Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Post Reply
Abere
Senior Member
Posts: 10852
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

የሆረስን እንቆቅልሽ ጥያቄ: < ሰዶ ማሳደድ ካማረህ፤ ዶሮህን በቆቅ ለውጥ> አብይ አህመድ ያገኘውን የህዝብ ድጋፍ ጥሎ፤ ከምዕራባዊያ ጋር በጓሮ በር ውል አድርጎ ባዶ እጁን ስለ መቅረቱ ነው

Post by Abere » 27 Jan 2022, 18:08

የሆረስን እንቆቅልሽ ጥያቄ ሳንሞክር: < ሰዶ ማሳደድ ካማረህ፤ ዶሮህን በቆቅ ለውጥ።> እኔ ግን አብይ አህመድ ያገኘውን የህዝብ ድጋፍ ጥሎ፤ ከምዕራባዊያን
ጋር በጓሮ በር ድብቅ ውል አድርጎ ባዶ እጁን ስለመቅረቱ ነው ባይ ነኝ። አብይ አሁን ባዶ ቀርቷል የአማራን፥አፋርን፥ጉራጌን፥ሶማሌን ወዘተ ድጋፍ አጥቷል። ኤርትራም እንድሁ የረሳችው ይመስለኛል። ከሩቅ ዘመድ የቅርብ ጎረቤት ይሻላል ትሉ ዘንድ ምዕራባዊያን ባህር አቋርጠው ይረዱኛል የሚል የቂል ሂሳብ ሰርቶ ከጥፋት ሃይል ወያኔ ጋር በመደመሩ - በሬ ሆይ ሳሩን አየህ እና ገደሉን ሳትይ እራሱ እየተረከ እራሱ ዘሎ ገደል ገባ ባይ ነኝ። ኢትዮጵያን በምዕራባiውያን የለወጠው ማሞ ቂሎ (መሽረፈት) የከሰረ ዐረብ ሁኖ በታል ፓላቲካው።

ሆረስ፤ አገር ስጠኝ አልልም ኢትዮጵያ አለችኝ (ደግሞ ሰድጀ አላሳድድም -ጎመን በጤና) :lol: ልክ ከሆንኩ ወይም ወደ መልሱ ከተቃርብኩ ጠቁመኝ ብቻ

Wedi
Member+
Posts: 7936
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: የሆረስን እንቆቅልሽ ጥያቄ: < ሰዶ ማሳደድ ካማረህ፤ ዶሮህን በቆቅ ለውጥ> አብይ አህመድ ያገኘውን የህዝብ ድጋፍ ጥሎ፤ ከምዕራባዊያ ጋር በጓሮ በር ውል አድርጎ ባዶ እጁን ስለ መቅረቱ

Post by Wedi » 27 Jan 2022, 19:14

Abere wrote:
27 Jan 2022, 18:08
የሆረስን እንቆቅልሽ ጥያቄ ሳንሞክር: < ሰዶ ማሳደድ ካማረህ፤ ዶሮህን በቆቅ ለውጥ።> እኔ ግን አብይ አህመድ ያገኘውን የህዝብ ድጋፍ ጥሎ፤ ከምዕራባዊያን
ጋር በጓሮ በር ድብቅ ውል አድርጎ ባዶ እጁን ስለመቅረቱ ነው ባይ ነኝ። አብይ አሁን ባዶ ቀርቷል የአማራን፥አፋርን፥ጉራጌን፥ሶማሌን ወዘተ ድጋፍ አጥቷል። ኤርትራም እንድሁ የረሳችው ይመስለኛል። ከሩቅ ዘመድ የቅርብ ጎረቤት ይሻላል ትሉ ዘንድ ምዕራባዊያን ባህር አቋርጠው ይረዱኛል የሚል የቂል ሂሳብ ሰርቶ ከጥፋት ሃይል ወያኔ ጋር በመደመሩ - በሬ ሆይ ሳሩን አየህ እና ገደሉን ሳትይ እራሱ እየተረከ እራሱ ዘሎ ገደል ገባ ባይ ነኝ። ኢትዮጵያን በምዕራባiውያን የለወጠው ማሞ ቂሎ (መሽረፈት) የከሰረ ዐረብ ሁኖ በታል ፓላቲካው።

ሆረስ፤ አገር ስጠኝ አልልም ኢትዮጵያ አለችኝ (ደግሞ ሰድጀ አላሳድድም -ጎመን በጤና) :lol: ልክ ከሆንኩ ወይም ወደ መልሱ ከተቃርብኩ ጠቁመኝ ብቻ

Abere, I think we can get the answer here. He has explained it very well based on his vast foreign policies experiences.

