Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የጎሳ ፊውዳሊዝም እና መሬት ለዜጋ ጥያቄ

Post by Horus » 21 Jan 2022, 10:29

የኢትዮጵያ ካንሰር የጎሳ ፖልቲካ ነው! ኢትዮጵያን የሚያወድማት የብሄር ጥያቄ ነው! ለምን?

የንጉስና የዘውድ ስልጣን ለዜጋዎች እንደ መስጠት ለጎሳ የዘር መሳፍንቶች ስለሰጠ።

የዘውድና ባላባቶች ግላዊ ንብረት የነበረው የኢትዮጵያ ምድር፣ እግዚአብሄር የፈጠረው የኢትዮጵያ መሬት ነጻ አውጪ ለሚባሉ የጎሳ መሳፍንት ግላዊ ንብረት በማድረግ የኦሮሞ መሬት፣ የአማራ መሬት፣ የትግሬ መሬት ወዘተ ብሎ መሬት ላራሹ የሚለው ፍትሃዊ ጥያቄን ጠልፎ የጎሳ ሌቦችና ግፈኞች መፈልፈያ ቆሻሻ የጦርነትና ቀውስ ረግረግ ስለፈጠረ።

በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ምን ግዜም ለማያበቃው የጎሳና ጎሳ ጦርነት መፍለቂያ ቆሻሻ ረግረግ፣ ኢትዮጵያን አለ ጥርጥር የሚደመስሰው የጎሳ መሬት ጥያቄ ነው። አብዮቱ መሬት ለአራሹ አልሰጠም ።

የመሬት ጥያቄ በብሄር ጥያቄ ተጠልፎ መሬት ላራሹ ለግለሰብ ገበሬ ሳይሆን መሬት ለመንግስት በመስጠት አዲስ የጎሳ ፊውዳሊዝም መሰረተ ።
የጎሳ መንግስት የመሬት ባለቤት ሆኖ ዛሬ ያለው አለምንም ጥርጥር የጎሳ ፊውዳሊዝም ነው።

በዛሬይቱ ኢትዮጵያ አንዴ በትግሬ፣ አንዴ በኦሮሞ፣ አንዴ ባማራ፣ አንዴ በሱማሌ፣ አንዴ በመተከል እያለ የሚፈነዳው የጎሳዎች የመሬት ጦርነት የጎሳ ፊውዳሊዝም እና የጎሳ መሬት ባለቤትነ ጥያቄ እስካልፈረሰ ድረስ በኢትዮጵያ ዕከልዊ መንግስት አይጸናም።

አሁን ይደረጋል የሚባለው እድገት ብልጽኛም መሰረተ ቢስ የጎሳዎች መተላለቂያ፣ መጠፋፊያ አዲሱ የጎሳ ፊውዳሊዝም፣ የጎሳ ይገባኛል የጎሳ ዘመን መሳፍንት የማያባራ እርስ በርስ ጦርነት ነው ።

በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ሃይማኖት ግጭቶች የሚባሉት በጎሳ መንግስትና በሙስሊሞች፣ በጎሳ መንግስትና በኦርቶዶክክስ መሃል ያለውና የሚኖረው ትግልና ጦርነት ሁሉ ዋና መነሾው የመሬት ጥያቄ ነው፣ የጎሳ ፊውዳሊዝም ያመጣው በአንድ ጎሳ የመሬት ቁጥጥርና ባለቤትነት ነው ።

የቀራንዮ ክርስቲያኖች ደም የፈሰሰው በመሬት የጎሳ ፊውዳል መሳፍንቶች ፣ በጎሳ የመሬት ነጋዴዎች እጅ ነው።

አንድም የኢትዮጵያ ጎሳ ወይ ክላን የኢትዮጵያን መሬት አልፈጠረም! አንድም ጎሳ ይህ አገር የኔ ንብረት ነው፣ ይህ መሬት የኔ ጎሳ ሃብት ነው የማለት መብት የለውም ! ይህ ነው የጎሳ ፊውዳሊዝም ማለት ።

የትግሬ ጎሳ መሳፍንት ባረቀቁት ሕግና በነደፉት ባንዲራ ተሸፋፍኖ አዲስ ሊቦካ የሚሞከረው ብልጽግ ና በሚባል የዳቦ ስም የሚሞካሸው አዲሱ የጎሳ ፊውዳሊዝም ምንነት ኢትዮጵያዊያን ሁሉ በቶሎ እንዲቃወሙት እንዲያፈርሱት ግድ ይላል ።

