Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Axumezana
Senior Member
Posts: 13224
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

ማህበረ፥ ቅዱሳንና፥ ዳንኤል፥ክብረት፤

Post by Axumezana » 27 Jan 2022, 22:29

ከዚህ፥ በፊት፥ ማሕበረ፥ቅዱሳን፥ ሕብዑና፥ኢመደበኛ፥ በሆነ፥መዋቅሩ፥ጥንታዊትዋን፥ቤተክርስትያን፥ እንደሚቆጣጠራትና፥እንድሚዘውራት፥ይገለጽ፥ የነበረ፥ጉዳይ፥ነው።አሁን፥ደግሞ፥ከመንግስት፥ጋር፥ የስልጣን፥ተጋሪ፥ሆኖ፥ ለወደፊት፥"የሚያልማትን፥ ኢትዬጵያ"፥ ተግባራዊ፥ለማድረግ፥እዬታተረ፥ይገኛል።
ዳንኤል፥ክብረት፥የዚህ፥ድርጅት፥ፊተውራሪ፥ሲሆን፥ በሰላ፥ምላሱ፥በትግራይ፥ህዝብ፥ላይ፥የዘር፥የአስተሳሰብና፥ የታሪክ፥የማጥፋት፥ዘመቻ፥ ተጠናክሮ፥እንዲቀጥል፥እየሰበከና፥እያስተማረ፥ይገኛል። ይኸ፥ የዳንኤል፥ክብረት፥ኢክርስትያዊ፥ አስተምሕሮ፥የትግራይ፥ህዝብ፥ላይ፥ብቻ፥ያነጣጠረ፥ሳይሆን፥ በማንኛውም፥ እንቅፋት፥ብለው፥በሚፈርጁት፥ህብረተሰብ፤ የሀይማኖት፥ድርጅት፥ራሷን፥የኦርተዶክስ፥ቤተክርስቲያንን፥ ጨምሮ፥ ተራ፥በተራ፥ተግባራዊ፥የሚደረግ፥መሆኑ፥ ግልጽ፥ነው። ስለሆነም፥ሁላችንም፥ልንቃወመውና፥ልናስቆመው፥ይገባል።ዳንኤልም፥የጥላቻ፥ስብከቱን፥በንስሃ፥አቁሞ፥ የክርስቶስን፥የፍቅርና፥የምህረት፥ወንጌል፥ብቻ፥በተግባር፥እዬኖረበት፥እንዲያስተምር፥ እመክረዋሎሁ።
Last edited by Axumezana on 27 Jan 2022, 23:17, edited 5 times in total.

sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: ማህበረ፥ ቅዱሳንና፥ ዳንኤል፥ክብረት፤

Post by sarcasm » 27 Jan 2022, 22:49

sarcasm wrote:
21 Jan 2022, 08:43
Finfinne Times

"አብይ አህመድ"..."ማህበረ ቅዱሳን" .."ፖለቲካ" ... "ዳንኤል ክብረት"


የቀድሞ የኢህአዴግ ባለስልጣን የነበሩት በረከት ስምኦን ሲናገሩ ..."ከምርጫ ዘጠና ሰባት በኃላ ኢህአዴግ ከማህበረ ቅዱሳን ጋር እንደተደራደረና የማህበሩ አባላትንም በኢህአዴግ አባልነት እንደመለመለ ይገልፃሉ" ....

የዚህ ምክንያትን ሲገልፁ ...."በምርጫ 97 በሸገር ከተማ የቅንጅት ደጋፊዎች የነበሩት ወጣቶች አብዛኛዎቹ የማህበሩ አባላት ሊሆኑ እንደሚችሉ በማመን የተደረገ እንደሆነም ያትታሉ።

ለአብዛኛው ህብረተሰብ ያልተገለፀት ነገር ቢኖር ..."ማህበረ ቅዱሳን በምርጫ 97 ቅንጅትን እየጋለበ ቤተመንግሥት ለመግባት ተቃርቦ እንደነበር ነው። ማህበሩ ተራ አይደለም። እንደየ አስፈላጊነቱ በህቡዕ ተቋዋሚ ፓርቲዎች ብሎም የተለያዩ ሚዲያዎችን ያቋቁማል።

ይህ የሚደረገው የተለያዩ እቅዶችን በማውጣት ሲሆን .. የማህበሩ የጀርባ አጥንት የሆነውን በመንግሥት መዋቅር ያለውን ጠንካራ ህብዕ የቢሮክራሲ ሰንሰለት እንዳለ ሆኖ መሆኑ ይሰመርበት።

ኢህአዴግ በአንድ ወቅት ማህበሩን በሽብርተኝነት ለመክክስ ከፍተኛ እንቅስቃሴ ጀምሮ ነበር። ውሎ ሳያድር ግን ይህ ጅምር እንቅስቃሴ ሊቆም ቻለ። ለምን ክሱ እንደቆመ ግን እስካሁን አልተገለፀም።