Horus
Senior Member+
Posts: 30578
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የሆረስን እንቆቅልሽ ጥያቄ: < ሰዶ ማሳደድ ካማረህ፤ ዶሮህን በቆቅ ለውጥ> አብይ አህመድ ያገኘውን የህዝብ ድጋፍ ጥሎ፤ ከምዕራባዊያ ጋር በጓሮ በር ውል አድርጎ ባዶ እጁን ስለ መቅረቱ

Post by Horus » 27 Jan 2022, 19:45

አበረ፣
ተረቱ የድሮ ነው፤ 'ሰደህ ማሳደድ ካማረህ ዶሮህን በቆቅ ለውጣት' ያሉት የድሮ ብልሆች 'የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች' ወይም ፈረንጆች a bird in had is better than two in the bush እንደ ሚሉት ነው! እንደ ምታስተውለው በአቢይ ላይ ያለኝ ምሬት ያንተን አያክልም ። ይህች አገር በአብዮትና በትግል በጣም ስለደከመች! እኔ የተማሪ ንቅናቄ ስጀምር 8ኛ ክፍል ነበርኩ፤ ነገሩ አላልቅ አለ ። በእድሚዬ 3 መንግስት ተኩል ተቃውሜያለሁ !

እኔ የነአቢይን ባህሪና እርምጃ የምለካበት ለብዙ ዘመን የቀረጽኩት የኢትዮጵያ አጀንዳ አለኝ፤ እዚህ ፎረም ላይ ብዙ ብዙ ግዜ ፖስት አድርጌዋለሁ ። አንድ መሪን በዚያ አጀንዳ ሚዛን ላይ አስቀምጥና ድጋፍም ወቀሳም ቅዋሜም የማደርገው ። ሌላው መለኪያዬ የሚሆነው የሚመጣው ውይይት ነው ። ለሱም የራሴ አጀንዳ ነጥቦች አሉኝ ለውይይቱ መለኪያ ማለት ነው ።

የሰሞኑ የአቢይ ባህሪያት በተመለከተ ትልቅ ማሳያው ከዲያስፖራ ሚዲያዎች (50 ሚሆኑ) ጋር ለድፍን 5 ሰዓት ወይይትና ጥያቄና መልስ ማድረጉ ነው፤ አንዳንዶቹ እንቅልፍ እስከ ሚወሳዳቸው ድረስ! ይህ የሚያሳየው በችኮላ የወሰዳቸው እርምጃዎች ብዙ እንዳስከፈሉት ነው ። ከአሜሪካ፣ ቻይና፣ አፍሪካ ህብረት እና ከአረብ አገሮች የሚደርስበት የግፊት ልክ ምን ያህል እንደ ሆነ ባላቅም በኔ ግምት ባንዳዎቹን መፍታትቱ ላይ ግዙፉ ስህተቱ የሕዝቡን ስሜት መለካት አለመቻሉና ግልጽ ኮሚኒኬሽን አለማደጉ ነው ። በመሰረቱ ካማራም ጋር የገጠመው አጣብቂኝ በግልጽ ከህዝቡ ጋራ መነጋገር ኣለመቻሉ ነው ። እኔ ብዙ ቦታ እንዳልኩት ሰራዊቱ መሪነት በወያኔ ስር ነበር። እነዚያ ትግሬ አዛዦች መላ ሰራዊቱ እንዲማረክ አድረገው አፍርሰውት ነበር። ጁንታው አማራን የወረረው የኢትዮጵያ ጦር ትንሽ፣ ደካማና በባንዳ ሰላዮች ተቦርቡሮ ስለነበር ነው ። አቢይ ይህን ሃቅ እንደ ደበቀ አለ። ያ ሃቅ ላማራ ቢገለጽ አሁን ያለው አጣብቂኝ አይገባም ነበር።

