Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Wedi
Member+
Posts: 7993
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

አማራ ህዝብ ዋና ጠላቶች እነዚህ ተላላኪ ብአዴን ናቸው!! እነዚህን ተላላኪዎች የአማራ ህዝብም ሆን ታሪክ ይቅር አይላቸውም!!

Post by Wedi » 29 Jan 2022, 19:08

የአማራ ህዝብ ዋና ጠላቶች እነዚህ ተላላኪ ብአዴን ናቸው!! እነዚህን ተላላኪዎች የአማራ ህዝብም ሆን ታሪክ ይቅር አይላቸውም!![/color]

ግርማ ካሳ

ፋኖ ትጥቅ እንዲፈታ እናደርጋለን ያሉ፣ ሲሞክሩ የነበሩት እነዚህ ናቸው። ሕወሃትና ኦነጎች በስፋት እየተንቀሳቀሱ ባሉበት፣ ስንት አገር እያጠፋ ኢመደበኛ አደረጃጀቶችቾ በኦሮሞ ክልል እያሉ፣ የነርሱ ነገር ሳያሳስባቸው፣ ከወያኔና ኦነግ ሕዝብን ለመታደግ ሲፋለሙ የነበሩ፣ የህዝብ ደጀንና አለኝታ የሆኑትን ፋኖዎች ግን እንደ ጠላት በመቁጠር በነርሱ ላይ በዚህ መልኩ ነው ሲመክሩ የነበሩት።

እዚህ ጋር ልብ እንድትሉ የምፈልገው በቀይ ያከበብኳቸውን ነው። ስለዚህ ዶር አብይ አህመድ፣ ሺመልስ አብዲሳ እየተባለ ማለቃቀስ ከዚህ በኋላ መቆም አለበት። ከነሺመልስ አብዲሳ አስር እጥፍ በሕዝቡ ሕይወት ቁማር እየተጫወቱና እየቀለዱ ያሉት የአማራ ብልጽግና ከፍተኛ አመራሮች ራሳቸው ናቸው።

ኦነግም ሕወሃት፣ ሸኔ፣ አብይ፣ ወዘተ ማለት ይቁም። ከነርሱ ባልተናነሰ ህዝብን እየበደሉ ያሉት፣ ይቅርታ ይደረግልኝና የአማራ ብልጽግናዎች ራሳቸው ናቸው።

ይሄንን ስል፣ "ተው ፣ አማራውን አትከፋፍሉ" የሚሉ አሉ። እንደዚያ እየተባለ ነው ግማሹ የአማራና የአፋር ክልል እንዲወድም የተደረገው።[
/size]


[facebook]https://www.facebook.com/ggkd60/posts/10226674111829705[/facebook]