Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30847
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ትላልቅ ካልቸራል ትዕይንቶች ዝርዝር

Post by Horus » 25 Jan 2022, 04:27

መስቀል (አገር አቀፍ)
ጥምቀት (አገር አቀፍ)
አረፋ (አገር አቀፍ)
መውሊድ
ኢድ አልፋጢር
ኢሬቻ (ኦሮሚያ)
ጨምበለላ (ሲዳማ)
አሸንዳ
አዊ እንጅባር የፈረስ በዓል
የጣና ጀልባ ውድድር
ገና ጨዋታ
አዳብና (ጉራጌ)
ታላቁ ሩጫ (አ አ)
የአድዋ ቀን (አ አ )

ጨምሩበት
Last edited by Horus on 26 Jan 2022, 16:06, edited 3 times in total.

kibramlak
Member
Posts: 2155
Joined: 26 Sep 2013, 09:27

Re: በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ትላልቅ ካልቸራል ትዕይንቶች ዝርዝር

Post by kibramlak » 25 Jan 2022, 04:44

የጣና ጀልባ ውድድር (ባህርዳር፣ ከአገር አቀፍ እስከ አለማቀፍ ሊሄድ የሚችል)
ገና ጨዋታ (መሃል ሸዋ) I think ሌላው አማራ ክልልም አለ
የአድዋ ቀን (አ አ )፣ አገር አቀፍ ግን ትዕይንቱ አአ
አሸንዳ (ጎንደር እና ወሎንም ይጨምራል)

ሌላ፣
ፋሲካ (አገር አቀፍ)
የፈረስ ጉግስ ትዕይንት (ከጥምቀት ጋር)

Horus
Senior Member+
Posts: 30847
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ትላልቅ ካልቸራል ትዕይንቶች ዝርዝር

Post by Horus » 25 Jan 2022, 05:05

kibramlak wrote:
25 Jan 2022, 04:44
የጣና ጀልባ ውድድር (ባህርዳር፣ ከአገር አቀፍ እስከ አለማቀፍ ሊሄድ የሚችል)
ገና ጨዋታ (መሃል ሸዋ) I think ሌላው አማራ ክልልም አለ
የአድዋ ቀን (አ አ )፣ አገር አቀፍ ግን ትዕይንቱ አአ
አሸንዳ (ጎንደር እና ወሎንም ይጨምራል)

ሌላ፣
ፋሲካ (አገር አቀፍ)
የፈረስ ጉግስ ትዕይንት (ከጥምቀት ጋር)
አው ቦታውን ማስታወስ አልቻልኩም እንጂ ወደ ምንጃር ወይም አንኮበር ገና ጨዋታ አለ ። በአምቦ ወሊሶ አካባቢ እንዳለ አውቃለሁ፣ አከባበሩ ከቦታ ቦታ ይለያያል ለዚህ ነው በጥቅሉ መሃል ሸዋ ያልኩት ። የአሸንዳ እርማት እቀበላለሁ በጎንደርና ወሎ መኖሩን አላቅም ነበር ። በትግራይና ወሎ ድምበር ያሉት ወደ ሰቆጣ አካባቢ ያየሁ ይመስለኛል ። አሸንዳ ከጉራጌ አዳብና ጋር ተመሳሳይ ነው ። አዳብና የወንድም የሴትም በዓል ነው ። ወንዶች በአሸንዳ መካፈላቸውን አላቅም ።

ኢትዮጵያ ብዙ ሃይቆችና ወንዞች አሏት፣ የዉሃ እስፖርቶች መጀመር አለብን ። ብዙ ተራራዎች አሉን የተራራ እስፖርቶች መጀመር አለብን!

የፈረስ እስፖርት ጉግስም ሆነ አክሮባት (ሶምሶማ፣ ደንገላሳ፣ ስግሪያ) አገር አቀፍ ውድድር ወይም ቶርናመንት ማድረግ ይቻላል!!

Guest1
Member
Posts: 1926
Joined: 28 Dec 2006, 01:02

Re: በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ትላልቅ ካልቸራል ትዕይንቶች ዝርዝር

Post by Guest1 » 25 Jan 2022, 06:32

አገር አቀፍ
1 መውሊድ
2 ኢድ አልፋጢር
3 የባንድራ ቀን ቀረንዴ?
በአንድ አገር አገራዊ በዓል ብቻ ይከበራል። ሌሎች ጥቃቅቹ ባህላዊ እሽክርክሪቶች እንደ ብሄሮቻችን ብዛት ብዙ ናቸው። የገረመኝ አፋርና ሶማሌዎች የራሳቸው የተለየ በኣል አለመኖር ብቻ ነው።

በአንድ አገር ውስጥ ባህልና ልዩነት ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ጉዳይ ነው። አሜሪካኖች እንግሊዞች ቻይናዎች እንኳን አንድ መልክ ኖሯቸው አንድ አይነት ባህል የላቸውም። የህንዶችማ የጉድ ነው። ለወደፊቱም እንደየ አገሩ አዲስ ባህልም መፈጠሩ የማይቀር ነው። አያስገርምም።

