**********************
የትምሕርት ሚኒስቴር በትምሕርት ጥራት ማስጠበቅን በተመለከተ ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ጋር እየመከረ ነው።
የትምሕርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኢትዮጵያ የትምሕርት ሥርዓት ግቦችና ይዘውት የመጡትን አዎንታዊና አሉታዊ ውጤቶች በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል።
ባለፉት ዓመታት የትምሕርት ሥርዓቱ ለሽፋን የሰጠውን ያክል ለጥራት ትኩረት አለመስጠቱ፣ ትምሕርት ቤቶች የፖለቲካ ማራመጃ ማዕከላት መሆናቸው፣ ብቁ ዜጋ ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ መፍጠራቸውን አንስተዋል።
በትምሕርት ሥርዓቱ አተገባበር ወጥነት አለመኖር፣ በግልና በመንግሥት የትምሕርት ተቋማት ላይ የትምሕርት አሰጣጥና አተገባበር መለያየት በተጨማሪም ችግር ፈች ዜጋ ለመፍጠር በሚደረገው ሂደት ላይ እንቅፋት እየፈጠሩ መሆኑን አብራርተዋል።
ሚኒስትሩ እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ ትምህርት ሚኒስቴር በሁሉም አካባቢዎች ጥራት ያለው ትምህርት እውን ለማድረግ እየሠራ እንደሚገኝ ነው የተናገሩት ሲል የዘገበው አሚኮ ነው።
"ሀገራችን ያሉ የከፍተኛ ትምሕርት ተቋማት ጥራት ያለው ትምሕርት በመስጠት ብቁ ዜጋ መፍጠር እስካልቻሉ ድረስ አዳዲስ ዩኒቨርሲቲዎች አንከፍትም" ሲሉም ለትምሕርት ጥራት በቀጣይ ሊሰጠው የሚችለውን ትኩረት አስረድተዋል።
የውይይቱ ተሳታፊ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ምሁራንም በትምሕርት ዘርፉ በሀገሪቱ ለዓመታት የዘለቀውን ችግር ለመቅረፍ ሚኒስቴሩ እያደረገ ያለውን ጥረት አድንቀዋል።
የሚታዩ ውስንነቶችን ለመቅረፍ የበኩላቸውን እንደሚወጡም አሳውቀዋል።
በውይይቱ የትምሕርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
Couldn't they improve quality and continue to extend the reach of universities in tandem, as in the rest of the world?
sarcasm wrote: ↑06 Jan 2022, 09:00
Prosperity Party's Library and TPLF's 52 Universities & 100,000 schools
የኢህአዴግ ትምህርትና የብልጽግና ላይብረሪ ወግ ....
By Finfinne Times
ኢህአዴግ 52 ዩኒቨርስቲዎችን ገንብቷል። በእነዚህ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ቢያንስ ከሶስት በላይ ትላልቅ ቤተመፅሀፍቶች ይኖሩታል። በመላው ሀገሪቱ የተገነቡ ቁጥራቸው ከ100 ሺህ በላይ የሚሆኑ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት አይረሱም።
በዘመነ ኢህአዴግ ከተሰሩ መሰረተ ልማቶች በተለይ በትምህርትና በጤና ዘርፎች የተከናወኑ ስራዎች አስደናቂ ነበሩ።
በ2010 አመተ ልደት በተደረገ ጥናት በኢትዮጵያ ከ30 ሚሊዮን በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ እንደሚገኙ ይፋ ሆኖ ነበር። በዘመነ ኢህአዴግ በተለይ ከ2003 በኃላ በአመት በአማካይ ከ100 እስከ 300 ሺህ ተማሪዎች ከመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች በተለያዩ ሙያዎች ተመርቀው ይወጡ ነበር።
ካለው የህዝብ ቁጥር ከተጨባጭ የሀገራችን ሁኔታ አንፃር የትምህርት ተደራሽነት ላይ ትኩረት አድርጎ ቀስ በቀስ ወደ ትምህርት ጥራት ማተኮር አስፈላጊ ነበር። ኢህአዴግም በጨለማው 27 አመታት ውስጥ ይህንን በተግባር አሳክቶታል።
በእነዚህ ሂደቶች የትምህርት ፖሊሲን ጨምሮ የገጠሙ የተለያዩ ችግሮች ቢኖሩም ለአንድ ሀገር የእድገት መሰረት የሆነው ትምህርት ላይ ታሪክ በፍፁም የማይረሳው ስራዎች ተሰርተዋል።
ኢህአዴግ መሃይም ያልተማረ ፥ የደነዘዘ ምንም አይነት ጠቀሜታ የሌለው ትውልድ አፍርቷል ብለው ጭፍኖች ሲናገሩ እገረማለሁ። ትምህርትን ያስፋፋና በነፃ ያቀረበ መንግስት ላይ ትውልድን በመግደል ሲታማ እስቃለሁ።
የትምህርት ጥራት ፖሊሲው ፥ የሚያጋጥሙ አሉታዊ ተግዳሮቶች .. ወዘተ ይኖራሉ። ነገር ግን እጁን እየቆጠረ ሂሳብ የሚሰራ ፥ ትምህርት ምን እንደሆነ የማይታወቅበት ፥ ትምህርት ቤቶች ያልነበሩት አካባቢዎች ላይ ቢያንስ ቢያንስ አንድ ትውልድ እስከ አስረኛ ክፍል እንዲማር አድርጓል።
በእርግጥ ኢህአዴግ ጥቂት የመሃል ሀገር ሰዎች ልብ ወለድ የሚያነቡበትና የሚዝናኑበት ላይብረሪ አልሰራም ይሆናል። ነገር ግን መላው የኢትዮጵያ ብሔረሰቦች እንዲማሩ ያስቻለ የትምህርት ተደራሽነትና የእውቀት አብርሆት እንዲፈነጥቅ ያደረገ አስደናቂ ስራዎችን ሰርቷል። ማንም ቢክድ ታሪክ ግን በፍጹም አይክደውም !!
Finfinne Times
Please wait, video is loading...