Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 10894
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

ወሎ ህዝብ አሁን መልሱን አገኘኸው?ጀ/ል አበባው እውነቱን አፈረጠልህ።መከላከያ በሙሉ ኃይሉ ሲጠብቅ የነበረ የአፋር ሚሌ እና ጎንደር ሁመራ ኮሪደር እንጅ ወሎ በማፈግፈግ ላይ ያተኮረ ነበር።

Post by Abere » 21 Jan 2022, 10:12

ወሎ ህዝብ አሁን መልሱን አገኘኸው? ጀ/ል አበባው እውነቱን አፈረጠልህ።መከላከያ በሙሉ ኃይሉ ሲጠብቅ የነበረ የአፋር ሚሌ እና ጎንደር ሁመራ ኮሪደር እንጅ ወሎ በማፈግፈግ ላይ ያተኮረ ነበር። ወሎ ብቻውን ነበር 5 ወር የተዋጋው - ከትግሬ ወያኔ ጋር። ሌላው የሚገርመው ሀቅ መከላከያ የነበረ 40,000 ወታደር ብቻ ነበር። ታዲያ ቀሪው ወታደር የወያኔን 250,000 ሃይል ለመግጠም ከየት የመጣ ይመስልችኋል? የሂሳብ መኪናውን መደመር እና መቀነስ ለሚችል ሰው መልሱ ቀላል ነው። ከአማራ ህዝብ የአማራ ፋኖ እና ገበሬ ሚሊሻ። ነገርዮው በጨው ደንደስ በርበሬ ተወደስ ነው - መከላከያ አልነበረም የሚኮፈሰው በአማራ ሃይል ነው - ውሸታሙ ብልጥግና እና መከላከያ ግን ትንፍሽ አይሉም ሰለሰማእታቱም ዝና እንድዘከር አይፈልጉም። ይበልጡን ክህደታቸው አስቸገረህ። የጀ/ል አበባው ንግግር በርካታ ሃቅ ይዟል- ከበርከታወቹ ደግሞ መከላከያ የቱን ያህል የስነ-ምግባር ጉድለት እንዳለበት ነው የሚያሳየው የወሎን ህዝብ ሂሳብ እንድወራረድበት አሳልፎ በመስጠት ሙሉ ጊዜውን መከላከያ ጎንደር እና አፋርን ሲጠብቅ መክረሙ። የሚገርመው ደግሞ ህዝብ ሲያታልሉ መክረማቸው።