Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30849
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የታቀደው ብሄራዊ ውይይት አጀንዳዎች ምን መሆን አለባቸው?

Post by Horus » 25 Jan 2022, 23:10

አራት ዋና ዋና ጉዳዮችን ያካትታል።
አጀንዳ አንድ፤ ሕዝብ፣ አገር፣ መንግስት
(1) የኢትዮጵያ ሕዝቦች ሳይሆን የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲባል መስማማት፤
(2) የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰንደቅ አላማ አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ መሆኑን መወሰን፤ ሌሎች ሰንደቆች የግል፣ የፓርቲ፣ የሪጅን፣ የቤተ እምነት ያሻቸውን ምልክት ማውለብለብ እንዲችሉ መስማማት፤
(3) የጎሳ ክልሎች በመልካምድር ክልል መለወጥ፤
(4) በጎሳ ላይ የተመሰረተ የፖለቲካ አደረጃጀት በሕግ መከልከል፣ ከፖለቲካ ውጭ ሰዎች በፈለጉት ሲቪል መደራጀት እንደ ሚችሉ መስማማት
(5) የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት ኮንትራት የጎሳ ስምምነት ሳይሆን የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደ ሉዓላዊ ግለሰብ ያቆሙት እንደሆነ መስማማጥ
(6) አንቀጽ 39 ን መሰረዝ
(7) የኢትዮጵያ ፌዴራሊዝም ከጎሳ ፌዴሬሽን ወደ ኢጎሳዊ እስትራክቸር መለወጥ፣ አስፈላጊ ከሆነ የባህልና ቋንቋ የበታች ምክር ቤት ለብቻ መፍጠር
(8) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ፌዴራል ተቋማት መከላከያ፣ ፖሊስ፣ ሴኩሪቲ፣ ልዩ ሃይሎች፣ ሚኒስቴሮች፣ ሹመቶች ሁሉ ከጎሳ ኮታ ቀመር ተወግደው በክህሎትና ሜሪት መሰረት ማቋቋም
(9) የክልል ጦር ሃይሎች ሁሉ ወደ ፌዴራል መከላከያ ተዋህደው፣ እንደ ኢትዮጵያ ሰራዊት አካባቢያቸውን እንዲጠብቁ መስማማት።

አጀንዳ ሁለት፤ ዴማክራሲ፣ ነጻነት፣ ፍትህ
(1) ኤትኖክራሲ ተሽሮ በዴሞክራሲ ለመተካት መስማማት፤

አጀንዳ ሶስት ፤ የመሬት ስሪት
(2) የመሬት ጥያቄን ላንዴም ለሁሌም መፍታት፣ የመሬት ስሪት ከጎሳ ባላባትነት አስወግዶ የግልና የሕዝብ ስሪት መለወጥ፤

አጀንዳ አራት፤ ቋንቋ፣ ባህልና እምነት
(1) መንግስት ከሃይማኖት ውጭ ማድረግ
(2) የቤተ እምነቶች መሬት ይዞታን መፍታት
(3) እያንዳንዱ ጎሳ ቋንቋውና ባህሉን እንዲያሳድግ መተው
(4) ፌዴራል መንግስት መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ እሴት ለሆኑ ካልቸራል አሴትና አሴቶች ብሄራዊ ድጋፍ እንዲሰጥ መስማማት ።

በቃ ከሞላ ጎደል እነዚህ ናቸው የብሄራዊ ወይይቱ አጀንዳዎች!

ሆረስ ነኝ

ethiopianunity
Member+
Posts: 9127
Joined: 30 Apr 2007, 17:38

Re: የታቀደው ብሄራዊ ውይይት አጀንዳዎች ምን መሆን አለባቸው?

Post by ethiopianunity » 25 Jan 2022, 23:49

Lame, instead of distracting with constucting buildings and Diais, noth not priority things, why not mobilize the people to get rid of Tplf and control Tigray? Because yiu cant develop in the middle of war. Guess that wont happen coz Eritrea/foreigners will not allow it?

kibramlak
Member
Posts: 2155
Joined: 26 Sep 2013, 09:27

Re: የታቀደው ብሄራዊ ውይይት አጀንዳዎች ምን መሆን አለባቸው?