ከ1966 ጀምሮ የሆነው ባጭሩ ይህ ነው ፤ መለኮታዊ ንጉሳዊ የዘውድ አገዛዝ በጎሳ በዘር መለኮታዊ አገዛዝ ተለወጠ። የንጉስ ዘር ስልጣን ከመለኮት ተገኘ ይባል ነበር ።

ዛሬ የጎሳ ዘር ስልጣንም ያው ምንጩ መለኮት ነው ። አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሰው፣ ህጋዊ ሰው ሳይሆን መለኮታዊ ጎሳ፣ መለኮታዊ ዘር ነው ። የጎሳ ዘር እግዚአብሄርን የሰራውን መሬት በጎሳ ፊውዳላዊ ክብረ ጎሳ ድንጋጌ የመሬት ባለቤት፣ የመንግስት ባለቤት፣ የኢኮኖሚ ማናምን እድገት ፎጋሪ ሆኖዋል።

ጎሳ ኢኮኖሚ አይገነባም፣ ግለሰቦች፣ ዘመናዊ ህዝቦች ናችው የስልጣኔ ፈጣሪዎች!!

ይህ ጸረ ጎሳ ፊውዳሊዝም ትግል ዛሬ መከሰቻው በመሬት ጥያቄ፣ በመንግስት ስልጣን እና በሰንደቅ አላማ ጥያቄ ላይ ተወጥሮ ይገኛል። ይህ ውጥረት የጎሳ ፊውዳሊም እስካለ ድረስ ፣ የጎሳ መሬት እስካለ ድረስ፣ የትግሬ ጎሳ ሰንደቅ እስካለ ደስ መላላት ሳይሆን እየተወጠረ ይሄዳል።

በ50 አመታት ትግል ያተረፍነው የዘውድ አገዛዝ በጎሳ አገዛዝ መተካቱ፣ የፊውዳል ባላባቶች መሬር ወደ ጎሳ መሳፍንቶች ባለቤትነት መሸጋገሩ እና የኢትዮጵያ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ መለያ በትግሬ ፔንታግራም ትርጉም የለሽ ምልክት መተካቱ ነው ።

ይህም በመሆኑ ኢትዮጵያ ለማያቋርጥ የዘር እና የሃይማኖት ጦርነት ተዳርጋ አለች !

ያለው መውጫ አንድ ቀዳዳ፣ አንድ መስኮት ነው ፤ የጎሳ ፊውዳሊአምን ማፍረስ፤ ያም ማለት ክልልና ያንድ ጎሳ መንግስት፣ ያም ማለት የጎሳ ኢኮኖሚ ብልጽኛ የሚባል ዘመናዊ ፊውዳል ስርዓትን ከስሩ መንቀል ነው ። ያ ሳይሆን ኢትዮጵያ የትም ፈቀቅ አትልም።

ሆረስ ነኝ

Last edited by Horus on 21 Jan 2022, 17:04, edited 2 times in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የጎሳ ፊውዳሊዝም እና መሬት ለዜጋ ጥያቄ

Post by Horus » 21 Jan 2022, 10:40




Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የጎሳ ፊውዳሊዝም እና መሬት ለዜጋ ጥያቄ

Post by Horus » 21 Jan 2022, 10:52


Abere
Senior Member
Posts: 10889
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: የጎሳ ፊውዳሊዝም እና መሬት ለዜጋ ጥያቄ

Post by Abere » 21 Jan 2022, 12:19

ሆረሰ፤

ጭራቁ የጎሳ ፓለቲካ ዜጎችን እየበላ የመኖር ዕድሉ ወደ ሚከስምበት የመጨረሻ የዕድገት ደረጃ ላይ ደርሷል። ይህን ያልኩበት ምክንያትም በአገራችን የከፋ ወረርሽኝ ደረጃ ላይ በመሆኑ የጎሳ አስተዳደር መወገዱ ግድ ብሏል። ኢ-ሳይንሳዊ እና ኢ-ስነመንግስት በመሆኑ ከሰብዓዊ እና ዘመናዊ ማህበረሰብ አኗኗር ጋር ስለማይሄድ እያስከፈለ ያለውም ዋጋ የሚልዮኖች ሞት እና የትሪሊዮን ሃብት ጥፋት ስለሆነ።በየትም የዓለም ክፍል የማይገኝ በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኘው ብቸኛ እና ብርቅየው አገር አጥፊ የጎሳ መንግስት ነው። ተነቅሎ መጣል አለበት።

