገር አይገባም የምልው "ማናችሁንም አልሰማም፤ ጥሩ ሰርተሃል የምትሉኝንም ሆነ በዛኛው ጎራ አጥፍተሃል ብላችሁ የምትወቅሱኝን ሁለታችሁንም አልሰማም" ያሉን ቀን ነው። ሰው እንዴት የሀገር መሪ ሆኖ ውዳሴም ሆነ ወቀሳ አልሰማም ይላል። እንኳን ሰው ስህተትን ልክ እንደ ሥጋ የለበሰ ፍጡር ይቅርና፥ ንፁህ መንፈስ፣ ስህተት የለሽ የሆነውም ፈጣሪ እኮ ሰውን ያዳምጣል። መልካም ጊዜ ወንድም Kibramlak.

sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: ጨረቃው መንግስታችን

Post by sarcasm » 10 Feb 2022, 19:45

ጨረቃ had positive, glorious connotation in my mind until PM Abiy came with "የጨረቃ ቤት" and "የጨረቃ ምርጫ". When I was in elementary school, a new kid joined our class about half way through the year. He could not speak Tigrigna and he had Amharic speaking friends who lived in a military camp about 1km from the school. We used to have song competition during break and this kid used to sing Neway Debebe's "ጨረቃ" song. He quickly became very popular in the school. Whenever I hear that song, I remember him.

Lets hope ጨረቃ returns to represent beauty very soon. Enjoy the below short poem.

Wedi
Member+
Posts: 7989
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: ጨረቃው መንግስታችን

Post by Wedi » 10 Feb 2022, 20:57

Some years ago Meles Zenawi said "Giving power to Galla is like giving for a child a glass to play with it"

Now we are watching that Meles' words are 100% true. Meles Zenawi was evil genius!!

kibramlak
Member
Posts: 2155
Joined: 26 Sep 2013, 09:27

Re: ጨረቃው መንግስታችን

Post by kibramlak » 11 Feb 2022, 00:16

Assegid S. wrote:
10 Feb 2022, 11:21
kibramlak wrote:
10 Feb 2022, 00:33
Assegid, thank you. I have been saying this for over two years after noticing each and every bits of his acts and the works of his tribal clans. I recently posted on who is benefiting and who is really losing from this war.

ስለ ሴረኛው የጨረቃ ምናምን ትዝብት ካነሳሀ ላይቀር የሚከተሉትን ልጨምርልህ፣

- ዱቄት ሆነዋል ብሎ በእጅ አዙር አስታጥቆ ህዝብ እና ንብረት ያስጨረሰ
- ዱቄትትን አሸባሪ ብሎ ከአሸባሪ ጋር ለመደራደር የተቀመጠ
- የኢትዮጵያ የከፍታ ማማ ብሎ የጎሳ ማማ እንዳይወርድ ቀን ተሌት የሚያሴር
- በኢትዮጵያ ጉዳይ አንገቴን እሰጣለሁ ብሎ በእንድ የስልክ ጥሪ ይፕሀግርን ጥቅም ጉዳት ላይ የሚጥል ስራ የሰራ
- አሸባሪወችን/ኦነግ ይለፈፀሙት ጭፍጨፋ ምንም የማይተነፍስ ግን እራሱን እና ህዝቡን የሚከላከልን ህዝብ መሳሪያ ጣሉና ታረዱ የሚል ጉድ (ለዛውም እራሱን ያዳነውን)

የጨረቃው ሴረኛ ጉድ ተዘርዝሮ አያልቅም
ሰላም Kibramlak; you're welcome, Bro. ለአስተያየትህ በጣም አመሰግናለሁ።

ጠቅላይ ሚንስትሩ ብዙ የማይባል ብለውን ስላበዙብን ማስታውስ ቢያዳግተን መልሰው እኛኑ "የማስታውስ ብቃታችሁ ውስን ነው" ሲሉ ዘለፉን። አንተም እንዳልከው ሁሉንም እንዘርዝረው ብንል በእርግጥም አስልቺ ይሆናል። እኔ ግን ዛሬም ድረስ ሰው አዕምሮውን ካልሳተ በስተቀር እንዲህ ብሎ ሊናገር አይገባም የምልው "ማናችሁንም አልሰማም፤ ጥሩ ሰርተሃል የምትሉኝንም ሆነ በዛኛው ጎራ አጥፍተሃል ብላችሁ የምትወቅሱኝን ሁለታችሁንም አልሰማም" ያሉን ቀን ነው። ሰው እንዴት የሀገር መሪ ሆኖ ውዳሴም ሆነ ወቀሳ አልሰማም ይላል። እንኳን ሰው ስህተትን ልክ እንደ ሥጋ የለበሰ ፍጡር ይቅርና፥ ንፁህ መንፈስ፣ ስህተት የለሽ የሆነውም ፈጣሪ እኮ ሰውን ያዳምጣል። መልካም ጊዜ ወንድም Kibramlak.
Assegid, all the decisions he has been making is exactly a reflection of this. He is a confirmed dictator with a well orchestrated narratives to build a king like image

Assegid S.
Member
Posts: 936
Joined: 11 Aug 2013, 07:11
Contact:

Re: ጨረቃው መንግስታችን

Post by Assegid S. » 11 Feb 2022, 18:20

Hello again guys;

Sarcasm: thanks a lot for the short poem and the song;
Wedi and Kibramlak: Thank you indeed for the comment.

Here I found the song that I referred in my writing. Enjoy it if you have time ... otherwise the quoted verses are sung at (1′53″ - 2") - By Ahmed Tshome.

Stay safe, Brothers.

Post Reply