Post by kibramlak » 26 Jan 2022, 00:53

Horus wrote:
25 Jan 2022, 23:10

አጀንዳ አንድ፤ ሕዝብ፣ አገር፣ መንግስት

(2) የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰንደቅ አላማ አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ መሆኑን መወሰን፤ ሌሎች ሰንደቆች የግል፣ የፓርቲ፣ የሪጅን፣ የቤተ እምነት ያሻቸውን ምልክት ማውለብለብ እንዲችሉ መስማማት፤
ፖርቲዎች ፣ የእምነት ተቋማት እና ማንኛውም የአሰተዳደር አካል (ክልል ከቆየ ክልሎች) በመሰረታዊው ሰንደቅ አላማ ላይ አርማቸውን ቢያስቀምጡ አንድ ቤዝ ያለው የሀገር ሰንደቅ አላማ ይሆናል፣፣ ካለዛ እንደምታየው የጎጥ ባንዲራ ለጎሳ ነጋዴዎች የማያባራ ግጭት መቀስቀሻ መሳሪያ ነው የሆነው፣፣

(3) የጎሳ ክልሎች በመልካምድር ክልል መለወጥ፤
(4) በጎሳ ላይ የተመሰረተ የፖለቲካ አደረጃጀት በሕግ መከልከል፣ ከፖለቲካ ውጭ ሰዎች በፈለጉት ሲቪል መደራጀት እንደ ሚችሉ መስማማት
ቁ3 የኦሮሚያ ሰዎች እንዲሆን አይፈልጉም፣፣ በዚህም ምክንያት ቁ4 ን ለመተግበር አስቸጋሪ ይሆናል፣፣ ይህም ለወደፊት ጦርነት ምክንያት ሊሆን ይችላል

(8) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ፌዴራል ተቋማት መከላከያ፣ ፖሊስ፣ ሴኩሪቲ፣ ልዩ ሃይሎች፣ ሚኒስቴሮች፣ ሹመቶች ሁሉ ከጎሳ ኮታ ቀመር ተወግደው በክህሎትና ሜሪት መሰረት ማቋቋም
አሁን ያሉት ባለስልጣኖች በሙሉ ከጎሳ የፀዱ አይደሉም ፣፣ ይህ biase ቢያንስ ለሁለት generation ይቆያል፣፣
(9) የክልል ጦር ሃይሎች ሁሉ ወደ ፌዴራል መከላከያ ተዋህደው፣ እንደ ኢትዮጵያ ሰራዊት አካባቢያቸውን እንዲጠብቁ መስማማት።
መፐወዝ ይኖርባቸዋል

አጀንዳ ሁለት፤ ዴማክራሲ፣ ነጻነት፣ ፍትህ
(1) ኤትኖክራሲ ተሽሮ በዴሞክራሲ ለመተካት መስማማት፤
አሁን ያሉት ባለስልጣኖች በሙሉ ከጎሳ የፀዱ አይደሉም ፣፣ ይህ biase ቢያንስ ለሁለት generation ይቆያል፣፣
አጀንዳ ሶስት ፤ የመሬት ስሪት
(2) የመሬት ጥያቄን ላንዴም ለሁሌም መፍታት፣ የመሬት ስሪት ከጎሳ ባላባትነት አስወግዶ የግልና የሕዝብ ስሪት መለወጥ፤
ያላግባብ መሬት የወሰዱ መነጠቅ አለባቸው፣፣ እና እንዳስፈላጊነቱ ለማህበራዊ አገልግሎት እንዲውል ማድረግ

ይህን ካልኩ፣ አሁን ተሰየሙ የተባሉት 25 አወያዮችን ስብጥር ስናይ ተስፋ የሚሰጥ አይመስልም ፣ ፣ አክራሪ ሙስሊም ኦሮሞወች ይበዛሉ፣፣ ከ70℅ በላይ ይሆናሉ ፣፣ ይህም ብዙ ነገር ያመለክታል ፣፣ ኢትዮጵያን ወደከፍታ ማማ ወይስ ኦሮሙማን ? እምናየው ይሆናል

Horus
Senior Member+
Posts: 30849
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የታቀደው ብሄራዊ ውይይት አጀንዳዎች ምን መሆን አለባቸው?

Post by Horus » 26 Jan 2022, 01:13

Kibramlak,

ያነሳሃቸው ችግሮች ባይኖሩማ መች ይህ አገራዊ ዉይይት ያስፈልግ ነበር?! ግን ልብ በል እነዚህ አጀንዳዎች እስካልተፈቱ ድረስ የኢትዮጵያ ሕዝብም ትግሉን አያቆምም፣ የጎሳ ከበርቴዎችም ሰላም አያገኙም! የውይይቱ አላማ ያ ነው። የምር ከተባለ ግን ችግሩም የሚፈታው ቢያንስ ለ5 እስከ 10 አመት ሁለተኛ ሎወር የታች ምክር ቤት ለጎሳው ጎራ ቢፈጠርለት ነው። ከዚያም አገሪቱ አንድ ሰው አንድ ድምጽ የሚመርጠው ፕሬዚዳንታዊ ስርዓት ነው የሚያስፈልጋት!

Post Reply