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የጎሳ ፊውዳሊዝም እና መሬት ለዜጋ ጥያቄ

Post by Horus » 21 Jan 2022, 15:25

አበረ፤
በትክክል! ጎሳ የፖለቲካ ኮሚኒቲ ወይም ፖለቲካዊ ስርዓት ማደራጃ ጽንሰ ሃሳብ አይደለም፣ ሊሆን አይችልም ስንል ድፍን 30 አመት ሆነ። አሁን እንዲያውም የኢኮኖሚ ብልጽኛ መተግበሪያ ሞዴል ሊያደርጉት ይዳዳችዋል፣ ሃቁ የሚያሳየው ግን የዚህ ህሳቤ ውጤት ገምብቶ ማፍረስ ነው ። አንድ ነገር ላጫውትህ ። ወያኔ አዲስ አበባ ስትወር የዛሬ 30 አመት ጎሹ ወልዴ መድህን የሚባል ፓርቲ መስርቶ እካፈል ነበር። ስለ ዴሞክራሲ ጽንሰ ነገር ምርምር ስናደርግ አንድ ሃሳብ መጣልኝ ። ዴሞክራሲ የሕዝብ አገዛዝ ከሆነ የጎሳ አገዛዝ ኤትኖክራሲ መባል አለበት በሚል ሰርች ሳደርግ ያገኘሁት አንድ ስለ እስራኤል ጂዊሽ እስቴት የተጻፈ አርቲክል ብቻ ነበር ። አመቱን ባላስታውም ኤልያስ ክፍሌ መጽሄቱን ወደዚህ ፎረም ከለወጠው ጀምሮ በየግዜው የኢትዮጵያ አገዛዝ ኤትኖክራቲክ ሲስተም ነው እያልኩ አለሁ ። በትክክል በአለም ላይ ኢትዮጵያ የሚመስል የጎሳ የዘር ኤትኖክራቲክ እስቴት የለም ።

ዛሬ ያንተን ኮሜንት ሳነብ ያ ትዝ አለኝና ethnocracy ሚባለው ሃሳብ እንደ ገና በዊኪፒዲያ ስመለከት የሚከተለውን አገኘሁ ። ይህ የትግሬ ባንዳ የፈጠረው ሃሳብ ሙሉ ራሱን የቻለ ዊኪፒዲያ ይፈልጋል! በዚህ አርቲክል ወስጥ ኤትኖክራቲክ የሚባሉ አገሮች አንዳቸውም እንደ ኢትዮጵያ የከፋ፣ ቆሻሻና ደደብ ሲስተም የላቸውም ። ስለዚህ ይህ ሁሉ የሚገነባው ከተማ፣ ግድብ፣ ፎቅ፣ እና ፋብሪካ በጎሳ ጦርነቶች መፍረሱ አይቀሬ ነው የጎሳ ፊውዳሊዝምን እስካልደመሰስን ድረስ!

https://en.wikipedia.org/wiki/Ethnocracy

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የጎሳ ፊውዳሊዝም እና መሬት ለዜጋ ጥያቄ

Post by Horus » 21 Jan 2022, 16:16


Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የጎሳ ፊውዳሊዝም እና መሬት ለዜጋ ጥያቄ

Post by Horus » 21 Jan 2022, 17:08




Abere
Senior Member
Posts: 10889
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: የጎሳ ፊውዳሊዝም እና መሬት ለዜጋ ጥያቄ

