Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 11068
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

አብዲ ዒሌ የአብይ አህመድ የግል የሆነውን ፍርድ ቤት መሳቂያ አደረገው። < እኔ አብዲ ዒሌ ከስብሃት ነጋ እና ጁሃር የሚበልጥ ወንጀል አለመፈጸሜን አምላክም ኢትዮጵያም ያውቃል> በማለት።

Post by Abere » 09 Feb 2022, 15:33

አብዲ ዒሌ የአብይ አህመድ የግል ድርጅት የሆነውን ፍርድ ቤት መሳቂያ አደረገው። ምን ብሎ? < እኔ አብዲ ዒሌ ከስብሃት ነጋ እና ጁሃር ሙሃመዲ የሚበልጥ ወንጀል አለመፈጸሜን አምላክም ኢትዮጵያም ያውቃል፤እኔ ግን የግል እስረኛ ነኝ> በማለት።በእርግጥ አብዲ ኢሌ የሶማልያ ህዝብን ያሰቃየ የእነ ስብሃት ሎሌ ነበር ቢሆንም ሎሌ ከጌታው የበለጠ ጥፋት ሊያደርስ አይችልም። ከጅሃር ሙሃመዲም የበለጠ ወንጀል አልፈጸመም። ጅሃር በርካታ ከተማዎችን አውድሟል በሀረር እና ጅጅጋ ላለው አለመረጋጋት ፥ መፈናቀል እና ሞት ዋና ተዋናይ ነው። ለነገሩ አባይ ወልዱም የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት ነበር እንደ አብዲ ኢሌ። ዳሩግን ስብሃትም፥ ጁሃርም፤ አባይ ወልዱም በነጻ ተለቀዋል፡ አብዲ ኢሌ ግን ግራ ገብቶታል፥ ወንጀል ስለመፈጸሙ ክዶ ሳይሆን ወንጀለኛ የሆነውን የአብይ አህመድ ጉዳይ ነው። እያለ ያለው እራሱ ወንጀል የሚፈጽም እንደት ወንጀለኛ ሊከስ እና ሊያስር ይችላል ነው። ትክክል ጥያቄ ነው። ግን አብይ አህመድ የሶማሌውን አብዲ ኢሌን በልዩ የግል እስረኛ ያደረገበት ምክንያት እንድሁ የሚታይ ይመስለኛል። አብዲ ኢሌ የኦሮሙማው ሱሴ ወይም ለማ መገርሳ የድሞግራፊ ለውጥ አቀንቃኝ ሁነው ነበር፥ አያቶላ ጁሃር ሜንጫው ደግሞ አለምሽ ዛሬ ነው ዛሬ ድንስ ላይ ነበር - ሁል ግዛት እስላማዊ ኦሮሙማ መሆን አለበት መሟሟቅ ላይ። ታዲያ አብድ ኢሌ ሰፋሪ የሚላቸውን ኦሮሞዎች ከሱማሌ ክልል እጅ እጃቸውን እየያዘ በማስወጣት 1 ሚልዮን ኦሮሞ ከሱማሌ አጽድቶ ያው እንደ ወትሮው ታሪክ ኦሮሞዎችን ወደ መሃል አገር አባረረ።(በነገራችን ላይ በ16ኛው ክፍለ ዘመን ሶማሌዎች የዳሮድ ጎሳዎች ኦሮሞዎችን በጦርነት በማባረረ ወደ መሀል አማራ አገር አሰድተዋቸውል። የአብዲ ኢሌ ተግባር ዳግማዊ የኦሮሞዎች መፈናቀል ነው።) This was during the time of Oromo migration to Ethiopia.

ይህ ተግባር ለርዕሰ ኦሮሙማው አብይ አህመድ ከፍተኛ ሃፍረት እና ሽንፈት በመሆኑ በቁጭት አብዲ ኢሌ የግል እስረኛው ነው ማለት ይቻላል። ለነገሩ ንጹህ ሰው እስከንድር ነጋን ያለምንም ስህተት እንሰሳ ሳይቀር ከሚወነጅላቸው ከጁሃር እና በቀለ ገሪባ ጋር ያሰረ እንደት 1 ሚልዮን ኦሮሞ ያባረረ በቀላሉ ይታያል። አብዲ ኢሌ ቂምሃ ያዝ - አንድየ ፍርድ እንድሰጥህ ብቻ።

ZEMEN
Member
Posts: 2492
Joined: 27 Jun 2011, 14:37

Re: አብዲ ዒሌ የአብይ አህመድ የግል የሆነውን ፍርድ ቤት መሳቂያ አደረገው። < እኔ አብዲ ዒሌ ከስብሃት ነጋ እና ጁሃር የሚበልጥ ወንጀል አለመፈጸሜን አምላክም ኢትዮጵያም ያውቃል> በማለት

Post by ZEMEN » 09 Feb 2022, 15:41

< እኔ አብዲ ዒሌ ከስብሃት ነጋ እና ጁሃር ሙሃመዲ የሚበልጥ ወንጀል አለመፈጸሜን አምላክም ኢትዮጵያም ያውቃል፤እኔ ግን የግል እስረኛ ነኝ>
In all fairness, he got a point. Abiy is afraid of the sub-humans. he terrified to no end.

Post Reply