አቡነ ማቲያስ በ2008 ለኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ብሎም ለተጠሪ ተቋማት በፃፉት ደብዳቤ ማህበረ ቅዱሳን በስራቸው ላይ ከፍተኛ ጫናና ተፅዕኖ እያሳደረባቸው መሆኑን ገልፀው ነበር።

እንደ አንዳንድ መፅሀፍት ገለፃ ከሆነ ... ማህበረ ቅዱሳን የሲንዶሱን እውቅና ያገኘው ያለውን ሀይል አሳይቶ እጅ በመጠምዘዝ እንጂ በውዴታ እንዳልነበር ይገልፃሉ። ይህንም ይላሉ የማህበሩን ሚስጥር የሚያውቁ አካላት ..."ይህንንም ድርጊት በኢህአዴግ ብሎም በብልፅግና ላይ ፈፅሞታል ብለው ይሞግታሉ።
ኢህአዴግ ተጠምዝዞ ብልፅግና ደግሞ ወዶና ፈቅዶ ይህንን ማህበር አስጠግተውታል። አብይ አህመድ ለማህበሩ ብሎም ለዳንኤል ያላቸው አክብሮት በነፃነት እንዲጋልቧቸው ምክንያት ሆኗል።

በተለይ የአብይ ንጉሰ ነገስት የመሆን ቅዥታቸው የአሃዳዊያን ቀልብ እንዲያርፍባቸው ሆኗል። ነግሰው መቀባትን ያልማሉ ሰባተኛው ንጉስ። እነ ዳንኤል ክብረት ደግሞ ንጉሱን ቀቢ ናቸው።


የሆነው ሆኖ የማህበሩ ቁልፍ ሰው ዳንኤል ክብረት ነው። የተጠለፈው ትግል በሚለው መፅሀፍ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት አራት ኪሎ ቤተመንግሥት ሲገባ ያለውን ተጨባጭ አቅም አሳይቶ እንደሆነ ይተርካል።

ሰውየው ተራ አይደለም። በማህበሩ የአመታት እንቅስቃሴዎች የተለያዩ ፖለቲካዊ ጥቅሞችን ለማስከበር አያሌ ሙከራዎችን አድርጓል። በአገዛዝ መዋቅሩ እጅግ ጠንካራ ፓርቲ የነበረውን ኢህአዴግ በምርጫ 97 በሴራም ይሁን በተግባር መጠምዘዝ እንደቻለ መታወቅ አለበት።

የቄሮ ትግል መጠለፉ አንዱ ምክንያት የነ ዳንኤል ክብረት ቡድን በቤተመንግስቱ ዙሪያ በማድፈጡ የተነሳ ነው። በአንድ ጀንበር የቄሮ ትግል አልተጠለፈም።
ለአመታት ሁሉን አቀፍ ዝግጅት ባደረጉ አሃዳዊያን በተጠና መንገድ እንደተጠለፈ የተለያዩ መከራከሪያዎችን እየተነተኑ ማቅረብ ይቻላል። (ይህንን ሌላ ጊዜ በሰፊው እመለስበታለሁ)

ዳንኤል ክብረት ለአመታት ውስጡ ሲብላላ የነበረውን የብሔረሰቦች ጥላቻ ብሎም የሀይማኖትን ፅንፈኝነት አንግቶ በሚኒሊክ ቤተመንግሥት ውስጥ ቁልፍ ቦታን ይዟል።

ይህ ስልጣን የማማከር የመጠቆም አቅጣጫ የማሳየት .. ለመንግሥት ባለስልጣናት ስልጠናን የመስጠት .. አስተሳሰብን የመጫን .. የሀገሪቱን ፖለቲካ ሂደት ግንባታ የማቀናበርን ..በፈለጉት ቅርፅ የማስኬድ ወዘተ .. ቦታዎችን ያጠቃልላል።

አሁን ላይ ማህበሩ በህቡዕ ይዟቸው የነበሩ የመንግስት ቢሮክራሲዎችን በይፋ እየተጠቀመ ነው። ለአመታት ውስጣቸው ሲቀጣጠል የነበረውን ጥላቻ በአደባባይ ዘርግፈውታል። ለዘመናት እነሱ ሲያስቧት የነበረችውን አሃዳዊ ኢትዮጵያን ለመገንባት ቆርጠው ተነስተዋል።

በዚህ ሁሉ መንገድ የኦህዴድ ፈረሶች ለግልቢያ ምቹ በመሆን ታሪካዊ አጋሰስነታቸውን አስመስክረዋል። ነገር ግን የሚኒሊኳና የማህበረ ቅዱሷ ኢትዮጵያ በፍፁም አትመለስም !!!

Finfinne Times


https://www.facebook.com/permalink.php? ... 1731586155



sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: ማህበረ፥ ቅዱሳንና፥ ዳንኤል፥ክብረት፤

Post by sarcasm » 27 Jan 2022, 23:11

ዳንኤል ክብረት generation


Post Reply