Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30898
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

እኔ ሆረስ ኬረቴ ነኝ፤ ወደፊት ኢትዮጵያን የሚያስተዳድሩት ብልጽግና እና ኢዜማ ናቸው !!!

Post by Horus » 17 Feb 2021, 03:16

በሚቀጥለው ምርጫ አቢይ ማጆሪቲ መያዝ መፈልግ ሳይሆን ማጆሪቲ ካልሆነው እንደ መለስ ዘመን ይሆናል !

ኢዜማ ጠካራ ማይኖሪቲ ፓርቲ ይሆናል እስከ 2018 ድረስ ማለት ነው ።

እኔ አቢይ ብሆን የሆነ ጎሳ ጋር ከመፎካከር ከኢዜማ ጋር መፎካከን እመርጣለሁ !!

ስለዚህ የዜጋ ፖለቲካ ብዙ ወንበር እንዲያገኝ ኢትዮጵያን የምትወዱ ከኢዜማ ጋር ተባበሩ

Abere
Senior Member
Posts: 11096
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: እኔ ሆረስ ኬረቴ ነኝ፤ ወደፊት ኢትዮጵያን የሚያስተዳድሩት ብልጽግና እና ኢዜማ ናቸው !!!

Post by Abere » 04 Feb 2022, 15:20

ሆረስ፤

አገራዊ ውይይት እና ዲያሎጉ ምንም አዲስ ነገር አያፈራም ማለት ነው። እኛ እኮ ተናግረናል፡ አዲስ ንጉሥእ ንጅ ለውጥ መቸ መጣ በሚል በገደምዳሜው። መገዛቱ ላይ አይደለም ህዝቡ ያለው ችግር በቅጡ የሚገዛው መጥፋቱ ነው። ችግር ካለ ችግር ይኖራል ማለት ነው። እስኪ ትንሽ ፀሎት አድርግ የተሻለ ራዕይ ቢያሳይህ - ብልፅግናው እኮ በልጽገን አድገን አድገን ጋሽበናል - ግን ፍሬ ማፍራት አልቻለም። የጋሸበ ደግሞ ይወድቃል።

TGAA
Member+
Posts: 5625
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

Re: እኔ ሆረስ ኬረቴ ነኝ፤ ወደፊት ኢትዮጵያን የሚያስተዳድሩት ብልጽግና እና ኢዜማ ናቸው !!!

Post by TGAA » 04 Feb 2022, 16:04

Horus wrote:
17 Feb 2021, 03:16
በሚቀጥለው ምርጫ አቢይ ማጆሪቲ መያዝ መፈልግ ሳይሆን ማጆሪቲ ካልሆነው እንደ መለስ ዘመን ይሆናል !

ኢዜማ ጠካራ ማይኖሪቲ ፓርቲ ይሆናል እስከ 2018 ድረስ ማለት ነው ።

እኔ አቢይ ብሆን የሆነ ጎሳ ጋር ከመፎካከር ከኢዜማ ጋር መፎካከን እመርጣለሁ !!

ስለዚህ የዜጋ ፖለቲካ ብዙ ወንበር እንዲያገኝ ኢትዮጵያን የምትወዱ ከኢዜማ ጋር ተባበሩ
If wishful thinking had taken us anywhere we would have arrived there by now. Abiy prosperity party institutes carbon copy of weyannes tribal ideology..but we still think it is the future, Ezema preaches about citizenship but mums while the citizens are stripped of their basic right to live, however, we still insist they are the future..it time to pause and examine our blind spot.
Last edited by TGAA on 05 Feb 2022, 00:05, edited 1 time in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 30898
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: እኔ ሆረስ ኬረቴ ነኝ፤ ወደፊት ኢትዮጵያን የሚያስተዳድሩት ብልጽግና እና ኢዜማ ናቸው !!!

