አንዱ መልስ እየመረረን የዋጥነው ዉሳኔ ነው የሚል ነው ። ይህ ተገደን የወሰድነው ውሳኔ ነው የሚል ነው ። ማነው የሚትዮጵያ መንግስት ይህን ዉሳኔ እንዲወስድ ያስገደደው፣ ያምበረከከው ሃይል? ይህ አስገዳጅ ሃይል ማን እንደሆነ ለምንድን ነው ለህዝብ የማይገለጸው?
የዚህ ጥያቄ መልስ ... ጠቅላይ ሚንስትሩ ሁሌም እንደሚያደርጉት፣ እኛም ዘወትር እንደምናየው "
እኔ ከደሙ ንፁህ ነኝ!" የማለትና
በሌላው የማላከክ ነባር ባህሪያቸው መገለጫ ነው። ውሳኔው የራሳቸው የጠቅላይ ሚንስትሩ እንደ ሆነ በሁለት ምክንያቶች ከፍተኛ ጥርጣሬ አለኝ:
1. ውሳኔው ከገና በዓል (የክርስቶስ ውልደት) ጋር ተያይዞ የተወሰደ በመሆኑ ... ጠቅላይ ሚንስትሩ ዘወትር ከሚያሳዩት ፖለቲካን ከሀይማኖት ጋር አጣምዶ በማረስ ፖለቲካዊ ምርት (ትርፍ) ከመሰብሰብ ባህሪያቸው ጋር በደንብ ይዛመዳል።
2. በቅርብ ቀን ከሹመታቸው ይነሳሉ ተብሎ የሚታሰቡትን ኣሜሪካዊውን አደራዳሪ ለማግኘት በተደጋጋሚ ፍቃደኛ ያልነበሩት ጠቅላይ ሚንስትር፥ በአሸናጋዩ የመጨረሻ ጉዞ ወቅት ግን ፍቃደኛ ሆነው ፊት ለፊት ከተገናኙ ቦኋላ የተሰማ ውሳኔ በመሆኑ … ምናልባትም ጠቅላይ ሚንስትሩ በኢትዮጵያና ሱዳን ስኬት ለራቃቸው አሜሪካዊ አሸናጋይ የሥራ (የሹመት) ስንብት ልክ እንደ
face saving token… ለስራቸው ክንዋኔ (CV) የሰጠዋቸው ገፀ በረከት ሊሆን ይችላል። ይህ ደግሞ ከጠቅላይ ሚንስትሩ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን እንደ ግል ንብረታቸው ቆጥሮ በየትኛውም ጉዳይ ላይ ያሻቸውን ውሳኔ በግላቸው ከመወሰን ባህሪያቸው ጋር በደንብ ይጋጠማል።
ከዚህ ባሻገር ግን ... በሀገራቸን ዕጣ ፈንታ ላይ ለመወሰን ከእኛ ከባለሀገሮቹ ውጪ ማንም መብትና ስልጣን ሊሰጠው አይገባም የሚል እምነት ስላለኝ፥ አሜሪካንን እና አውሮፓን ከዚህ vague equation ውስጥ በማውጣት፥ በኣዲሱ የመከላከያ መ/ቤት ህንፃ ምረቃ ሥነስርዓት ላይ ሲናገሩ እንደሰማኋቸው ... ሌላ ታዲያ ማን ነግሯቸው ነው ጠቅላይ ሚንስትሩ "
እኛም ለመጀመሪያ ጊዜ ስንሰማ ደንግጠናል" ብለው የተናገሩት? ብዬ ልጠይቅ።
ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን? ወይንስ ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ? አሁን ነው "
አሆ! በል ጅቦ" ማለት። መቼም አቶ ደመቀ መኮንን እንደማይሆኑ እርግጠኛ ነኝ። ምክንያቱም፦ ጎራቸው (ፓርቲያቸው)
እንኳን ሌላውን ማስፈታት እራሳቸውም ካሉበት የአሽከርነት እስራት መፍታት ከማይችሉት ብአዴን ከሚሉት በድን ቡድን ነውና።
የነዚህ ሽማግሎችና በሽተኞች፣ የተሸነፉ የትግሬ ባንዳ አባቶች መፈታት ለኢትዮጵያ አንድነት ወዘተ ጠቃሚ ነው … የስብሃት ነጋ መፈታት ለኢትዮጵያ ሰላምና አንድነት እንዴት እንደ ሚጠቅም ...
