የጥቅሞች ዝርዝር
• የኢትዮጵያ ጥቅም፤ ይህ የኢትዮጵያ አጀንዳ የሚባለው ነው ። ኢትዮጵያን የአፍሪካ መሪ፣ የቀጠናችን ሃያል አገር፣ ብሄራዊ አንድነት፣ ጠንካራ መንግስት፣ ጠንካራ የጦር ሃይል፣ ዴሞክራሳዊ፣ የበለጸገች አገር ፣ ወዘተ ያካተተ ነው የኢትዮጵያ አጀንዳ።
• የመንግስት ስልጣን ላይ ያሉት ፓርቲዎች ወይም የነሱ የስልጣን ጥቅም ነው። ስለዚህ አቢይ ስልጣኑን በሌላ ስልጣን ፈላጊ ላለመነጠቅ መታገሉ የእሱን ክፉነት የሚያሳይ ሳይሆን የፖለቲካ ሳይንስ ህግ ነው ።
• የልዩ ልዩ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጥቅም
• የህዝብ የጋራ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ጥቅም
• የኦርቶዶክስ፣ የሙስሊምና የቴንጤዎች ጥቅም
• የትግሬ ጥቅም
• የአማራ ወልቃይትና ራያ ትቅም
• የልዩ ልዩ ጎሳዎች ክልል ጥቅም
• የአሜሪካ ጥቅም
• የቻይና ጥቅም
• የአውሮፓ ጥቅም
• የቱርክ ጥቅም
• የአረቦች ጥቅም
• የግብጽ ጥቅም
• የቀጠናው አገሮች ጥቅም
• የዲያስፖራ ጥቅም
የኢትዮጵያ ፖለቲካ የነዚህ ሁሉ ሰዋስው ነው ። በትንሹ እነዚህ 15 የጥቅም ቡድኖች የኢትዮጵያን ፖለቲካ በራሳቸው መነጽርና ከራሳቸው ጥቅም አንጻር ብቻ ሲመለከቱ ሁሉም እርስ በርስ የሚጋጩ፣ የሚቃረኑ ነገሮች ስለሆኑ እያንዳንዱ ቡድን ተነስቶ የእኔ ጥቅም ነው ከሁሉም የላቀውና ትክክል ቢል ትርፉ ቀውስ ብቻ ነው ። ይህን የእኔ ብቻ፣ እኔ ነኝ ባለጉልበት ወዘተ ትግሬዎች ሞክረውት ብዙ ደምና ሃብት አባክነው አሁን ወደ ምድራዊ ሃቅ እየወረዱ ነው ። የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሰዋስው እየገባቸው ነው ።
እኔ አሁን ባለው የአቢይ መንግስትም ሆነ ሌሎች ታላልቅ የፖለቲካ፣ ጂኦግራፊና ኢኮኖሚ ክስተቶችን ስናስተውል ቆም ብለን ምን ላይ ቆመን ነው ይህን የፖለቲካ ስዕል የምናየው እያልን መጠየቅና ማሰብ አለብን። ሁልግዜ ትክክለኛ አቋምና መልስ ላይ የሚወስደን ዘዴ የኢትዮጵያ ጥቅም፣ የኢትዮጵያ አጀንዳ፣ የኢትዮጵያ ፐርፐዝ መነጽር ነው!
የትግሉ ተዋንያን አሜሪካ ሆነ ቻይና፣ ቱርክ ሆነ ግብጽ፣ አማራ ሆነ ትግሬ፣ ኦሮሞ ሆነ ሱማሌ። ኤርትራ ሆነች ሱዳን ... ሁልግዜ መጠየቅ ያለብን ይህ ክስተት፣ ይህ ፖሊሲ፣ ይህ እርምጃ ለኢትዮጵያ አጀንዳ ምን ፋይዳ አለው ብለን እንጠይቅ!
- ኢትዮጵያን አንድ ያደርጋል ወይስ ይከፋፍላል?
ኢትዮጵያን ያጠነክራል ወይስ ያዳክማል?
አገራችንን ያረጋጋል ወይስ ያቃውሳል?
ዴሞክራሳዊ ነው ወይስ አምባገነናዊ?
ፍትሃዊ ነው ወይስ ኢፍትሃዊ?
ሕዝባችንን ያበለጽጋል ወይስ ያደህይል?
ወጣቱን ያስተምራል ወይስ ያደኖቅራል?
ለሰዎች ጤና ይሰጣል ወይስ ያሳምማል?
ካልቸራችንን ያለመልማል ወይስ ያፈርሳል?
መንፈሳዊ ሕይወታችንን ያጠነክራል ወይስ እምነት አልባ ሞራል አልባ ፍጡራን ያደርገናል?
ይህን መሰረታዊ እውነትና ሳይንስ ያልተገነዘቡ ናቸው በነሲብ እየተነሱ በጦርነትና በትግል ህይወትና ሃብታቸውን የሚያወድሙት!
ድንቁርና ያስከፍላል!
የኢትዮጵያን ፖለቲካ ሰዋስው ምን እንደሆነ መማር ለአንድ ፖለቲካ ሰው የፊደል ገበታን ይዞ ሃ ሁ ሂ ሃ ! አቡ ጊ ዳ እንደ ማወቅ ነው !
የአቢይ ባህሪም፣ የአሜሪካ ጨዋታም፣ የቻይና እርምጃም፣ ሌላውም ሌላውም በዚህ ሜቱዶሎጂ እንመርምር!
ኬር ዬሁን! ዬቦ!
በአ ሆረስ