Post by Horus » 04 Feb 2022, 16:43

ኤደን የዛሬ አመት ምርጫው ምን ቢሆን ያልኩትን ዛሬ ለጥፎታል ። በመሰረቱ የምርጫው ውጤትና ዛሬ ያለው ሁኔታ አንድ ግዙፍ የሲስተም ቲኦሪ መርህ አረጋግጧል። ያ መርህ የኢመርጀንስ መርህ ይባላል። በዚያ መሰረት ሰዎች ባንድ ማህበራዊ (ፖለቲካዊ) ሲስተም ውስጥ ወደፊት በእርግጠኝነት ምን እንደሚከሰት መተንበይ (ፕሪዲክት ማድረግ) አይችሉም፤ ነገር ግን ምን ኢመርጅ ማድረግ እንዳለበት ሊመርጡና፣ አንድ ነገር ኢመርጅ ካደረገ በኋላም ምን እንደ ሚፈልጉ መምረጥ ይችላሉ ይላል።

የኢትዮጵያ ግዙፉ አዙሪት በልማት ዘመንና በጥፋት ዘመን መሃል ነው። ዛሬ ባብዛኛው በጥፋት አዙሪት ውስጥ ነው ያለነው ። ባለፈው ሰኔ ብልጽግና የእኔን ምክር ሰምቶ (የኔን መሰል አመለካከት ማለቴ ነው) ይበልጥ ሚዛናዊ የሆነ የጎሳ/የዜጋ ቅይጥ መንግስት አቁሞ ቢሆን ኖሮ ባሁኑ ወቅት ከዘመነ ጥፋት ወደ ዘመን ልማት መሸጋገር ጀምሮ ነበር ። ግን የትግሬ አገዛዝ በኦሮሞ አገዛዝ ሊተካ የሚጥረው ብልጽግና ከትግሬ ዘመነ ጥፋት ወደ ኦሮሞ ዘመነ ጥፋት እየነጎደ ነው ። በሚቀጥለው ውይይት ካልታረመ ማለት ነው ።

ዛሬ የብልጽግናን ልጅ ያቦካው ነገር ከልቡ የሚያምን ጥቂት የማህበረሰብ ክፍል ነው ፣ ያገሩ ጉዳይ ሆኖበት ቂጣውን ከማገላበጥ ያለፈ ማለት ነው ። ከኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ አንስቶ እስከ መለስ ህገመንግስት፣ ከፖለቲካ ምንቸቶች መከማቻ ከሆነው ብልጽኛ እስከ ተረኛ ሹመቶች ሁሉንም በአይነ ቁራኛ እየጠበቅነው ነው ። አዳነች አቤቤ ይባስ ብላ አዲስ ጦርነት ከኦርቶዶክስ ጋር ከፍታለች! እንዲህ ያለው የፖለቲካ ድድብና የወዳቂ መንግስት እንጂ የሴኬታማ መንግስት ባህሪ አይደለም ። በማንኛውም መለኪያ ቢመዘን የአቢይ አገዛዝ በዚህ መልክ ሊጸና ከቶም አይችልም ።

ይህ እንግዲህ የብሄራዊ መግባባቱ ውይይት አካል ነው ። ታዲያ ይህ ብሄራዊ ጉዳይ መፍታት ያለበት በተመለከት ያላችሁን ጀባ በሉ!

Abere
Senior Member
Posts: 11096
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: እኔ ሆረስ ኬረቴ ነኝ፤ ወደፊት ኢትዮጵያን የሚያስተዳድሩት ብልጽግና እና ኢዜማ ናቸው !!!

