Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

"ግን ይሄ ጦርነት መቆም አለበት። የዱሮው ሰላም መመለስ አለበት። ሰላም እንዲመጣ መታረቅ ግድ ይላል። እርቅ ደግሞ ማንንም አያረካም።"

Post by sarcasm » 02 Feb 2022, 21:49

#ከላይ

By Eyob Mihreteab Yohannes


ከአመት በላይ ቆየ ይሄ የአሁኑ፤ የኔና የአንተ ትውልድ - ያንቺና የሱ - የኛ ዘመን መተላለቅ። . . . እኛ 'የህልውና ጦርነት፣ ኢትዮጵያን ሊያፈራርሷት ነው የሚወጉን' እንላለን። እነሱም 'የExistential ጉዳይ ነው፣ ዘራችንን ከምድረ ገፅ ሊያጠፉት ነው የሚወጉን' ይላሉ።
¤
ሁለቱም የቡድን አባቶች ጀሌዎቻቸውን 'ሊፈጁህ ተነሱብህ' ብለውታል። እንጂ በስልጣን ተጣላን አይሉትም። 'በቀደም ለታ እኮ አብረን አገር ስንመራ ነበረ፤ አሁን በገዢነት የሼር ድርሻ ስላልተግባባን ነው የተጣላነው' አይሉትም።

ማን ጀመረው? ምን ፈየደ? ምነው ባልተዋጋን ኖሮ? ለምን ሊስማሙ አልቻሉም? አሰልቺ፣ አዝግ፣ የተበላባቸው የካርታ ቁማር ካርዶች ናቸው - እርሳቸው።

¤
(ግን ግን ግን)

¤
ግን ይሄ ጦርነት መቆም አለበት።
የዱሮው ሰላም መመለስ አለበት።
ሰላም እንዲመጣ መታረቅ ግድ ይላል።
እርቅ ደግሞ ማንንም #አያረካም።

¤

እርቅና ድርድር (Negotiation) በባህሪው ሁለቱም ወገኖች የሆነ ነገር #አጥተው፣ አሳጥተው የሚታረቁበት አካሄድ ስለሆነ የሁለቱንም ጀሌ አንጀት አያርስም።
(ልንታረቅ ግን ግድ ይለናል)

'መንግስት ሽብርተኛ ብሎ ከፈረጀው ቡድን ጋራ እንዴት ይነጋገራል? ይሄ ሁሉ ሰው ሞቶ ለምን እንታረቃለን? ለዚህ ነው ወይ የተዋጋነው? ይሄንን ካስመለሱማ ሞተናል ማለት ነው!!!' ወዘተ. . . የስሜታዊ ሰው፣ የአላዋቂ ሰው፣ ተጨባጭ ሁናቴን ያልተረዳ፣ Pragmatic ያልሆነ እልኸኛ ሠው ንግግሮች ናቸው።

¤

[እና እንቀጥል ወይ ውጊያውን?]

(አንድ)

በጦርነቱ ከቀጠልን አሜሪካንን ጨምሮ፣ ምእራባውያን ብድርና እርዳታ መስጠት ያቆማሉ። የከፋ የኢኮኖሚ ማእቀብ ይጥሉብናል። እንደዛ ከሆነ ደግሞ ስድስት ወርም እንደ አገር አንቆይም። ሰርተንና በቂ አምርተን ሳይሆን ፈልጠንና ቀፍለን የምንኖር ሕዝቦች ነና። (ጥሬ ሐቅ!) የበቀደሙ የአጎአ ማእቀብ በራሱ አንድ ሚልዮን ሰዎችን ስራ አጥ አድርጓል። ከዛ ውጪ የአሜሪካ ብድርና የእርዳታ መጠን ቀነሰ፣ እንዲሁም የተወሰኑ ስማቸው ያልተነገረን ባለስልጣናት አሜሪካ እንዳይመጡ ታገደ - እንጂ ሌላ እርምጃ አልተወሰደብንም። ግን ደግሞ ይሄ እኮ የአሜሪካን የቅጣት እርከን ላይ ጢኒጢዬው ቁንጠጣ ነው፣ ዋናው ጥፊ አይደለም። . . . ኧረ ገና ነው እሱ! 😁😁

(ሁለት)

የWar Time Economy በተፈጥሮው አድቃቂ ነው። ያቀረጫል። ያገረጣል። ያመነምናል። ያጠወልጋል። ይቦጠቡጣል። ያዛባል።
አርሷደር ተረጋግቶ ማረስ አይችልም። እህል እንደልብ አይመረትም። ሚልዮኖች ተፈናቅለው የአገር ሸክም ይሆናሉ። የመሳሪያ ግዢ ወጪ እጅግ ውድ ነው - በዶላር ነው። ጦርነት ማለት ቁጭ ብሎ ዶላር መቅደድ በለው። በዛ ላይ ቱሪስትና ኢንቨስተር ድርሽ አይሉም። አበዳሪ ፊቱን ያዞራል። ነጋዴ እንደልቡ እቃ በየክልሉ አይልክም፣ አይቀበልም። አይገዛም አይሸጥም።

¤
በዚህም ኑሮ ይወደዳል። እንኳንስ ጦርነት ይዞት፣ ከዛም በፊት ኢኮኖሚውን አዝረክርኮ የያዘ፣ በአስፈሪ የሙስና ኔትዎርክ የተወረረ መንግስት ነው - ብልጽግና። ስለዚህ በዚህ ከቀጠልን ኑሮና የዋጋ ተመን አሁን ካለው በእጥፍ እንደሚጨምር አትጠራጠር። ያውም በቅርቡ።

¤

(BBC ዳታ አጣቅሶ እንዲህ ይልሃል)
''Ethiopia's overall economic growth for this year is forecast to slow significantly from 6% in 2020 to just 2% in 2021 - the lowest level in almost two decades, according to the IMF.
The country imports about $14bn of goods per year, while it exports just $3.4bn.
Also worrying economic observers is Ethiopia's national debt, which some expect to reach $60bn this year, or nearly 70% of GDP.