ድሮም የነበሩ ባህሎችን እየቀሰቀሱ፤ አዲስም እየፈጠሩ፤ የነበረውን እየሰረዙ የባህል ልዩነትን ማጋነን እንደሆነም ሁሉም የተማረውም ያልተማረውም ያውቃል። ይህም ሆኖ ባህል አያበላም አያጠጣም? ማን ይብላ? GDፕን ማየትና እንዴት የአንድ አገር ሃብት እንደሚከፋፈል ማየት ነው። አሃ! ባጀት! አሃ! ብላብላብላ ክክክክ

ባህል አያበላም አያጠጣም። የተፈለገውን ያህል ቢጨፈር ቢዘፈን ሃብትም በባህል ቢከፋፈልም የሰው ልጅ ነጻ የሚሆነው መሰረታዊ የሆነ ፍላጎቱ ሲሟላ ብቻ ነው። ምግብ፤ ቤት፤ ልብስና የሚጠብቀው መንግስት ሲኖረው ብቻ። ይህ ሲሆን ሌላው ሁሉም እንደችሎታው የስራውን ማግኘቱ አይቀርም። በአገራችን ልዩ የሆነው (አፍሪካ
ብለን ብናጠቃልለው) እንደብሄርም መሰረታዊውን አላገኘም። እንደችሎታውም የማያገኝበት ሁኔታ ተፈጥሯል። መንግስት የለም ማለት አይደለም?

ምነው ሽዋ! ቀዝቀዝ በል! ፡)

Horus
Senior Member+
Posts: 30847
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ትላልቅ ካልቸራል ትዕይንቶች ዝርዝር

Post by Horus » 25 Jan 2022, 13:07

የመእሊድና የኢድ ትክክል ነህ ። የባንዲራ ቀን ይቆይ? ገና ብሄራዊ ስምምነት እንኳ አልደረስንም! እኔ ሳየው ከሚያስጠላኝ ነገር ያ የመለስ ባለ ፔንታግራም ባንዲራ ነው እንኳንስ የፌስቲቫል ምልክት ሊሆን።

በተረፈ እነዚህ በአላት ሶሺያ ፕራክቲስ ይባላሉ፤ የራሳቸው የተለያየ ሃይማኖታዊ፣ ሶሺያል፣ ፖለቲካል፣ ሳይኮሎጂካል ዋጋ አላቸው ። ዛሬ ደሞ ከቱሪዝም እና ለበአላቱ ከሚሰሩ ሸቀጥና ምግብ አልባሳት ጋር ስለተያያዙ ግዙፍ የኢኮኖሚ ፋይዳል አላቸው ። እያንዳንዱ ጎሳ እነዚህ በአላት በዩኔስኮ ለማስመዝገብ የሚለፋውኮ ቱሪስት ለመሳብ ነው። ችግሩ ባህሎቹና በአሎቹ መብዛት አይደለም፣ መደራጀትና መዋብ አለባቸው! ኤስተቲክስ ወይም ስነ ዉበት የሚባል ሳይንስ ሳይንስ ወደ ኢትዮጵያ መስረጽ አለበት!

Abere
Senior Member
Posts: 11070
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ትላልቅ ካልቸራል ትዕይንቶች ዝርዝር

Post by Abere » 25 Jan 2022, 13:18

ሆረስ፤
ከይቅርታ ጋር አንዳንዶች በበርካታ ክፍለ ሀገራት ስለሚከበሩ ስማቸውን በቅንፉ ውስጥ በመጨመር በቀይ ቀለም ተመልክተዋል።
Horus wrote:
25 Jan 2022, 04:27
መስቀል (አገር አቀፍ)
ጥምቀት (አገር አቀፍ)
አረፋ (አገር አቀፍ)
መውሊድ
ኢድ አልፋጢር
ኢሬቻ (ኦሮሚያ)
ጨምበለላ (ሲዳማ)
አሸንዳ (ትግራይ፥ወሎ፥ጎንደር)
አዊ እንጅባር የፈረስ በዓል
የጣና ጀልባ ውድድር
ገና ጨዋታ (መሃል ሸዋ፥ወሎ፥ጎንደ)
አዳብና (ጉራጌ)
ታላቁ ሩጫ (አ አ)
የአድዋ ቀን (አ አ )
---ቡሄ (ወሎ - እስላም ክርስቲያኑ ያከብረዋል፤ የጅራፍ ወይም ግርፊያ ትርዒት- አሁን የቀረ ባህላዊ ትርዒት ነው)
--ቅዱስ ዮሀንስ ( እዮሀ ደመራ እና ችቦ ትርኮሳ)

ጨምሩበት

Horus
Senior Member+
Posts: 30847
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ትላልቅ ካልቸራል ትዕይንቶች ዝርዝር

Post by Horus » 25 Jan 2022, 14:21

አበረ፣
ገና በሃይማኖታዊ አከባበሩ እና በልዩ ልዩ ዘፈኖች ያለውን ሳይሆን ህጻናቶችና ወጣቶች በዱላ ሜዳ ላይ በባህል የሚጫወቱትን ተራ በተራ እለጥፋለሁ ፣ አንተም ቪዲዮች ካሉህ ለጥፋቸው ።

አክሊል ምሁር በሚባለው ጉራጌ ያለው ይህን ይመስላል



ይህ ጨዋታውን ፕሮፌሽናል ለማድረግ የሚደረግ ነው ልክ እንድ ኳስ ማለት ነው



ይህ ደሞ ሃዲያ አካባቢ ያለው ነው
Last edited by Horus on 25 Jan 2022, 14:55, edited 2 times in total.