Post by Abere » 04 Feb 2022, 17:22

በእኔ ግምት በተደጋጋሚ ወርቃማ ዕድሎች ወይም አጋጣሚዎች እያገኘች አንዱንም ያልተጠቀመችበት እና ሁሉንም ያበላሸቻቸው ብቸኛ አገር ብትኖር ኢትዮጵያ ናት። በብልጽናው መሪ ዐብይ አህመድም ዘመንም ወርቃማ ዕድል ተገኝቶ ነበር - ከ27 ዓመታት የህዝብ እሮሮ እና መስዋዕትነት። ግን ልማድ ብሎ እንደ እንቁላል ህዝብ እራሱም፤ ዐብይ አህመድም እያገሙት ነው። ህዝብ እንደት ለሚለው፤ የኢትዮጵያ ህዝብ መሪ ማበላሸት ባህሉ ነው። በውጭ አገር ያሉ ተቃዋሚዎች ሳይደራደሩ፥ቅድመ ሁኔታ ሳያስቀምጡ ወይም በእስኪ እያደር እንየው መስፈርት ሳይወቅቱ (stop gap measure) በአንድ ሌሊት ሻንጣቸውን ቆልፈው ከጫማህ ስር ነን ሙሴያችን በማለት አዲስ አባባ ነው ቤተ እየዘመሩ ሸራተን ከተሙ - ገና ጉተናው ያልጠና ታዳጊ የኢህአድግ ልጅ ጌታችን አሉት። አሁን አገር ቤት ገብተው ያለቅሳሉ፥ይወቅሳሉ፥ ራዕያቸውን አጥተው ቅስናውን እንዳፈረሰ ቄስ የፓለቲካ አጆንጆላ ሁነዋል - ከተራው ህዝብ በታች በማሰባቸው ተጽእኖ መፍጠር አልቻሉም።

ዐብይ አህመድ በአፉ የሚለው እና ምድር ላይ ያለው ነገር እጅግ የተለያየ ነገር ነው። በየሳምንቱም ከእራሱ ጋር በሚሰጠው ንግግር ይጋጫል። የህዝብ እና የአገር የሆነውን መልካም አጋጣሚ እና ወርቃማ ዕድል ከጎል ለማስገባት ሳይሆን እንደት ወጭ እጠርዛታለሁ ወይም በቀላል አነጋገር እንደት ለጸረ-ኢትዮጵያ ኦሮሙማ አቀብላታለሁ። ማን ይነጥቀኝ ይሆን ከሚል ቅዠት ላይ ነው። ሰውየው ሲጉደፈደፍ ዕድሉ ከእጁ ላይ ይቃጠላል። አሁንም የኢትዮጵያ ህዝብ መልካም አጋጣሚ አለ - ምንም እንኳን ባለቀ ሰዓት ቢሆንም። እንደት ለሚለው:-

ዐብይ አህመድ እና ብልጽግና ቁማር ጨዋታቸውን ማቆም አለባቸው። ውይይት ምና ምን የሚለው ቅራቅንቦ ለጊዜው ተወት በማድረግ ጦርነቱን በድል ማጠናቀቅ ላይ መሆን አለበት። አሁን ብልጽግና ከማን ጋር ነው የሚደራደረው? ሁሉም ተቃዋሚ ፓርቲነን ባዮች ችግር አይደሉም (የአገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታ ለጊዜው ተረድተዋል) - ችግር ሆኑት ሁለት የሽብር ቡድኖች ናቸው ( ወያኔ እና ኦነግ)። ሊደራደር እና ዲያሎግ እያለ የሚያናፍሰው ከእነዚህ ጋር ከሆነ እርሱም እራሱ አሸባሪ ነው። ደግሞ በእርግጥ ከእነኝህ አሸባሪዎች ጋር ነው። ይህ ማለት ደግሞ የሌሎች ቅን እና እውነተኛ ለውጥ ፈላጊ ዜጎችን እና ድርጅቶችን ምኞት አመቻችቶ አሳልፎ የለውጡን እድል ማበላሸት ነው። ይህ ስለሆነ ሁለት አይቀሬ ነገሮች ይከሰታሉ፤ 1) ዐብይ አህመድ የህዝብ መልካም አጋጣሚ ቁመራው ስልጣኑን ያሳጣዋል 2) አገሪቱ ቀጣይ መልካም ዕድል ፍለጋ ሌላ ዙር ውስጥ ትደክማለች።

eden
Member+
Posts: 9265
Joined: 15 Jan 2009, 14:09

Re: እኔ ሆረስ ኬረቴ ነኝ፤ ወደፊት ኢትዮጵያን የሚያስተዳድሩት ብልጽግና እና ኢዜማ ናቸው !!!