የስብሃት መፍታትም እንዲሁ ። እከሌ እከሌ የሚባሉ አገሮች ይህን ይህን ውጥረት ውስጥ ስለከተቱኝ ይህን ለማድረግ ተገድጃለሁ ማለት አልቻለም! ይህ የሚያሳየው እሱም ሕዝቡን ሙሉ በሙሉ አያምንም፣ እዝቡም አሁን ቡሉ በሙሉ እሱን ስለማያምን ሁለቱም ባይነ ቁራኛ እይተጠባበቁ ነው ። ያለው ይህ ነው ።

እኔን እጅግ ያበሳጨኛ በጉጉት እየጠበቅኩት ያለ ያቢይ አቋም የኢትዮጵያን ህዝብ ሰንደቅ አላማ በሚመልከት ነው ። ያ ሆነ ብሎ ብልጽኛ አሁን ሕዝቡ በሆሆታ እየደገፈን ስለሆነ የነሱን ወያኔያዊ አይዲዮሎጂ ለማስረጽ ያደረጉት ስለሆነ ምንግዜም ይቅር የማይባል ነው ። ዞሮ ዞሮ ሺ ግዜ እንዳልኩት በጎሳ ፖለቲካና በዜጋ ፖለቲካ መሃል ያለው የዘመናት ትግል ነው ።

እናም በአቢይ ዘንድ የሆነ ጥድፊያ አለ! ለዚህ ነው ከስህተት ወደ ስህተት የሚዞረው ፤ ሌላ ግዙፍ ድክመቱ ያሻውን ነገር አድርጎ ህዝቡን ወደ ሃሳቤ የመሳብ ችሎታ አለኝ የሚል የተሳሳተ ሳይኮሎጂ ወስጥ የገባ ይመስለኛል ። ልብ በል የኢትዮጵያ ሕዝብ በአለም ላይ ለድፍን 50 አመት አለማቋረጥ የፖለቲካ ትግል እያደረገ ያለ ብቸኛ ህዝብ ነው ። ስለሆነም ብልጽኛዎች እንደ ትግሬዎቹ መሆን ካልፈለጉ መሬት ወርደው ህዝቡን ማዳመጥ ይኖርባቸዋል ።

በእኔ መለኪያ መሰረት ኢትዮጵያን የሚጠቅም የማይጎዳ ነገር ሲያደርጉ በርቱ እላለሁ። ከኢትዮጵያ አጀንዳ ውልፍ ሲሉ እቃወማለሁ እተቻለሁ ። ቴዲ አፍሮ እንዳለው የምናፍቃት ኢትዮጵያ እስከ ምትጸና ደረስ !

ተረቱ አስቤበት ያልኩት ነው። ይሀው መንግስት በየቀኑ እዚም እዛም የስህተቱን እሳት ማጥፋት ላይ ነው የተጠመደው! አቢይ ኢትዮጵያዊያኖች እንዲያምኑት ከፈለገ በተረት፣ በሜታፎር መናገር አቁሞ ግልጽ በሆነ ቋንቋ ምን ማድረግ እንዳሰበ እና ለምን ለህዝቡ መግለጽ አለበት ። ሁሉን ነገር የሚደብቅ አንድም በሚሰራው ነገር ትክክለኛነት የማያምን አንድም ህዝቡን የማያምን መሪ ነው ። ሕዝብ ሁሉን ነገር ያቃል፣ እውነት ከተነገው ደሞ ይቅር ባይና ተባባሪ ነው ።
viewtopic.php?f=2&t=287716

Wedi
Member+
Posts: 7936
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: የሆረስን እንቆቅልሽ ጥያቄ: < ሰዶ ማሳደድ ካማረህ፤ ዶሮህን በቆቅ ለውጥ> አብይ አህመድ ያገኘውን የህዝብ ድጋፍ ጥሎ፤ ከምዕራባዊያ ጋር በጓሮ በር ውል አድርጎ ባዶ እጁን ስለ መቅረቱ