Abere
Senior Member
Posts: 11070
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ትላልቅ ካልቸራል ትዕይንቶች ዝርዝር

Post by Abere » 25 Jan 2022, 14:40

የተቀረጸ ቪድዮ ካገኘሁ ለመለጠፍ እፈልጋለሁ። ግን እኔ በደንብ አውቃለሁ። ልጆች በእነኝህ አካባቢዎች ልክ የመኸር እህል በህዳር ወር መሰብሰብ ሲጀምር የእህል ማሳ ላይ ከተነሳ ጀምሮ ልጆች እሩር እና ሽልም ገና አዘጋጅተው ከወር በላይ ገና ይጫወታሉ። በተለይ የታህሳስ ወር ሲገባ በሰፊ ሜዳ ላይ የየመንደሩ ጎበዛዝት ጥንግ ከጠፍር ሰርተው ሙግ እየገጠሙ ሆታ /ድንበር/ አበጅተው ይጫወታሉ። ህጻናት እና ወጣቶች አንድ ላይ አይጫወቱም፤ ህጻናቱም በጎን ከአቻቸው ጋር ይጫወታሉ። ጥንጓን ያሆተው ቡድን የገና ሆታ አሲና በል ይላላ - በአብዛኛው ግን ተቃራኒውን ቡድን በማንኳሰስ እና በማብሸቅ ነው። የዋናው ገና እለት ድግስ ይቀርባል ሽማግሌዎች ይመርቃሉ። በዛን እለት አዋቂዎች የቤት እንሰሳት ይጠብቃሉ ልጆች አዲስ የተገዛላቸውን ልብስ ለብሰው ሽልም ገና ይዘው ገና መምቻ ሜዳ ይሄዳሉ። ልጆች መኸር እንደ ተሰበሰበ በጉጉት የሚጠብቁት በአል ነው - እስከ ጥምቀት ድረስ ይጫታሉ። በከተራ ቀንም ገና ጫወታ አለ- ታቦት ሲነሳ ደግሞ የፈረስ ሽምጥ ግልቢያ ውድድር አለ። የማን ፈረስ ቀደመ ቀደመ አይነት። ባህሉ በሁሉም ዘንድ ይከበራል።
Horus wrote:
25 Jan 2022, 14:21
አበረ፣
ገና በሃይማኖታዊ አከባበሩ እና በልዩ ልዩ ዘፈኖች ያለውን ሳይሆን ህጻናቶችና ወጣቶች በዱላ ሜዳ ላይ በባህል የሚጫወቱትን ተራ በተራ እለጥፋለሁ ፣ አንተም ቪዲዮች ካሉህ ለጥፋቸው ።

Abere
Senior Member
Posts: 11070
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ትላልቅ ካልቸራል ትዕይንቶች ዝርዝር

Post by Abere » 25 Jan 2022, 14:58

ሆረስ፤

በጣም የሚደንቅ ባህል ነው። የሚገርመው ደግሞ ሺ ዘመን በብዙ መልኩ በሁሉም ኢትዮጵያዊ ዘንድ ተጠብቆ መኖሩ። በዚህ መልኩ አልጠበቅኩም ነበር። ድንቅ ነው። በአጋጣሚ ቪድዮ ሳፈላልግ ሰሜን ወሎ ስታይሽ አካባቢ የተቀረጸ አገኘሁ፡ ግን ብዙም ሰፊ ዝርዝር የለውም። ለማንኛውም ግን በገጠሩ ህዝብ ዘንድ በደንብ ይጫወቱታል።




Horus wrote:
25 Jan 2022, 14:21
አበረ፣
ገና በሃይማኖታዊ አከባበሩ እና በልዩ ልዩ ዘፈኖች ያለውን ሳይሆን ህጻናቶችና ወጣቶች በዱላ ሜዳ ላይ በባህል የሚጫወቱትን ተራ በተራ እለጥፋለሁ ፣ አንተም ቪዲዮች ካሉህ ለጥፋቸው ።

አክሊል ምሁር በሚባለው ጉራጌ ያለው ይህን ይመስላል


Horus
Senior Member+
Posts: 30847
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ትላልቅ ካልቸራል ትዕይንቶች ዝርዝር

Post by Horus » 26 Jan 2022, 15:47

አበረ፤

በጣም ጥሩ! ይህ የመጀመሪያዬ ነው ይህን ሳይ! ችግሩኮ የኮሚኒኬሽን ችግር ነው ። ብሎግ አድራጊዎች ይህን መሰል ኮንቴንት እንደ መዘገብ የራሳቸውን ቲርኪ ሚርኪ ነው የሚያሳዩን! Thank you.

Post Reply