Post by eden » 04 Feb 2022, 22:35

Horus wrote:
04 Feb 2022, 16:43
የዛሬ አመት ያልኩትን ዛሬ
ሲጀመር ስተሽ ነበር፣ የዛሬ አመት

ያኔ ለምን ሳትኩኝ የሚለው ጥያቄ ላይ አተኩር። መልሱ ይጠቅምሃል፣ የዘንድሮ ስህተትህን ለመቀነስ

ስህተትን ሳያርሙ መንጎድ፣ ከእውነታ የባሰ መራቅ ነውና

ንገረኝ ካልክ፣ የሚታየኝን ልበል። አለምን ነጭና ጥቁር አርገህ ማየትህ ነው ችግርህ። የዜጋ ፖለቲካ አራማጆች መልአክ፣ የህብረብሄር ፖለቲካ አራማጆችን ደግሞ ሰይጣን አርገህ ነው የምታያቸው። እውነታው ግን አለም ግራጫ እንጂ ጥቁርና ነጭ አይደለችም። ከሁለቱም አሳቢ አለ፣ እንዲሁም አጥፊ።

እንደዚህ ብታስብ ኖሮ፣ የዛሬ አመት እንደዚህ ሳይሆን:
እኔ ሆረስ ኬረቴ ነኝ፤ ወደፊት ኢትዮጵያን የሚያስተዳድሩት ብልጽግና እና ኢዜማ ናቸው !!!
እንደዚህ ይሆን ነበር ሃሳብህ:
ብልጽግና የሚባል እምነት አልባ የጎሳ ጥርቅም!
ግን አመት አባከንክ

ለምን የዛሬ አመት የሚታወቅ ነገር አሁን ገና በራልኝ ብለህ ራስህን ጠይቅ። አትፍራ
Last edited by eden on 04 Feb 2022, 22:49, edited 1 time in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 30898
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: እኔ ሆረስ ኬረቴ ነኝ፤ ወደፊት ኢትዮጵያን የሚያስተዳድሩት ብልጽግና እና ኢዜማ ናቸው !!!

Post by Horus » 04 Feb 2022, 22:46

eden,

አንተ ዉሸታም ... ተመለስና ያልኩትን አንብብ? ሰነፍ ተማሪ!!

" ባለፈው ሰኔ ብልጽግና የእኔን ምክር ሰምቶ (የኔን መሰል አመለካከት ማለቴ ነው) ይበልጥ ሚዛናዊ የሆነ የጎሳ/የዜጋ ቅይጥ መንግስት አቁሞ ቢሆን ኖሮ ባሁኑ ወቅት ከዘመነ ጥፋት ወደ ዘመን ልማት መሸጋገር ጀምሮ ነበር ።"

ነጭ ዉሸታም :x :x

Educator
Member
Posts: 2004
Joined: 03 Jun 2021, 00:14

Re: እኔ ሆረስ ኬረቴ ነኝ፤ ወደፊት ኢትዮጵያን የሚያስተዳድሩት ብልጽግና እና ኢዜማ ናቸው !!!