Post by Abere » 21 Jan 2022, 18:09

ሆረስ፤

ትክክል ነህ የኢትዮጵያ ዓይነት የጎሳ መንግስት ስርዐት በዓለም ላይ በቅሎ አያውቅም። የተገድራ ስርዓት ነው- ከ30 አመታት ወድህ የገጠመን። ከማህበራዊ ህግጋት እና ሂደት የተለየ ስለሆነ ነው አሁን በአፍ ጢሙ እየተደፋ ያለው - የፈጠሩትን ሰዎች ሳይቀር ሲኦል ያወረዳቸው። እየተነገረው የማይሰማን ሲደርሰብት ሲኦል ይዞት ይሄዳል። ብዙ ቅን አገር ወዳድ ሰዎች አነተን የሚመስሉ ሁሉ 30 አመታት በላይ ጮኸዋል ይኸ ነገር አይሆንም ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅ እባካችሁ በኋል እልቂት ያመጣል እያሉ። ይኸው ዛሬ የአለም መሳቂያ መሳለቂያ ሁኑ - እራሱን የጎሳ ቅራቅንቦ ድጓስ የጻፉት እና የመሰረቱት። ዛሬ እነ ደብረጽዮን እጃቸውን ዘርግተው በጉልበታቸው ተንበርክከው አውሮፓ እና አሜሪካን አድኑን እያሉ ያነባሉ። ልጆቻቸው በአውሮፓ እና አሜሪካ አስፋልት ላይ እየተንከባለሉ በልብሳቸው አቦራ ይቅማሉ። ሰምተው ቢሆን ኑሮ ይህ አይሆንም ነበር። የሚያሳዝነው ግን አሁን የዝሆን ጆሮ የሰጣቸው መማር የማይችሉ ኦሮሙማ የሚባሉ ጀንፈሎች አሉ። እግዜር ምድርን ጠፍጥፎ ከላዩላይ ጽፎ ኦሮሞ ብሎ የሰጣቸው የሚመስላቸው - ገና ገና የዋሻ ዘመን ሰዎች በመሃል ከተማ ይኖራሉ፤የቤተ መንግስት አማካሪ ሁነው ተዘርፍጠዋል። የወያኔን ሪኮርድ ለመስበር የማይቧጥጡት ግድግዳ፥ከሰማይ በታች ኬኛ የማይሉት ነገር የለም። መጨረሻቸውን ለማየት ያብቃህ እውነት በጢምቢራቸው ደፍታ ትዘርራቸዋለች። አይሰሙም።
Horus wrote:
21 Jan 2022, 15:25
አበረ፤
በትክክል! ጎሳ የፖለቲካ ኮሚኒቲ ወይም ፖለቲካዊ ስርዓት ማደራጃ ጽንሰ ሃሳብ አይደለም፣ ሊሆን አይችልም ስንል ድፍን 30 አመት ሆነ። አሁን እንዲያውም የኢኮኖሚ ብልጽኛ መተግበሪያ ሞዴል ሊያደርጉት ይዳዳችዋል፣ ሃቁ የሚያሳየው ግን የዚህ ህሳቤ ውጤት ገምብቶ ማፍረስ ነው ። አንድ ነገር ላጫውትህ ። ወያኔ አዲስ አበባ ስትወር የዛሬ 30 አመት ጎሹ ወልዴ መድህን የሚባል ፓርቲ መስርቶ እካፈል ነበር። ስለ ዴሞክራሲ ጽንሰ ነገር ምርምር ስናደርግ አንድ ሃሳብ መጣልኝ ። ዴሞክራሲ የሕዝብ አገዛዝ ከሆነ የጎሳ አገዛዝ ኤትኖክራሲ መባል አለበት በሚል ሰርች ሳደርግ ያገኘሁት አንድ ስለ እስራኤል ጂዊሽ እስቴት የተጻፈ አርቲክል ብቻ ነበር ። አመቱን ባላስታውም ኤልያስ ክፍሌ መጽሄቱን ወደዚህ ፎረም ከለወጠው ጀምሮ በየግዜው የኢትዮጵያ አገዛዝ ኤትኖክራቲክ ሲስተም ነው እያልኩ አለሁ ። በትክክል በአለም ላይ ኢትዮጵያ የሚመስል የጎሳ የዘር ኤትኖክራቲክ እስቴት የለም ።

ዛሬ ያንተን ኮሜንት ሳነብ ያ ትዝ አለኝና ethnocracy ሚባለው ሃሳብ እንደ ገና በዊኪፒዲያ ስመለከት የሚከተለውን አገኘሁ ። ይህ የትግሬ ባንዳ የፈጠረው ሃሳብ ሙሉ ራሱን የቻለ ዊኪፒዲያ ይፈልጋል! በዚህ አርቲክል ወስጥ ኤትኖክራቲክ የሚባሉ አገሮች አንዳቸውም እንደ ኢትዮጵያ የከፋ፣ ቆሻሻና ደደብ ሲስተም የላቸውም ። ስለዚህ ይህ ሁሉ የሚገነባው ከተማ፣ ግድብ፣ ፎቅ፣ እና ፋብሪካ በጎሳ ጦርነቶች መፍረሱ አይቀሬ ነው የጎሳ ፊውዳሊዝምን እስካልደመሰስን ድረስ!

https://en.wikipedia.org/wiki/Ethnocracy

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የጎሳ ፊውዳሊዝም እና መሬት ለዜጋ ጥያቄ

Post by Horus » 04 Feb 2022, 17:46

ታሪክ የራሱ ዜማ አለው፣ ሂስትሪ ራይምስ ይባላል። ደሞ ታሪክ ሁልግዜ ራሱን ይደግማል! ቀን ቦታ ሁኔታ ይለየዋል እንጂ! ድሮ ስብሃት ነጋ ነበር ባንዲራ አትያዝ የሚል ፣ ዛሬ አቤቤ ነች! በቃ ! ታሪክ ይደጋገማል

Post Reply