ጠቅላይ ሚንስትሩ በዛሬው ንግግራቸው ላይ እኮ ... እነዚህን ግለሰቦች በእስር መጠበቁ ምንም ፋይዳ የለውም፤ ምክንያቱም ባለው አሁናዊ የሀገሪቱ ተጨባጭ ፖለቲካ ላይ የሚጫወቱት ምንም ሚና የለም በማለት ተናግረዋል። ታዲያ እንዴት ነው "
ለኢትዮጵያ አንድነትና ወዘተ ጠቃሚ የሚሆኑት?"። ጠቅላይ ሚንስትሩ ነገር አለሙ ሁሉ ተጠቅልሎባቸዋል ወይ አውቀው ጠቅልለውብናል።
... ለምንድን ነው በግልጽ ለህዝብ ቀርቦ የህዝብ ሃሳብና ፈቃደኝነት ያልተጠየቀው?
ይህ እኔም የማስበውና የምጠይቀው ጥያቄ ነው።
የተደፈሩት ከሀገራዊ እምነትና ባህላችን ውጪ የተዋረዱት … የምስኪን ኣራሹ ሚስትና ሴት ልጆች እንጂ የጠቅላይ ሚንስትሩ ቤተሰቦች አይደሉም፤
የፈረሰው ... የምሲኪኑ ጎጆ እንጂ የጠቅላይ ሚንስትሩ ቤተመንግስት አይደለም፤
የተቃጠለው ... ምስኪኑ ገበሬ በባዶ ሆዱ አርሶ ጎልጉሎና አርሞ ለእሸት ያበቃው ማሳ እንጂ የጠቅላይ ሚንስትሩ ባለሟሎች ሽንኩርትና በርበሬ የሚሸምቱበት የገበያ አዳራሽ አይደለም። ይቅርታ ማድረግ ካለበት ...
ልጁ የተደፈረችበት አባት እንጂ ጠቅላይ ሚንስትሩ አይደሉም። ይቅርታ ማድረግ ካለባት…
ህፃናት ልጆቿን ያለ አባት ለማሳደግ የተገደደች፣
ባሏ በግፍ የተገደለባት እናት እንጂ ቀዳማዊ እሜቲቱ አይደሉም። ይቅርታ ማድረግ ካለባቸው …
የህወሃት አረር ደረታቸውን እንደ ወንፊት በሳስቶት ሜዳ ላይ የቀሩት እግረኛ ወታደር ቤተሰቦች እንጂ በእነሱ ደምና ህይወት ደረታቸውን በከፍተኛ የጦር ሜዳ ጀብዱ ሜዳሊያ ያስጌጡት የዛሬዎቹ ተሽላሚዎች አይደሉም።
ስለዚህ፦ ጠቅላይ ሚንስትሩ ቢያውቁበት ኑሮ፥ ዛሬ እንደሰበሰቡት የጦር ሠራዊት፥ የጦር ጉዳተተኛና ቤተሰቦቻቸውንም ከመላው ሀገር ሰብስበው ሲያበቁ፤ እስረኛና ምርኮኛ የህወሃት አመራሮችና ድጋፍ ሰጪዎችንም በዛው መድረክ ላይ በማቆም … "
በሉ ይቅርታ ጠይቁ" ብለው ለበደላቸው ምህረት ከተጎጂዎቹ እንዲለምኑ ካደረጉ ቦኋላ ነበር፥ "
እሺ ... እናንተስ ምን ትላላችሁ? የበደል ስርየት ምልጃቸውን ትቀባላላችሁ?” ብለው መጠየቅና ማጠያየቅ የነበረባቸው። እሳቸው ግን … ሀገሩን ሁሉ ንቀው፣ የፈሰሰውን ደም፣ የተሰበረውን አጥንት እና ቅስም አራክሰው፥ ክስ አቋራጭ - ምህረት ሰጪ ሆኑ።