Post by Educator » 04 Feb 2022, 22:54

Eden, what a smart person you're. This Horus made me LMAO when he called the election, 70- 100 seats for Ezema..omg :mrgreen: :mrgreen: :mrgreen:
eden wrote:
04 Feb 2022, 22:35
Horus wrote:
04 Feb 2022, 16:43
የዛሬ አመት ያልኩትን ዛሬ
ሲጀመር ስተሽ ነበር፣ የዛሬ አመት

ያኔ ለምን ሳትኩኝ የሚለው ጥያቄ ላይ አተኩር። መልሱ ይጠቅምሃል፣ የዘንድሮ ስህተትህን ለመቀነስ

ስህተትን ሳያርሙ መንጎድ፣ ከእውነታ የባሰ መራቅ ነውና

ንገረኝ ካልክ፣ የሚታየኝን ልበል። አለምን ነጭና ጥቁር አርገህ ማየትህ ነው ችግርህ። የዜጋ ፖለቲካ አራማጆች መልአክ፣ የህብረብሄር ፖለቲካ አራማጆችን ደግሞ ሰይጣን አርገህ ነው የምታያቸው። እውነታው ግን አለም ግራጫ እንጂ ጥቁርና ነጭ አይደለችም። ከሁለቱም አሳቢ አለ፣ እንዲሁም አጥፊ።

እንደዚህ ብታስብ ኖሮ፣ የዛሬ አመት እንደዚህ ሳይሆን:
እኔ ሆረስ ኬረቴ ነኝ፤ ወደፊት ኢትዮጵያን የሚያስተዳድሩት ብልጽግና እና ኢዜማ ናቸው !!!
እንደዚህ ይሆን ነበር ሃሳብህ:
ብልጽግና የሚባል እምነት አልባ የጎሳ ጥርቅም!
ግን አመት አባከንክ

ለምን የዛሬ አመት የሚታወቅ ነገር አሁን ገና በራልኝ ብለህ ራስህን ጠይቅ። አትፍራ

Horus
Senior Member+
Posts: 30898
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: እኔ ሆረስ ኬረቴ ነኝ፤ ወደፊት ኢትዮጵያን የሚያስተዳድሩት ብልጽግና እና ኢዜማ ናቸው !!!

Post by Horus » 04 Feb 2022, 23:08

eden/Educator ፌክ ስም እየለዋወትክ ትመጣለሕ...
አው ኢዜማ ከ70 እስከ 100 ወንበር እንዲያሸንፉ ፈልጌ ተስፋ አድረጌ ነበር፣ አሁን ያለው አይነት ምስቅልቅል እንዳይፈጠር ። ያ ሆኖ ቢሆን 200፣000 ትግሬ አይሞትም ያ ሁሉ ያማራ ውድመት አይኖርም ነበር . አንተ የፖለቲካ መሃይም ! ኢዜማ እራሱ በዚያ ደረጃ መሸነፉ ራሱን አስገርሞታል !!! ግ ን ምንድን ነው ውጤቱ የዛሪው መሰረቱ የጠበበ የቀውስ መንግስትና የፈረስርች ትግሬ ነው ትርፉ ... ዱቄት ባመድ ይስቃል !!!

Abere
Senior Member
Posts: 11096
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: እኔ ሆረስ ኬረቴ ነኝ፤ ወደፊት ኢትዮጵያን የሚያስተዳድሩት ብልጽግና እና ኢዜማ ናቸው !!!

Post by Abere » 05 Feb 2022, 12:30

ሆረስ፤

--- በወያኔ ጦርነት ያለቀውን የትግሬ ቁጥር ትክክለኛ መረጃ ያለህ አልመሰለኝም። ወያኔ በቅርቡ እራሱ በጅምላ መርዶ ሪፓርት ያደረገው 300,000 ነው። በገለልተኛ ጥንቅር እና ሳታቲስቲካል ጥናት መሰረት ግን 900,000 ይደረሳል እየተባለ ነው። ወያኔ ያመነቺው 1/3ኛውን ብቻ ነው።