"This is a conservative estimate," says Ms Erasmus, adding Ethiopia's military spend could be higher than forecast, and it has taken on unreported debt in the past.''

¤
በሌላ አማርኛ - ባለፉት ሃያ ምናምን አመታት ያላየኸው የከፋ ድህነት ውስጥ ልትገባ ነው እያለህ ነው፣ ያውም በConservative Estimate.

(ይሄን)

ይሄንን የምልህ፣ በጦርነቱ ስለሚፈጠር የሰው ሞትና የአካል ጉዳት ትቼ፤ ወይንም በዛ በኩል ትግራይ ክልል ላይ ያለን ረሃብ እና በረሃብ ሳቢያ በየቀኑ የሚረግፈውን ኢትዮጵያዊ ሳላነሳ አልፌው ነው።
¤
(እና)

¤
እና በምን ሒሳብ ነው ሊታረቁ ነው ሲባል እፎይ ማለት ሲገባን ኡኡ የሚባለው?! '' . . . ይሄ ሁሉ ግፍ ተፈጽሞ፣ ሰው ሞቶማ አንታረቃትም!'' እንዴት ያለ የቂል ድንፋታ ነው? ሌላም አገር ተዋግቶ፣ ከዛም ታርቆ ያውቃል እኮ። እኛም ከዚህ በፊት ተዋግተን፣ ከዛም ታርቀን እናውቃለን። እና - ደርሶ ዘራፍ ዘራፍ ወግ ነው?
¤

(ታሪክን እናጣቅስ)
“. . . ጠላሁት” ይልሃል ንጋቱ ቦጋለ (ሻለቃ) በዛ፣ ስለ ደርግ vs ተገንጣይና አስገንጣይ ወንበዴዎች ጦርነት ታሪክ በጻፈበት ዝነኛው መጽሃፉ። ይህቺን አናቅጽ ቆርጬ አመጣሁልህ።

¤
“ጠላሁት። ወታደርነትን ጠላሁት፡፡ ሃገሪቱ ጦርነት ውስጥ ሆና መኮንን ሆኜ የውትድርና ህይወት ጀመርኩ፡፡ ለነገሩ የተወለድኩትም በጦርነት ዘመን ውስጥ ነው፡፡ እኔ ስወለድ ኤርትራ ውስጥ የርስ በርስ ጦርነት ተጀምሯል፡፡ “ማርያም በሽልም ታውጣሽ” ብሎ እናቴን መርቆ ከወጣ በኋላ ውትድርና ተቀጥሮ ኤርትራ የገባው አጎቴ ሻምበል ማዕረግ ደርሶ እዚያው ኤርትራ ውስጥ እስከሞተ ድረስ ከጦርነት ውስጥ አልወጣም ነበር፡፡ በጦርነት ዘመን የተወለድኩት እኔም አጎቴን ለመጨረሻ ያገኘሁት ኤርትራ አልጌና ግንባር ነው፡፡ የአንድ ትውልድ ጦርነት አባትና ልጅን ጦር ሜዳ ላይ አገናኘን፡፡

ከኤርትራ ወጥቼ ትግራይ ከገባሁ በኋላ የከፋ እንጂ የተሻለ ነገር አልገጠመኝም ነበርና እዚያው ትግራይ ውስጥ ሆኜ ከባለቤቴ ጋር ተጋባን፡፡ የመጀመሪያ ልጃችንን ስሟን “ሠላም” ብዬ ጠራኋት፡፡ ነፍሴ ሠላምን አጥብቃ የምትሻበት ወቅት ነበር፡፡ ሠላም እንዴት ሊመጣ እንደሚችል ባላውቅም ሠላምን እመኝ ነበረ፡፡”
-
[ሻለቃ ንጋቱ ቦጋለ፡“ትውልድ ያናወጠ ጦርነት” (አዲስ አበባ፡ 2001 ዓ.ም)፡ ገጽ 230]

(እና)

ከበቀደሙ ስህተታችን መማር አቅቶን እንዲህ እየተባላን፣ እየተጋደልን፣ ወታደርና ሲቪል እየቀበርን፣ እየተላለቅን እንቀጥል ነው የምትለኝ? በድንቁርናችን የደገምነውን ''#ሠበብ ፈጥሮ የመተላለቅ'' እሽክርክሮሽ፤ ተቧድኖ የመወጋጋትና የጦርነት ቅሌታችንን አናቁመው ወይ? . . . ለመሆኑስ - ይሄ ጦርነት ለዚህ ባለ ዲግሪና ለእናቱ ምናቸው ነው?
¤

[. . . እኔ ምለው ፈጣሪ ከላይ ረግሞን ይሆን እንዴ?]
Please wait, video is loading...