Post by Wedi » 27 Jan 2022, 20:55

Horus wrote:
27 Jan 2022, 19:45
የሰሞኑ የአቢይ ባህሪያት በተመለከተ ትልቅ ማሳያው ከዲያስፖራ ሚዲያዎች (50 ሚሆኑ) ጋር ለድፍን 5 ሰዓት ወይይትና ጥያቄና መልስ ማድረጉ ነው፤ አንዳንዶቹ እንቅልፍ እስከ ሚወሳዳቸው ድረስ! ይህ የሚያሳየው በችኮላ የወሰዳቸው እርምጃዎች ብዙ እንዳስከፈሉት ነው ። ከአሜሪካ፣ ቻይና፣ አፍሪካ ህብረት እና ከአረብ አገሮች የሚደርስበት የግፊት ልክ ምን ያህል እንደ ሆነ ባላቅም በኔ ግምት ባንዳዎቹን መፍታትቱ ላይ ግዙፉ ስህተቱ የሕዝቡን ስሜት መለካት አለመቻሉና ግልጽ ኮሚኒኬሽን አለማደጉ ነው ። በመሰረቱ ካማራም ጋር የገጠመው አጣብቂኝ በግልጽ ከህዝቡ ጋራ መነጋገር ኣለመቻሉ ነው ። እኔ ብዙ ቦታ እንዳልኩት ሰራዊቱ መሪነት በወያኔ ስር ነበር። እነዚያ ትግሬ አዛዦች መላ ሰራዊቱ እንዲማረክ አድረገው አፍርሰውት ነበር። ጁንታው አማራን የወረረው የኢትዮጵያ ጦር ትንሽ፣ ደካማና በባንዳ ሰላዮች ተቦርቡሮ ስለነበር ነው ። አቢይ ይህን ሃቅ እንደ ደበቀ አለ። ያ ሃቅ ላማራ ቢገለጽ አሁን ያለው አጣብቂኝ አይገባም ነበር።

Horus do you have link for that video/discussion? Pls post it here if you have seen it somewhere.
Thank you in advance!

Horus
Senior Member+
Posts: 30578
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የሆረስን እንቆቅልሽ ጥያቄ: < ሰዶ ማሳደድ ካማረህ፤ ዶሮህን በቆቅ ለውጥ> አብይ አህመድ ያገኘውን የህዝብ ድጋፍ ጥሎ፤ ከምዕራባዊያ ጋር በጓሮ በር ውል አድርጎ ባዶ እጁን ስለ መቅረቱ

Post by Horus » 27 Jan 2022, 22:12

Wedi wrote:
27 Jan 2022, 20:55
Horus wrote:
27 Jan 2022, 19:45
የሰሞኑ የአቢይ ባህሪያት በተመለከተ ትልቅ ማሳያው ከዲያስፖራ ሚዲያዎች (50 ሚሆኑ) ጋር ለድፍን 5 ሰዓት ወይይትና ጥያቄና መልስ ማድረጉ ነው፤ አንዳንዶቹ እንቅልፍ እስከ ሚወሳዳቸው ድረስ! ይህ የሚያሳየው በችኮላ የወሰዳቸው እርምጃዎች ብዙ እንዳስከፈሉት ነው ። ከአሜሪካ፣ ቻይና፣ አፍሪካ ህብረት እና ከአረብ አገሮች የሚደርስበት የግፊት ልክ ምን ያህል እንደ ሆነ ባላቅም በኔ ግምት ባንዳዎቹን መፍታትቱ ላይ ግዙፉ ስህተቱ የሕዝቡን ስሜት መለካት አለመቻሉና ግልጽ ኮሚኒኬሽን አለማደጉ ነው ። በመሰረቱ ካማራም ጋር የገጠመው አጣብቂኝ በግልጽ ከህዝቡ ጋራ መነጋገር ኣለመቻሉ ነው ። እኔ ብዙ ቦታ እንዳልኩት ሰራዊቱ መሪነት በወያኔ ስር ነበር። እነዚያ ትግሬ አዛዦች መላ ሰራዊቱ እንዲማረክ አድረገው አፍርሰውት ነበር። ጁንታው አማራን የወረረው የኢትዮጵያ ጦር ትንሽ፣ ደካማና በባንዳ ሰላዮች ተቦርቡሮ ስለነበር ነው ። አቢይ ይህን ሃቅ እንደ ደበቀ አለ። ያ ሃቅ ላማራ ቢገለጽ አሁን ያለው አጣብቂኝ አይገባም ነበር።

Horus do you have link for that video/discussion? Pls post it here if you have seen it somewhere.
Thank you in advance!
Wedi,
Of course, the event was closed to public and no phone etc. So there is no record or video of it but Syoume Teshome has gathered pieces from the participants and had interesting video presentation on on 1/24 which I had attached to the following post on mine. Now I just discovered that the video is removed! viewtopic.php?f=2&t=287716

Post Reply