ያዲስ አበባ ፖሊስ በሉት ያዲሳባ ማዘጋጃ ምነው የቋንቋ አዋቂዎች ቢያማክሩ!
አንደኛ የዎያኔ ጸረ ኢትዮጵያ መንግስት ይህን የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ለማጥፋት ሲሞክር እራሱ ጠፍቷል!
ይህኛው ያቢይ መንግስትም ተመሳሳይ ስህተት ከመስራት ራሱን ይጠብቅ! ይህ ሰንደቅ አላማ አይለወጥም፣ አይጠፋም!!
የሆነው ሆኖ አርማ የሌለው ምን ማለት ነው? አርማ ማለት ምን ማለት ነው?
ሰንደቅ አላማ የሚለው ስም ከሁለት ቃላት የተሰራ ጽንስ ነው ። አንዱ ሰንደቅ ነው ፤ ሌላው አላማ ነው ።
ሰንደቅ ማለት ስነ ደቅ፣ ስነ ዲካ፣ ስነ ማሳያ ወይም አመልካች፣ ማሳያ ስልት፣ ማሳያ ዘዴ ማለት ነው ።
አርማ ማለት አላማ፣ መለያ፣ ማሊያ፣ መታወቂያ ማለት ነው ። ስለዚህ አርማ የሌለው ማለት መለያ የሌለው፣ መታወቂያ የሌለው ሰንደቅ ማለት ነው ። ይህ ትርጉም የለሽ አላዋቂ የሚለው ነገር ነው ። ባንዲራ ማለት አርማ ማለት ነው ። አላማ ማለት ነው ። አርማ ያንድ ነገር መለያ ቀለም ወይም መልክ ማለት ነው ።
ስለዚህ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርማ፣ ማሊያ፣ መለያ ቀለም ምልክት ራሱ ባንዲራው አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ነው ። ያ ነው አርማ የሚባለው።
ሰንደቅ ማሳየት፣ ስነ ደቂያ መምራት ማሳየት ማለት ነው ! ደቂቅ፣ ደቂቀ መምህር፣ ተከታይ፣ ተመሪ እንዲሉ ማለት ነው!
ስነ ደቅ ማለት ቀለም፣ አርማ፣ አላማ፣ መለያ ምልክት፣ ማሊያ ማለት አይደለም ። የባንዲራ ዋና ትርጉሙ ያለው አርማ የሚለው ላይ ነው ። ያ አርማ ፣ ያ መለያ ያለው ዎያኔ የለጠፈው ባይተዋር ፔንታግራም (አምስት ጫፍ ያለው ምስል) ሳይሆን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ህብረ ቀለም ነው!!!
ያዲሳባ ፖሊስ አርማ ያለው ሰንደቅ አላማ አትያዙ ሲል ቋንቋ አለማወቁን ነው የነገረን !! ያሳዝናል !! ዞሮ ዞሮ የኢትዮጵያ አርማ፣ የኢትዮያ ሕዝብ ማሊያ ምን እንደ ሆነ ሕዝቡ ያውቀዋልና ፖሊስ ከንቱ ልፋቱን ይርሳው እንላለን !!!!