--- ዋናው ቁም ነገሩ የጎሳ ፓለቲካ እናት የሆነችው ትግራይ በእራሱ በጎሳው ጭራቅ 1 ሚልዮን ትግሬ አስበልታለች ማለት ነው - ቢያንስ 35% ከአጠቃላይ የትግሬ ኗሪ።
---የጎሳ ቅይጥ ፓርቲ ምና ምን የሚባል ነገር አገሪቱ አያስፈልጋትም። ጎሳ የሚባል ፓለቲክ በአለም ላይ የለም - ትግሬ ውስጥ ብቻ ነው ያለው፡ It is endemic to Tigray። የጎሳ ድርጅት የመረዳጃ እና የጎሳው የእድገት በጎ አድራጎት ሊሆን ይችላል። For instance, the Traditional Gurage Self-help organizations to the extent during the Emperor's era built roads and highways. እንጅ የእንትና ጎሳ ለዛኛው ለእንትና ጎሳ ምን የፓለቲካ አላማ አለው - ልቅማህ ለእኔ ብቻ እንጅ - የጋራ ሰዋዊ የሆነ አላማ የለውም - እንሰሳዊ እና ደመ-ነፍሳዊ ነው። የአውሬ መንጋ መገለጫ ነው። አገሪቱ በርዕዮተ አለም ላይ የተመሰረተ ዜጎች በማህበራዊ፥ኢኮኖሚያዊ እና ፓለቲካዊ ቅርጽ እና ይዘት ላይ ባላቸው የአዋጭነት አመለካከት የሆነ እንጅ በጎሳ ላይ የተመሰረተ ሰዋዊ ያልሆነ ግዑዝ ላይ አይደለም።

---የጎሳ ፓለቲካ እና መንግስት ሙሉ በሙሉ ከኢትዮጵያ መጥፋት እና ህገ-ወጥ መደረግ አለበት። ከዚህ በላይ ዕብደት ምን ይባላል - ከአመት በላይ ድፍን አለም በኢትዮጵያ ውርደት ሳቀ - ምስጋና ለትግሬ ወያኔዎች።

Horus wrote:
04 Feb 2022, 23:08
eden/Educator ፌክ ስም እየለዋወትክ ትመጣለሕ...
አው ኢዜማ ከ70 እስከ 100 ወንበር እንዲያሸንፉ ፈልጌ ተስፋ አድረጌ ነበር፣ አሁን ያለው አይነት ምስቅልቅል እንዳይፈጠር ። ያ ሆኖ ቢሆን 200፣000 ትግሬ አይሞትም ያ ሁሉ ያማራ ውድመት አይኖርም ነበር . አንተ የፖለቲካ መሃይም ! ኢዜማ እራሱ በዚያ ደረጃ መሸነፉ ራሱን አስገርሞታል !!! ግ ን ምንድን ነው ውጤቱ የዛሪው መሰረቱ የጠበበ የቀውስ መንግስትና የፈረስርች ትግሬ ነው ትርፉ ... ዱቄት ባመድ ይስቃል !!!

Horus
Senior Member+
Posts: 30898
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: እኔ ሆረስ ኬረቴ ነኝ፤ ወደፊት ኢትዮጵያን የሚያስተዳድሩት ብልጽግና እና ኢዜማ ናቸው !!!

Post by Horus » 05 Feb 2022, 15:14

አበረ፣
የጎሳ ፖለቲካ ተሸንፎ የዜጋ መንግስት የምንፈልገው ክፍሎች አንድ ድምጽ ይዘን እስካልቆምን ድረስ የጎሳ አገዛዝ ምንም አይነካውም ። ባለፈው ምርጫ ቢቻል ቢቻል ቅይጥ አገዛዝ ማቆም ነበረብን! አልሆነም! ያ የሆነው በዜጋ ቋንቋ የሚነገሩት ሁሉ የዘር ፖለቲካ አስሊዎች ነበሩ! ዛሬም ያለው ነው ! ይህ ያለፈው 30 አመት ታሪክ ነው ! ገና ቢያንስ ለ10 አመት ይቀጥላል። ይህ ሁሉ በሚቀጥለው ድርድር ይታያል!

Post Reply